cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Legal Service Provider

በማንኛውም የህግ ጉዳዮች የጥብቅና እና የህግ ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን !!!

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
204
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በየመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች መግቢያ ንብረት ማፍራት እና መጠቀም አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ሰብዓዊ መብቶች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያም የንብረት መብት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት ጀምሮ በተለያዩ ፖሊሲዎች እና ህጎች ውስጥ ተካቶ ይገኛል። በህገ መንግስቱ አንቀፅ 40/1 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረቱ ባለቤት መሆኑ/መሆኗ ይከበርለታል/ይከበርላታል። እንዲሁም በንዕስ አንቀፅ 7 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ በመሬት ላይ ለሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም ለሚያደርገው ቋሚ መሻሻል ሙሉ መብት አለው። ቋሚ ንብረት ከሚባሉት ውስጥ ቤት አንዱ ነው። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊጠቀምበት ከሚችልባቸው ሁኔታዎች ውስጥ በኪራይ ለሌላ ሰው በማስተላለፍ የቤት ኪራይ ክፍያ በመግኘት ነው። ቤቱን የሚያከራይ ሰው ለራሱ ከኪራዩ መጠቀሙ እንዳለ ሆኖ ቤቱን በማከራየቱ ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የሚያደርግ ስለሆነ የቤት ኪራይ ጥቅሙ ለሁለቱም ወገን ማለት ለአከራይም ለተከራይም ይሆናል። የቤት ባለቤት የሆነ ሰው ቤቱን ሊያከራይ ከሚችልባቸው አገልግሎቶች ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት ማከራየት ይገኝበታል። በአከራይ እና በተከራይ መካከል የሚኖረው ግንኙነት በህግ የተደገፈ ሲሆን የሁለቱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ይሆናል። በመሆኑም የመኖሪያ ቤት ኪራይን የሚቆጣጠር እና የሚያስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ታውጆ በስራ ላይ እንዲውል ሆኗል። በመሆኑም በዚህ አጭር የንቃተ ህግ ትምህርታዊ ፅሁፍ ስለ አዋጁ አስፈላጊነት እና የተፈፃሚነት ወሰን፣ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን፣ ለአከራይ ስለሚሰጥ ማበረታቻ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚታደስበት ሁኔታ፣ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች በወፍ በረር ይዳሰሳሉ። • የቤት ኪራይ ውል ምንነት በአዋጁ አንቀፅ 2(1) ስር እንደተደነገገው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማለት ለመኖሪያነት የሚያገለግል አንድ ወይም ከአንድ በላይ ክፍሎችን የያዘ ቤትን ተከራይቶ በመጠቀም ለሚያገኘው አገልግሎት ለአከራይ ክፍያ እየፈፀመ የሚኖርበት የውል ግንኙነት ነው። ይህን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ የሚቆጣጠር አካል በክልል እንደሚሰየም አዋጁ ያስቀምጣል። • የአዋጁ አስፈላጊነት በሀገራችን አሁን ባለው ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ እና በዜጎች ኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት አንገብጋቢ እና መሰረታዊ የመብት ጉዳይ እንደመሆኑ መንግስት የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን ለማሟላት እያደረገ ካለው ጥረት ጎን ለጎን እየናረ ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማህበረሰቡን አቅም ያገናዘበ እና ተመጣጣኝ እንዲሆን በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት ንረት በአግባቡ መቆጣጠርና ማስተዳደር በማስፈለጉ አዋጁን ማውጣት አስፈላጊ ሆኗል። በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ያለው እና የአከራዮችን እና ተከራዮችን ጥቅም እና መሰረታዊ መብቶች ሚዛን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ ወጥቷል። • የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሰን ይህ አዋጅ ተፈፃሚ የሚሆነው ተጠሪነታቸው ለክልል በሆኑ ከተሞች፣ በአዲስ አበባ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ላይ በሚፈፀም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ ሲሆን ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በሌሎች ከተሞች ላይ ተፈፃሚ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ ክልሎች ነባራዊ ሁኔታውን እያዩ እንደሚወስኑ አዋጁ ያስቀምጣል። በተጨማሪም አዋጁ ተፈፃሚ ከሚሆንበት ሁኔታ ውጪ ተፈፃሚ የማይሆንበት ሁኔታን የተመለከተ ሲሆን አዋጁ በሆቴል፣ ሪዞርት፣ የእንግዳ ማረፊያ እና ሌሎች በንግድ ፈቃድ መሰረት በሚከራዩ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ተደንግጓል። • ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እና ዋጋ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል በፅሁፍ የሚደረግ ሆኖ በተቆጣጣሪው አካል መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት የአዋጁ አንቀፅ 4(1) የሚደነግግ ሲሆን የኪራይ ክፍያውም በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤሌክትሮኒክ ዘዴ ብቻ የሚፈፀም ይሆናል። ተቆጣጣሪው አካል የማረጋገጥ እና የምዝገባ ስራውን ሲሰራ በክልሉ ሰነድን የማረጋገጥ ስልጣን ካለው አካል ጋር የሚሰራ ሲሆን ውሉ በፅሁፍ የመሆን መስፈርት፣ የማረጋገጥ እና የመመዝገብ ግዴታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እድሳት ላይም ተፈፃሚ ይሆናል። አከራይ እና ተከራይ ውሉን በተፈራረሙ 30 ቀናት ውስጥ የማረጋገጥ እና እንዲመዘገብ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። በአዋጁ አንቀፅ 4(5) ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገበ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል እንዳልተደረገ ይቆጠራል። የማረጋገጥ እና የምዝገባ ግዴታን ያለመወጣት በአከራይ ወይም በተከራይ ላይ በተቆጣጣሪው አካል በሚወጣ መመሪያ የሚወሰን የገንዘብ ቅጣት የሚያስከትል ሲሆን የገንዘብ ቅጣቱ በማንኛውም ሁኔታ ባልተመዘገበው ውል ላይ ካለው የሶስት ወር ኪራይ ሊበልጥ አይችልም። በተጨማሪም አዋጁ ተቆጣጣሪው አካል የቤት ኪራይ ውል ሞዴል ማዘጋጀት እና የተቋሙ ድረ-ገፅ ጨምሮ በሌላ በማናቸውም መንገድ ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ እንዳለበት ይደነግጋል። ሌላው በአዋጁ የተካተተው ጉዳይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ሲሆን የተመዘገበ የኪራይ ውል ላይ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ የቤቱ የኪራይ ዋጋ እንደሆነ ተደርጎ እንደሚወሰድ ነው። ይህ እንደለ ሆኖ ተቆጣጣሪው አካል በአዋጁ መሰረት የወሰነው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ማሻሻያ መነሻ በማድረግ አከራይ የጨመረው የቤት ኪራይ ዋጋ የመኖሪያ ቤቱ ኪራይ ውል ላይ የተመለከተው የኪራይ ዋጋ አካል ተደርጎ ይወሰዳል። ውሉ በሚታደስበትም ሆነ በሚፈረምበት ወቅት በነባር ተከራይም ሆነ በአዲስ ተከራይ ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚቻለው ከላይ የተመለከተውን የቤቱ ኪራይ ዋጋ መነሻ አድርጎ በመውሰድ ነው። በአዋጁ አንቀፅ 8(4) ስር እንደተደነገገው አከራይ ለነባር ተከራይ ወይም ለአዲስ ተከራይ በሚያከራየው የመኖሪያ ቤት ላይ ቀደሞ በነበረው ኪራይ ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው ተቆጣጣሪው አካል በአመት አንድ ጊዜ ነባራዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ጉዳዮች ከግምት በማስገባት ሊወስን የሚችለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ መሰረት በማድረግ ነው። በዚሁ መሰረት የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ በተቆጣጣሪው አካል በሰኔ አንድ ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የፀና ይሆናል። አከራይ በአዋጁ መሰረት የቤት ኪራይ ውሉ የተመዘገበን የመኖሪያ ቤት ውል የውል ዘመኑ መጠናቀቅ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሳያከራየው ቆይቶ በኋላ ለኪራይ ሲያቀርበው የቤቱ የኪራይ ዋጋ የሚሆነው የቤቱ ኪራይ ሳይቋረጥ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ የሚኖረው የኪራይ ዋጋ ነው። አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ወደኋላ ሁለት ዓመት በፊት የኪራይ ውሉ የተቋረጠ የመኖሪያ ቤት አዋጁ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ ለኪራይ ከቀረበ በአዋጁ መሰረት ሊጨመር የሚችለው የኪራይ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለመጨረሻ ጊዜ ሲከራይ በነበረው ዋጋ የሚከራይ ይሆናል። የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የዋጋ ግመታ ሥርዓት በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ እስከሚወሰን ድረስ አዲስ የተገነባ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ለኪራይ የቀረበ የመኖሪያ ቤት በሚከራይበት ጊዜ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት የሚወሰን ይሆናል።
إظهار الكل...
በሌላ በኩል አከራይ ቀደም ሲል ሲከራይ የቆየ የመኖሪያ ቤት ወይም ግንባታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ አዲስ ቤት ያለአገልግሎት ከ 6 ወር በላይ እንዲቀመጥ ካደረገ ቤቱ ቢከራይ ሊከፍል ይችል የነበረውን መኖሪያ ቤት ኪራይ ገቢ ግብር ተሰልቶ እንዲከፍል እንደሚደረግ የአዋጁ አንቀጽ 8(10) ያስቀምጣል። • የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ዘመን በአዋጁ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን በስምምነት፣ በማስታወቅ ወይም በማስጠንቀቂያ ስለማቋረጥ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት አመት ሊያንስ እንደማይችል በአንቀፅ 6(1) ስር ተደንግጎ ይገኛል። እንዲሁም ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ውል ሲገባ አከራይ ከተከራይ ላይ ሊጠይቅ የሚችለው ቅድሚያ ክፍያ ከ2 ወር የቤቱ ዋጋ ሊበልጥ አይችልም። ይህም በተለምዶ የሶስት ወር የቤት ኪራይ በቅድሚያ ተከፍሎ ለስድስት ወር የሚደረግ የቤት ኪራይ ውልን ያስቀረ፣ ለተከራይ ረዘም ያለ የኪራይ ጊዜ የሰጠ እና አነስተኛ ቅድመ ክፍያ ያስቀመጠ መሆኑን ያመለክታል። በአዋጁ አነስተኛ የውል ዘመንን የተመለከተው እንዳለ ሆኑ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በፅሁፍ የተደረገ የመኖሪያ ቤት ከራይ የውል ዘመን በውሉ ላይ የተቀመጠው የውል ዘመን ይሆናል። የአንድ ቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በእዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ወገን ከተላለፈ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የ6ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራዩ በመስጠት ነው። ይሁንና ቤቱ ለሌላ ወገን የተላለፈው በስጦታ ከሆነ ተከራይ የውል ዘመኑ እስኪያልቅ ድረስ በተከራየው ቤት የመቆየት መብት ይኖረዋል። የቤት ባለቤትነት በውርስ፣ በሽያጭ፣ በእዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት ለሌላ ሰው በመተላለፉ ውሉ የተቋረጠ እንደሆነ በአዋጁ መሰረት የሚደረግ የቤት ኪራይ ጭማሪ እንደተጠበቀ ሆኖ የቤቱ የኪራይ ዋጋ በተቋረጠው ውል ላይ የተቀመጠው የኪራይ ዋጋ ነው። በአዋጁ እንቀፅ 6(7) ስር እንደተደነገገው የቤት ኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ ተከራይን ከቤት ማስወጣት ወይም በአዋጁ ከተፈቀደው ሁኔታ ውጪ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። • ለአከራይ ስለሚሰጥ ማበረታቻ በአዋጁ አንቀፅ 10(1) ስር እንደተደነገገው አዲስ ቤት ሰርቶ ለኪራይ ያቀረበ አከራይ በአዋጁ ከሚወጡ የቤት ኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚቆጠር አራት አመት ነፃ ይሆናል። እንዲሁም አከራይ ነባር እና ተከራይቶ የማያውቅ የመኖሪያ ቤቱን ለኪራይ ካቀረበ በአዋጁ መሰረት ከሚወጡ የቤት ኪራይ ዋጋ ጣሪያ ግዴታዎች የመጀመሪያውን የቤት ኪራይ ውል ካስመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ለሚቆጠር ሁለት አመት ነፃ ይሆናል። ይሁንና የኪራይ ምዝገባን የሚመለከቱ እና ሌሎች የአዋጁ ድንጋጌዎች እና ግዴታዎች ተፈፃሚነት አላቸው። በሌላ በኩል የመኖሪያ ቤትን ሳያከራዩ በባዶ ወይም በሌላ አግባብ ለንግድ ወይም ለመኖሪያ ወይም መሰል ተመጣጣኝ ማህበራዊ ፋይዳ ያለው አገልግሎት ሳይሰጥ ከአንድ ዓመት በላይ የሚያቆዩ የቤት ባለቤቶች የቤቱን የንብረት ግብር ተመን 25% የሚያክል ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አሰራር ከፍተኛ የቤት እጥረት ባለባቸው የከተማ አስተዳደሮች በመመሪያ ሊዘረጋ ይችላል። • የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚታደስበት ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ውል ዘመኑ ሲያበቃ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት በፅሁፍ ሊታደስ ይችላል። ውሉ ሲታደስ አከራዩ ሊያደርግ የሚችለው የቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ተቆጣጣሪው አካል በዓመት አንድ ጊዜ ከሚያደርገው ጭማሪ ጣርያ ሊያልፍ አይችልም። • የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ስለሚቋረጥበት ሁኔታ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ዘመኑ ሳይጠናቀቅ በአከራዩና ተከራዩ ስምምነት፣ ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ወይም የቤት ባለቤትነት በህጋዊ መንገድ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ የ6 ወር ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊቋረጥ ይችላል። እነኚህ ውሉ በማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ምክንያቶች ሲሆኑ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በአንቀፅ 16 ስር እንደሚከተለው ተዘርዝረው ይገኛሉ። • የቤት ኪራይ በውሉ በተመለከተው የመክፈያ ጊዜ ለመጀመሪያ ከሆነ ከ15 ቀን ካሳለፈ፣ • የቤት ኪራዩን በውሉ ከተመለከተው ቀን ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣ • ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣ • የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ፣ • በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈፅም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀምበት ከሆነ፣ • አስቦ ወይም በቸልተኝነት በቤቱ ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ወይም በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት ነው። በተጨማሪ አዋጁ የቤት ኪራይ ውል መቋረጥ የሚያስከትለውን ውጤት በአንቀፅ 17 ስር ያስቀመጠ ሲሆን ውሉ ያለማስጠንቀቂያ ከተቋረጠ በአዋጁ መሰረት ጭማሪ ሊደረግባቸው በሚችሉ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ቤቱ ለሌላ ሰው ሲከራይ ቀድሞ ከነበረው የኪራይ ዋጋ ላይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም። አከራይ ይህን ክልከላ በመጣስ የዋጋ ጭማሪ ያደረገ ከሆነ ተቆጣጣሪ አካሉ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ሊጥለው ከሚችለው የገንዘብ ቅጣት በተጨማሪ፣ በአዲሱ ተከራይ አመልካችነት የቤት ኪራዩ ውሉ ወደ ቀድሞ የኪራይ ዋጋ እንዲመለስ ሊያደርገው ይችላል። በአዋጁ አንቀጽ 21(1) እና 22 ላይ እንደተደነገገው ማንኛውም በአከራይ እና ተከራይ መካከል የሚያጋጥም እና የአዋጁን አፈፃፀም የተመለከተ አለመግባባት እንዲፈታ ለተቆጣጣሪ አካሉ በአከራይም ሆነ በተከራይ በፅሁፍ የአለመግባባቱ ማመልከቻ መነሻ የሆነው ጉዳይ ባጋጠመ በ30 የስራ ቀናት ውስጥ በፅሁፍ መቅረብ አለበት። ማመልከቻው የቀረበለት አካልም ቅሬታውን መርምሮ በ 30 የስራ ቀናት ውስጥ ውሳኔ መስጠት አለበት። በመጨረሻም በአዋጁ መሰረት የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና ቅጣቶች ተቆጣጣሪው አካል በሚያወጣው መመሪያ የሚወሰኑ ሲሆን አዋጁም በህዝብ ተመካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ማለትም በመጋቢት 24/2016 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል። በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
إظهار الكل...
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መልቀቅ ማቆሙ ተሰምቷል ንግድ ባንኩ ብድር ለማግኘት የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ፤ ብድሩ ተፈቅዶላቸው የመልቀቅ ሂደት ላይ ያሉትም እንዲቆም ነው ያዘዘው ። ባንኩ ይህን ትእዛዝ ያስተላለፈው ረቡዕ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም መሆኑንም ሰምተናል ። ንግድ ባንኩ በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ከማቆሙ በስተቀር ባስተላለፈው ትእዛዝ ላይ ብድር መልቀቅ ያቆመበትን ምክንያት አልገለጸም። ሆኖም ከብድር መልቀቅ መለስ ያሉት የብደር ጥያቄ እና ሂደቶቹ አለመቆማቸውን ሰምተናል ። መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ እስከ ዛሬ የሰጠው ብድርም ሆነ የሰበሰበው ቁጠባ ከአንድ ትሪሊየን ብር ያለፈ ብቸኛ ባንክ መሆኑ የሚታወቅ ነው ። ባንኩ በቅርቡ በተገበረው የሲስተም ማሻሻያ ሳቢያ በተፈጠረ ስህተት 801 ሚሊየን ብር ለምዝበራ ተዳርጎበት እንደነበረ እና ከዚህ ውስጥ አብዛኛውን ገንዘብ ባደረገው ክትትል ማስመለሱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ በሰጡት መግለጫ ተናግረው ነበር ። ባንኩ ገንዘቡን የማስመለስ አካል ነው ያለውን ባልተገባ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ ተሳትፈዋል ያላቸውን ደንበኞች ፎቶ ሳይቀር ለህዝብ ይፋ አድርጓል ። አሁን በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ ማቆሙ ከዚህ ጋር ይገናኝ አይገናኝ አልታወቀም ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፈው አመት ብቻ 151 ቢሊየን ብር ብድር የሰጠ ሲሆን ፤ በተመሳሳይ አመት 165 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ቁጠባን ደግሞ ሰብስቦም ነበር ።ሆኖም ይህ በጀት አመት ከገባ ግን የቁጠባ አሰባሰቡ ከእቅዱ ጋር እየሄደ አለመሆኑ ተሰምቷል ። ለአብነትም በዚህ በጀት አመት የመጀመርያ ስድስት ወራት የሰበሰበው ቁጠባ ከእቅዱ አንጻር ከግማሽ በታች መሆኑም ተዘግቧል ። ለዚህ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ያለው ችግር እንደ ምክንያት ተጠቅሷል ። ምናልባትም የአሁኑ የባንኩ በጊዜያዊነት ብድር የማቆም ውሳኔ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከተፈጠረ የገንዘብ እጥረት ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ተዘግቧል። ዋዜማ
إظهار الكل...
ከወራት እስር በኋላ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሀንስ ቧያለው ዛሬ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው ክስ ሳይመሠረትባቸው ለስድስት ወራት በእስር ቆይተው ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀረቡት የፌደራል እና የክልል ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ፖለቲከኞች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተሰምቷል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እንዲሁም የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሀንስ ቧያሌው እና ሌሎች ፖለቲከኞችን ጨምሮ ከስድስት ወራት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉት በአማራ ክልል የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ነው። ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው ለስድስት ወራት በእስር ላይ ቆይተው ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ በአቶ ክርስቲያን ታደለ፣ በአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ በአቶ ዮሐንስ ቧያለው እና በአዲስ አበባ ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ካሳ ተሻገር ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ረቡዕ መጋቢት 18/2016 ዓ.ም. ክስ መሥርቷል። የፍትሕ ሚኒስቴር ክሱን የመሰረተው የፀረ ሽብር አዋጅን ጠቅሶ የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ዮሐንስ ቧያለው ስም ነው።
إظهار الكل...
በአጠቃላይ በውጭ ሀገር የተሰጠን ፍርድ እና የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ለማስፈፀም በህጉ የተደነገጉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡ በመሆኑም በውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድ ወይም የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ውሳኔ ማስፈፀም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በቅድሚያ ቅድመ ሁኔታዎቹ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ በንቃተ ህግትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
إظهار الكل...
በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ ወይም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ የሚፈፀምበት ሁኔታ የሰው ልጆች መስተጋብር በተለይ በአሁኑ የአለም ሁኔታ በሀገራት ድንበር የተገደበ አይደለም፡፡ በዚህ መስተጋብር መካከል ወደ ፍርድ ቤት ወይም ወደ ሌሎች አማራጭ የግጭት መፍቻ ዘዴዎች የሚሄዱ እና አፈፃፀማቸው በተለያዩ ሀገራት የሚሆኑ ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ መሰል የውጭ ሀገር ፍርዶችን የማስፈፀም ጉዳይ የአለም አቀፍ የግለሰቦች ህግ (private international law) አካል ሲሆን ሀገራት የውጭ ሀገር ፍርድ ለማስፈፀም እንዲረዳቸው የህግ ማእቀፍ ያዘጋጃሉ፡፡ በተጨማሪም በርካታ ሀገራት ሁለት ውይም ከሁለት በላይ ባሉ ሀገራት በሚደረግ የአለም አቀፍ ስምምነት የውጭ ሀገር ፍርድን ያስፈፅማሉ፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ በውጭ ሀገር የተሰጡ ፍርዶች እና በውጭ ሀገር የተሰጠ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ በሀገራችን የሚኖረውን የአፈፃፀም ሥርአት እንመለከታለን፡፡ በውጭ ሀገር የተሠጡ ፍርዶች ምንነት የውጭ ሀገር ፍርድ ማለት በውጭ ሀገር መንግስት ፍርድ ቤት የተሰጠ ፍርድ ማለት እንደሆነ እና የውጭ ሀገር ፍርድ ቤት ማለት ደግሞ ከኢትዮጵያ ግዛት ክልል ውጭ የሚገኝ በሀገሩ ህግ መሰረት የተቋቋመ የማናቸውም ሀገር ፍርድ ቤት እንደሆነ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ አንቀፅ 3 ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ በተጨማሪም የግልግል ዳኝነት እና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 ዓ.ም አንቀፅ 2(8) በውጭ ሀገር ለተሰጠ የግልግል ዳኝነት ውሳኔ ትርጉም የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ ባፀደቃቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሠረት በውጭ ሀገር እንደተሰጠ የሚቆጠር የግልግል ውሳኔን ወይም የግልግል ዳኝነቱ መቀመጫ በውሳኔው ውስጥ ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ መሆኑ የተገለፀበት ውሳኔ እንደሆነ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡ በውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ እንዲፈፀም የሚቀርብበት ሥርአት በአለም አቀፍ ስምምነት በተለየ እንዲፈፀም የሚያደርግ ልዩ ህግ ከሌለ በስተቀር ከኢትዮጵያ ግዛት ውጭ የተሠጠ ፍርድ፣ ውሳኔ ወይም ብይን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀመው በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ መሰረት እንደሚሆን በሥነ ሥርአት ህጉ አንቀፅ 456 ተመልክቷል፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ አንቀጽ 456(2) መሰረት የውጭ ሀገር ፍርድ የሚፈፀመው እንዲፈፀም ማመልከቻ ከቀረበ ብቻ ነው፡፡ በፌ.ዴ.ራ.ል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ዓ.ም መሰረት የውጭ ሀገር ፍርድ ማስፈፀም ስልጣን የተሰጠው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሆኑ ማመልከቻው መቅረብ ያለበት ለዚሁ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ይህ ማመልከቻ ሲቀርብም  የሚፈፀመው የውጭ ሀገር ፍርድ ትክክለኛነት የተረጋገጠበት የፍርድ ግልባጭ  ፍርዱ በተሰጠበት ሀገር ፍርዱ የመጨረሻ እና መፈፀም የሚገባው መሆኑን የሚያረጋግጥ በፈረደው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወይም ሬጅስትራል የተፈረመ የምስክር ፅሁፍ በአባሪነት አብሮ መቅረብ አለበት፡፡ የውጭ ሀገር የተሰጠ ፍርድ እንዲፈፀም ማመልከቻ የቀረበለት ፍርድ ቤት ባለእዳው ቀርቦ አስተያየቱን እንዲገልፅ መብት መስጠት ያለበት ሲሆን ለዚህም ቀነ ቀጠሮ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ጉዳይ ለማጣራት ተከራካሪ ወገኖችን አስቀርቦ ክርክራቸውን መስማት አስፈላጊ ነው ብሎ ካላመነ በስተቀር ውሳኔ የሚሰጠው በቀረበለት ማመልከቻ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የውጭ ሀገር ፍርድ የሚፈፅመው ፍርድ ቤት በማናቸውም ግዜ የሚያጠራጥር ሁኔታ ያጋጠመ እንደሆነ አጠራጣሪ የሆነው ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ በአንቀፅ 459(3) መሰረት የውጭ ሀገር ፍርድ አፈፃፀም ውሳኔን ሊያግደው ይችላል፡፡ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ተቀብሎ ፍርዱን ለማስፈፀም ከወሰነ አፈፃፀሙ የሚመራው በኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠ ፍርድ በሚፈፀምበት ሥርአት እንደሚሆን በሥነ ሥርአት ህጉ አንቀፅ 460(3) ተመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ ሲወስን ስለወጪ እና ኪሳራ አከፋፈል አብሮ መወሰን አለበት፡፡ በውጭ ሀገር የተሠጠ ፍርድ ወይም ብይን የማስፈፀም ቅድመ ሁኔታዎች በውጪ ሀገር የተሰጠ ፍርድ ይፈፀም ዘንድ ሥነ ሥርአት ህጉ በአንቀፅ 458 ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎቹም መሟላት አለባቸው፡፡ ይኸውም እንዲፈፀም የተጠየቀውን ፍርድ የሰጠው ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ የተሰጠን ፍርድ የሚፈፅም መሆኑ መረጋገጥ ፍርዱ የተሰጠው በህግ በተቋቋመ ፍርድ ቤት መሆን ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት የፍርድ ባለእዳው መቃወሚውን እና መከራከሪያውን ለማሰማት መብት ተሰጥቶት የነበረ መሆኑ መረጋገጥ የሚፈፀመው የውጭ ሀገር ፍርድ የመጨረሻ እና ተፈፃሚነት ያለው መሆኑ መታወቅ (የመጨረሻ ፍርድ የሚባለው በይግባኝ የሚታይበትን ሂደት በሙሉ የጨረሰ እና እንደገና የማይታይ ሲሆን ነው፡፡) የሚፈፀመው የውጭ ሀገር ፍርድ ለህዝብ ሞራል (public moral) እና ፀጥታ (public order) ተቃራኒ ያልሆነ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የህዝብ ሞራል ሲባል የሚፈፀመው የውጭ ሀገር ፍርድ በሀገራችን ህብረተሰብ ዘንድ በጠቅላላው ተቀባይነት ያለው ወይም ለባህል ተቃራኒ ያልሆነ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ህግ ተቀባይነት ሌላቸው የኮንትራት(የውል ጋብቻ) ወይም ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በሌላ ሀገር ቢከናወን እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በተነሳ ክርክር አፈፃፀሙ ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ ለህግ እና ለሞራል ተቃራኒ በመሆኑ ኢትዮጵያ ማመልከቻውን ተቀብላ አታስፈፅምም፡፡ እነዚህን በህጉ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች የማያሟላ የውጪ ሀገር ፍርድ በኢትዮጵያ ሊፈፀም አይችልም፡፡ በተመሳሳይ በውጭ ሀገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን በሀገራችን የሚፈፀመው በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ አንቀፅ 461 የተመለከቱ ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላ ብቻ ነው፡፡ ይኸውም፡- በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ አንቀፅ 458(ሀ) መሰረት የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይኑ የተሰጠበት ሀገር በኢትዮጵያ የሚሰጥን ብይን የሚፈፀም የሆነ እንደሆነ ብይኑ የተሰጠው ተከራካሪዎቹ ወገኖች ለግልግል ወይም ለሽምግልና ዳኞች ጉባኤ ባቀረቡት ስምምነት መሰረት ወይም ብይን የተሰጠበት ሀገር ህግ በሚፈቅደው መሰረት የሆነ እንደሆነ ተከራካሪ ወገኖች የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኞችን ለመምረጥ የእኩልነት መብት ተሰጥቷቸው እንደሆነ ወይም በክርክር ላይ ማስረጃቸውን ለማቅረብ እና ክርክራቸውንም ቀርቦ ለመስማት የእኩልነት መብት አግኝተው እንደሆነ የግልግሉ ወይም የሽምግልናው ዳኝነት ጉባኤ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ተቋቁሞ ከሆነ ብይኑ የተሰጠበት ጉዳይ በኢትዮጵያም ህግ በግልግል ወይም በሽምግልና ዳኝነት ሊታይ የሚችል እንደሆነና የፍርዱም አፈፃፀም የህዝቡን ሞራል እና ፀጥታ የማይቃረን እንደሆነ የተሰጠው ብይን የኢትዮጵያ ህግ በሚያዘው እና በሚፈቅደው ሁኔታ ሊፈፀም የሚችል እንደሆነ ነው፡፡ በውጭ ሀገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን በፍትሐብሔር ህግ አንቀፅ 461 ስር የተጠቀሱትን ካላሟላ በስተቀር ሊፈፀም አይችልም፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በግልግል ዳኝነት እና ዕርቅ አሰራር ሥርአት አዋጅ ቁጥር 1237/2013 አንቀፅ 53 ጭምር የተመለከቱ ናቸው፡፡ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህጉ በውጭ ሀገር ለተሰጠ ፍርድ አፈፃፀም የተደነገጉ ድንጋጌዎች ሁሉ በውጭ ሀገር የተሰጠ የግልግል ወይም የሽምግልና ዳኝነት ብይን ላይም በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
إظهار الكل...
የንግድ ባንክ የግለሰቦችን ፎቶና ምስል የመለጠፍ ህጋዊነት:) ንግድ ባንክ በቅርቡ የደረሰበትን የሲስተም ችግር ተከትሎ በተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች የደምበኞቹን ስምና ፎቶግራፍ እያሰራጨ ይገኛል። ይህ ከባንኩ እሳቤ አንፃር ስንመለከተው ገንዘቤን ተሎ ያስገኙልኛል ብሎ ያሰባቸውን አማራጮች ሁሉ ጥቅም ላይ እያዋለ መሆኑን እንደ አንድ ጉዳት እንደ ደረሰበት ተቋም በየዋህነት እየፈፀመው ያለ ተግባር መሆኑን መገንዘብ እንችላለን። ሆኖም ግን የድርጊቱን ህጋዊነት ስንመለከት ግን በተለያዬ መልኩ ድርጊቱ ህገወጥ መሆኑን መገንዘብ እንችላለን። በመጀመሪያ ደረጃ በየትኛውም መንገድ ይሁን የገንዘብ ጉዳት የደረሰበት አካል ትክክለኛውን የህግ ስርዓት ተከትሎ ጉዳት ያደረሰበት አካል በፍትሃብሔርም ሆነ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንበትን ሁኔታ ከፍትህ አካላት ጋር በመተባበር ይፈጥራል እንጅ የግለሰቦች መረጃና ምስል እጁ ላይ ስላለ ብቻ እራሱን ፖሊስም ፍርድ ቤትም አድርጎ እዚህ እርቀት ድረስ እርምጃ መውሰዱ ከስነስርዓትም ሆነ ከህግ አኳያ ተገቢነት የሌለው አካሄድ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ባንኩ ገንዘቡን ለማስመለስ እየተከተለው ያለው ሂደት ከደምበኞቹ ጋር የገባውን የውል ስምምነት የሚጥስ ነው። ማንኛውም አገልግሎት ሰጭ አካል ከደምበኞቹ ጋር ያለውን ግንኙነት መሰረት አድርጎ የሚያገኛቸውን የግለሰብ መረጃዎች በማንኛውም መንገድ ያለግለሰቡ ፍቃድ መጠቀም ወይም በህግ እስካልተገደደ ድረስ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችልም። ይህ መርህ በየትኛውም የውል ግንኙነት ውስጥ የሚሰራ መርህ ነው። ይህ በሆነበት ሁኔታ ባንኩ የደንበኞቹን ግለሰባዊ መረጃዎች የመጠበቅ ሀላፊነቱን ወደ ኋላ በማለት ከፍርድ ቤት ወይም ከየትኛውም የህግ አካል ፈቃድ ባላገኘበት ሁኔታ የራሱን ፍላጎት ለማሳካት በማሰብ ብቻ በዚህ መልኩ ጥቅም ላይ ማዋሉ ተገቢነት የሌለው አካሄድ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከስነስርዓት አንፃርና ከውል ግዴታ አንፃር ያለው ውጤት እንኳን ብንተወው የግለሰቦችን ፎቶና መረጃ ያለፍቃዳቸውና ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በአደባባይ መለጠፍና ለህዝብ ማሰራጨት በህገመንግስቱ በግልጽ የተደነገገውን የግለሰቦችን የመረጃ ጥበቃ መብት የሚጥስ ከመሆኑም ባለፈ በወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎችን በህግ ፊት ነፃ ተደርጎ የመገመት መብትም የሚጥስ ተግባር ነው። በአጠቃላይ ንግድ ባንክ የሚወስዳቸው ተግባራት ከደረሰበት የገንዘብ ጉዳት አንፃር ለተቋሙ አሳማኝ ቢመስሉም ከስነስርዓትና ከህግ አንፃር ስንመዝናቸው ግን የግለሰቦችን መብት የሚጥሱ ህግን ያልተከተሉ መሆናቸውን በቀላሉ መገንዘብ እንችላለን።
إظهار الكل...
በንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ ሱቆች የኪራይ ተመን በገበያ ዋጋ ተሰልቶ የኪራይ ገቢ ግብር እንዲከፍሉ ተወሰነ የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን በጋራ ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የዲቪደንድ (የትርፍ ድርሻ) ታክስን ጨምሮ የተለያዩ የግብር ዓይነቶችን እንዲከፍሉ ወስኗል። በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎችን ገንብተው በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ አክሲዮን ማኅበራት የሕንፃውን ሱቆች በማከራየት ከሚያገኙት ገቢ ላይ ለሚገኙበት ከተማ ወይም የአካባቢ አስተዳደር የኪራይ ገቢ ግብር ብቻ ሲከፍሉ ቆይተዋል። ሚኒስቴሩ በአክሲዮን ማኅበራት ባለቤትነት ሥር የሚገኙና የሚተዳደሩ የንግድ ማዕከላት ላይ ጥናት ያካሄደ ሲሆን የጥናቱ ግኝትም ፣ አክሲዮን ማኅበራቱ በሕግ የተጣለባቸውን ግብር በተገቢው መንገድ እየተወጡ አለመሆናቸው ያረጋገጠ ነው ተብሏል። ገቢዎች ሚኒስቴር በጥናት የደረሰባቸውን ግኝቶች መሠረት በማድረግ ሊወሰዱ ይገባል ያላቸውን የማስተካከያ ዕርምጃዎች የተመለከተ ምክረ ሐሳብ ለመንግሥት አቅርቦ በቅርቡ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት ፥ በአክሲዮን ተደራጅተው የተገነቡና በንግድ ማዕከልነት የሚያገለግሉ ሕንፃዎች ባለቤት አክሲዮን ማኅበሩ በመሆኑ፣ የንግድ ማዕከሉን የሚመለከቱ የግብር ግዴታዎች ላይ ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት ተወስኗል። በመሆኑም በንግድ ማዕከልነት በሚያገለግለው ሕንፃ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በማከራየት የሚገኘው ገቢ ላይ በግብር አዋጁ መሠረት የሚጣለውን የኪራይ ገቢ ግብር እንደ ከዚህ ቀደሙ በከተማ አስተዳደሮች እንደሚሰበሰብ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል። ይሁን እንጂ ሚኒስቴሩ ባካሄደው ጥናት አክሲዮን ማኅበራቱ በሚያስተዳድሯቸው የንግድ ማዕከላት ውስጥ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ኪራይ ተመን ፦ - ከወቅታዊ ገበያው በእጅጉ አነስተኛ መሆኑ፣ - በርከት ያሉ ማኅበራትም በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን በርካሽ ዋጋ ለማኅበሩ አባላት እንዳከራዩ ፣ - ሌሎች በርከት ያሉ አክሲዮን ማኅበራት ደግሞ የባለቤትነት ማስተላለፍ ሥርዓቶችን ሳይከተሉ በንግድ ማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እንደ አክሲዮን ድርሻ ለማኅበሩ አባላት አከፋፍለው መገኘታቸው ተመላክቷል። በመሆኑም ፣ ከ2016 ዓ.ም. የግብር መክፈያ ወቅት ጀምሮ በንግድ ማዕከላቱ ውስጥ የሚገኙ ሱቆች የኪራይ ተመን በገበያ ዋጋ ተሰልቶ የኪራይ ገቢ ግብር እንዲከፍሉ መወሰኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
إظهار الكل...
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቀረቡ የዲሲፕሊን መዝገቦች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ***** የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል ዳኞች የስነ ምግባር ጉዳዮች ኮሚቴ መርምሮ ባቀረባቸው የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ የስነ ምግባር ደንብ ጥሰት አቤቱታ በቀረበባቸው 10 የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች ላይ መልስ እንዲሰጡ ውሳኔ አስተላለፏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ክስ የቀረበባቸው ሌሎች ሁለት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ዳኞች የቀረበባቸው አቤቱታ የማያስከስስ ነው በማለት ወስኗል፡፡ በሌላ መልኩ ጉባኤው ከዚህ በፊት በነበሩ አመታት የተከማቹ የዲሲፕሊን ክሶችን ውሳኔ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ሲሆን በሂደት ላይ ያሉ የክስ መዝገቦች በተፋጠነ ሁኔታ እልባት ማግኘት እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
إظهار الكل...
አዲሱ የቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ይዟቸው ከመጡ ጉዳዮች መካከል፦ - ማንኛውም የቤት ኪራይ ውል በፅሁፍ መደረግ ያለበት ሲሆን ውሉ በተደረገ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሰነድ ለመመዝገብና ማረጋገጥ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል። - የቤት ኪራይ ውል ቲንሹ የቆይታ ጊዜ ሁለት አመት ተደርጎ ይወሰዳል። - የቤት ኪራይ ውል በተከራዮች ስምምነት ፣ በተከራዩ ከሁለት ወር በፊት በሚሰጥ ማስጠንቀቂያና ቤቱ ከውርስ ውጭ ለሶስተኛ ወገን በሚተላለፍበት ወቅት ከስድስት ወር በፊት በሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ካልሆነ በቀር የኪራይ ውል ዘመኑ ሳይጠናቀቅ ማቋረጥ አይቻልም። - የቤት ኪራይ የመጀመሪያ ዋጋ በአከራይና በተከራይ ስምምነት በጋራ ይወሰናል። በሰነዶች ምዝገባ ላይ የተመዘገበው ዋጋም ትክክለኛው የቤቱ የኪራይ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል። የቤት ኪራይ ውሉ ከተመዘገበ በኋላ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ የየክልሉ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ተቆጣጣሪ በሚያወጣው የዋጋ ተመን የሚወሰን ይሆናል። - ይህ አዋጅ ብዙዎች ሲጠብቁት እንደነበረው የቤት ኪራይ ዋጋ ተመንን የሚወስን ሳይሆን በአከራይና ተከራይ መካከል በሚደረግ ስምምነት የኪራይ ዋጋ ከተወሰነ በኋላ የሚኖሩ ግንኙነቶችን የሚገዛ ነው። - በአዋጁ መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቅድመ ክፍያ ከሁለት ወር ክፍያ መብለጥ አይችልም። - የቤት ኪራይ ክፍያ በባንክ ወይም በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገድ ብቻ እንዲፈፀም አዋጁ ያስገድዳል። - በአዋጁ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የማስፈፀምና ተቆጣጣሪ አካል የማቋቋም ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል። - ከተከራዩ ፀባይና ተግባራት ጋር የሚገናኙ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ዝርዝር ሁኔታዎችም በአዋጁ ውስጥ ተካተዋል። - ከአንድ ተከራይ ጋር የተደረገ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሲቋረጥ ቤቱ ለሌላ ተከራይ ሲከራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ተመላክቷል። - አዋጁ ከዛሬ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
إظهار الكل...
👍 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.