cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

HEALTHY MIND psychiatric/የስነ አእምሮ CLINIC

ጤናማ አእምሮ የስነአእምሮ ክሊኒክ በonline፣በስልክ እንዲሁም ቤት ለቤት የማማከር እና የስነ አእምሮ ህክምና በተለያዪ የስነ አእምሮ ባለሙያዎች በኩል እየሰጠ ይገኛል። ለማማከር/For consultation Telegram~ https://t.me/psychaconsult phone no~ 0949220950

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
201
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-27 أيام
-530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🌟Healthy mind psychiatric clinic በተለያዩ የስነ አእምሮ እና የስነ ልቦና ጉዳዮች ላይ ዋናዉ አድርጎ በተጨማሪነት የተለያዩ የጤና እና ጤና ነክ ጉዳዮችም ላይ የስነ ተዋልዶ እና የእናቶች ክትትልንም አካቶ እየሰራ ይገኛል። ለተማሪዎችም በትምህርት እንዲሁም በተለያዩ የህይወት ዘርፎቻቸዉ እንደፆዎታዊ ግንኙነት የአቻ ለአቻ ግፊት የመሳሰሉት ላይ በመርዳት ላይ እንገኛለን። በየትኛዉም ቦታ እና ሰአት አገልግሎታችንን መግኘት እንደምትችሉ ለማሳወቅ ወዳለዉ ። ለዚህም በዉስጥ መስመር @psychaconsult በመፃፍ ወይም በስልክ ደግሞ ከታች በማስቀምጥላችሁ ልታገኙን ትችላላችሁ። psychiatry professional Nuhamin ☎️0949220950 psychologist saron ☎️0969223795 በአካል ለምትፈልጉ 📍በአዲስ አበባ 📍በሀዋሳ 📍በዲላ 📍በአምቦ እና አካባቢዋ 📍በአሰበ ተፈሪ ልታገኙን ትችላላችሁ ። ☎️ 0949220950 ደዉለዉ ያሳዉቁን። ለሌሎች በማጋራት ሰዎችን እርዱ 🔗🔗የቻናሉ link 👇👇 http://t.me/yourmindmatter
إظهار الكل...
HEALTHY MIND psychiatric/የስነ አእምሮ CLINIC

ጤናማ አእምሮ የስነአእምሮ ክሊኒክ በonline፣በስልክ እንዲሁም ቤት ለቤት የማማከር እና የስነ አእምሮ ህክምና በተለያዪ የስነ አእምሮ ባለሙያዎች በኩል እየሰጠ ይገኛል። ለማማከር/For consultation Telegram~

https://t.me/psychaconsult

phone no~ 0949220950

በፍጹም አታቁም! “አንድ ጊዜ ነገሮችን በቀላሉ የማቆም ልምምድ ከጀመርክ ሁኔታው ልማድ ይሆንብሃል” - Vince Lombardi በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ጠቃሚና ዋጋ ያለው ግብን የምትከታተል ከሆነ፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከዚህ በታች ያሉትን ሃሳቦች ማስተናገድህ አይቀርም፡ • “ይህ ነገር ካሰብኩት በላይ ከባድ ነው፡፡” • “ለምንድን ነው ይህ ነገር ይህን ያህል ረጅም ጊዜ የወሰደብኝ?” • “ይህ ነገር ወደፊት አላራምድ አለኝ፡፡” • “ይህ ግብ ደጋግሞ እየተበላሸብኝ ነው፡፡” • “ይህንን ነገር መቀጠል የምችል አይመስለኝም፡፡ ምን አስቤ ነው የጀመርኩት?” በእዚህና በመሰል ስሜቶች ከጀመርከው ነገር እንዳትገታ ከፈለክ “በፍጹም አላቆምም” የሚልን አመለካከት አዳብር፡፡ ተስፋ አለመቁረጥ የአመለካከት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም አመለካከት ልታዳብረው የምትችለው አመለካከት ነው፡፡ ይህንን አመለካከት ለማዳበር ከሚረዱህ ልምምዶች መካከል የሚከተሉትን ሃሳቦች ደግመህና ደጋግመህ ለራስህ መናገር ነው፡- • ነገሮች ሲከብዱብኝ በዓላማዬ ጸንቼ እቀጥላለሁ፡፡ • መንገድን እፈልጋለሁ ወይም እፈጥራለሁ፡፡ • ማንኛውም ችግር መፍትሄ አለው፣ እኔ ደግሞ መፍትሄውን ለማግኘት ብቃቱ አለኝ፡፡ • በየቀኑ የሚሰራውንና የማይሰራውን የመለየትን እውቀትና ግንዛቤ እያገኘሁ ነው፣ ይህም ማለት በጥንካሬና በጥበብ እየጨመርኩኝ ነው ማለት ነው፡፡ • መሰናክሎች ጊዜያዊ ናቸው፡፡ ከላይ ያሉትን ሃሳቦች ለራስህ ከተናገርክ በኋላ ቆም ብለህ አስብ! እንደገናም ወደፊት ቀጥል! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) Healthy mind Please join and share👇👇👇 http://t.me/yourmindmatter
إظهار الكل...
HEALTHY MIND psychiatric/የስነ አእምሮ CLINIC

ጤናማ አእምሮ የስነአእምሮ ክሊኒክ በonline፣በስልክ እንዲሁም ቤት ለቤት የማማከር እና የስነ አእምሮ ህክምና በተለያዪ የስነ አእምሮ ባለሙያዎች በኩል እየሰጠ ይገኛል። ለማማከር/For consultation Telegram~

https://t.me/psychaconsult

phone no~ 0949220950

👍 2
የተዳፈነ ስሜት ረመጥ ነው! **** ስሜቶቻች(Emotions) ህይወታችን ጣዕም ይኖራት ዘንድ የተሰጡን ውድ ስጦታዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ:: በሚያስደስተው መደሰት፣ በሚያስለቅሰው ማልቀስ፣ በሚያስፈራው መፍራት፣ በሚያናድደው መናደድ፣ በሚያስጠይፈው መጠየፍ ካልቻልን ከሮቦቶች በምን እንሻላለን? Limbic System የተሰጠን ለይስሙላ አይደለም:: ከአዕምሮ ህመም ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ የስሜት መዛባት ነው:: Mania ላይ ከሚታየውን ምክንያት አልባ ፈንጠዝያ እስከ Melancholic depression ላይ የሚታየው ስሜት አልባነት የየአዕምሮ ህመም ምልክቶች ናቸው:: አሁን ላይ ስለ ድብርት፣ የተራዘመ የሃዘን ችግር(Prolonged grief disorder) እና መሰል ችግሮች አብዝተን መስማታችን: ምናልባትም በሃዘን ወቅት ይደረግ የነበረው 'እርምን የማውጣት' ክዋኔ እየቀረ ከመምጣቱ ጋር ይገናኝ ይሆን?? የታመቀ ስሜት ልክ እንደ ረመጥ ነው: እፍ የሚለው ሽውታ ሲገጥመው መልሶ መፋጀቱ አይቀርም:: ደግሞም እንደ አዥ ነው: ቀስ በቀስ ሙሉ የሰውነት ስርአትን የሚያውክ እና ከበሽታ የሚጥል:: ስሜቶቻችንን አጉል መግታት ከተፈጥሮ እና ከፈጣሪ እንደመጣላት ነው ብዬ አስባለሁ:: ይህ የታመቀ ስሜት ከተዳፈነበት አፈፍ ብሎ: ብዙዎችን ለተስፋ መቁረጥ እና ውድ የሆነች ነብስያቸውን ለማጥፋት እስከመወጠን ሲያደርሳቸውና እና ከፈጣሪያቸው ጋር ሲያኳርፋቸው አይተናልናም: ሰምተናልናም:: ቸር ይግጠመን! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://t.me/yourmindmatter
إظهار الكل...
1
ጥልቅ ትርጉም የሚሰጡ 6 የሕይወት ታሪኮች! 1- አንድ ጊዜ የአንድ መንደር ሰዎች ዝናብ እንዲጥልላቸው ለመጸለይ ወሰኑ። በጸሎቱ ቀን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዣንጥላ ይዞ የመጣው ግን አንድ ሰው ብቻ ነበር። ይሄ እምነት ነው! 2- ሕጻናትን ወደ ላይ ከፍ አድርገህ ስትወረውራቸው፣ የሚስቁት እንደማትጥላቸው ስለሚያውቁ ነው። ይሄ መተማመን ነው! 3- ማታ ወደ አልጋችን ሄደን ስንተኛ፣ ነገ በሕይወት እንደምንኖር ምንም ማረጋገጫ የለንም፤ ግን የሚቀሰቅሰን አላርም እንቀጥራለን። ይሄ ተስፋ ነው! 4- ስለ ወደፊቱ ምንም እውቀት ሳይኖረን ትልልቅ ነገሮችን እናቅዳለን። ይሄ በራስ መተማመን ነው! 5- ዓለም በስቃይ ላይ መሆኗን እናያለን፤ ግን ትዳር እንይዛለን፣ ልጆችም እንወልዳለን። ይሄ ፍቅር ነው! 6- ሽማግሌው የለበሰው ቲቨርት ላይ እንዲህ የሚል ነገር ተጽፏል "80 ዓመቴ አይደለም፤ የ64 ዓመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የ16 ዓመት ጎረምሳ ነኝ!" ይሄ አመለካከት ነው! መልካም ጊዜ ይሁንልህ፤ ሕይወትህን እንደነዚህ 6 ታሪኮች ኑር። ደግሞ አስታውስ— ጥሩ ወዳጆች የሕይወት ብርቅ ጌጦች ናቸው። ለማግኘት እጅግ የሚከብዱና በሌላ ሊተኳቸው የማይችሉ ናቸው! Via Ankipage http://t.me/yourmindmatter
إظهار الكل...
HEALTHY MIND psychiatric/የስነ አእምሮ CLINIC

ጤናማ አእምሮ የስነአእምሮ ክሊኒክ በonline፣በስልክ እንዲሁም ቤት ለቤት የማማከር እና የስነ አእምሮ ህክምና በተለያዪ የስነ አእምሮ ባለሙያዎች በኩል እየሰጠ ይገኛል። ለማማከር/For consultation Telegram~

https://t.me/psychaconsult

phone no~ 0949220950

👍 1
የመነመነ ማንነት በአካል ከተለያችኋቸው ወራትና ዓመታት ካስቆጠራች በኋላ፣ እንደገና እንደማታገኟቸው እያወቃችሁ በሃሳባችሁና በስሜታችሁ ለመለየት ያልቻላችኋቸው ሰዎች ጉዳይ ሕይወታችሁን ያመነምነዋል፡፡ በቀን ውስጥ ሳታስቧቸው መዋል ካቃታችሁ . . . ስለ እነሱ ስታስቡ ስሜታችሁ የሚወርድባችሁ ከሆነ . . . ከእነሱ ውጪ ኑሮ የማይገፋ ከመሰላችሁ . . . የሌላ ሰውና ሁኔታ ነገር አልጥም ካላችሁ . . . ተስፋ ቢስነት ከተጫጫናችሁ . . . አስቡበት! ለመነሻ የሚጠቅሟችሁ ሃሳቦች • ከእነሱ ውጪ መኖር እንደምትችሉ ራሳችሁን አሳምኑ፡፡ • ራሳችሁን በጤናማ ልምምድና ዓላማችሁን በመከተል “Busy” አድርጉ፡፡ • እነሱን የምታስታውሱባቸውን ነገሮችና ሁኔታዎች ማየትን፣ መስማትን . . . ለመቀነስ ሞክሩ፡፡ • እነሱን ለመርሳት ስትሉ በሚገባ ካላሰባችሁበት ግንኙነትና ሁኔታ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ • ወደፊት እንድትራመዱ የሚደግፏችሁን ሰዎች ለይታችሁ እወቁና ከእነሱ ጋር አዘውትሩ፡፡ ራሳችሁን አትጣሉ! ስሜታችሁንና ሃሳባችሁን መለስ አድርጉ! ቀና በሉ! ይህቺ ሕይወት የተሰኘት ሂደት ገና ብዙ ነገር እንደገና እንድትጀምሩ የማድረግ እውነታ ስላላት እንደገና መጀመርን ልመዱ! https://t.me/yourmindmatter
إظهار الكل...
1
ትላንት ብዙ ዋጋ አስከፍሏችሁ ያለፏችሁት ዛሬም እየደጋገማችሁት የምትኖሩት የተላመዳችሁት ማንነታችሁ ምንድነዉ?? መልስ ለራሳችሁ ያዙ እና ምን ላድርግ እንዴት ልቀይር በሚለዉ ሀሳብ ዉስጥ ስመጡ። ሰናይ ቀን
إظهار الكل...
1
በአእምሮም በአካልም ሸንቀጥ በል! እስቲ ጤንነትን በራስህ መንገድ ግለጸው። ለአንተ ጤናማ ሕይወት ምን ይመስላል? እንዴት እንዲሰማህ የሚያደርግህ ነው፤ ምንስ እያደረግህ ሊሆን ይችላል? ሁላችንም የተለያዩ ፍላጎቶች፣ ምርጫዎችና ፕሮግራሞች ያሉን በመሆኑ አንድ ሰው ብቻ የሚሰጠውን የጤንነት ፍቺ መመልከት አስቸጋሪ ነው። ከዚያ ይልቅ ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርግህ ምን እንደሆነ እወቅ። የትኛው የጤናማ አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና እንቅልፍ ጥምረት ለአንተ ትክክል እንደሆነ ወስንና እርሱን ተከተል። ልክ እንደሌሎች ብዙ ነገሮች፣ ጤናማ ልማዶችም በተሻለ የሚመሰረቱት ቀስ በቀስ ነው። ስለዚህ ማለዳ 12 ሰአት ላይ ተነስተህ የአንድ ሰአት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ራስህን ለማስገደድ ከመሞከር ይልቅ 15 ደቂቃ ለመስራት ሞክር ወይም ከፕሮግራምህ ጋር የሚጣጣም ጊዜ ፈልግ። ስኬታማ መሆንን ለራስህ ቀላል አድርገው። ምግብህን አዘጋጅ ወይም ቀኑን ሙሉ መጠጣት እንድትችል ጠረጴዛህ አጠገብ ውሃ አስቀምጥ። ለአኗኗርህ የሚሆን ጤናማ ልማዶችን በመምረጥ ራስህን ቀስ በቀስ አስተካክል። 📝ተክሉ ጥላሁን
إظهار الكل...
1
የወደፊት ሲደምቅ! “ለወደፊቱ ራእይ የሌለው ሰው ሁል ጊዜ ወደኋላው ይመለሳል” (Kevin Gates) ካለፈውና ካከተመለት ነገር ትምህርትን አግኝቶ ወደፊት ከመገስገስ ይልቅ እሱን እንደገና እያሰቡ የመጨናነቅ፣ የመረበሽና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የሚያጠቃችችሁ ከሆነ ምናልባት የወደፊት ራእይ ያለመኖሩ ምልክት እንዳይሆን ጠርጥሩ፡፡ የወደፊታችሁ እየፈዘዘ ከሄደና ማየት ከተሳናችሁ የኋላችሁና ያለፋችሁት ነገር መድመቅና መጉላት ይጀምራል፡፡ በሌላ አገላለጽ የአንዱ መድመቅ የሌላኛው መደብዘዝ ነው፡፡ ምርጫው ግን በእጃችሁ ነው፡፡ ያለፈ ጉዳት … ያለፈ የተሳሳተ ውሳኔ … ያለፈ ክስረት … ያለፈ ተጀምሮ የተቋረጠ ነገር … ያለፈ ጎድቶንና ትቶን የሄደ ሰው … እየተመላለሰ ስሜታችሁን ቀውስ ውስጥ የሚጨምረው ከሆነ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚቀርፍላችሁ ብቸኛ ነገር የወደፊታችሁን ራእይ ማየትና እሱ ላይ ማተኮር ነው፡፡ የወደፊት ራእያችሁ ካለፈው ታሪካችሁ ሊጠነክርና ሊደምቅ ይገባዋል፡፡ ያለፈው ታሪካችሁ ከሚሰጣችሁ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይልቅ የወደፊታችሁ የሚሰጣችሁ የመጓጓት ስሜት ሊያይል ይገባዋል፡፡
إظهار الكل...
ጥልቅ ትርጉም የሚሰጡ 6 የሕይወት ታሪኮች! 1- አንድ ጊዜ የአንድ መንደር ሰዎች ዝናብ እንዲጥልላቸው ለመጸለይ ወሰኑ። በጸሎቱ ቀን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዣንጥላ ይዞ የመጣው ግን አንድ ሰው ብቻ ነበር። ይሄ እምነት ነው! 2- ሕጻናትን ወደ ላይ ከፍ አድርገህ ስትወረውራቸው፣ የሚስቁት እንደማትጥላቸው ስለሚያውቁ ነው። ይሄ መተማመን ነው! 3- ማታ ወደ አልጋችን ሄደን ስንተኛ፣ ነገ በሕይወት እንደምንኖር ምንም ማረጋገጫ የለንም፤ ግን የሚቀሰቅሰን አላርም እንቀጥራለን። ይሄ ተስፋ ነው! 4- ስለ ወደፊቱ ምንም እውቀት ሳይኖረን ትልልቅ ነገሮችን እናቅዳለን። ይሄ በራስ መተማመን ነው! 5- ዓለም በስቃይ ላይ መሆኗን እናያለን፤ ግን ትዳር እንይዛለን፣ ልጆችም እንወልዳለን። ይሄ ፍቅር ነው! 6- ሽማግሌው የለበሰው ቲቨርት ላይ እንዲህ የሚል ነገር ተጽፏል "80 ዓመቴ አይደለም፤ የ64 ዓመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የ16 ዓመት ጎረምሳ ነኝ!" ይሄ አመለካከት ነው! መልካም ጊዜ ይሁንልህ፤ ሕይወትህን እንደነዚህ 6 ታሪኮች ኑር። ደግሞ አስታውስ— ጥሩ ወዳጆች የሕይወት ብርቅ ጌጦች ናቸው። ለማግኘት እጅግ የሚከብዱና በሌላ ሊተኳቸው የማይችሉ ናቸው! Via Ankipage @yourmindmattee
إظهار الكل...
👍 1
የመነመነ ማንነት በአካል ከተለያችኋቸው ወራትና ዓመታት ካስቆጠራች በኋላ፣ እንደገና እንደማታገኟቸው እያወቃችሁ በሃሳባችሁና በስሜታችሁ ለመለየት ያልቻላችኋቸው ሰዎች ጉዳይ ሕይወታችሁን ያመነምነዋል፡፡ በቀን ውስጥ ሳታስቧቸው መዋል ካቃታችሁ . . . ስለ እነሱ ስታስቡ ስሜታችሁ የሚወርድባችሁ ከሆነ . . . ከእነሱ ውጪ ኑሮ የማይገፋ ከመሰላችሁ . . . የሌላ ሰውና ሁኔታ ነገር አልጥም ካላችሁ . . . ተስፋ ቢስነት ከተጫጫናችሁ . . . አስቡበት! ለመነሻ የሚጠቅሟችሁ ሃሳቦች • ከእነሱ ውጪ መኖር እንደምትችሉ ራሳችሁን አሳምኑ፡፡ • ራሳችሁን በጤናማ ልምምድና ዓላማችሁን በመከተል “Busy” አድርጉ፡፡ • እነሱን የምታስታውሱባቸውን ነገሮችና ሁኔታዎች ማየትን፣ መስማትን . . . ለመቀነስ ሞክሩ፡፡ • እነሱን ለመርሳት ስትሉ በሚገባ ካላሰባችሁበት ግንኙነትና ሁኔታ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ • ወደፊት እንድትራመዱ የሚደግፏችሁን ሰዎች ለይታችሁ እወቁና ከእነሱ ጋር አዘውትሩ፡፡ ራሳችሁን አትጣሉ! ስሜታችሁንና ሃሳባችሁን መለስ አድርጉ! ቀና በሉ! ይህቺ ሕይወት የተሰኘት ሂደት ገና ብዙ ነገር እንደገና እንድትጀምሩ የማድረግ እውነታ ስላላት እንደገና መጀመርን ልመዱ!
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.