ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

♥ፍኖት…✍🏾

♥ፍኖት…✍🏾

الذهاب إلى القناة على Telegram

#አጫጭር ታሪኮች #ከመፅሀፍ የወጡ ሀሳቦች #የግል ምልከታዎች #ትዕዝብቶች #እውነታዎች ያገኙበታል። ………………አሁኑኑ ይቀላቀሉ😍 😊😊😊😋 youtube ቻናላችንን subscribe ያርጉ👍 https://youtube.com/@finottube-u8w?si=a-13vZOq0UKv8BnP

إظهار المزيد
1 011
المشتركون
-224 ساعات
-67 أيام
-2430 أيام
أرشيف المشاركات
ተኩላ በምክር በግ ሊሆን አይችልም❗️
@Evangadi21 @Evangadi21

ድህነት ብዙ ሴቶችን ገንዘብ ያለው ወንድ ለትዳር ብቁ እንደሆነ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል❗️
@Evangadi21 @Evangadi21

“ጥበብና እምነት ከፊትህ ቢቀርቡ ቢቻልህ_ እምነትን ምረጥ፥ ባይቻልህ ደግሞ እምነትን አስቀድም” ::
📚እመጓ @Evangadi21

09_ላሜ_ቦራ_Lame_Bora_Theodros_Kassahun.mp37.35 MB

ትቼው እረኝነቴን እሷን እሷን ሳይ... ከብቶቼ ከሰው ማሳ ገቡ...❤

ሰው ካላበላሸው ፍቅር አያረጅም‼
@Evangadi21

የማፍቀርም ዕድሜ አንድ ቀን ሲያከትም የትውስታን ያህል ኃያል ነው መርሳትም። ትዝታን በማልቀስ ትዝታን በማውሳት ትዝታን በዘፈን ትዝታን በግጥም አቅም ካላዋሱት እንዳስታወሱት ነው ሰውን የሚረሱት❗️ 📚ምናልባት አንድቀን @Evangadi21 @Evangadi21

ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ?🙌 ዛሬ ድንቅ የሆኑ  ግጥሞች🥰... ልብ አንጠልጣይ ድርሰት😘... የተዋቡ ወጎች 😍...አጓጊ ገጠመኞች😂😭...ያለበት ግሩኘ ላስተዋውቃችሁ🤗 😋መፃፍ ውስጤ ነው…🤗 🕯️ስሜትን በቅኔ፣ ልብን በቃል እተርካለሁ።✍️ ❤️ ለፍቅር 🤍 ለይቅርታ 🕊️ ለሐዘን 🎂 ለልደት ⛪ መንፈሳዊም…      ✨ ርዕስ ስጡኝ፤ ቃላትን አበባ አድርጌ እሸልማችኋለሁ 🌸 “የልባችሁን ጥልቅ ቃል በብዕር አበራዋለሁ፣ ያልተነገረ ስሜት በግጥም እናገራለሁ…” ✍️🖤   ግጥምን ከህላዌ ጋ✍🫶 join እያላችሁ ተቀላቀሉ ትደሰቱበታላችሁ😍👇 https://t.me/poem_Hiwe

ሲጀመር ሰውን የምትቀርበው ሌላ ሰው ስለሆነ ነው ሁሉን ነገር ስታውቀው ሌላ መሆኑ ይቀራል ።ትንሽ የማይታወቅ ነገር ማስቀረት አብሮ ለመኖር ሁሌም ይጠቅማል !! 📚አለመኖር @Evangadi21 @Evangadi21

🔥 በየቀኑ ልብ የሚነኩ ጽሁፎች እና የማይረሱ ስሜቶች ይጠብቁሃል! ❤️📖 👉 ከሌሎች ተለይተህ ጥሩ ነገር ማንበብ ከፈለግህ ቻናሉን ተቀላቀል—እዚህ የልብ ታሪክ ይነገራል! 🔥❤️ https://t.me/senoriah https://t.me/senoriah https://t.me/senoriah https://t.me/senoriah

ከአመታት በኋላ ተገናኘን ሳይሆን ተያየን ...ለዚያውም አያታለሁ ብዬ ያልጠበኩት ቦታ ..እኔ ስላየኋት እላፊ ደስ ብሎኛል የምር በፊት ከነበራት ውበት 2 እጥፍ ጨምራለች! እኔን ግን እንድታየኝ አልፈለኩም ነበር! በሰዓቱ ከምቾት ቀጠና ወጥቼ ሰውነቴ ከስቶ ፊቴ ገርጥቶ ፀጉሬ ተንጨባሮ  ለአለባበሴም ሆነ ለፀጉሬ ብቻ ሰው ምን ይለኛል ተብሎ ለሚደረግ ወይም በሰው ፊት ደምቆ ለመታየት ለሚደረግ መሽሞንሞን ደንታ የማይሰጠኝ ሰዓት ላይ ነበርኩ!  አዎ ባታየኝ ምኞቴ ነበረ ግን ለሰከንዶች ተፋጠጠን አየችኝ አየኋት አስተያየቷ የዋዛ አልነበረም ለመጀመሪያ ጊዜ ስወዳት የነበረው ስሜት እንዲሰማኝ ጋበዘችኝ ... ከወትሮው በተለየ መልኩ ታቦታቱን ለማክበር የመጣው ሰው እየጎረፈ ባለበት በዛ ጎን ለጎን ሆኖ ሰው በሚጠፋፉበት ሰዓት ነበር ከሰንበት ተማሪዎች ጋ እየዘመርኩ ከመዝሙሩ ጋ ትዝታ ስላለኝ ተመስጬ ድንገት ቀና ስል  ከዛ ሁሉ ሰው መሃል  ፊት ለፊቴ ያየኋት። መለከት ይነፍል ..ከበሮው ይጮሃል.. ጭብጨባና እልልታው ደምቋል መዝሙር ይዘመራል
አባ ዘራ ብሩክ ፃድቁ አባታችን... .ክብርህ ይሁነን ግርማ ሞገሳችን ...ፀጋህ ይትረፈን በረከት ይሙላብን ከመዳህኒአለም በምልጃህ አቅርበን...ተግቶ የፀለየ ..
በኔ በኩል ዝማሬዬን አላቆምኩም ግን እንተያያለን ፈገግ አልኩ ፈገግ አለች ሰላም ልላት ፈለኩ እንዴት ልበላት? ምን ማረግ እንዳለባችሁ ጠፍቷችሁ ያውቃል? በቃ እንደዛ ! ወዲያው ከዛጋ ተሰወርኩ ቆየት ብሎ በግንባሬ ሰላም ብላትስ ኖሮ የሚል ፀፀት ተሰማኝ! ታቦታቱ ወደ መንበራቸው ሲመለሱ ድጋሚ ከዛ የህዝብ ማዕበል ውስጥ ባይኔ ልፈልጋት ከራሴ ጋ ቀጠሮ ያዝኩ!   አየሁ አየሁ አየሁ... ፈለኩ ፈለኩ ...ማተርኩ ማተርኩ ...አሰስኩ አሰስኩ ...  ተንከራተትኩ ተንከራተትኩ .... እንደምንም በድጋሜ አየኋት ግን ባሁኑ በጣም ተራርቀናል እይታየዬን ወደ ሌላ አቅጣጫ ቀይሼ ስመለስ ጠፋችብኝ! ከዛ በኋላ ነው ኤጭ የሚል ቃል ውስጤ ያቃጨለው! ኤጭ ቆይ ምን ልፈጥር ነው ባገኛትስ? እሷ እንደኔ አገርሽቶባት አሁንም አረሳሁህም የሚል ፊት አታሳየኝ ! ሌላ አለም ውስጥ ነዋ የኖረችው ! ብታሳየኝስ ምን ላመጣ?ሁለታችንም የተለያየ አለም ሰዎች ሆነናላ ! እና ብንገናኝ ምን ጥቅም?  ኤጭ ማለት መተው ነው! ኤጭ ማለት ተስፍ መቁረጥ ነው! ኤጭ ማለት  መድከም ነው! ኤጭ ማለት መገደብ ነው! እንዲሁ እንዳየኋት ፊቴን ሳልመልስ እዛው ቤተክርስቲያን ግቢ ትቻት ወደ ቤቴ ነጎድኩ ገጽታዋ ግን ፊቴ ላይ ነው እንቅፋት ቢሆን ስንቴ በጣለችኝ ነበር! ምናገባኝ ከፈለጋችሁ ሼር አርጉላት ❗️ @Evangadi21 @Evangadi21

ተለያየን ማለት ተጣላን ማለት አይደለም ...የሆነ ጊዜ ተቀራረብን ተዋደድን..ጥሩ ጊዜ አሳለፍን የሚናፈቁ ትዝታዎችን አፈራን... ከዛ መንገዳችን ተለያየ እና እኛም ተለያየን አደለ?...ለምን ጠላት እንሆናለን? ጥልን ምን አመጣው? በጎሪጥ መተያየት ውይ እሱ ባለበት ውይ እሷ ያለችበት አልሄድም ማለትን ምን አመጣው? ለምንድነው ጥሩ ነገር የማናስበው? ለምንድነው ስለዛ ሰው ክፉ ነገር ብቻ የምናወራው ሀሜቱንስ ምን አመጣው? እርግጥ ነው ተበድለን ይሆናል ግን በሆነ ጊዜ መልካም ተደርጎልናል እነዛ ሰዎች አስደስተውናል ነገን አስናፍቀውናል.. እኛምኮ በድለን ይሆናል ሰው ነንና በደሉን እንጂ በድለናል አንልም እንጂ ምናልባት በዳዮቹ እኛ እንሆናለን.... ያለፈው አልፎ ዛሬ ላይ መንገዳችን ተለያየ ተብሎ ይሄን ያህል አይን ያወጣ ጥላቻን ምን አመጣው? እንዲው ተዋደን በሩቁ መቀጠል አንችልም ነበር? ይቅር መባባሉምኮ አንድ ጤንነት ነው ! ጥላቻ መርዝ ነው ውስጥ ውስጡን እያደር ይገ-ድላል! መተው መለያየት ከመጣላት ጋ አይገናኝም! ነገሮችን ባናከብድ ጥሩ ነው፡፡ Tiktok @Evangadi21 @Evangadi21

እ..."ናት" አንዳንድ ጊዜ በንግግሮቻችን መሐል የሆነን ነገር ለመግለጽ ፈልገን፤ ሀሳቡን የሚሸከሙ ቃላቶች ያጥረንና " እ.. እ..." እያልን ቃላትን ፍለጋ ላይ ታች እንላለን። እናትነትን በሦስት ፊደላት ወስኖ መግለጽ መቻል ቅድስና ይፈልጋል። የምሬን'ኮ ነው፤ እንደውም ሲመስለኝ ስም አውጪው ራሱ አባት፣ ወንድም፣ እህት ብሎ እሷ ጋ ሲደርስ፤ ሀሳቡን ለመሸከም የሚበቃ ቃል አጥቶ ሚያደርገው ሲያጣ ነው መሰል እ... ናት ብሎ የዘጋው። በቃ እ.. ናት☺️ @Evangadi21

ጅል የሚነቃው ሲዘንብ ነው፡፡ ያኔ ይበሰብሳል እንጂ መጠለያ አያገኝም፡፡ የሚወዱን ሰዎች በፍቅር እንደ ዣንጥላ ከበላያችን የሚዘረጉበት ዘመን አለ፤ ከብቸኝነት ዶፍ ከመልከስከስ ንዳድም ጠባቂዎቻችን የሚሆኑበት፡፡ ሁልጊዜ ግን እንደዚያ አይቀጥልም፣ አንድ ቀን ግፋችን ከብዷቸው ቸልተኝነታችን አድክሟቸው እንደ ዣንጥላ ይታጠፋሉ፡፡ ወይም አያያዛችንን ዓይቶ ጠንካራ ነፋስ ከእጃችን ይነጥቃቸዋል፡፡ ዶፍ ውስጥ ካለመጠለያ የመቆሚያ ዘመን አለ፡፡ ጅል ግን ይኼን ቀድሞ አይረዳም፡፡ ጅል ከጅልነቱ ይፈወስ ዘንድ፤ በመከራ መጠመቅ አለበት፡፡ በመከራ ያልተፈወሰ ጅል፤ ሞት ብቻ ነው የሚገላግለው።💯 📚አልተዘዋወረችም @Evangadi21

​🎁 በየቀኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ እውቀቶችን በነፃ ያግኙ!🦊 ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የቴክኖሎጂ አለምን በቀላሉ ለመረዳትና ስልክዎን በብቃት ለመጠቀም፡ ​✦ የተመረጡ እና Premium (Paid) በቀላሉ የማይገኙ Android እና iOS አፖች ✦ ለስልክና ለPC የሚሆኑ ምርጥ ገራሚ ጌሞች ✦ ከዓለም ዙሪያ አስገራሚ የቴክኖሎጂ መረጃዎች ✦ የስልክዎን ፍጥነት በ2X የሚጨምሩ አጠቃቀሞች ✦ ጠቃሚ የስልክ አጠቃቀም Trick እና Tip-ዎች ​ከስር ያለውን JOIN የሚለውን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ👇 JOIN CHANNEL / ቻናሉን ይቀላቀሉ

"
ብዙዎቻችን እንደጨርቅ ብንጠመዘዝ ከውስጣችን ተንጠባጥቦ የሚወጣው ፈረንጅና ፈረንጅ ነኬዎች በምላሳቸው፣ በድርሳኖቻቸውና በማባበያ ሙርጣቸው በአንጎላችን የዘሩት ባርነታችን ነው፡፡"
📚መረቅ ✍🏾 አዳም ረታ @Evangadi21 @Evangadi21

===============እረበሻለሁ===========              እንደሰው ስሜቴን እሚረብሹ ነገሮች ትንሽ እሚባሉ አይደሉም።      ግን ደግም ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፥ በሰው ሀገር ጎዳና ዳር ወድቀው  ፥ እሚያሳይ vedio ስመለከት እና        አባት የሌላት ልጅ ፥ ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ፥ ሳይ እንዲህ አይደለሁም ፤ "እረባሻለሁ!" ደግሞ እኮ ምንም ላላደርግ።     የመጀመሪያውስ እሺ ብሔርተኝነት(strong nationalism i.e chauvinism) እሚባለው  የዘመን መንፈስ ተጋብቶብኝም ይሆናል ። የሁለተኛውስ?                                         ማሙሽ ✍️ @Evangadi21

በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ፈተናዎች የሚፈጥሩብንን ስሜት በቃል ማስቀመጥ የሚቸግርበት ዕለት አለ፡፡ አንዳንድ ስሜቶች መብራራት አይችሉም። አንዳንድ ቁስሎች የሚሽሩት በሰው ቃል ሳይሆን በጊዜ ርዕቱነት ነው:: በሰውም፥ በራሳችንም ልንድናቸው ያልቻልናቸውን ሕመሞች ጊዜ እንዲያከመን ዕድል መስጠት አለብን፡፡ 📚ፀሐይ ከጨለማዬ ምን አለሽ

“መሄድ ያለበትን ሁሉ እንዲሄድ ስትፈቅድ የሚቀረው ከሁሉም በላይ የምንፈልገው ነገር ነው፡፡"
@Evangadi21

“መሄድ ያለበትን ሁሉ እንዲሄድ ስትፈቅድ የሚቀረው ከሁሉም በላይ የምንፈልገው ነገር ነው፡፡"
@ Evangadi21