Waliya Entertainment
الذهاب إلى القناة على Telegram
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!! Follow us on social medias Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
إظهار المزيد296
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
-230 أيام
جاري تحميل البيانات...
القنوات المماثلة
سحابة العلامات
لا توجد بيانات
هل تواجه مشاكل؟ يرجى تحديث الصفحة أو الاتصال بمدير الدعم الخاص بنا.
الإشارات الواردة والصادرة
---
---
---
---
---
---
جذب المشتركين
مايو '25
مايو '25
+1
في 0 قنوات
أبريل '250
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '25
+2
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '25
+1
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '250
في 0 قنوات
Get PRO
ديسمبر '24
+8
في 0 قنوات
Get PRO
نوفمبر '24
+46
في 1 قنوات
Get PRO
أكتوبر '24
+14
في 0 قنوات
Get PRO
سبتمبر '24
+34
في 2 قنوات
Get PRO
أغسطس '24
+22
في 0 قنوات
Get PRO
يوليو '24
+16
في 0 قنوات
Get PRO
يونيو '24
+18
في 0 قنوات
Get PRO
مايو '24
+15
في 1 قنوات
Get PRO
أبريل '24
+6
في 0 قنوات
Get PRO
مارس '24
+3
في 0 قنوات
Get PRO
فبراير '24
+37
في 0 قنوات
Get PRO
يناير '24
+230
في 0 قنوات
| التاريخ | نمو المشتركين | الإشارات | القنوات | |
| 16 مايو | 0 | |||
| 15 مايو | 0 | |||
| 14 مايو | 0 | |||
| 13 مايو | 0 | |||
| 12 مايو | 0 | |||
| 11 مايو | 0 | |||
| 10 مايو | 0 | |||
| 09 مايو | 0 | |||
| 08 مايو | 0 | |||
| 07 مايو | 0 | |||
| 06 مايو | 0 | |||
| 05 مايو | 0 | |||
| 04 مايو | 0 | |||
| 03 مايو | 0 | |||
| 02 مايو | +1 | |||
| 01 مايو | 0 |
منشورات القناة
ቬሮኒካ በአውሮፓ የሙዚቃ ዝግጅቶቿን ልትጀምር ነው
"Europe ለምትገኙ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ቤተሰቦቼ ጊዜው ደርሶ የመጀመርያውን መጠሪያዬ ቱር ከእናንተ ውድ ቤተሰቦቼ ጋር ላሳልፍ ስለሆነ የተሰማኝን ደስታ እየገለፅኩ; ቀኖቹን እንዳሳውቃችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት ቀኖቹን ይዤላችሁ መጥቻለሁ፤ ይሄ ቱር በተለያዩ አዳዲስ ነገሮች ብቅ የምልበትም ስለሆነ በዚህ የህይወቴ ታሪክ ውስጥ እንድትሳተፉልኝ በትህትና እገልፃለሁ ; እወዳችዋለሁ፤
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን 🙏🏽 " - ቬሮኒካ አዳነ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane
| 2 | ዘቢባ ግርማ ለግንቦት 1 ቀጠሮ ሰጥታለች ።
ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሆነበት የዘቢባ ግርማ "እንደምንም" የሙዚቃ አልበም መውጫው ቀን ይፋ ሆኗል!
ይህ "እንደምንም የተሰኘው አልበም በግጥም ይልማ ገብረአብ፣ ሞገስ ተካ፣ አለምጸሀይ ወዳጆ፣ መስለ ጌታሁን፣ ናትናኤል ግርማቸው፣ ወንደሰን ይሁብ፣ ፍሬዘር አበበወርቅ፣ እልፍአግድ እምሻው፤ ኒና ግርማ፤ ገዳ ሀምዳ በግጥም የተሳተፉ ሲሆን
በዜማ ደግሞ አበበ ብርሃኔ ፣ ሞገስ ተካ፣ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ፣ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፤ አንተነህ ወራሽ፣ ምህረትአብ ደስታ፤ ካሙዙ ካሳ፣ ዳንኤል ዘውዱ (ዳኒ ቀዮ)፣ አብዲ ያሲን
በመዚቃ ቅንብር አቤል ጳውሎስ፣ ታምሩ አማረ፣ ሸካሙዙ ካሳ፣ ፋኑ ጊዳቦ፣ አዲስ ፍቃዱ ማስተሪንግ ክሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡
"እንደምንም" የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት አንድ በዘቢባ ግርማ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ይገኛል፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #zebibagirma | 68 |
| 3 | "ደጃዝማች " የተሰኘው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስምንተኛ አልበሟ የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ይለቀቃል
ታላላቅ ገጣሚዎችና የዜማ ደራሲያን የሙዚቃ አቀናባሪዎች የተሳተፉበት "ደጃዝማች " የተሰኘው የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ስምንተኛ አልበሟ የፊታችን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በእራሷ በኩኩ ሰብስቤ የዩቲዮብ ቻናል እና በሁሉም የዲጂታል መተግበሪያዎች ለአድማጭ እንደሚደርስ ተገልጿል ።
ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ለሰባት ዓመታት በደከመችበት "ደጃዝማች " በተሰኘው አዲስ የሙዚቃ አልበም ላይ አስራ ሶስት /13/ ዘፈኖችን የያዘ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህ አስራ ሶስት ዘፈኖች ውስጥ የስምንቱ ዘፈኖች ግጥምና ዜማ የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ / ሲሆኑ ሌሎቹን ሙዚቃዎች ደግሞ በግጥም ገጣሚ ይልማ ገብረአብ ፡ ገጣሚ መሰለ አስማማው ፡ ገጣሚ ናትናኤል ግርማቸው የሰሩ ሲሆኑ ሞገስ ተካ እና ምስክር አወል በግጥምና ዜማ በመስራት በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል
ከተቀሩት ስራዎች ውስጥ "ወለላዬ" የተሰኝው ሙዚቃ ደግሞ የኩኩ የድሮ ስራ ሲሆን ቴዲ ማክ እንደገና ሪአሬንጅ /Re Arrange/ አድርጎ የሰራው ሙዚቃ ነው ተብሏል። የድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ " ደጃዝማች " በተሰኘው አዲስ አልበም ላይ ስመጥር የሆኑ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን የሙዚቃ አቀናባሪው አቤል ጳውሎስ ዘጠኙን ሙዚቃዎች በማቀናበር እንዲሁም አስራ አንዱን ሙዚቃዎች ሚክስ በማድረግ እንደተሳተፈ ተነግሯል ።
ሁለቱን ሙዚቃዎች አሬንጅ ያደረገው ማሩ ዓለማየሁ ሲሆን ሙዚቀኛ ያሬድ ተፈራ ፡ ሙዚቀኛ አክሊሉ ወ/ዩሐንስ (ጆኒ ሳክስ) እና ሙዚቀኛ ዘሪሁን በለጠ በሳክስፎን ፡ ግሩም መዝሙር እና ሳሙኤል አሰፋ በጊታር ተሳትፈዋል ።
@waliyaentmt
@waliyaentmt
@waliyaentmt | 80 |
| 4 | በሽርጉድ ኮንሰርት ላይ ያለፈው ቅዳሜ ዝግጅታቸውን ያቀረቡት አርቲስቶቹ ስንት እንደተከፈላቸው ታወቀ።
ሶስት የሙዚቃ ትውልዶችን በአንድ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ያገናኘው ሽርጉድ ኮንሰርት ያለፈው ቅዳሜ እለት በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄዱ ይታወቃል። በዝግጅቱም ላይ በርከት ያሉ ታዳሚዎች የተገኙም ሲሆን ድምፃዊያኖችም በአሪፍ የመድረክ አቀራረብ ገነው ታይተዋል።
በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ አርቲስቶቹ ስራየውን ለማቅረብ ከሽርጉድ ኢንተርቴይመንት ጋር የተፈራረሙ ሲሆን ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከአንዳንድ የውስጥ ታማኝ ምንጮች እንዳጣራው ኤፍሬም ታምሩ በዝግጅቱ ላይ 10 ስራዎችን እንዲያቀርብ ለሱም 3 ሚሊዮን ብር ሊከፈለው ጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶም የተለያዩ የሙዚቃ ስራቸውን ሊያቀርቡ ለእነሱም ለእያንዳንዳቸው 3 ሚሊዮን ብር ሊከፈላቸው ተስማምተው እንደነበር ዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃ ደርሶታል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #shirgoodconcert #ephremtamru #gossayetesfaye #alemayehuhirpo | 89 |
| 5 | "በሙዚቃ ዝግጅቴ አምስትም ሆነ አስር ሰው ቢመጣ ታዳሚዬን አከብራለሁ":- ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ
ወጣቱ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ከመጀመሪያ አልበሙ በኃላ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሁለተኛ የሙዚቃ ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት ያካሂዳል::
ልዑል ከወራት አስቀድሞ መድረኩን የሚመጥን ዝግጅት ማድረጉን ይገልፃል::
"በእርግጥ ይህ በአዲስ አበባ የሚኖረኝ ሁለተኛ ዝግጅቴ ነው። አሁንም በመድረክ እንይህ የሚሉ ጥያቄዎች ስለነበሩ እኔም ጥያቄውን ተቀብዬ ተዘጋጅቻለሁ" ሲል ይናገራል::
ልዑል ባለፈው ከነበረው የሙዚቃ ኮንሰርቱ በርካታ ጠቃሚ ልምድን ማግኝቱን ገልፆ ከራሱ ስራዎች ባለፈ የተለያዩ ድምፃዊያንን ስራም አብሮ እንደሚጫወት ገልፆል::
የኮንሰርት የመጨረሻው ሰዓታ ጥንቃቄ ይፈልጋል ከዚህ አንፃር ምን ልምድ አለህ? ያልነው ልዑል
"ብዙ ጊዜ ከቤት አልወጣም ድብቅ ለማለት እፈልጋለሁ። በአመጋገብ አትክልት በመጠጥ ውሃን አዘወትራለሁ" ብሏል::
ልዑል የሙዚቃ ዝግጅቱን በሚያቀርብበት ተመሳሳይ ሰአት ሌሎች ዝግጅቶም በአዲስ አበባ ይካሄዳሉ። ስለሁኔታው የተጠየቀው ድምፃዊው
"የእኛ ቀደም ብሎ የተደረገ ነው በዕለቱ አድማጭ ሊሻማ ቢችልም ሁላችንም የራሳችን ተከታይ እንዳለን መዘንጋት የለበትም። በግሌ አምስትም ሆነ አስር አድማጭ ቢመጣ ታዳሚዬን አክብሬ እጫወታለሁ" ብሏል::
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #leul_sisay | 80 |
| 6 | የሳምንቱ ምርጥ 10 ሙዚቃዎች
1. ዓይዋ
467,009 Views | + 467,009 Views
2. አሞራው ካሞራ – አስቻለው ፈጠነ
9,741,769 Views | + 430,788 Views
3. Sona Takele – WARRA BOOLEE
19,533,830 Views | + 422,378 Views
4, ማህሌት ወንድሞ - ዝም
4,313,400 Views | + 412,976 Views
5, Amanuel Yemane - Niskila
7,946,782 Views - +355,971 Views
6, ቬሮኒካ አዳነ - እናነይ
25,243,113 Views | + 319,082 Views
7, ያሬድ ነጉ - አለምድም
4,613,587 Views | + 288,143 views
8, አንዷለም ጎሳ - ማሬ
2,028,385 Views | + 253,180 Views
9, Ibiddo Galaan - Dammee
480,030 Views | + 237,409 views
10, ኤደን ገብረስላሴ - ይኹን
8,894,539 Views | + 237,306 Views
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #top10 | 92 |
| 7 | እኔንም ስሙኝ ብሏል :-
እኔ አድናናን እባላለው ባለትዳር እና የሴት ልጅ አባት ነኝ::
ዳግማዊ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩ ግዜ ጏደኛዬ ነበረች የባሏ ቤተሰቦች እና የባሏ የድሮ ፍቅረኛ የሚያደርጏትን ጭምር ታጫውተኝ ነበር:: ከዛ ለረዥም ግዜ ተለያይተን በድጋሚ ፃፍኩላት ይሄ ዛቻ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ እኔ ለቀልድ ነው ያልኳት እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም እኔ የምኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ አይደለም::
አድናን ነኝ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #dagimawittsehaye #adnan | 76 |
| 8 | ታዋቂ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች በእግር ኳስ ሜዳ ላይ ይፋለማሉ
#Ethiopia | የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ ጋር በመተባበር ልዩ የሆነ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫል ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለጸ።
በዚህ የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ድምፃውያን እና ቲክቶከሮች የሚሳተፉበት የእግር ኳስ ውድድር የፊታችን ሚያዚያ 23 እና ሚያዚያ 26 በልደታ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ ይካሄዳል።
የቅዳሜ ሚዲያ እና አድሽርታይዚንግ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ አዳረ ረጋሳ ይህንን መርሃ ግብር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት " ከዚህ ቀደም መሰል ውድድሮች በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት የነበራቸው ሲሆን ዘንድሮም ይህንን የአብሮነት እና የመዝናኛ ጊዜ ለመፍጠር ታስቧል።
አክለውም በቅርብ ጊዜያት ህዝቡ በቤተሰቡ ልጆቹን ይዞ ወደ መዝናኛ እና ስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች በስፋት እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ በእነዚህ ቦታዎች ላይ አዝናኝ ፕሮግራሞች ቢዘጋጁ ህዝቡ በሰፊው እንደሚታደም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ይህ የታዋቂ ሰዎች የስፖርት ፌስቲቫልም በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ በመሆኑ ብዙዎች በጉጉት እንደሚጠብቁት "ተናግረዋል።
በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው ሚያዚያ 23 የዋንጫ ማለፍ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን የፍጻሜው የዋንጫ ጨዋታ ደግሞ ሚያዚያ 26 ይካሄዳል። ከዚህ የትኬት ሽያጭ የሚገኘው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ይውላል።
@waliyaentmt
@waliyaemtmt
@waliyaentmt | 112 |
| 9 | አርቲስት ዳግማዊት ፀሐዬ በፌስቡክ ገጿ እንደገለጸችው "አድናን ሱልጣን" የተባለ ግለሰብ "ለምን አታናግሪኝም" በሚል ሰበብ እኔን ለማሳገት እየዛተብኝ ጉዳዩን ወደ ህግ እስክወስደው እወቁልኝ ብላለች።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #dagimawit_tsehay | 60 |
| 10 | በእስራኤል የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት
አቦጊዳ ባንድ በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ “
April 30 2025 “ ለሚካሄደው የቴዲ አፍሮ
የሙዚቃ ዝግጅት ወደ ስፍራው አቅንተዋል::
📷Henok Henry
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #teddyafro #abogidaband | 81 |
| 11 | የሙዚቃው ንጉስ ድምጻዊ ጥላሁን ገሰሰ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ዛሬ 16 ዓመት ሞላው።
መስቀል አደባባይ በነበረው ሽኝት መርሀ ግብር ላይ በርካታ ታዋቂ ሰዎችና አድናቂዎቹ መገኘታቸው የሚታወስ ነው።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Tilahungessese | 71 |
| 12 | እነዚህ ሰዎች ማንም ላይ ምንም ሲደርስ መርካቶ ወይም መንደር ውስጥ ያለውን መደብራቸውን ይዘጋሉ ? " በእኔ ወገኖች ላይ በደል ስለደረሰ " ብለው ከመ/ቤት ይቀራሉ ? ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ ? መብላታቸውን ይተዋሉ ? ሰርግ ሳይሄዱ ይቀራሉ ? ልጃቸውን አይድሩም ? የትኛውን ገቢያቸውን ይተዋሉ ? ከሕይወታቸው ላይ ምን ይቀንሳሉ ? እነዚህ ሰዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ከእራኤል መንግሥት ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲያቋርጥ ለምን መሬት አንቀጥቅጥ ሰልፍ አይጠሩም ? ሰዎች ለምን ወደ እስራኤል ወይም እንግሊዝ የሚያደርጉትን ጉዞ እንዲሰርዙ አያደርጉም ? ለምን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ እስራኤል ወይም እንግሊዝ የሚያደርገውን በረራ እንዲያቋርጥ አላደረጉም ? አንዱንም አልሞከሩም ። ሌላ ቀርቶ ድምጻውያን እስራኤል ሄደው ሲዘፍኑ ማንም ምንም አይልም ። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ምንድነው የሚታያቸው ? ኧረ ጎበዝ !
Via ቴዎድሮስ ተክላረጋይ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Teddyafro | 72 |
| 13 | ቴዲ አፍሮ ሲሆን ፖለቲካውም ፣ ሀይማኖቱም ለሚታያችሁ !
" ቀና ካልክ ይተኩሱብሀል ! " ይላል ጋሽ ስብሐት ገእግዚአብሔር
ሰሞኑን የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ ) በእስራኤል ለአድናቂዎቹ ስራውን ማቅረቡን ተከትሎ ጉዳዩን የሀይማኖት ቅርጽ አስይዘው እንዲሰርዝ የሚጠይቅ ጽሑፍ አያየሁ ። እነዚህ የሀይማኖቱ ወገንተኞች ናቸው ። በቀደም ደግሞ ይኸው ድምጻዊ በእንግሊዝ ስራውን ሊያቀርብ ሲል ጥቂት የተደራጁ ብሔረተኞች እንዲሁ ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል ። እነዚህ ሰዎች ሌሎች ድምጻውያን እንግሊዝም ፣ እስራኤልም ሄደው ስራቸውን ሲያቀርቡ ያላነሱትን ጥያቄ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ለምን እንደሚታያቸው ምክንያቱ ግልጽ ነው ። የድምጻዊው ጎላ ብሎ መታየት እሱን መቃወም የሀይማኖታቸውንም ፣ ብሔራቸውንም አጀንዳ ጎላ ስለሚያደስግላቸው ነው ። ቀና ስላለ ነው የሚተኩሱበት ። ጋሽ ስብሐት ይህን ነው የሚለው ። እስራኤል በፍልስጤም ላይ ላደረሰችው ቴዲ አፍሮ ተጠያቂ የሚሆነው እንዴት ነው ?
ካሁን ቀደም ( በቅርቡም ) እስራኤል በርካታ ድምጻውያን ሄደው ስራቸውን ሲያቀርቡ ምንም ትንፍሽ ብለው የማያውቁትን ጥያቄ ቴዲ አፍሮ ሲሆን የሚያነሱት ለምን ነው ? ለእስልምና ጭራሽ አብዱ ኪያር አይቀርብም ? እሱም እኮ እዚያው እስራኤል ሄዶ ስራውን አቅርቧል ፤ ነገም ቢጠራ ይሄዳል ። ስራ ነዋ ። እንግሊዝ ሄዶ ስራውን ያቀረበ አማርኛ ድምጻዊስ ቴዲ አፍሮ ብቻ ነው ? ( የእንግሊዞቹን እንኳን ራሱ ሰዉ መልስ ሰጥቷቸዋል ። ) እነዚህ ሰዎች የሚዘነጉት ሙዚቃ ለድምጻዊው ተሰጥዖው ብቻ ሳይሆን ስራው ፣ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት ብቸኛ ገቢው መሆኑን ነው ። ቤት ኪራዩን የሚከፍልበት ፣ ሲገዛ የሚገዛበት ፣ የተቸገረ ሲገኝ የሚያግዝበት ብቸኛ ገቢው ሙዚቃ ነው ። እሱን ነው " ዝጋ " የሚሉት ። | 66 |
| 14 | ቴዲ አፍሮ በቴልአቪቭ ለማቅረብ ያሰበው ኮንሰርት ሁለት ጎራ ከፍሏል ።
ቴዲ አፍሮ ሚያዝያ 22,2017 ዓም በእስራኤል ኮንሰርት ሊያቀርብ መሆኑን ይፋ አድርጓል ።
መተዳደሪያ ስራው እስከሆነ ድረስ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ልክ ነው ያሉ ያሉ እንዳሉ ሁሉ
በጋዛ ህፃናቶች በእስራኤል እየተገደሉ የሙዚቃ ድግስ ማቅረቡ ትክክል አይደለም የሚሉ አሉ ።
ሀማስ በድንገት በሙዚቃ ድግስ ላይ ጥቃት አድርሶ በርካቶችን ከገደለ እኔ አፍኖ ከወሰደ በኋላ ጦርነት ተቀስቅሶ እስካሁን መቆምያው መንገድ ከጠፋ ሰነባብቷል።
ቴዲ አፍሮ የእስራኤል የነፃነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ኮንሰርቱን ያቀርባል ።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #teddyafro | 62 |
| 15 | የታዋቂ ሰዎች አዝናኝ የስፖርት ፌስቲቫል ሊካሄድ ነዉ
አርቲስቶች ፣ ድምፃዉያን ፣ ጋዜጠኞች እና ቲክቶከሮች የሚሳተፉበት ደማቅ ስፖርታዊ ዉድድር ሊደረግ ቀን ተቆርጦለታል
ሚያዚያ 23 ለዋንጫ የጥሎ ማለፍ ዉድድር የሚደረግ ሲሆን ሚያዚያ 26 ደግሞ የፍፃሜዉ የዋንጫ ጨዋታ ይደረጋል።
ትኬቱን ከቴሌ ብር ላይ ከዛሬ ጀምሮ መግዛት የሚቻል ሲሆን ከትኬት ሽያጭ የሚገኘዉም ገቢ ለመቄዶንያ የአረጋዉያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የሚዉል ይሆናል።
ውድድሩ ከልደታ ቤተክርስቲያን ጀርባ በሚገኘው ብሪሞ ሜዳ ይደረጋል፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #celebrity | 58 |
| 16 | ሁለት ትላልቅ ኮንሰርት በአንድ ቀን
ከቅርብ ጊዜ ወዲ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ የሙዚቃ ዝግጅቶች መብዛታቸው የሚታይ ሲሆን ለዚህም ማረጋገጫ የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 18 ሁለት ለየት ያሉ ከ 10 ሺ እስከ 15ሺ ሰው ሊገኝባቸው የሚችሉ ዝግጅቶች ተሰናድተዋል።
አንደኛው ሽር ጉድ ኮንሰርት የተሰኘው የሶስት ዘመን ድንቅ ድንቅ ዘፋኞችን የሚያገናኝ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ አንጋፋው ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩን ጨምሮ የዘጠናዎቹ የኢቫንጋዲ አልበም ድምቀቶች ጎሳዬ ተስፋዬ እና አለማየሁ ሂርጶ እንዲሁም ከዘመኑ ድምፃዊ ደግሞ ሜላት ቀለመወርቅን ያገናኘ ሆኗል።
ሁለተኛው በጊዬን ሆቴል የሚካሄደው ደግሞ ልኡል ኮንሰርት የተሰኘው ሲሆን ተወዳጆችን የዘመኑ ሙዚቀኞች እራሱ ልኡል ሲሳይን ጨምሮ ሃና፣ ስካት ናቲን እና ዊሃን አገናኝቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Leulsisay | 58 |
| 17 | 'እዚራ' አልበም እዚራ አንድ ኢትዮጲያዊ የሆነ የሙዚቃ መሳርያ ነው፡፡ በዚህ ስያሜ መምጣቱ አልበሙን በብዙ መንገድ እንዳስበው አርጎኛል፡፡ በሙዚቃዎቹ ውስጥ ተወዳጁን ማዲንጎ አፈወርቅን እንድናስታውስ የሚደርገን ብሎም አብዛኛው በዜማ የሰራው እራሱ ማስተዋል ሲሆን ይህ ሌላኛው የማዳመጥ ክህሎት የመጣበት የሙዚቃ ደረጃ ምን ያህል እንደሆነ ይነገርናል፡፡የሙዚቃ ቫራይቲ(የተለያየ አይነት ስልት እና ሐሳብ ) ሬጌ ፣ ሱዳኒክ ፣ ትዝታ፣ ፎክ (ባህላዊ የሙዚቃ አዛዝያም)፣የቅኝትሙዚቃዎች ተሰርተዋል፡፡14 የሙዚቃ ክሮች ሲኖሩት ደጉ ትዝታ ፣ መጥቼ ነበር ፣ በምን ቃል፣ ደግሰን ፣ ከፋኝ ፣ እንዚራ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡
ከአልበሙ የገረመኝ እና የወደድኳቸው የሙዚቃ ስራዎች ከአብዛኛው ጥቂቱን ልገልፅላችሁ፡፡
"ከፋኝ" (ትዝታ) የተሰኘ ሙዚቃ ሐሳብ የግጥም ውህደቱ ለዚህ ዓለም ጉዞ በሰውኛ አገላለፅ ሌላው መንገድ ሰውኛ እውነትን ሆኖ እዉነትነትን ሳይስት ይናገናል፡፡ በመከፍት በህመም መደራረብ ውስጥ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች አሉ አብረን የኖርነው መልክ እያየነው ሲጠወልግ ዛሬ ላይ ያሉ ትናንትናዋን ያላወቁ ሰዎች በመልኳ ሲሳለቁ እሱ ግን ቆም ብሎ ትናንት አውቃታለሁ ለዚህ እንኳን ገላጋይ ዳኛ አያስፈልግም እኔ ምስክር ነኝ በምንም በሁሉም የትማርክ ነበረች ጊዜ ጥሏት እንጂ፡፡ግጥም ጥላሁን ሰማው ዜማ አበበ ብርሀኔ ቅንብር ታምሩ አማረ(ቶሚ)
"የማለዳው ለምለም- ውበቷ ቄጤማው
ጠውልጎ አየሁ ዛሬ - ሲፈርድ እድሜ ዳኛው
አወይ ዘመን - ባዳ አቤት ጊዜ ክፉ
ለምልክት እንኳን - አንድ አለ ማትረፉ"…
"(እቴ)" (ሞደርን ፎክ) ባህል ዘመናዊ የተሰኘው ሙዚቃ ቅንብሩ የዘጠዎቹ /ሰባዎቹ ሙዚቃ ቅርፅ እንድናስታውስ ያደርገናል የሙዚቃ ቅንብሮቹ በምክንያት የተሰሩ የማስተዋል የድምፅ እርከን ስፋት በሚገባው የድምፅ ጉልበት የተጠቀመበት ድንቅ ሙዚቃ ፅዱ ማንነት ገለጣ፡፡ ዜማ ምረት አብ ደስታ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ)::
"የቆንጆ ፍቅር - እና- ትንታ ያለበት
ሞት ቅርቡ ነው- እና- ውሀ አታርቁበት
ችዬው ልኑር እንጂ - ስራበው ወይ ስጠማሽ
መቼም ሰው አይድንም - ከሐመልማሎ ገላሽ"
"ጉብልዬ(ቅኝት)" የነፀብራቅ ድምፅ የሙዚቃ ጉልበቱ የታየበት የመጀመርያ ቅኝትን መቆጣጠር ፣ ሁለተኛው የእተቀባበሉ መዝፈን ፈተናው እና የውበት ፍሰቱን በመግለፅ ብዙ ነገሩ ስኬታማ አጫዋች ሆኖ ያየንበት ነው፡፡ሐሳቡ ትዝታን ወደ ኃላ እየቃኘ ስለ አንድ ሰው እሱ በሌለበት ወዳጆቹ ሲነጋገሩ ሲጨዋወቱ፡፡ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ዜማ የህዝብ እና መስተዋል እ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡
''አጋርሽ መሆኑን ሰምቼ ፣ ያ የጥንት ወዳጅሽ ወዳጄ
እቴ ሙች ግራ ነው የገባኝ ፣ ሕይወት እንቆቅልሽ ሆኖ ባይ
እስኪ ግለጪልኝ ይሄን ነገር ፣ ያ ሰው የዛን ጊዜ ምንሽ ነበር''::
"እመጣለሁ" የፍቅር ትርጉም አንዱ አገላለፅ ይህንን አሳብ የተሸከመ ነው፡፡የግጥሙ ሐሳብ የምትወደው ሰው ህመምን መዋዋስ ሳይሆን እመምን ብቻህን መጋፈጥ ለምትጋፈጥበለት ሰው ደስታውን ሁሉ መመልከት ምክንያቱም ፍቅር በስቃይ ይጣፋል እና…ግጥም እና ዜማ አቡዲ ቅንብር ሚካኤል ሀይሉ፡፡
ከጀርባሽም ብሆንም - እንደ ዓይንሽ ልይልሽ
እንቅፋት ሲያይብኝ - እኔ እንድመታልሽ
------------
እኔ አንቺን - ስለምወድ ስለምወድ
እመጣለሁ ሂጂ እና - በአንቺ መንገድ
እነዚህ እና የመሳሰሉት ጣዕም ያላቸው ሙዚቃዎች ሰቶናል፡፡ነፍስ እንዲዘራ ደግሞ የሙዚቃ ከያኒያን በዚህ ልክ አጥብቀው ሙዚቃ የሚፈልገውን ስሜት ሰተውታል በቅንብር ብሩክ አፈርቅ ፣ ሚካኤል ሀይሉ(ሚኪ ጃኖ) ፣ ታምሩ አማረ(ቶሚ) በጥግም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ፍሬዘር አበበ ወርቅ ፣ ማስተዋል እያዩ ፣ አብዲ ፣ጥላሁን ሰማሁ ፣ ታመነ መኮንን ፣ ብሬ ብራይት ፣ እሱባለሁ ይታየሁ( የሺ )፣ አበበ ብርሀኔ ፣ ቢኒያምር አህመድ ፣ አንባቸው እሸቱ፣ ምረት አብ ደስታ ማስተሪንግ ሰለሞን ሀይለማርያም የመሳሰሉ ሰርተውታል፡፡
በዚህ አልበም ላይ እጃችሁ ያሳረፋችሁ ሁሉ በግሌ አመሰግናለሁ
የሙዚቃ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Mastewal_eyayu | 69 |
| 18 | የድምፃዊ የሺ ደመላሽ አዲስ አልበም የመውጫው ቀን ተቆረጠለት…
#Ethiopia | ድምፃዊት የሺ ደመላሽ ብዙጊዜ የተለፋበትን አልበም ውብ ሰው የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ሚያዚያ 12/2017 አመተ ምህረት እንደ ሚወጣ ጠቁማለች፡፡
ድምፃዊ የሺ ደመላሽ "ውብ ሰው" የሙዚቃ አልበም በራስዋ ዩትዮብ ቻናል እና በሌሎች የሙዚቃ መተግበርያ ወደ ህዝብ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ድምፃዊ የሺ ደመላሽ የመጀመርያ አልበምዋ "ቅኔ" አልበም ማድረሷ ይታወሳል በውስጡ 12 የሙዚቃ ክር ሲኖረው ቅኔ ፣ፋኖ፣ትኩስ እና በራድ ፣ኮከብ፣ዛሬ፣መልካም እና ክፊ እና የመሳሰሉት ሲካተቱ በርካታ ከያኒያን ተሳትፈዋል በግጥም ዜማ አብዛኛውን ድምፃዊት የሺደም ደመላሽ ስትሆን ቀሪውን ሰለሞን ሙሄ እና አንድዋለም አባተ ሰርተውታል፡፡
ቅንብር ፡ሮቤል ዳኜ(10) ትራክ፣እዮብ ፋንታሁን(2) ቀሪው ትራክ ሰርተውታል ሬጌ ሮክ፣ ሬጌ ስልተምት እና ሌሎችም ስልተ ምት ተካተዋል፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #yeshi_demelash | 127 |
| 19 | ⚽️❤️GUNNERS መድፍ
ዛሬ ማታ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 4 ስአት ላይ በኢትዮጵያ ብዙ ሚሊዮን ደጋፊዎች እንዳላቸው የሚነገረው መድፈኞቹ በስፔኗ ማድሪድ ከተማ ታላቁን እና ግዙፉን " ሪያል ማድሪድን " ይፋለሙታል::
ባለፈው ሳምንት የመጀመሪያው ዙር ኢምሬትስ ስታዲዮም ላይ 3 ለ 0 ያሸነፉ መሆኑን የሚታወቀ ሲሆን
ይህን የዛሬን ወሳኝ ጭዋታ ሚሊዮኖች በጉጉት
እየጠበቁት ይገኛል::
እንዲሁም ከኢትዮጵያ ታዋቂ ድምፃዊያን ቀንደኛ የአርሰናል ደጋፊዎች ውስጥ :-
1. ልጅ ሚካኤል
2. ሳሚ ዳን
3. አስጌ ዴንዳሾ
4. ታደለ ሮባ
5. ሰይፉ ( አርሰናል ከፍ ሲል ብቻ የሚደግፍ)
6. ድምፃዊ ተሙ (የሽንብራው ጥርጥር)
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Arsenal | 127 |
| 20 | እውቋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ የጠፈር ጉብኝቷን አጠናቃ ተመለሰች
የፖፕ ኮከቧ ኬቲ ፔሪን ያካተተው የብሉ ኦርጂን ኩባንያ የጠፈር ቡድን ሰኞ ማለዳ ወደ ጠፈር ለጉብኝት ተጉዟል።
በረራው በሙሉ የሴቶች ቡድን የተደረገ ሲሆን እንደ ኩባንያው ገለጻ ይህ በረራ ከአውሮፓውያኑ 1963 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የተደረገ የጠፈር በረራ ሆኗል::
ከታዋቂዋ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ ጋር፣ የብሉ ኦርጂን ባለቤት የሆነው የጄፍ ቤዞስ እጮኛ ላውረን ሳንቼዝም በጉብኝቱ ውስጥ ተካታለች።
ኬቲ ፔሪ ከብሉ ኦርጂን የጠፈር በረራ አጠናቃ ወደ ምድር እንደተመለሰች ደስታዋን እና ምስጋናዋን ገልጻለች።
ሙዚቀኛዋ ልምዷን "ሕይወትን የሚቀይር" በማለት ስትሰይም በረራው ስለሚሰጠው ጥልቅ የአመለካከት ለውጥ አፅንዖት ሰጥታ ተናግራለች::
"ይሄ ከሁሉ የላቀ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነው" በማለት ነው የገለፀችው።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #kettyperry | 108 |
