ar
Feedback
SparkRise Academy

SparkRise Academy

الذهاب إلى القناة على Telegram

Welcome to SparkRise Academic Channel! Igniting curiosity, inspiring growth, and guiding you to reach your highest potential. Join us for expert tutoring!!

إظهار المزيد
427
المشتركون
-124 ساعات
-37 أيام
-1030 أيام
أرشيف المشاركات
❤️የመምህር ሚና ከምንም በላይ ነው
የፑቲን እና የቀድሞ መምህርቱ አስደናቂ ገጠመኝ‼️ 1960ዎቹ አጋማሽ ይህ ወቅት በመጎርመስ ላይ ያለው ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ ካሉ አስቸጋሪ ልጆች ጋር ገጥሞ እንደ መፈንዳት ያለበት ጊዜ ነበር ። ..... እና ከማይሆኑ ልጆች ጋር ጓደኝነት በመመስረቱ ባህሪው እየተቀየረ መሆኑን ያየች የፑትን የጀርመንኛ ቋንቋ መምህርት እና የክፍል ሀላፊው በተማሪዋ ላይ ያየችውን የባህሪ ለውጥ ዝም ብላ ማለፍ አልፈለገችም ። ስለዚህ ትከታተለው ትመክረው እና ልክ እንደወላጅ ትቆጣጠረው ጀመር ። .... አንተ ዝም ብሎ ሰው ለመሆን አልተፈጠርክም ። በውስጥህ ታላቅ የሆነ ስብእና ያለው ሰው ነው የሚታየኝ ፡ ከራሱ አልፎ ሀገርን የሚጠቅም ጎበዝ ልጅ ። ... እያለች. ....ከማይሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ  ልቡ እንደማበጥ ያለበትን ትንሹን ፑቲን ለመመለስ ሞከረች ። .... እና ተሳካላት ። .... ቭላድሚር ፑቲን በመምህሩ እገዛ ከመጥፋት   ከመበላሸት ድኖ ትምህርቱ ላይ ማተኮር ጀመረ ። ... ለዛም ነው ቭላድሚር ፑቲን ስለ ህይወት ልምዱ ሲናገር ፡ በወጣትነት እድሜዬ ቬራ ዲሚትሪቭና ን  የመሰለ መምህር ባላገኝ ፡ አሁን የደረስኩበት ደረጃ ላልደርስ እችላለሁ ሲል የሚናገረው ። ........ እና ፡ እኚህ በአንድ ወቅት የቭላድሚር ፑቲን መምህርት የነበሩት ቬራ ዲሚትሪቭና ፡ ከትናንት ወዲያ ምሽት በክሬምሊን ቤተመንግስት  ተካሂዶ በነበረው አንድ የእራት ግብዣ ላይ እንዲገኙ ፡ ውለታውን አስቦ ለአመታት ሲደግፋች በቆየው ቭላድሚር ፑቲን በኩል ተጋብዘው ነበር ። ...... በመሆኑም ካሉበት ከተማ ተጉዘው ሞስኮ በሚገኝ አንድ ሆቴል በማረፍ የግብዣው ሰአት እስኪደርስ እየተጠባበቁ እያለ የሩሲያ ምርት የሆነ ጥቁር አውረስ V8 ከሆቴሉ በር ላይ  ቆመ ። .... የአውረሱ መኪና ነጂ ቭላድሚር ፑቲን ነበሩ ። እና ከመኪናው ከወረዱ በኋላ በእጃቸው ትልቅ አበባ ይዘው የዘጠና አመቷ የልጅነት መምህራቸው ወዳሉበት ቦታ ሄደው አገኘኟቸው ። .....   የሩሲያን የድል ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን ታላቅ የእራት ግብዣ ላይ እንዲካፈሉ የተጋበዙትን መምህርት ቬራ በሾፌር ወደ ቤተመንግስት  እንዲመጡ ከማድረግ ይልቅ  ፡ ራሳቸው ፕሬዝደንት ፑቲን መምህርቷን ይዘው መምጣት ስለፈለጉ ነበር  እየነዱ እዚህ ድረስ የመጡት  ። ... እና. . ቭላድሚር ፑቲን ሰኞ እለት  ባደረጉት በዚህ ነገር ውስጥ ትህትና ፡  ውለታን አለመርሳትና    ቅንነት ይህ ሁሉ አለበት ።

📌 በኢንተርኔት ዓለም ውስጥ "ኩኪዎች" (Cookies) ምንድን ናቸው? ለምንስ የግላዊነት ጥያቄ ያስነሳሉ? ብዙዎቻችን የተለያዩ ድረ-ገጾችን ስንከፍት "ይህ ድረ-ገጽ ኩኪዎችን ይጠቀማል፣ ትቀበላለህ?" የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይገጥመናል። አብዛኛው ሰው ዝርዝሩን ሳያነብ "Accept" የሚለውን ይጫናል፤ ነገር ግን እነዚህ ትናንሽ ፋይሎች በዲጂታል ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው። ኩኪ (HTTP Cookie) ማለት አንድን ድረ-ገጽ ስንጎበኝ ያ ድረ-ገጽ ወደ ስልካችን ወይም ኮምፒውተራችን የሚልከው በጣም ትንሽ የሆነ የጽሁፍ ፋይል (Data) ነው። ይህ ፋይል ድረ-ገጹ እኛን ለይቶ እንዲያውቀንና ቀጣይ ስንመለስ ምርጫዎቻችንን እንዲያስታውስ የሚያገለግል እንደ "ዲጂታል መታወቂያ" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የኩኪዎች ዋነኛ ጥቅም ለተጠቃሚዎች ድረ-ገጾችን ምቹና ፈጣን ማድረግ ነው። ለምሳሌ፣ በአንድ ድረ-ገጽ ላይ አካውንታችንን ከፍተን ከገባን በኋላ (Login)፣ በየደቂቃው ድጋሚ የይለፍ ቃል እንዳይጠይቀን የሚያደርጉት እነዚህ ኩኪዎች ናቸው። እንዲሁም በቋንቋ፣ በገጽ ቀለም ወይም በሌሎች የግል ምርጫዎች ደረጃ የሰጠናቸውን ትዕዛዞች በቃላቸው ይዘው በመቆየት፣ በቀጣይ ጉብኝታችን ድረ-ገጹ በትክክል እኛ በፈለግነው መልኩ ተስተካክሎ እንዲጠብቀን ያደርጋሉ። ያለ ኩኪዎች አጠቃቀም፣ የኢንተርኔት ቆይታችን አሰልቺና በእያንዳንዱ እርምጃ መረጃን ደጋግመን የምናስገባበት ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ኩኪዎች ከጥቅማቸው ጎን ለጎን "ለምን ህግና ጥበቃ አስፈለጋቸው?" የሚለው ጥያቄ በስፋት ይነሳል። ምክንያቱም አንዳንድ ኩኪዎች የእኛን የኢንተርኔት እንቅስቃሴ (Browsing History) በዝርዝር የመከታተል አቅም አላቸው። በተለይ "Third-party cookies" የሚባሉት፣ ከአንድ ድረ-ገጽ አልፈው በሌሎች ገጾች ላይ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በመከታተል ምን አይነት ምርቶችን እንደምንፈልግ መረጃ ይሰበስባሉ። ይህ መረጃ ደግሞ ለትልቅ የማስታወቂያ ኩባንያዎች ተላልፎ ስለሚሰጥ፣ በፌስቡክ ወይም በዩቲዩብ ላይ የግል ፍላጎታችንን የሚመስሉ ማስታወቂያዎች ተከታትለው እንዲመጡብን ያደርጋል። ይህ ሁኔታ የሰዎችን የግል ሚስጥርና ነፃነት ይጋፋል ተብሎ ስለሚታመን፣ እንደ አውሮፓ ህብረት (GDPR) ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድረ-ገጾች ማንኛውንም መረጃ ከመሰብሰባቸው በፊት የተጠቃሚውን ፈቃድ እንዲጠይቁ በህግ አስገዳጅ አድርገዋል። ለማጠቃለል ያህል፣ በድረ-ገጾች ላይ የሚመጡ የኩኪ ምርጫዎችን ስናይ በዘፈቀደ ከመጫን ይልቅ አማራጮቹን ማየት ተገቢ ነው። ድረ-ገጹ በትክክል እንዲሰራ የሚያስፈልጉ (Essential) ኩኪዎችን መፍቀድ የግድ ቢሆንም፣ የእኛን የግል መረጃ ለንግድና ለማስታወቂያ የሚጠቀሙ ኩኪዎችን ግን የመከልከል መብት አለን። በዲጂታል ዘመን ስለ ቴክኖሎጂው አሠራር በቂ ግንዛቤ መያዝ፣ የግላዊነት መብታችንን ለማስከበር የመጀመሪያውና ዋናው እርምጃ ነው። #ShareThisPost ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት! Mohammed Seid #Technology #Cookies #DigitalPrivacy #CyberSecurity

photo content

በነዳጅ ጉዳይ የምትጠቅም አንድ ሲስተም ላስተዋውቃችሁ‼ ============================== ✍️ ያው ሰሞኑን የነዳጅ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኖ የለ። በማደያዎች ላይ የሚታየው ረጃጅም ሰልፍ አድካሚ ነው፣ በየትኛው ማደያ ናፍጣ ወይም ቤንዚን እንዳለ፤ በአካል እዛ ተሂዶ ካልሆነ በስተቀር አድካሚ ነው። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በ24 ሰዓት ቆይታ በፌስቡክ ገፁ የሚለቀው መረጃ አለ፣ በየትኛው የአዲስ አበባ 132 ገደማ ማደያዎች ምን ያክል መጠን ያለው ነዳጅ እንዳለ የሚጠቁም። ግን 24 ሰዓት ረጅም ነው፣ የንግድ ቢሮውን የፌስቡክ ገፅ የማይጠቀሙም ይኖራሉና የመረጃ ክፍተት ይኖራል። ይህንን ችግር ለመፍታት "EthioFuel" የተሰኘውን አዲስ የዲጂታል መፍትሄ ይዤ ብቅ ብያለሁ። EthioFuel ምንድን ነው? ይህ ስርዓት የነዳጅ አቅርቦትን ከነበረው የተዘበራረቀ እና በእጅ የሚሰራ አሰራር ወደ ዘመናዊ፣ ዳታን መሰረት ያደረገ እና ፈጣን ስርአት የሚቀይር የነዳጅ ክትትል እና የወረፋ መጠበቂያ ሲስተም ነው። ከተወሰኑ ፌቸሮቹ መካከል፦ ✅ የነዳጅ ክምችት እና ሎኬሽን (Live Map): ማደያው ነዳጅ አለው ወይስ የለውም? ምን ያህል ቀርቶታል? ያ ማደያ የሚገኘው አሽከርካሪው ካለበት በምን ያክል ርቀት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች በስልክ ብቻ በቀጥታ ማግኘት ይቻላል። ✅ ነዳጅ ለመቅዳት ስታስቡ በኦንላን ወረፋ ቀድሞ መያዝ(Virtual Queue): መንገድ በመዝጋት ሰልፍ መጠበቅ ይቀራል። በስልክ ቁጥር ብቻ ወረፋ በመያዝ፣ ከፊት ለፊታችሁ ስንት መኪና እንዳለ ማወቅ ይቻላል። በቦታው ስትደርሱም ወረፋ ስትይዙ ሲስተሙ የሰጣችሁን QR Code ስካን ያደርግና የማደያው ተቆጣጣሪ፣ ይቀዳላችኋል። ✅ የማጭበርበር መከላከል: የነዳጅ ስርቆትን ወይም ያለአግባብ መጠቀምን ለመቆጣጠር መኪኖችን በታርጋ እና በታንከር መጠናቸው ይቆጣጠራል። አንድ አሽከርካሪ የሆነ ማደያ ቀድቶ ሂዶ፣ በህገ ወጥ መምገድ ሽጦና ቶሎ ጨርሶ ወደ ሌላው ሂዶ እየቀዳ የሌላውን እድል እንዳያጣብብ፣ ሲስተሙ በቀላሉ በኤአይ ፌቸሩ ይለየዋል። ✅ ለባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ዳሽቦርድ: Ethiopian Ministry of Trade and Regional Integration እና የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በቀጥታ ስርጭት (Real-time) መረጃን በመከታተል የተሻለ ውሳኔ እንዲወስኑ ያግዛቸዋል። ይህ አሽከርካሪዎች፣ የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች ወይም የመንግስት አካላት ከሆናችሁ፡ ❓ በዚህ ዘርፍ ሌላ ምን አይነት ችግር አለ? ❓ ምን አይነት ፌቸር ቢጨመር ትፈልጋላችሁ? ሀሳባችሁን አጋሩኝ። ሞክሩት፡ 📲 ethiofuel.muradtadesse.com እንደ አሽከርካሪ ሆናችሁ ለማየት: ስልክ: 0912345678 ፓስወርድ: 12345678 OTP የሚልከውን ቀለል ያደረግኩት፣ ለእያንዳንዱ ኦቲፒ ክፍያ ስላለው ነው። ትክክለኛ ኦፊሲያል ለተግባር ሲውል፤ በዛ መልኩ ይስተካከላል። ከአዲስ አበባ ባሻገር፣ በየትኛውም ክልል የሚገኝን ማደያ ወደ ሲስተሙ ማስገባት ይቻላል። የማደያ ዝርዝር የተጠቀምኩት የአዲስ አበባዎቹን ነው። ሎኬሽን ጦር ኃይሎች ያለውን ኖክ ማደያ ነው ለሁሉም ያደረግኩት፤ ምክንያቱም በቀላሉ የሌሎቹን ማደያ ሎኬሽን ማፕ ላይ ላገኘው አልቻልኩም። ወደ ሲስተሙ የተመዘገበ የዛ ማደያ ተቆጣጣሪ ትክክለኛውን የራሱን ማደያ ሎኬሽንና መሰል መረጃ በትክክል ማስገባት ይችላል። https://www.linkedin.com/posts/muradtadesse_ethiofuel-techforgood-activity-7449476550158168064-pyP-?utm_source=share&utm_medium=member_desktop&rcm=ACoAACaUP2oB3u_jeD6TvqRssom8jDTi6earRyc

ብዙ አስደናቂ እውቀት እና አቅም ያላቸው ኢትዮጵያኖች ወደ አሜሪካ መጥተው ጥራት ያለው ትምህርት ቢያገኙ ለሀገራቸውም ሆነ ለራሳቸው ትልቅ ጥቅም ነው። ነገር ግን ፕሮሰሱን ባለማወቅ፣ የትምህርት ቪዛ
ብዙ አስደናቂ እውቀት እና አቅም ያላቸው  ኢትዮጵያኖች ወደ አሜሪካ መጥተው ጥራት ያለው ትምህርት ቢያገኙ ለሀገራቸውም ሆነ ለራሳቸው ትልቅ ጥቅም ነው። ነገር ግን ፕሮሰሱን ባለማወቅ፣ የትምህርት ቪዛ እና ስኮላሽርፕ የማግኘት መንገዱን ስለማያውቁ ባክነው ይቀራሉ። Mulu Law Group አንዱ ከሚያደርገው ማህበራዊ አገልግሎት ውስጥ ይሄን ክፍተት መሙላት ነው። በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ በስኮላርሽፕ እና በF-1 እና J-1 የተማሪ ቪዛ ወደ አሜሪካ ለትምህርት መጥተው ትልልቅ ቦታ የደረሱ ኢትዮጵያውያንን በመጋበዝ ፥ የትምህርት ቪዛ እና ስኮላርሽፕ ለማግኘት የሚፈልጉ በኢትዮጵያ ላሉ ተማሪዎች የቀጥታ ዙም መርሐ ግብር እ.ኤ.አ ኤፕሪል 25 ቀን 2026 ዓ.ም. በ8፥00 Eastern Time (በኢትዮጵያ አቆጣጠር  ቅዳሜ ሚያዚያ 17 ቀን 2018 ዓም በ11፥00 ሰዓት) ያዘጋጀ ሲሆን፣ በዚህ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ስለ ቪዛ እና ስኮላርሽፕ ማመልከት ሂደት ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን እንዲሁም ጥያቄ መጠየቅ እና መልስ ማግኘት ትችላላችሁ። መርሐ ግብሩ የማይቀዳ እና በቀጥታ ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል። ይሄን በማጋራት ብዙ ሰው ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጉ። Direct line: ☎️ +1 (877) MULULAW. ☎️ + (877)  685-8529. ☎️ + (952)  245-0454. ☎️ + (612)  541-1321. ☎️ + (612)  296-7582. WhatsApp 📱 +1 (651) 528-2677

@Cdub:It suddenly hit me with the fact that When you look at Earth from space, it doesn’t look like a place full of borders,
@Cdub:It suddenly hit me with the fact that When you look at Earth from space, it doesn’t look like a place full of borders, religions, egos, and wars it just looks like a tiny, fragile blue ball floating in endless darkness. And yet, on this small planet, more than 8 billion people wake up every day with completely different stories, different dreams, different fears, and different battles. Somewhere someone is falling in love, somewhere someone is crying themselves to sleep, somewhere families are laughing over dinner, and somewhere people are fighting over land, power, and beliefs. All of this happiness, sadness, success, jealousy, war, love, hope is happening at the same time on this small, quiet planet spinning in space. It makes you realize how small our problems, our pride, and even our differences really are, and how we are all just temporary visitors sharing the same tiny home.

This never gets old 😂
This never gets old 😂

1ኛ.​"ሰይፍ የገደለው አንድ ሰው ነው፤ አንደበት ግን ሺዎችን ይገድላል።" ንግግር ከመውጣቱ በፊት ያላትን ጥንቃቄና ክብደት የሚገልጽ 2ኛ.​"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ፣ የሰው ልጅም ጥንካሬው በሚገጥመው መከራ ይለካል፡፡" አስቸጋሪ ጊዜያት ማንነትን ለማጥራት እንደሚረዱ የሚያሳይ 3ኛ.​"ሞኝ ሰው ባወቀው ነገር ሁሉ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን በሚናገረው ነገር ሁሉ ያውቃል።" የዝምታንና የማስተዋልን ዋጋ የሚጠቁም 4ኛ.​"ትናንት የታረመ ታሪክ ነው፤ ነገ ደግሞ ያልተከፈተ ምስጢር፤ ዛሬ ግን የተሰጠ ስጦታ ነው።" — በዛሬው ቀን ላይ ትኩረት አድርጎ በአግባቡ መጠቀምን የሚመክር 5ኛ.​"አንበሳ ወደ ኋላ የሚያፈገፍገው ፈርቶ ሳይሆን፣ ርቆ ለመዝለል እንዲመቸው ነው።" — በህይወትህ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ወደ ኋላ ሲመለሱ ለትልቅ ለውጥ እየተዘጋጀህ መሆኑን ተረዳ 6ኛ.​"የሰው ልጅ ትልቁ ጠላት የራሱ ድንቁርና ሳይሆን፣ አውቃለሁ ብሎ ማሰቡ ነው።" — ለመማር ዝግጁ መሆንንና ትህትናን የሚያስተምር 7ኛ.​"እንጨት ሲቆረጥ መጥረቢያው ይረሳል፤ ዛፉ ግን ጠባሳውን አይረሳውም።" — በሰዎች ላይ የምናደርሰው ጉዳት በእኛ ዘንድ ቢረሳም በተጠቂው ዘንድ ግን ጠባሳ ሆኖ እንደሚኖር የሚያሳስብ። 8ኛ.​"ባህር እስኪጎድል መጠበቅ አያስፈልግህም፤ መሻገር ከፈለግክ ጀልባህን ስራ።" — ለለውጥ እድልን ከመጠበቅ ይልቅ ራስን ማዘጋጀት እንደሚሻል 9ኛ.​"ከሺህ ቃላት ይልቅ አንዲት ተግባር ትልቅ ድምፅ አላት።" — በወሬ ሳይሆን በስራ መታወቅን የሚመክር 10ኛ.​"ወደ ፀሐይ ብርሃን ፊትህን ካዞርክ፣ ጥላህ ከበስተኋላህ ይወድቃል።" — ሁልጊዜ መልካም እና ተስፋ ሰጪ ነገሮች ላይ ካተኮርክ፣ ጨለማና ተስፋ መቁረጥ ይሸሹሃል። እርሶ የትኛው ወደዱት በኮሜንት ያስቀምጡልን!!!

photo content

#BREAKING የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ (ጁምዓ) ይውላል። ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል። ዒድ ሙባረክ ! #Ha
#BREAKING የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ (ጁምዓ) ይውላል። ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል። ዒድ ሙባረክ ! #Haramain ቲክቫህ ኢትዮጵያ መጋቢት 9 ቀን 2018 @tikvahethiopia

🧠 ሳይንሳዊ የጥናት እና የፈተና ዝግጅት ስልቶች ለኢንትራንስ ተፈታኞች በሳይንስ የተረጋገጡ (Evidence-based) ውጤታማ የጥናት መንገዶች፦ 1. የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልቶች (Cognitive Strategies) * Active Recall (መረጃን የማውጣት ልምምድ)፦ ማጠቃለያዎችን ደጋግሞ ከማንበብ ይልቅ፣ መጽሐፉን ዘግቶ ያነበቡትን ለማስታወስ መሞከር (Self-testing) በጭንቅላት ውስጥ ያለው የነርቭ ትስስር እንዲጠነክር ያደርጋል። * Spaced Repetition (የተራራቀ ክለሳ)፦ አንድን ትምህርት በአንድ ቀን ለ 5 ሰዓት ከማጥናት ይልቅ፣ ለ 5 ቀናት በየ 1 ሰዓቱ መከፋፈል መረጃው ከረጅም ጊዜ ትውስታ (Long-term memory) ጋር እንዲዋሃድ ይረዳል። * The Pomodoro Technique፦ አእምሮ ለረጅም ሰዓት ትኩረት ማድረግ ስለሚዝል፣ በየ 25 ወይም 50 ደቂቃ ጥናት የ 5 ወይም 10 ደቂቃ እረፍት መውሰድ የትኩረት አቅምን (Focus) እንደተጠበቀ ያቆያል። 2. የባዮሎጂካዊ ዝግጁነት ሚና * Sleep and Memory Consolidation፦ እንቅልፍ መረጃን በጭንቅላት ውስጥ የማደራጀት (Consolidation) ስራ የሚሰራበት ወቅት ነው። በቂ እንቅልፍ ማጣት የተማሩትን መረጃ የማውጣት (Recall) ብቃትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። * Cortisol Management (ጭንቀትን መቆጣጠር)፦ ከፍተኛ ጭንቀት በሰውነታችን ውስጥ የኮርቲሶል ሆርሞን እንዲጨምር ያደርጋል። ይህ ሆርሞን ደግሞ የማስታወስ ኃላፊነት ያለበትን የጭንቅላት ክፍል (Hippocampus) ስራ ያውካል። ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ (Deep breathing) ይህንን ያረጋጋል። 3. የፈተና አሰራር ሳይንስ (Exam Mechanics) * The First Impression Bias፦ ጥያቄዎችን ስታነቡ የመጀመሪያው የሚመጣላችሁ መልስ ብዙ ጊዜ ትክክል የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ያለ በቂ ምክንያት መልስን መቀያየር ለስህተት ይዳርጋል። * Pre-read Strategy፦ ፈተናውን ከመጀመርዎ በፊት ለ 2 ደቂቃ ጥያቄዎቹን በሙሉ አይን ማየት (Scanning) አእምሮዎ ለከባዶቹ ጥያቄዎች በኋለኛው ክፍል (Subconscious mind) መልስ እንዲያዘጋጅ ይረዳዋል። * Elimination Method፦ ትክክለኛውን መልስ በቀጥታ ካላወቁት፣ የማይሆኑትን በመቀነስ (Eliminating) የመገመት ዕድልዎን ከ 25% ወደ 50% ወይም ከዚያ በላይ ማሳደግ ይቻላል። 📌 ማጠቃለያ መልዕክት "ብልህ ጥናት ከብዙ ጥናት ይበልጣል (Study Smarter, Not Harder)"። የኢንትራንስ ፈተና የእውቀታችሁን ያህል የዝግጅታችሁ እና የሥነ-ልቦና ጥንካሬያችሁ መለኪያ ነው። በሳይንሳዊ መንገድ ተዘጋጁ፣ በራሳችሁ እመኑ! በርቱ! እናንተ ለዚህ ትልቅ ቦታ ለመድረስ ለዓመታት የለፋችሁ ተማሪዎች ናችሁ፤ ይህ ደግሞ የመጨረሻው ጥቂት እርምጃ ነው። https://t.me/Aksipspg

+7
Condensed Note for G-12
For Grade 12 Tutorial program
- Fourth month https://t.me/Aksipspg

Why School Buses in America Look Like They Have “Super Authority” 🚌🇺🇸 In the United States, a school bus is not just a vehicle — it becomes a moving safety zone. When a school bus stops and the red lights start flashing: 🚫 ALL cars must stop 🚫 Traffic from BOTH directions must wait (on most roads) 🚫 No passing allowed until the bus moves again Yes — even if you are late. Why are the rules so strict? Because children are unpredictable. They may cross suddenly, run behind the bus, or not understand traffic danger. So the law puts children’s lives above driver convenience. These rules are strongly enforced and promoted by the National Highway Traffic Safety Administration to prevent accidents and save lives. ⚠️ Breaking this law can lead to: 💵 Heavy fines ($300–$1000 or more) 📄 License penalty points ⚖️ Possible court charges ✅ When CAN you pass? Only if there is a divided highway with a physical median separating the two directions. So it’s not “too much authority” — for a few seconds, society simply chooses safety over speed.

photo content

ቴሌግራም ቻናል ወይም ግሩፕ ፕሮፋይል ሪፖርት በማድረግ ብቻ ባለቤትነት ሊወሰድ ይችላልን?👇👇 በአጭሩ መልሱ፦ አይችልም። ቴሌግራም አንድን ቻናል ለሌላ ሰው አሳልፎ የሚሰጠው የፕሮፋይል ፎቶን ወይም ስምን በማመሳሰል በሚቀርብ "የኔ ነው" የሚል ሪፖርት ብቻ አይደለም። ​ይህ ጉዳይ እንዳያሰጋዎት የሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ፦ ​1. የቴሌግራም የሪፖርት አያያዝ ​ቴሌግራም አንድን ቻናል እንዲዘጋ (Ban) ወይም ባለቤቱ እንዲቀየር እርምጃ የሚወስደው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ብቻ ነው፦ 👉​የቅጂ መብት ጥሰት (Copyright Infringement): ኦፊሴላዊ የሆኑ ድርጅቶች (ለምሳሌ የፊልም ኩባንያዎች፣ የሙዚቃ አሳታሚዎች) የቅጂ መብት ጥያቄ በሰነድ አስደግፈው ሲያቀርቡ። 👉​ማንነትን መላክ (Impersonation): ሃከሩ እርስዎን መስሎ የሰዎችን መረጃ እየሰረቀ ወይም እያታለለ መሆኑ ከተረጋገጠ ቻናሉ ሊዘጋ ይችላል። ነገር ግን ቻናሉን ለሃከሩ አሳልፎ አይሰጠውም። 👉​ህገ-ወጥ ይዘቶች: የሽብር፣ የወሲብ ወይም የህፃናት ጥቃት ይዘቶች ሲኖሩ። ​2. ቻናሉን ለሌላ ሰው አሳልፎ ለመስጠት (Transfer of Ownership) ​አንድ ቻናል ከእርስዎ እጅ ወጥቶ ለሌላ ሰው እንዲሰጥ የሚከተሉት ነገሮች መሟላት አለባቸው፦ 👉​እርስዎ እራስዎ "Transfer Channel Ownership" የሚለውን መጫን አለብዎት። ​ይህንን ለማድረግ ደግሞ በእርስዎ አካውንት ላይ Two-Step Verification መብራት አለበት፤ ካበሩትም በኋላ ቢያንስ 7 ቀናት ማለፍ አለበት። 👍​ስለዚህ ሃከሩ የእርስዎን አካውንት ሙሉ በሙሉ ካልሰረቀ በስተቀር በሪፖርት ብቻ ቻናሉን የግሉ ማድረግ አይችልም። ​3. "Username" እና የንግድ ምልክት (Trademark) ​የእርስዎ ቻናል ዩዘርኔም (Username) ለምሳሌ @YourChannel ቢሆን እና ሃከሩ የንግድ ምልክት (Trademark) ሰነድ ቢኖረው እንኳን፣ ቴሌግራም የሚወስደው እርምጃ ዩዘርኔሙን "እንዲለቀቅ" ማድረግ ወይም ቻናሉን መዝጋት እንጂ ቻናሉን ለሌላ ሰው መስጠት አይደለም። 🇪🇹​ማድረግ ያለብዎት ጥንቃቄዎች፦ ​ሃከሩ "ሪፖርት አድርጌ አስወስደዋለሁ" የሚለው እርስዎን ለማስፈራራት እና በዚህ ሰበብ የሆነ ሊንክ እንዲጫኑ ወይም መረጃ እንዲሰጡት ለማድረግ ሊሆን ይችላል። 🇸🇦​መፍራት የለብዎትም: በሪፖርት ብቻ የለፋችሁበት ቻናል አይወሰድም። 👆​Two-Step Verification: በአካውንትዎ ላይ ፓስወርድ መኖሩን በድጋሚ ያረጋግጡ። 🇪🇹​የዩዘርኔም ጥበቃ: ቻናልዎ ትልቅ ከሆነ እና የራስዎ ድርጅት ካለዎት፣ በተቻለ መጠን በሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች (Facebook, X, Instagram) ላይ ተመሳሳይ ስም ይኑርዎት። ይህ ቴሌግራም ጋር ቅሬታ ቢፈጠር "እውነተኛው ባለቤት እኔ ነኝ" ለማለት ይረዳል።

Repost from Star Exams
የ2017 ዓ.ም ን ጨምሮ የ9 ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፈተናዎችን ያግኙ፦ ✨ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ግልጽ እና በሚገባ የተዘጋጁ ማብራሪያዎች 🤖 ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት Google Geminiን
የ2017 ዓ.ም ን ጨምሮ የ9 ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፈተናዎችን ያግኙ፦ ✨ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ግልጽ እና በሚገባ የተዘጋጁ ማብራሪያዎች 🤖 ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት Google Geminiን ይጠይቁ 💯 100% ነፃ ምንም ክፍያ ፣ ማስታወቂያዎችና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች የሉትም 📲 መተግበሪያውን ያውርዱ 👉https://play.google.com/store/apps/details?id=com.easycodesolution.starexams&hl=en 📢 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ 👉 https://t.me/star_exams 🚀 Our goal is to use our technical skills to build free, impactful tools and give back to the community. 📤 ያውርዱት፣ ይጠቀሙበት ለጓደኞችዎም ያጋሩት ❤️

🌟 ከኪሳራ አፋፍ ወደ ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ፡ የአንድ መነፅር ተአምራዊ ጉዞ! 🕶️✨ **** የ106 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ታዋቂው የፈረንሳይ መነፅር አምራች "ሄነሪ ጁሊያን" (Henry Jullien
🌟 ከኪሳራ አፋፍ ወደ ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ፡ የአንድ መነፅር ተአምራዊ ጉዞ! 🕶️✨ **** የ106 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋው ታዋቂው የፈረንሳይ መነፅር አምራች "ሄነሪ ጁሊያን" (Henry Jullien) ከጥቂት ዓመታት በፊት ሕይወቱ ሊያበቃ፣ በሩ ሊዘጋ የደረሰ ኩባንያ ነበር። ምንም እንኳን አገግሞ ወደ ሥራ ቢመለስም፣ ገበያው ቀዝቅዞበት "ነፍስና ሥጋው" ሳይለያይ ለዓመታት ቆይቷል። ነገር ግን ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ የሆነው ነገር ተአምር ነው! 🚀 ታሪኩ የተቀየረው በስዊዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ነው። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የኩባንያውን "Pacific S 01" የተሰኘ ሞዴል መነፅር አድርገው መድረክ ላይ ብቅ አሉ። ማክሮን በዚህ መነፅር አጊጠው ንግግር ሲያደርጉ፣ የዶናልድ ትራምፕን "የአሽሙር አድናቆት" ጨምሮ የአለምን ሚዲያዎች ትኩረት በአንድ ጊዜ ሳቡት። ውጤቱ ምን ሆነ መሰላችሁ? 🔥 📍 ዌብሳይቱ ተጨናነቀ፦ ማክሮን በታዩ በደቂቃዎች ውስጥ የኩባንያው የኦንላይን መሸጫ በጎብኚዎች ብዛት ተጨናነቀ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች "የማክሮኑን መነፅር" ለመግዛት ሲሻሙ፣ ዌብሳይቱ ከአቅም በላይ ሆኖበት "ክራሽ" አደረገ! 📍 የነፃ ማስታወቂያ በፕሬዝዳንት፦ ኩባንያው ምንም ዓይነት የማስታወቂያ በጀት ሳይመድብ፣ በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት አማካኝነት ባገኘው "የነፃ ማስታወቂያ" በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትዕዛዞችን ተቀበለ። 📍 የዋጋ ዝላይ፦ በ106 ዓመት ታሪኩ አይቶት በማያውቀው ሁኔታ የኩባንያው የገበያ ዋጋ በ 65% አሻቀበ! 📍 መጋዘኑ ባዶ ቀረ፦ በመጋዘን ተከማችተው የነበሩ መነፅሮች እያንዳንዳቸው በ770 ዶላር (ከ150 ሺህ ብር በላይ) በሰዓታት ውስጥ ተሸጠው አለቁ። አሁን ኩባንያው ከመላው ዓለም የሚጎርፉ ትዕዛዞችን ለማስተናገድ ሌት ተቀን እየሠራ ይገኛል። አንዳንድ ጊዜ ለስኬት ጠንክሮ መሥራት ብቻ ሳይሆን፣ ትክክለኛ ሰው፣ በትክክለኛው ቦታ፣ የእርስዎን ውጤት ተጠቅሞ መታየቱ ተአምር ይፈጥራል! እርስዎስ እንዲህ አይነት ዕድል ቢሰጥዎት ምን እንዲሸጥልዎት ይፈልጋሉ? ሀሳብዎን በአስተያየት መስጫው ያጋሩን! በዋሲሁን ተስፋዬ

ጎግል በAI መተግበሪያው Gemini ላይ ሰዎች በነፃ የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተናን መለማመድ እንደሚችሉ አስታወቀ። ጎግል ፕሪስተን ሪቪው ከተሰኘ የትምህርት ተቋም ጋር በመተባበር ሰዎች በGemini
ጎግል በAI መተግበሪያው Gemini ላይ ሰዎች በነፃ የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተናን መለማመድ እንደሚችሉ አስታወቀ። ጎግል ፕሪስተን ሪቪው ከተሰኘ የትምህርት ተቋም ጋር በመተባበር ሰዎች በGemini የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ ፈተናን (SAT) በነፃ እንዲለማመዱ ማስቻሉን ገልጿል። በኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ከሚወስዷቸው ፈተናዎች አንዱ የሆነው የአፕቲቲዩድ ፈተና፣ በርካታ የውጪ ሃገር ኮሌጆችም ተማሪዎችን ለመቀበል የሚሰጡት ፈተና ነው። ጎግል በAI መተግበሪያው የመለማመጃ ፈተናን ይፋ ያደረገ ሲሆን ተጠቃሚዎች " I want to take a practice SAT test” የሚለውን "prompt" በመጠቀም የመለማመጃ ፈተናውን ማግኘት ይችላሉ። የመለማመጃ ፈተናውን ከጨረሱ በኋላም Gemini ተፈታኞች የቱ ጋር ጥሩ እንደሆኑና የቱ ጋር በይበልጥ ማጥናት እንዳለባቸው ግብረ መልስ ይሰጣቸዋል ሲባል፣ ትክክለኛ ምላሾች በሚጠይቁበት ወቅትም ከማብራሪያ ጋር ምላሽ ይሰጣል። ጎግል ለጊዜው የአፕቲቲዩድ ፈተናን ይጀምር እንጂ ተጨማሪ ፈተናዎችን ወደፊት እንደሚያካትት ገልጿል። ©:  ቲክቫህ ማጋዚን