cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethio real Madrid fun 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
193
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
-730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድን ይለቅ ይሆን ? የኪልያን ኤምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣት በወጣቱ ብራዚላዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ ጎዬስ ላይ ጥላን አጥልቷል። ከኤምባፔ መምጣት በኃላ ባለፉት ቀናቶች በሮድሪጎ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ የሰነበቱ ሲሆን ይህም ተጨዋቹን በጥብቅ ከሚፈልጉት ከፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር ተዳምሮ ተጨዋቹ ከበርናባው የመልቀቅ ግምቱን እንዲጨምር አድርጓል። በመቀጠልም የርገን ክሎፕን የሸኝዉ ሊቨርፑል ለሮድሪጎ ፊርማ ሁነኛ ተፎካካሪ ሆኖ ብቅ ብቅ ሲል ፣ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሊቨርፑል ብራዚላዊዉን ወጣት ለማስፈረም €120 ሚሊዮን ለሪያል ማድሪድ እንዳቀረበ ተነግሯል። ሆኖም እንደ Diario SPORT ዘገባ ከሆነ ሪያል ማድሪድ ሊቨርፑል ለሮድሪጎ ያቀረበውን ከፍተኛ መጠን ያለዉን የዝዉዉር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ይህ ማለት ግን ተጨዋቹ አይሸጥም ማለት እንዳልሆነ ዘገባዉ አመላክቷል። ሮድሪጎ ባሳለፍነዉ ሳምንት ማንችስተር ሲቲ የአለማችን ትልቁ ክለብ ነዉ በማለት ከሪያል ማድሪድ ሊለቅ ስለሚችል ሁኔታ ፍንጭ መስጠቱ በክለቡ ጥሩ ተቀባይነት አላገኘም። የኤምባፔ መምጣት ለጊዜው ቦታውን የሚይዝ በሚመስል መልኩ እና የኤንድሪክ መምጣት በአጥቂ ስፍራዎች ላይ ፉክክር እየጨመረ በመምጣቱ ሪያል ማድሪድ በመጪው ክረምት ብራዚላዊውን ኮከቅ ለመሸጥ በቂ አቅም ሊኖረው ይችላል ሲል RELEVO በዘገባዉ ላይ አስፍሯል። ሮድሪጎ እና ተወካዮቹ በሪያል ማድሪድ የመቆየት ፍላጎት እንዳላቸው ቢናገሩም ሁኔታው ​​​​ቀስ በቀስ የሚቀየር ይመስላል። በስፔን ሚዲያዎች ላይ የወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ሮድሪጎ ይህንን ዝውውር በንቃት የማይፈልግ ቢሆንም የጨዋታ ግዜዉን በመቀነስ የወደፊት ህይወቱ ላይ በጥሞና እንዲያስብ ሊያነሳሳው ይችላል ተብሏል። @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15
إظهار الكل...
የሌኒ ዮሮ ዝዉዉር መዘግየት በናቾ ዉሳኔ ላይ ተመርኩዟል ! ሪያል ማድሪድ ሁነኛ የመሀል ተከላካይ  በዚህ ክረምት ለማስፈረሙ እርግጠኛ አይደለም። ናቾ ፈርናንዴዝ በዚህ ክረምት ክለቡን ለመልቀቅ ወስኖ የነበር ቢሆንም አሁን በክለቡ ለመቆየት በማመንታት ሂደት ዉስጥ ይገኛል። ሪያል ማድሪድም የተጨዋቹን ዉሳኔ አሁን እየጠበቀ በጉጉት ነው። በሌላ በኩል ሪያል ማድሪድ ለረጅም ግዜ መሀል ሜዳዉን ይቆጣጠራል ተብሎ የረጅም ወራቶች ታርጌት የሆነዉ ፈረንሳዊዉ የሊል ተከላካይ ሌኒ ዮሮን አሁንም በማሳደድ ላይ ይገኛል። ናቾ ክለቡን የሚሰናበት ከሆነ ይህንን ፈረንሳዊ ለማስፈረም የሚደረገዉ እንቅስቃሴ ሊያፋጥን ቢችልም ሪያል ማድሪድ የተከሊካዩን መሸጫ ዋጋ እንዲቀንስ ከሊል ጋር ድርድር እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ተጨዋቹን በትእግስት እንዲጠብቅ መልእክቱን ልኮለታል። ነገር ግን አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ይህንን ወጣት ተከላካይ ለማስፈረም ወደ ድርድሩ መቀላቀሉ ሪያል ማድሪድን ስትራቴጂ አወሳስቧል ሲል MARCA ተናግሯል። የካስቲያ የመሀል ተከላካዮች አልቫሮ ካሪሎ እና ማርቬል አዲስ ክለብ እንዲፈልጉ የተነገራቸው ሲሆን ራውል አሴንሲዮ ፣ ጃኮቦ ራሞን እና ኪኬ ሪብስ በዚሁ ክለብ እንደሚቆዩ ተረጋግጧል። የ 19 አመቱ ተከላካይ ጆአን ማርቲኔዝ በካስቲያዉ ቡድን በቦታኹ ከፍተኛ ደረጃ ከተሰጣቸዉ ተጨዋቾች አንዱ ቢሆንም በዋናዉ ቡድን ላይ ተፅእኖ መፍጠር የሚችል ተጨዋች ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም። በዚህም ሪያል ማድሪድ ዮሮን ካላስፈረም  እና ናቾ ክለቡን ከለተቀቀ ቡድኑ ሹዋሜኒን ከአንቶኒዮ ሩዲገር ፣ ከኤደር ሚሊታኦ እና ከዴቪድ አላባ ቀጥሎ እንደ አራተኛ የመሀል ተከላካይ አድርጎ እንደሚመለከተዉ መረጃዎች አስረድተዋል። ሹዋሜኒ በዚህ ቦታ እንዲጫወት ከተጠየቀ የግድ ይጫወታል ነገር ግን Center back የሹዋሜኒ ተወዳጅ ፖዚሽን እንዳልሆነ እራሱ ተጨዋቹ መናገሩ ይታወሳል። @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15

Photo unavailableShow in Telegram
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሪያል ማድሪድ ቤት ድንቅ ጊዜን ካሳለፉት የክለባችን ተጫዋቾች አንዱ ኦሪሊየን ችዋሚኒ ነው፤ ሪያል ማድሪድ በመሃል ሜዳውም ሆነ በተከላካይ ስፍራ ላይ በቋሚነት በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች አለመሸነፉም ምን ያህል ለሪያል ማድሪድ መከላከል እፎይታን የሚሰጥ ቨርሳታይል ተጫዋች መሆኑን ማሳታ ነው። ዛሬ አመሻሹን የማርካው ጋዜጠኛ ሆዜ ፌሊክስ ዲያዝ በዘገባው እንዳሰፈረው ሪያል ማድሪድ የሌኒ ዮሮ ዝውውር የማይሳካለት ከሆነ አስፈላጊ በሆኑ ጨዋታዎች ላይ ቿሚኒን እንደ መሃል ተከላካይነት ለማጫወት እያሰበ መሆኑን ጠቁሟል። [Marca]🎖 @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15
إظهار الكل...
በቴሌግራም ገቢ ከምናገኝባቸው አንደኛ መንገድ የሆነውን Hamster combat ሊስት ሊደረግ የጥቂት ቀናት እድሜ የቀረው ሲሆን ያልጀመራችሁ አሁኑኑ ጀምሩ👆👆👆ይፍጠኑ
إظهار الكل...
👍 3
إظهار الكل...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

Hamster Combat አሁን ላይ ካሉ AirDrop ከሁሉም በላይ ተጠባቂ እና ውድ ዋጋ ያወጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲቀጥልም ከሁሉም ኤርድሮፕ በላይ ብዙ ተጠቃሚ ያለው ነው። አሁን ላይም ሀምስተር ኮምባት ከዋሌት ጋር መገናኘት ተጀምሯል ! 🔥 ሀምስተር ኮምባት እስካሁን ያልጀመራችሁ ካላችሁ ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጀምሩ። 👇👇
إظهار الكل...
Hamster Kombat

Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!

Photo unavailableShow in Telegram
በስተመጨረሻ እርቅ የተፈጠረ ይመስላል ! 😁 @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
⚠️ በኒኮላስ ፉልክሩግ እና አንቶኒዮ ሩዲገር መካከል ዛሬ የጦፈ ግጭት በጀርመን ብሄራዊ ቡድን ልምምድ ወቅት ነበረ። በልምምዱ ወቅት ከሩዲገር ጠንካራ ታክል የተሰነዘረበት ፉልክሩግ መሬት ላይ ወደቀ፤ ከወደቀበት ሲነሳ ወደ ሩዲገር እየሮጠ ሩዲገርን እየተሳደበ እና በቁጣ እየጮኸ ነበር፤  ከዚያም በመሃል ተጫዋቾች እስኪገቡ እርስ በርሳቸው ተፋጠው ነበር። [SPORT BILD] @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ሞድሪች ወይስ ሳቢትዘር ? :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ በርናንዶ ሲልቫ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ፔድሪ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ስኮልስ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ላምፓርድ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ዴብሩይኔ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ቶኒ ክሩስ :- ''ሞድሪች'' ሞድሪች ወይስ ኢኔስታ :- ''ሞድሪች'' እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች የመለሰዉ ጋሬዝ ቤል ነው ! @ETHIO_REAL_MADRID_15 @ETHIO_REAL_MADRID_15
إظهار الكل...
🥰 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.