cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! Inbox me via telegram @DrEstifanos

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 104
المشتركون
+824 ساعات
+1567 أيام
+32930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Obsessive Compulsive Disorder *** ምሳሌ 1 OCD ያለባቸው ሰዎች የቆሸሸ የመሰላቸውን ነገር ነኩ እንበል ▻▻▻ይህ ከፍተኛ ጭንቀትን ይፈጥርባቸዋል አዕምሯቸውም አያርፍም▻▻▻እጃቸውን ይታጠቡ እና ቀለል ይላቸዋል▻▻▻ደግሞ እንደገና ይጠይቃሉ.. 'ባልታጠብ ኑሮ የከፋ ችግር መውደቄ ኑሯል....ለመሆኑ ግን በደምብ ታጥቤያለሁ?' ▻▻▻  ፍርሃቱ ያገረሻል... ቀስ በቀስ ትንሽ እንኳን መቆሸሽን መቋቋም እያቃታቸው ይመጣል▻▻▻ ተደጋጋሚ ጭንቀት▻▻ ተደጋጋሚ መታጠብ----- ምሳሌ 2 ሰውነታችሁ ላይ የሚያሳክክ ቁስል ወጣባችሁ እንበል... ▪️'እከኩኝ እከኩኝ' ስሜት ይሰማችኋል...Obsession እንደዚያ ነው..'ቆሽሻችኋል፣ በሩን አልዘጋችሁትም..'አይነት እከኩኝ ባይ ሃሳቦች... ደግሞም አንዳንዴ ፈጣሪን ስደቡ ስደቡ የሚል አይነት ግፊት/impulse... ልቅ የሆኑ ምስሎች(images).. ሌላም ሌላም... ▪️ የማከኩ ስሜት አሸንፎን እናክ ይሆናል... compulsion እንደዚህ ነው.. እረፍት ለነሱን ሃሳቦች ጊዜያዊ መፍትሄ እንዲሆን የምናደርገው ክዋኔ:: ታዲያ ባከክን ቁጥር ቁስሉን ማስፋት ይሆንብናል..Compulsion በፈጸምን ቁጥርም እነዚያ እረፍት የነሱን ሃሳቦችን የበለጠ እያጠናከርናቸው እንሄዳለን:: ሌላኛው አማራጭ የማሳከኩን ስሜት እንደምንም ታግሰነው ቁስሉ እንዲጠግ ማድረግ ነው:: ለሚመጡብን አላስፈላጊ ሃሳቦች፣ ምስሎች ምላሽን ባለመስጠት በሂደት ሃሳቦቹ እየቀነሱ እንዲሄዱ ማድረግ:: መፍትሄ ለነዚያ እየተመላለሱ ላስቸገሩን ሃሳቦች ሆን ብሎ በማጋለጥ(ለምሳሌ ቆሽሻለሁ የሚልን ሰው የሆነ ነገር እንዲነካ በማድረግ) ጭንቀቱ ቢመጣባቸውም እንዳይታጠቡ በመከልከል (ያው የተወሰነ ደቂቃ ያህል ጭንቀቱ ረብሿቸው መቀነሱ አይቀርምና)... 'ባልታጠብም ምንም የከፋ ነገር አይደርስብኝም' የሚል እሳቤ እንዲያዳብሩ እና እንዲላመዱት፤ በጊዜ ሂደት በሆነው ባልሆነውም መታጠቡን እንዲቀንሱ ማድረግ ላይ ያተኮረ... ይህ የስነልቦና ህክምና Exposure and Response Prevention ይባላል:: አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት follow for more https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif https://www.tiktok.com/@drestifanospsychatrist?_t=8nTLzCsx9XR&_r=1
إظهار الكل...
Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! Inbox me via telegram @DrEstifanos

8👍 1
የአዕምሮ ህመምን እንዲከሰት ብሎም እንዲያገረሽ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መሃከል ◊ ሃዘን እና ማጣት/ grief and loss ◊ ግጭቶች/dispute ◊ የሁኔታዎች መለዋወጥ/Role transition ◊ ባይተዋርነት/Interpersonal deficiency ይገኙበታል:: ታዲያ እነዚህ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የስነልቦና ህክምና Interpersonal Therapy(IPT) ይባላል:: ከ 4 ሴሽኖች ጀምሮ ይሰጣል:: በተለይም ከላይ በተጠቀሱት ጫናዎች ምክንያት ለተከሰቱ/ለተባባሱ የአዕምሮ ህመሞች(ማለትም እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና የተራዘመ ሃዘን...የመሳሰሉ) የሚሰጥ የስነልቦና ህክምና ነው:: እርስዎም እንደዚህ አይነት ችግሮች ካጋጠመዎ ባለሞያ ያማክሩ:: አሻም ለአለማችን! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ:- https://www.facebook.com/DrEstif https://t.me/DrEstif
إظهار الكل...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

👍 10 2
ኢጎው ከባድ ነው.. *** ይህን አባባል ብዙዎቻችን ስንጠቀምበት ይስተዋላል:: 'Ego is enemy' የሚሉም አሉ:: 🔸 ኢጎ ምንድን ነው? ◊ ኢጎ ከሶስቱ የልቦና መዋቅሮች አንዱ ነው::(ኢድ፣ ኢጎ፣ ሱፐር ኢጎ) ◊ ከሶስቱ እውነታን ከግምት ውስጥ የማስገባት ችሎታ (Reality testing) ያለው እና በነባራዊ እውታዎች የሚመራው ኢጎ ነው::  የ Prefrontal cortex ስነልቦናዊ  ስሙ ነው ይባላል.. ኢጎ😊 ▻ ኢድ ፍላጎት/ደስታ መር ሲሆን፥ ሱፐር ኢጎ ደግሞ ሞራል መር ነው:: ሁለቱ የተለያየ እሳቤን እንደማራመዳቸው  ሁሌም እንደተቃረኑ ነው:: ኢጎ ያስታርቃቸዋል:: 😊 🔸ኢጎ የሚከተሉትን ስራዎች የሚሰራልን ወሳኝ የልቦናችን ክፍል ነው:- ◊ ከነባራዊው እውነታ በመነሳት ደመነብሳዊ ፍላጎቶችን የሚቆጣጠር (Control and regulate instinctual drives) ◊ ስሜታችንን እና ውስጣዊ ግፊቶችን የሚቆጣጠር/የሚመጥን (Impulse control) ◊ የእውነታን አለም እንድንቃኝ፣ እንድንረዳ እና እንድንላመድ የሚያስችል (sense, testing, and adaptation to reality) ◊ ከሌሎች ጋር አቻችሎ የሚያኖረን (Object relation) ◊ ኢጎ ዳኛ ነው: ነገሮችን ከአለው ነባራዊ እውነታ አንጻር በመረጃ እና ማስረጃ መዝኖ ኢድ እና ሱፐር ኢጎን የሚያስታርቅ...በዚህም መሰረት የተፈጠረብንን የጭንቀት ስሜት የሚከላከል እና የሚያስወግድ( በ Defense mechanism አማካኝነት) ** ምናልባት ኢጎ መጥፎ ነገር ነው የሚለው እሳቤ: አንዳንድ ያልዳበሩ እና ለራስ ጥቅም ያደሉ  ዲፌንስ ሜካኒዝሞችን እንደ ብቸኛ የ ኢጎ መገለጫ አድርጎ ከመውሰድ የመጣ ሊሆን ይችላል:: ዳሩ ግን እነዚህ ያልዳበሩ ዲፌንስ ሜካኒዝሞች የኢጎ ስራ መድከሙን የሚጠቁሙ ናቸው 😊 ኢጎ ግን ከእነዚህ ዲፌንስ ሜካኒዝሞች በላይ ነው.. ብዙ በጎ ነገሮችን የሚከውንልን የልቦናችን ክፍል:: እንዲያውም የኢጎ ስራ መዳከም..ከጭንቀት፣ ድብርት፣ ሳይኮሲስ እና ሌሎች የአዕምሮ ህመሞች ጋር ይገናኛል:: በዚህ መሰረት...ለመሆኑ ኢጎ ጥሩ ነገር ነው ወይንስ መጥፎ? አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ እነዚህን ገጾች ይወዳጁ:- https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif
إظهار الكل...
11👍 7🙏 1
Attachment styles/ በወላጅና ልጆች መሃል የሚኖር ቅርርብ ➖➖➖➖➖➖➖ በልጅታችን ከወላጅ/አሳዳጊዎቻችን: በተለይም ከእናታችን ጋር የሚኖረን ግንኙነት እና መቀራረብ ወደፊት አድገን አለምን የምናይበትን መንገድ(Working model) የሚወስን ወሳኝ ሁነት ነው:: ልጆች ከተወለዱ በኋላ ያሉት የመጀመርያዎቹ 1000 ቀናት ለአካል እና አዕምሮ እድገት ብቻ ሳይሆን ለስነልቦና መዋቅራችን ግንባታም ወሳኝ ጊዜያት ናቸው:: ይህን ጽንሰ-ሃሳብ በተመለከተ John Bowlby እና ሌሎችም ጥናትና ምርምሮችን ሰርተዋል:: ይህ በወላጅና ልጅ መሃል የሚኖረው መቀራረብ Secure እና Insecure Attachment ተብሎ ይከፈላል:: Insecure Attachment ከድብርት፣ ጭንቀት፣ የስብእና ችግሮች እና ሌሎችም የአዕምሮ ህመሞች ጋር ይያያዛል:: 1️⃣ Insecure- Anxious/Preoccupied ወላጆቻቸው ጥለዋቸው እነደሚሄዱ በስጋት ያደጉ ልጆች መለያ ነው:: ሁሌም አብረዋቸው እንዲሆኑ ይፈልጋሉ..ግን ወላጆች በተለያዩ ምክንያቶች ይሄን ስጋታቸውን መፍታት ሳይችሉ ይቀሩ እና ይህ ፍርሃት አብሯቸው ያድጋል:: ሲያድጉም ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት የሚሰጡ እና በራስ መተማመን የሌላቸው ይሆናሉ:: ድንጉጥና ሽቁጥቁጦች ናቸው:: በጓደኝነት መሃል እንከዳለን ብለው አብዝተው የሚፈሩ እና እንደማይከዷቸው ዘወትር መተማመኛን የሚሹ ናቸው:: 2️⃣ Insecure- Avoidant/Dismissive ልጆች እያሉ የወላጆቻቸው መኖር አለመኖር ግድ የማይሰጣቸው አይነት ናቸው:: ይህም በወላጆቻቸው ቸልተኝነት ምክንያት የሚያዳብሩት ስሜት ነው:: ካደጉ በኋላ በራስ መተማመናቸው ደህና ቢሆንም: ለሌሎች የሚኖራቸው አሉታዊ ምልከታ ጓደኝነታቸው ላይ ችግር ይፈጥራል:: ብቸኝነትን ይመርጣሉ:: ከሌሎች ሰዎች ጋር መቀራረብን እና መተጋገዝን እንደ ጥገኝነት ይቆጥሩታል::: በዚህም ምክንያት ጋብቻንና ሌሎች መወዳጀቶችን ሲሸሹ ይስተዋላል:: 3️⃣ Insecure-Disorganized ልጆች እያሉ ወላጆቻቸው ሲሄዱ ለያዥ ለገናዥ የሚያስቸግሩ : ከሄዱበት ሲመለሱም ለማባበል በጣም የሚያስቸግሩ ናቸው:: ታዲያ ካደጉም በኋላ ግልፍተኞችና ራሳቸውን ለማረጋጋት የሚቸገሩ ይሆናሉ:: ስሜትታቸውን ለማጋራት ይሰስታሉ:: ይህም የሚሆነው እንከዳለን ብለው ስለሚሰጉ ነው:: Trust issue አለባቸው:: ግልፍተኝነት፣ ራሳቸው ላይ ጉዳት ማድረስ(በሰበብ አስባቡ ራስን ለማጥፋት ማንገራገር እና መሞከር) እና የስሜት መለዋወጦች እና የባዶነት ስሜት መለያ ያስቸግሯቸዋል:: ይህ አይነት Attachment ከ Borderline personality disorder ጋር ይያያዛል:: 4️⃣ Secure Attachment ከወላጆቻቸው ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የነበራቸው፣ ወላጆቻቸው በአግባቡ ፍቅርን እና እንክብካቤን ያሳዩዋቸው ልጆች መለያ ነው:: ካደጉም በኋላ የተረጋጉ እና ሰላማዊ የሆነ ማህበራዊ ህይወት ያላቸው ናቸው:: *** አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ለበለጠ መረጃ እነዚህን ገጾች ይወዳጁ:- https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif
إظهار الكل...
Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! Inbox me via telegram @DrEstifanos

👍 5 3🙏 1
🔸ከወላጆቻቸው ጋር የጨዋታ ጊዜ ያላቸው ልጆች እነዚህን ጥቅሞች ያገኛሉ:- 1️⃣ ከውጥረት ስሜት እንዲወጡ ያግዛቸዋል 2️⃣ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸውን ቅርርብ ያጠናክርላቸዋል: 3️⃣ ስሜቶቻቸውን በጨዋታው አሳበው እንዲገልጹ እና ቀለል እንዲላቸው ያደርጋል 4️⃣በራስ መተማመናቸውን ያጎለብትላቸዋል መረጃውን ያገኘሁት ከዩኒሴፍ የፌስቡክ ገጽ ነው:: ሰናይ ቀን ተመኘሁላችሁ:: ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ገጾች ይወዳጁ:- https://t.me/DrEstif
إظهار الكل...
👍 5 3
የሳይኮሲስ ህመሞች እና ህክምናው **** ሳይኮሲስ ስንል  ሃሉሲኔሽን እና ዴሉዥንን ማለታችን እንደሆነ አይተናል::  እነዚህን የሳይኮሲስ ምልክቶች የሚያሳዩ የአዕምሮ ህመሞችን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:: 1️⃣ ራሳቸውን ችለው  የሳይኮሲስ ምልክቶችን በዋነኝነች የሚያሳዩ የአዕምሮ ህመሞች- Primary Psychotic disorders እንደ ስኪዞፍሬኒያ(ማለትም ከባድ የሆነ የአዕምሮ ስራ መቃወስ)፣ የዴሉዥን ህመሞችን(Delusional disorders) እና መሰል ህመሞችን ማንሳት እንችላለን:: 2️⃣ በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች በተጓዳኝነት የሚከሰት ሳይኮሲስ- Secondary psychotic disorders እነዚህም:- ከከባድ ድብርት እና የስሜት መለዋወጥ(ማለትም ባይፖላር ህመም) ፤ ከሱስ እና አንዳንድ መድሃኒቶች ጋር፤ ከአንጎል እና ሌሎች አካላዊ ህመሞች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱትን ያካትታል:: 🔸ሳይኮሲስ እንዴት ይታከማል? ሳይኮሲስ የሚከሰተው በዶፓሚን ስርዓት መዛባት ነው ካልን ፥ ህክምናውም የተዛባውን የዶፓሚን ስረዓት ማስተካከል ላይ ያተኩራል ማለት ነው:: ይህን የተዛባ የዶፓሚን ስርዓትን ለማስተካከል የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች ይሰጣሉ:: እነዚህ የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች 1st እና 2nd generation ተብለው ይከፈላሉ:: አንዳቸው ካንዳቸው የሚያለያያቸው ባህርያት አላቸው:: እንደማነኛውም መድሃኒት ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ይኖራሉ:: እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች በአግባቡ ከተለዩ መታከም የሚችሉ ናቸው:: የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች ምርጫችን እድሜን፣ አጠቃላይ የጤና ሁኔታን፣ የእርግዝና እና የማጥባት ሁኔታን፣ በገበያ ላይ እንደ ልብ መገኘት አለመገኘታቸውን እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ይሆናል:: ሳይኮሲሱን አምጥተዋል ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮችን መፍትሄ ማበጀት የህክምናው አካል ነው:: በሱስ ምክንያት የመጣ ሳይኮሲስ ሱሱ በቆመ በወር ጊዜ ውስጥ መሻሻልን ያሳያል: ይጠፋልም::  ተጓዳኝ በሽታዎች ከሆኑ ያመጡት: እስፈላጊው ህክምና ሲደረግ ሳይኮሲሱም መጥፋት ይጀምራል:: የስነልቦና ህክምና- CBT for Psychosis *** አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif
إظهار الكل...
Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! ለማማከር በ 0949476776 ይደውሉ:: Inbox me via telegram @DrEstifanos

👍 5 1
የሳይኮሲስ ህመሞች እና ህክምናው **** ሳይኮሲስ ስንል  ሃሉሲኔሽን እና ዴሉዥንን ማለታችን እንደሆነ አይተናል::  እነዚህን የሳይኮሲስ ምልክቶች የሚያሳዩ የአዕምሮ ህመሞችን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:: 1️⃣ ራሳቸውን ችለው  የሳይኮሲስ ምልክቶችን በዋነኝነች የሚያሳዩ የአዕምሮ ህመሞች- Primary Psychotic disorders እንደ ስኪዞፍሬኒያ(ማለትም ከባድ የሆነ የአዕምሮ ስራ መቃወስ)፣ የዴሉዥን ህመሞችን(Delusional disorders) እና መሰል ህመሞችን ማንሳት እንችላለን:: 2️⃣ በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች በተጓዳኝነት የሚከሰት ሳይኮሲስ- Secondary psychotic disorders እነዚህም:- ከከባድ ድብርት እና የስሜት መለዋወጥ(ማለትም ባይፖላር ህመም) ፤ ከሱስ እና አንዳንድ መድሃኒቶች ጋር፤ ከአንጎል እና ሌሎች አካላዊ ህመሞች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱትን ያካትታል:: 🔸ሳይኮሲስ እንዴት ይታከማል? ሳይኮሲስ የሚከሰተው በዶፓሚን ስርዓት መዛባት ነው ካልን ፥ ህክምናውም የተዛባውን የዶፓሚን ስረዓት ማስተካከል ላይ ያተኩራል ማለት ነው:: ይህን የተዛባ የዶፓሚን ስርዓትን ለማስተካከል የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች ይሰጣሉ:: እነዚህ የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች 1st እና 2nd generation ተብለው ይከፈላሉ:: አንዳቸው ካንዳቸው የሚያለያያቸው ባህርያት አላቸው:: እንደማነኛውም መድሃኒት ሊከሰቱ የሚችሉ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ይኖራሉ:: እነዚህ የጎንዮሽ ጉዳቶች በአግባቡ ከተለዩ መታከም የሚችሉ ናቸው:: የጸረ-ሳይኮሲስ መድሃኒቶች ምርጫችን እድሜን፣ አጠቃላይ የጤና ሁኔታን፣ የእርግዝና እና የማጥባት ሁኔታን፣ በገበያ ላይ እንደ ልብ መገኘት አለመገኘታቸውን እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ይሆናል:: ሳይኮሲሱን አምጥተዋል ተብለው የሚታሰቡ ጉዳዮችን መፍትሄ ማበጀት የህክምናው አካል ነው:: በሱስ ምክንያት የመጣ ሳይኮሲስ ሱሱ በቆመ በወር ጊዜ ውስጥ መሻሻልን ያሳያል: ይጠፋልም::  ተጓዳኝ በሽታዎች ከሆኑ ያመጡት: እስፈላጊው ህክምና ሲደረግ ሳይኮሲሱም መጥፋት ይጀምራል:: አሻም! ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት https://t.me/DrEstif https://www.facebook.com/DrEstif
إظهار الكل...
Dr. Estifanos(Psychiatrist)-ዶ/ር እስጢፋኖስ

ስለ አዕምሮ ጤና እንወያያለን! ለማማከር በ 0949476776 ይደውሉ:: Inbox me via telegram @DrEstifanos

1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.