ASTU Network ®️
الذهاب إلى القناة على Telegram
🛜 ASTU Network ®️ ➲ Join us || @ASTU_Network || || @ASTU_Network_Group || 📚 Library: @ASTU_Network_Library 👁🗨 We are here to keep you updated! ➲ Admin 📩 👤 @NS_Nazu Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷] |➲| @ASTU_Network
إظهار المزيد4 800
المشتركون
+1124 ساعات
+537 أيام
+28530 أيام
أرشيف المشاركات
4 803
በአዲስ አበባ ከተማ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ሊከሰት እንደሚችል ተነገረ
ዝቅተኛው የሙቀት መጠን እስከ 1.4 ዲግሪ ሴልሺየስ ሊወርድ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስጠነቅቋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ለመናኸሪያ ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ባለፉት አስር ቀናት የታየው ደረቅና ቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ ቀናትም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች አመልክተዋል።
ከዋና ከተማዋ በተጨማሪ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በመካከለኛው ደቡብ እና በደጋማ የሀገሪቱ ክፍሎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እጅግ ከፍተኛ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በእነዚህ አካባቢዎች በብዙ ቀናት የሙቀት መጠኑ ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በደጋማ ስፍራዎች ለሚኖሩ ነዋሪዎችና ለግብርና ስራዎች ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ይጠበቃል።
የዘንድሮው የበጋ ወቅት መደበኛና ከመደበኛ በታች የሆነ የዝናብ መጠን እንደሚኖረው የተተነበየ ቢሆንም፣ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ግን በተወሰኑ አካባቢዎች ለውጥ ሊታይ ይችላል። በዚህም መሰረት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በመጨረሻዎቹ ቀናት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።
የኢንስቲትዩቱ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ይህ ብርቱ ቅዝቃዜ ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተጠናከረና እየተስፋፋ የመጣ ክስተት ነው። በመሆኑም ህብረተሰቡ በተለይም ለቅዝቃዜ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የአየር ሁኔታ መረጃዎችን በንቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል።
ምንጭ፦ መናኸሪያ ሬዲዮ
4 803
በጅማ ዩንቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የስፖርት ፌስቲቫል በሁለቱሞ ፆታ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ስማችሁ የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ የገባ ተማሪዎች ዛሬ የፎቶ ፕሮግራም ስለሚኖር ጠዋት 4:00 ሳትበታተኑ በየቡድናቹ ኦዳ ነቤ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።
©️
ASTU SU 🤝 ASTU Sport
|| @ASTU_Network4 803
Barattoonni dhiiras ta'ee shamarran festival yuunivarsiitii jimmaatti qophaa'e irratti ispoortii gosa garaa garaa irratti galmooftanii calallii hunda dabartanii leenji'aa(shaakalaa) turtan guyyaa boruu sagantaa suuraa waan qabaannuf garee keessan waliin sa'aati 4:00 irratti galma odaa Nabeetti akka yeroon argamtan kabajaan isin beeksifnaa
በጅማ ዩንቨርሲቲ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ ስፖርት ፌስቲቫል በሁለቱሞ ፆታ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ስማችሁ የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ የገባ ተማሪዎች ነገ የፎቶ ፕሮግራም ስለሚኖር ጠዋት 4:00 ሳትበታተኑ በየቡድናቹ ኦዳ ነቤ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።
For the sports festival organized by Jimma University, all male and female students whose names are on the final list for different sports are informed that there will be a photo session tomorrow. Please arrive at Oda Nabe Hall with your respective teams at 4:00 a.m. on time.
4 803
+2
#Fun 😸
The probability others know:
P(E) = n(E)/n(S)
*The probability we know: 👇😅4 803
Hello everyone, how’s it going?
As I mentioned before, we’re working to organize all the course materials from our campus into one library group — ASTU Network Library.
I’ve started setting this up, and now I need students from each department to join as admins. These admins will be responsible for posting any materials related to their department’s courses and will serve as representatives for their department in the library group.
Requirements:
1. Must be a current student in the department they represent.
2. Should be dedicated to the group and able to post course materials whenever available.
3. Preferably, they should be class representatives.
If you’re interested, please contact me: Nazarene
Join our official library group:
📚: @ASTU_Network_LibraryThank you! || @ASTU_Network
4 803
♟ ASTU Chess Team in Preparation
The ASTU Chess Team is actively preparing for the upcoming Inter-University Sports Festival, to be conducted at Jimma University.
As part of their preparation, the team is undergoing intensive training and has played several friendly and competitive matches with the Adama City Chess Club, gaining valuable experience and strengthening their skills.
✨ We wish our ASTU Chess Team great success, sharp focus, and victory in every match. May your preparation turn into outstanding performance and make our university proud! ♟🏆
Join our Official telegram channel:-https://t.me/AstuChessc
4 803
ለነዳጅ ማደያ ምርቃት በሚል ነዳጅ ያላአግባብ ያፈሰሱ አካላት የሶስት ወር እገዳ ተጣለባቸው
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ አገር የሚገባን ነዳጅ ኃላፊነት በተሞላው መንግድ ለህዝብ ጥቅም ማዋል ሲገባው ያለአግባብ እንዲፈስ ያደረገ ማደያ ለሶስት ወር ከነዳጅ ጭነት ትስስር እገዳ ተጣለበት፡፡
በአሪሲ ዞን ዳክሲሰ በሚባል ቦታ ሥራ የጀመረ ግሎባል የሚባል ማደያ ከነዳጅ መቅጃ ማሽን ነዳጅን ሲያርከፈክፍ በማህበራዊ ትስስር ገፆች መታየቱን ተከትሎ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ጉዳዩን በማጣራት ድርጊቱን መፈጸሙን አረጋግጧል። ይህን ድርጊት የፈጸመው ማደያ በነዳጅ ግብይት አዋጅ ቁጥር 1363/2017 አንቀጽ 7(10)ስር ያለዉን ግዴታ በመጣስ በአንቀጽ 11(9)መሠረት ህገ ወጥ ድርጊት ፈጽሞ ስለተገኘ የወንጀል ተጠያቂነቱ የሚቀጥል ሆኖ በአዋጁ አንቀጽ 23(1)መሠረት ለ3ወራት ፈቃዱ ታግዷል፡፡
ከባለስልጣን መ/ቤቱ የማደያ ፈቃድ አውጥተው ምርቱን ለህብረተሰቡ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ፈቃድ ሲሰጥ ከሚገቡ የፈቃድ ግዴታዎች መካከል አንዱ የነዳጅ ደህንነቱን እና ደረጃውን በጠበቀ ማዳያ በቂ የሆነ የድንገተኛ አደጋ መከላከያ ግብዓቶችን አሟልቶ በወጣው የእለታዊ ዋጋ በጥብቅ ዲስፕሊን እና ጥንቃቄ ለተጠቃሚው መሸጥ ግዴታዎችን የጣሱ በመሆኑ ባለስልጣን መ/ቤቱ ጉዳዩን ተከታትሎ ተገቢው የህግ ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ክትትል እንደሚያደረግ ያሳውቃል። ህገወጥ የነዳጅ ግብይትን የመከላከል ስራ የመላው ህዝብ ሃለፊነት በመሆኑ ይህን ድርጊት ለጠቆማችሁ ምስጋነችን እናቀርባለን። ዳጉ_ጆርናል
@Ethionews433 @Ethionews433
4 803
#Fun 😸
So... if this is accurate and ppl chose correctly, it basically means there is one female for every two males... lol 🙈😅
.
4 803
#Random
I just wanted to know this for fun! 🙂 Vote for your gender so that I can see which number is greater! 😁
4 803
Caterpillar የተሰኘው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች አምራች ድርጅት በተሽከርካሪዎቹ ላይ AI Automation መግጠም መጀመሩን አስታውቋል።
"Cat AI Assistant" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ሲስተም የተሰራው Jetson Thor በተሰኘ የNvidia physical AI አማካኝነት ነው።
ከግዙፉ የAI Hardware አምራች ድርጅት NVidia ጋር በመተባበር መካከለኛ መጠን ባላት CAT 306 CR Mini ኤክስካቫተር በመግጠም ለእይታ አብቅቷል።
በCaterpillar የDataና AI ምክትል ፕሬዘዳንት የሆነው Brandon Hootman እንደተናገረው CAT AI assistance የማሽን ኦፕሬተሩን ጥያቄዎች መመለስ፣ የደህንነት መረጃዎችን መስጠት፣ስራዎችን ማቀድ እንዲሁም የተለያዩ የሳይት መረጃዎችን በመሰብሰብ አንድ project ምን ያክል የግንባታ እቃዎች እንደሚያስፈልጉት calculate ማድረግ ይችላል።
*Physical AI is artificial intelligence that lives inside physical machines robots, vehicles, drones, or devices that can sense the real world, think, and take actions in it.
ስለNVIDIA Jetson Thor የበለጠ ማንበብ ከፈለጋችሁ
👉 Introducing_NVIDIA_Jetson_Thor, the_Ultimate_Platform_for_Physical_AI
©️@bighabesha_softwares
4 803
#SoMCME
Attention second-year SoMCME students!
Some students sent me this schedule and asked if it's right. I can't be sure of it. It says there is an "Introduction to Engineering Materials" exam in the afternoon. Almost everyone takes the exam tomorrow except a few, not this afternoon. But I just posted it here so that you can check it yourself and act accordingly. That's it! 🤷♂️😶
|| @ASTU_Network
4 803
#Library #Update
ከዚህ በፊት በገና በዓል ምክንያት የዩኒቨርስቲው ቤተ-መጽሐፍት እስከ ሐሙስ እለት ማታ እንደሚዘጉ ከዩኒቨርስቲው የቤተመጽሐፍት አገልግሎት መረጃ እንዳገኘን ነግረናችሁ ነበር።
አሁን ግን ነገ ፈተና በመኖሩ ምክንያት ተማሪዎች እንዲያነቡ በማሰብ ቤተመጽሐፍቱ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ አገልግሎት እንዲሰጡ እንደተወሰነ የቤተመጽሐፍት አገልግሎት ቢሮው አሁን ጠዋት አሳውቆናል።
በመሆኑም ተማሪዎች ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ቤተ-መጽሐፍቱን መጠቀም ትችላላችሁ።
|| @ASTU_Network
4 803
Repost from 𝐀𝐒𝐓𝐔 𝐄𝐧𝐭𝐞𝐫𝐭𝐚𝐢𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 ™️
I posted this meme last year when it was final exams during Christmas time... 🫠 The same thing happened this year and I posted the same meme... 😁
And next time will likely be the same and I'll post this meme again! 😅
Anyways, Merry Christmas! 🌲❤️🔥😂
.
4 803
+5
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች የገና በዓልን በደስታና በአንድነት ከዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ጋር አከበሩ
==================================
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ከተማሪዎች ጉዳይ ዲንና ከተማሪዎች ህብረት ጋር በመተባበር የገና በዓልን በደስታና በአንድነት በተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ታህሳስ 29/ 2018 ዓ. ም አከበሩ::
በዚህ የበዓል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ተማሪዎችና የተለያዩ ክፍሎች ሰራተኞች ተገኝተው የአንድነት፣ የፍቅርና የመተጋገዝ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ሰለሞን ጥሩነህ በንግግራቸው ተማሪዎች ብቸኝነት ሳይሰማቸው የገና በዓልን በአንድነት፣ በመተጋገዝና በክርስቶስ ፍቅር ተምሳሌት እንዲያከብሩ አሳስበዋል። በዓሉ የፍቅር፣ የይቅርታና የአብሮነት መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን በመጠቀስ፣ ተማሪዎች እርስ በርሳቸው በመደጋገፍ የበዓሉን ደስታ እንዲጨምሩ ጠይቀዋል።
ዶ/ር ሰለሞን በዓሉ የማህበራዊ እሴቶችን ለማጠናከር እና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የሰላምና የትብብር ባህልን ለማበረታታት ያለውን ሚናም አስረድተዋል።
ተማሪች በበኩላቸዉ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች በአሉን ከእነሱ ጋር በማክበራቸዉ የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዋል::
ASTU, the very University for you!
We are dedicated to innovative knowledge!
4 803
Repost from 𝐀𝐒𝐓𝐔 𝐄𝐧𝐭𝐞𝐫𝐭𝐚𝐢𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 ™️
POV: IT'S CHRISTMAS TODAY! 🎄🥳
Everybody wishes an awesome Christmas! 😌🥰😇
How do your families celebrate: 🍗🍖🥩🥂😍😘
How do your teachers celebrate it at home: 😎😜😝😋🥚🥩🍗
*ASTU: 👇😸
4 803
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንዲሁም የ ASTU Network ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
📖 — ሉቃስ 2፥11 “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”🌲 መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ🎄 || @ASTU_Network
4 803
Repost from 𝐀𝐒𝐓𝐔 𝐄𝐧𝐭𝐞𝐫𝐭𝐚𝐢𝐧𝐦𝐞𝐧𝐭 ™️
📞 እቤት ደወልኩ... 📲
Me: Hello mom 👋 እንዴት ናችሁ?
Mom: ደህና ነን ልጄ! እንኳን አደረሰህ!
እኔም ..😰🥺🥹💔 ... "እንኳን አብሮ አደረሰን" አልኩኝ ልቡ ከተሰበረ ሰው በሚወጣ ድምፅ... 💔🥹
Mom: ምነው ደህና አይደለህም እንዴ? ችግር አለ?
... ይህንን ስትናገር ከስር ከስር የገና በዓል መዝሙር ይሰማ ነበር ... እኔም ለተወሰኑ ሴኮንዶች ዝም ብዬ እቤት ያለውን ነገር ማሰብ ጀመርኩ 🤔... Imagine ማድረግ ጀመርኩ ... እቤት በዓል ሳከብር እና በዋዜማው ምሽት የሚደረጉ የተለመዱ ነገሮች በምናቤ ታዩኝ 🥹🥺 ... ቤቱ ሞቅ ሞቅ እያለ ነው 🥰 ... ሽር-ጉዱ ተጧጡፏል 🔥 ... እናም ከቤተሰብ ጋር ብሆን እንዴት ያለ ጊዜ ላሳልፍ እንደምችል ማሰብ ጀመርኩ 😔... ይህን ሳስብ ልቤ ተሰበረ 💔
በዚህ ሃሳብ ተውጬ ለካ mom ደጋግማ እየጠራችኝ ነበር... እኔማ ሌላ አለም ውስጥ ገብቼ ነበር 😁
"ኧረ ደህና ነኝ ... የገና ዋዜማው እንዴት ነው?" አልኩ 😣
Mom: "ደስ ይላል ፤ ግን በጣም ደብሮናል"... አለችኝ። 😰
Me: "ምንድነው ምን ተፈጠረ?" ብዬ ጠየኩኝ...😨
Mom: "ያለአንተ በዓልን ስናከብር ደስ አይልም" አለችኝ... 🥲🥲🥲
ይህን ስትለኝ ቀድሞ በፈተና እና በተለያዩ ምክንያቶች የተሰበረው ልቤ 💔 በድጋሚ ተሰበረ 💔💔 ... ከዚያም ተሰባበረ 💔💔😞
እኔም ... "አዎ ምን ይደረጋል እንግዲህ" አልኩኝ። 😢
Mom: በቃ አይዞህ ፤ በርታልን!..😥
Me: እሺ mom መልካም ምሽት 🥹
Mom: ደህና እደርልኝ! 💔
Me: 🥺😍😞😰😭💔... 👋
🎄 ለማንኛውም መልካም የገና በዓል 🎅
.
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
