ar
Feedback
Havan Academy

Havan Academy

الذهاب إلى القناة على Telegram

╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ The First and Leading Freshman Tutoring Platform in Ethiopia❕ Mark this phrase #Your GPA Matters❗️ Ask: @havanstudentsupport Testimony: https://t.me/havanacademyinfo/44 Register: @havanacademybot Website: www.havanacademy.com

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Havan Academy

تُعد قناة Havan Academy (@havanacademyofficial) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 32 732 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 776 في فئة التعليم والمرتبة 1 026 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 32 732 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 11 يوليو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -637، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -4، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 20.52‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 6.55‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 6 717 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 2 144 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 30.
  • الاهتمامات الموضوعية: يركز المحتوى على مواضيع رئيسية مثل jimma, chapter, coc, matter, ጥያቄዎችን.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ The First and Leading Freshman Tutoring Platform in Ethiopia❕ Mark this phrase #Your GPA Matters❗️ Ask: @havanstudentsupport Testimony: https://t.me/havanacademyinfo/44 Register: @havanacademybot Website: www.havanacademy.com

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 12 يوليو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة التعليم.

32 732
المشتركون
-424 ساعات
-1347 أيام
-63730 أيام
أرشيف المشاركات
እባካችሁ በሀሰተኛ መረጃዎች አትሸወዱ፤ ሁልጊዜም ትክክለኛና የታመኑ የመረጃ ምንጮችን ብቻ ተከታተሉ! የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (AAU) እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (UAT) ምዝገባ አልጀመረም። ነገር ግን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚሰራጩ መረጃዎች ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ምዝገባ ስለመኖሩ ደውለው በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ። እኛ እንደተለመደው ሁሉ ዘንድሮም ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናው (UAT) ትክክለኛውንና ወቅታዊውን መረጃ በፍጥነት ለማድረስ ዝግጁ ነን። ይህ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለ UAT መረጃ በመስጠት ቀዳሚና ዋነኛው መድረክ ነው። ትክክለኛውን መረጃ እዚህ ያገኛሉ፣ ይከታተሉን! please share this for all 2019 UAT exam taker🙏 https://t.me/UATtutorialofficial

🌟 ከካምፓስ ቅጥር ግቢ እስከ ሰፈሩ አደባባይ፡ የአቤል የክረምት አሻራ ክረምቱ ሲገባ አቤል (የ2ኛ ዓመት የIT ተማሪ) እንደማንኛውም ተማሪ ወደ ትውልድ ሰፈሩ ተመለሰ። አብዛኞቹ የሰፈሩ ጓደኞቹ ክረምቱን በካፌ፣ በቦርሳ ጨዋታ እና ፊልም በማየት እንደሚያሳልፉት ያውቃል። አቤል ግን በዚህ ክረምት ፍጹም የተለየ ነገር ማድረግ ፈለገ። "ለምን ተመራቂ (Senior) ስንሆን እንጠብቃለን? ለውጥ መጀመር ያለበት አሁኑኑ ነው" በማለት እራሱን ጠየቀ። አቤል በዩኒቨርሲቲ ቆይታው ያገኘውን የቴክኖሎጂ እውቀት እና የማርኬቲንግ ፍላጎት በአንድ ላይ አጣምሮ ለመጠቀም ወሰነ። 1. ሀሳቡ ሲወለድ አቤል ሰፈሩ ውስጥ ያሉ በርካታ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናውን ከጨረሱ በኋላ ሰዓታቸውን በከንቱ እያባከኑ እንደሆነ አስተዋለ። እቤት ተቀምጠው ስልካቸውን ከሚያዩ፣ ለምን ጠቃሚ የዲጂታል ክህሎት እና የኮምፒውተር እውቀት አያካፍላቸውም? ነገር ግን ይህንን ብቻውን ማድረግ እንደማይችል ስላወቀ፣ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች (በቢዝነስ እና በጤና ሳይንስ) የሚማሩ የሰፈሩን የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹን አስተባብሮ "የክረምት ብርሃን" የተሰኘ አነስተኛ የበጎ ፈቃድ ቡድን መሰረተ። 2. የሰፈሩን ወጣቶች ማንቃት ቡድኑ በአካባቢው ከሚገኝ የመንግስት ትምህርት ቤት ጋር በመነጋገር ቅዳሜና እሁድ አንድ ክፍል በነፃ ተፈቀደላቸው። አቤል እና ጓደኞቹ ለታደጊዎቹ ህጻናት እና ወጣቶች የሚከተሉትን ስልጠናዎች መስጠት ጀመሩ፦ አቤል መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት አሰሳ እና የ-AI መተግበሪያዎችን (እንደ ቻት ጂፒቲ) ለትምህርት እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ አሳያቸው። የቢዝነስ ጓደኞቹ፡ ስለ ቁጠባ፣ ስለ ስራ ፈጠራ (Entrepreneurship) እና እራስን እንዴት ማስተዋወቅ እንደሚቻል (Personal Branding) ቀላል ስልጠና ሰጡ። የጤና ሳይንስ ጓደኞቹ ስለ መጀመሪያ እርዳታ አሰጣጥ እና ስለ ጤና አጠባበቅ ግንዛቤ ፈጠሩ። 3. ከበጎ ፈቃድ ወደ "Side Hustle" የአቤል የክረምት ስራ በበጎ ፈቃደኝነት ብቻ አላበቃም። በአካባቢው ያሉ አነስተኛ ነጋዴዎችና ሱቆች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እንደሚቸገሩ ተረዳ። አቤል ከተማረው የIT እውቀት ተነስቶ ለአንድ ትልቅ የሀገር በቀል ልብስ ስፌት ቤት እና ለአንድ ካፌ የቴሌግራም ቻናል እና የቲክቶክ ገጽ ከፍቶ ዲጂታል ማርኬቲንግ መስራት ጀመረ። ይህ ስራው በክረምቱ መጨረሻ ላይ አነስተኛ ነገር ግን ቋሚ ገቢ ማስገኘት ጀመረለት። ከሁሉም በላይ ደግሞ በትምህርት ቤት በንድፈ-ሀሳብ የተማረውን ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ በተግባር ፈተሸበት። 4. ወደ ካምፓስ በታላቅ በራስ መተማመን መመለስ ክረምቱ አልቆ መስከረም ሲጠባ አቤል ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመለሰው ልክ እንደ ቀድሞው ተራ ተማሪ ሆኖ አልነበረም። ከ30 በላይ ለሚሆኑ የሰፈሩ ታዳጊዎች አዲስ ተስፋ እና እውቀት አጋርቷል። የራሱን የገቢ ምንጭ መፍጠር የሚችልበትን የመጀመሪያ በተግባር የተደገፈ የልምድ ማህደር (Portfolio) ገንብቷል። ከክፍል ውጭ ያለውን ማህበረሰብ የማስተባበር ትልቅ የአመራር (Leadership) ብቃት አሳይቷል።
የክረምት ዕረፍት ትልቅ ድርጅት ውስጥ ገብቶ ወንበር መያዝን አይጠይቅም። ካለን አነስተኛ እውቀት ተነስተን፣ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎችን በማስተባበር ትልቅ ለውጥ ማምጣትና ለቀጣዩ አመት እራሳችንን ብቁ ማድረግ እንደምንችል ማሳያ ነው። በ2017 e.c የተድረገ እውነተኛ ታርክ
———————————- @havanacademyofficial ———————————

Today we officially commence our Summer Marketing & Sales Training! This program is completely FREE and designed to equip university students with practical marketing and sales skills that help them earn income, create value, and build real world experience while on campus. The second round will begin soon, and our goal is to train 500+ university students at no cost. share and Join ———————————- @havanacademyofficial ———————————-

ተማሪዎች በክረምት እረፍት ወቅት የሚሰሯቸው 5 ዋና ዋና ስህተቶች፦ 1. ሙሉ በሙሉ ከንባብ እና ከአካዳሚክ ህይወት መራቅ ትምህርት ሲዘጋ ደብተርን ጨርሶ ጥሎ መዘናጋት ትልቅ ስህተት ነው። አእምሮ ለረጅም ጊዜ ምንም አዲስ ነገር ካላነበበ፣ የነበረውን የማስታወስ እና የማስተዋል ብቃት ይቀንሳል። በሚቀጥለው ዓመት ትምህርት ሲጀመር ወደ ነበረበት የአጠናን ሪትም ለመመለስ በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል። 2. ጊዜን ያለ እቅድ ማባከን "ክረምት እኮ ረጅም ነው፣ በኋላ እሰራዋለሁ" በማለት ሰዓትን ያለ አግባብ ማሳለፍ። አብዛኛው ተማሪ ቀኑን ሙሉ በየማህበራዊ ሚዲያው (TikTok, Telegram...) ላይ በማሸብለል ወይም ተከታታይ ፊልሞችን (Series) በማየት ብቻ ያሳልፋል። ክረምቱ ሳይታወቅ አልቆ፣ ትምህርት ሲከፈት የሚቆጭ ትልቅ ስህተት ነው። 3. ለቀጣዩ ክፍል ቅድመ-ዝግጅት አለማድረግ በተለይ ወደ ከፍተኛ ክፍል ወይም ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች (ለምሳሌየ 12ና፣ የፍሬሽማን ወይም UAT ተፈታኞች፣ ቀጣይ የሚጠብቋቸውን ከበድ ያሉ ኮርሶች አስቀድመው ፍንጭ ሳያገኙባቸው ሲቀሩ ይቸገራሉ። ክረምቱን ትንሽ ቀደም ብሎ ለማየት አለመጠቀም በትምህርት መጀመሪያ አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ይፈጥራል። 4. ተግባራዊ ክህሎቶችን አለመልመድ ክረምት እውቀትን ወደ ተግባር ለመቀየር ወይም አዳዲስ ክህሎቶችን (Soft Skills) ለማዳበር ምርጥ ጊዜ ነው። ተማሪዎች በዚህ ወቅት የኮምፒውተር እውቀታቸውን፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ የንግግር ብቃታቸውን (Communication Skills)፣ ወይም እንደ ዲጂታል ማርኬቲንግ ያሉ ተፈላጊ ነገሮችን መማር ሲችሉ ሳይጠቀሙበት ይቀራሉ። 5. የስራ ልምምድ (Internship) እና የበጎ አድራጎት ዕድሎችን አለመፈለግ በክረምት ወራት ከቤት ወጥቶ በየተቋማቱ የልምምድ ስራ (Internship) አለመስራት ወይም በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ አለመሳተፍ። እነዚህ ነገሮች ለሲቪ (CV) ግንባታ፣ አዳዲስ ሰዎችን ለማወቅ (Networking) እና የስራ አለምን ቀድሞ ለመረዳት ወሳኝ ቢሆኑም፣ ብዙዎች ግን በሰነፍ እረፍት መተካትን ይመርጣሉ። Havan Academy @havanacademyofficial

ክረምቱን በዓላማ እና ፍሬያማ በሆነ ነገር ለማሳለፍ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ያለፉት ዓመታት የፍሬሽማን (Freshman) ኮርስ ፈተናዎችን እና ጥያቄዎችን ሰብስቦ፣ በየምዕራፉ በጥራት ማደራጀት የሚችል ጎበዝ ተማሪ እንፈልጋለን። ይህ ስራ Paid Internship ሲሆን፣ ስራውን በብቃት ለሚያጠናቅቁ ደግሞ በቀጥታ የቋሚ የሙሉ ሰዓት የስራ ዕድል Full-Time Job እናመቻቻለን! Contact : @hobban

ክረምት ማለት ከክፍል ትምህርት ዕረፍት ነው፤ ከሕልም ግን አይደለም። አሁን ብዙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤት ናቸው። ቀናቸውን በሶሻል ሚዲያ፣ በፊልም፣ በጨዋታ ወይም በተለያዩ ነገሮች እያሳለፉ ነው። ከሁለት ወራት በኋላ ግን ብዙዎች አንድ ጥያቄ ይጠይቃሉ፦ "ይህን ሁሉ ጊዜ በምን አሳለፍኩት?" ዛሬ ያለው ትልቁ ሀብት ጊዜ ነው። ገንዘብ ሊገኝ ይችላል፣ እድል እንደገና ሊመጣ ይችላል፤ ነገር ግን የዛሬ ቀን አንዴ ካለፈ በፍጹም አይመለስም። ስለዚህ ይህን ክረምት የሚለይ ያድርገው። - አዲስ ክህሎት ተማር። - መጽሐፍ አንብብ። - ለሙያህ የሚጠቅሙ ኮርሶችን ውሰድ። - ራስህን አሻሽል። - ወደ ካምፓስ ስትመለስ ከገባህበት የተሻለ ሰው ሁን። ከሌሎች ተማሪዎች የሚለይህ ብልህነትህ ብቻ አይደለም፤ ዛሬ ጊዜህን እንዴት እንደተጠቀምክበት ነው። አንድ ቀን የምታገኘው ውጤት፣ ዛሬ የወሰንከው ውሳኔ ውጤት ይሆናል። ይህን ክረምት በኩራት የምታስታውሰው አድርገው፤ Havan Academy @havanacademyofficial

ከ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ እዝራ አንዱዓለም ከወሰዳቸው አጠቃላይ ኮርሶች 43 A+ እና 9 A በማምጣትና CGPA 4.00 ነጥብ በማስመዝገብ የዋ
ከ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ እዝራ አንዱዓለም ከወሰዳቸው አጠቃላይ ኮርሶች 43 A+ እና 9 A በማምጣትና CGPA 4.00 ነጥብ በማስመዝገብ የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል። @havanacademyofficial

ከ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሜሮን ገብረሂወት ከአካውንቲግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል CGPA 3.98 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት የዋንጫ እና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች። ከወሰደቻቸው አጠቃላይ ኮርሶች
ከ ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሜሮን ገብረሂወት ከአካውንቲግ እና ፋይናንስ ትምህርት ክፍል CGPA 3.98 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት የዋንጫ እና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆናለች። ከወሰደቻቸው አጠቃላይ ኮርሶች 43 A+ እና 10 A አስመዝግባለች። @havanacademyofficial

የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት 🎓 ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሚገኙ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ለምታከብሩና በመላው ኢትዮጵያ ለምትገኙ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ፦ እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬ በዕድሎች፣ በዕድገትና በተለየ ዓላማ የተሞላው አዲሱ የሕይወታችሁ ምዕራፍ መጀመሪያ ነው። ለዚህ ታላቅ ስኬት እንድትበቁ ያደረጋችሁት : የከፈላችሁት መስዋዕትነት፣ የነበራችሁ ጽናት እና ትጋት በመሆኑ፤ እኛም በዚህ ታላቅ ውጤታችሁ ታላቅ ኩራት ይሰማናል። ወደ ቀጣዩ የሕይወት ጎዳናችሁ ስትሸጋገሩ፤ መማርን፣ መምራትን እና በበጎ ተጽዕኖ ማሳደርን እንድትቀጥሉበት እንመኛለን። የ2018 ዓ.ም (የ2026 እ.ኤ.አ) ተመራቂዎች፦ እንኳን ደስ አላችሁ! ሃቫን አካዳሚ (Havan Academy) Share with your friends @havanacademyofficial

ከማትሪክ ፈተና 1ሳምንት በፊት! 12ተኛ ክፍል እያለሁ፣ ከማትሪክ አንድ ሳምንት በፊት የነበረውን ስሜት ዛሬም ድረስ አልረሳውም። የሶሻል ተማሪዎች ሊፈተኑ ሲገቡ በተለያዩ የጭንቀት ስሜቶች ተወረርኩ። ክፍሌን ዘግቼ ከማጥናት ይልቅ መተኛት ሆነ ስራዬ (አቤት የዛን ሰሞን ያለው እንቅልፍ! 😴) ​የኛ ፈተና Online ስለነበር፣ የኛ ባች ተማሪዎች ፈትነው ወደ ቤት ይመለሱ ነበር። ለግማሹ ያህል 'ፈተናው እንዴት ነበር?' ብዬ Text ፅፌ በጭንቀት መልስ እየጠበኩ... ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ላይ 'ቀላል ነበር በጣም!' የሚል Text ገባልኝ። በትንሹም ቢሆን ተረጋጋሁ። ግን አሁንም አርፌ ማንበብ ስላልቻልኩ፣ ማትሪክ እንደጨረሰ ሰው ለ1 ሳምንት ተኛሁ! ​የእንግሊዘኛ ፈተናን መጀመሪያ ሳየው 'ውይ... ወዳቂ ነኝ!' ብዬ አስቤ ነበር። ግን በየጊዜው ፈተናዎቹ እየተሻሻሉ የተሻለ ሆኑልኝ፣ ፈጣሪ ይመስገን!" ​ ለዘንድሮ የማትሪክ ተፈታኞች በሙሉ ​📌 ፍርሃትና ጭንቀት ተፈጥሯዊ ናቸው:: ስለ ፍርሃታችሁ ብዙም ሳታስቡ፣ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ጥያቄዎችን በመስራት ራሳችሁን አዘጋጁ። 📌 ከ'ወከባ' ራቁ! ወከባና አላስፈላጊ ውጥረት ከሚፈጥር ጓደኛ ራሳችሁን አርቁ። በተቻላችሁ መጠን እናንተም ለሌላው ሰው ጭንቀት መንስኤ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። 📌 ጤናችሁን ጠብቁ! አእምሯችሁ በትክክል እንዲሰራ በቂ እንቅልፍ ማግኘት ግድ ነው። 📌 በየእምነታችሁ ጸሎት አድርጉ። ​ፈጣሪ ይርዳችሁ! 🙏 ለ12ተኛ ክፍሎች share አርጉልኝ @havanacademyofficial

A graduating student from Wollega University who achieved 35 A+ grades Duresa Danboba is a top performing graduate from the D
A graduating student from Wollega University who achieved 35 A+ grades Duresa Danboba is a top performing graduate from the Department of Pharmacy at Wollega University for the 2018 E.C academic year. He graduated with the highest distinction, achieving a CGPA of 3.98 and receiving a trophy award. During his university studies, he earned 35 A+ grades and 3 A grades, making him a medal recipient as well. Duresa says that using his time effectively was the key secret to his success. He also plans to use the knowledge he gained, supported by technology, to engage in innovation and research aimed at addressing the medication shortage problem in the country. @havanacaddemyofficial

🔥 ​ልጅ ሳለሁ አባቴ ሁልጊዜ የሚመክረኝ አንድ ትልቅ እውነት ነበር፤ "ክረምትን በደንብ የተጠቀመ ሰው፣ የሚቀጥለውን ዓመት በስኬትና ያለ ጭንቀት ያጠናቅቃል" ይለኝ ነበር። በዚህም ምክንያት በክረምት ዕረፍቴ የተለያዩ መጻሕፍትን እንድበረብርና ስለ ዓለም እንዳውቅ ሳያሰልስ ይገፋፋኝ ነበር።​ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው የአባቴ ምክር እጅግ እውነት ነበር። ብዙዎቻችን የክረምት እረፍትን ሙሉ በሙሉ ለመዝናናት ብቻ ልናውለው እንችላለን። ነገር ግን እውነተኛው የስኬት ምስጢር ያለው እረፍትን ከዕውቀት ጋር አጣምሮ መጓዝ ላይ ነው። ​ክረምት መጻሕፍትን የምናነብበት፣ ስለ ዓለም የምናውቅበት እና አዳዲስ ክህሎቶችን (Skills) የምናዳብርበት ልዩ የዕድገት ወቅት ነው። ​ዛሬ በክረምቱ ቅዝቃዜ ሰነፍ ሳንሆን ራሳችንን ካነፅን፣ ነገ መስከረም ሲጠባ አዲሱ የትምህርትም ሆነ የሥራ ዘመን ቀለል ያለና በስኬት የተሞላ ይሆንልናል። ​ ​የአባቶቻችንን ምክር በተግባር አውለን፣ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም በቀጣዩ ዓመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ዛሬውኑ እንነሳ! @havanacademyofficial

የ ክረምቱን Online ስልጠና ከሚሰጡአቹ አሰልጣኞቻችን አንዷን እናስተዋውቃችሁ ስም- ሊዲያ ዜናዊ ሀገር- Hong Kong 🇨🇳 ዩኒቨርሲቲ- The University of Hong Kong (HKU) በ Hong kong በጣም ውድድር በበዛበት University Fully funded scholarship በማሸነፍ እየተማረች ትገኛለች። በዚህ ልዩ ፕሮግራም ላይ ሊዲያ ለስኬት ያበቃትን ሚስጥር በዝርዝር ታካፍላችኋለች። ከ ሊዲያ ምን ትማራላችሁ ? 1. በ ዩኒቨርሲቲዎች ይሚወደዱ እና እናንተን ከሌሎች applicant's ለየት የሚያረጋችሁን profile እንዴት እንደምታዘጋጁ። 2. አሪፍ እና scholarship የሚያስገኙ applications እና essays እንዴት ማዘጋጀት እንደምትችሉ። 3. በ Hong Kong እና በሌሎች የ China ሀገራት ውስጥ ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ (Fully Funded) ስኮላርሺፖችን ለማግኘት የሚጠቅሙ መረጃዎችን አንድ በአንድ (Step by Step )በዝርዝር ታካፍላችኋለች። ቦታዎች በፍጥነት እየተያዙ ነው! ለዚህ አጠቃላይ የሥልጠና ፕሮግራም የተዘጋጀው ቦታ ለ65 ተማሪዎች ብቻ የተገደበ ስለሆነ፣ ቦታው ሳያልቅ አሁኑኑ ተመዝገቡ! ለመመዝገብ👉[https://forms.gle/9XJq8un2j4qwNJek9] ንጉስ ኮንሳልታንትስ የነገ ህልምዎን፣ ዛሬ ከንጉስ ጋር! ____ For more @negushelpcenter

Online Job Opportunity Interested in sales and looking to earn money? Start with a commission based opportunity and begin earning from your performance. Outstanding performers may later be offered a salary based position based on their results and commitment. If you're ready to start by Sunday, June 28, contact @hobban on Telegram.

አብዛኛው የዩንቨርስቲ ተማሪ experience ያደረገው loop ቢኖር 😁 I'll do this in the summer. I'll learn that skill. I'll prepare for something.
አብዛኛው የዩንቨርስቲ ተማሪ experience ያደረገው loop ቢኖር 😁 I'll do this in the summer. I'll learn that skill. I'll prepare for something... Then summer happens, but the mindset, friends, and habits are all the same. Soon, summer is no longer the right time to do it all, and the same promise gets pushed to campus. But we're cooking up support for you that works both on and off campus. Stay tuned, visit havanacademy.com ! ----------------------------------------- 👉 @havanacademyofficial -----------------------------------------

የዕውቀት እውነተኛ ኃይል🌟 በአሁኑ ጊዜ "ዋናው ነገር ገንዘብ ነው፤ ዕውቀት ቦታ የለውም" የሚሉ አመለካከቶች ይደመጣሉ። እርግጥ ነው፣ ማንኛውም ንግድና የዕለት ተዕለት የገንዘብ እንቅስቃሴ የራሱ የሆነ ትልቅ ጠቀሜታና ዋጋ አለው። ነገር ግን ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ያለው፣ ሥር ነቀል ለውጥ (disruptive) የሚያመጣና ታሪክ የሚቀይር ትልቅ የንግድ ተቋም ለመገንባት መሠረታዊ ዕውቀት (fundamental knowledge) ወሳኝ ነው። ዓለምን የቀየሩና ታላቅ ግሎባል ተፅዕኖ የፈጠሩ ግዙፍ ፈጠራዎች በሙሉ የዕውቀት ውጤቶች ናቸው። የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለሀብት (ትሪሊየነር) ኢሎን ማስክ ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው። በSpaceX፣ በሮኬት እና በሳተላይት ንግድ ላይ የሚሠራው ሥራ ያለምንም ጥርጥር የፊዚክስ ፣ በኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ እና በሌሎች ሳይንሳዊ ዘርፎች ያላቸው ጥልቅ ዕውቀት የተደገፈ ነው። ዛሬ ዓለምን እየቀየሩ ያሉ እንደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV)፣ የኢነርጂ ንግድ፣ አውሮፕላኖችና የኢንተርኔት አብዮት በሙሉ በገንዘብ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በመሠረታዊ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ዕውቀት የተገነቡ ናቸው። የዕውቀት ልዩነት በንግድ ውስጥ
ዕውቀት መር ንግድ፦ አዳዲስ አሠራሮችን፣ ምርቶችንና ሙሉ በሙሉ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በመፍጠር ረጅም ዕድሜ ያለው ትውልድ ተሻጋሪ ሀብት ይገነባል።
ገንዘብ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን ዘላቂ ዋጋና ተፅዕኖ የሚፈጥረው ዕውቀት ነው። —————————————— 👉 @havanacademyofficial ——————————————

This post 😃 What would you say? Join @AdmasInsights
+1
This post 😃 What would you say? Join @AdmasInsights

ያለ ጫና አንደኛ መሆን! የፊንላንድ አስገራሚ የትምህርት ምስጢር 🇫🇮🎒 ያለ ምንም የቤት ስራ (Homework)፣ ያለ አስጨናቂ ፈተና እና ያለ ብሄራዊ ፈተና (National Exams) ተማሪዎችን በአለም አንደኛ የሚያደርግ የትምህርት ስርዓት ቢኖር ይገርማችኋል? አዎ፣ ይህ በጭንቅላት እረፍት ላይ የተመሰረተ ስርዓት በሰሜን አውሮፓዊቷ ሀገር ፊንላንድ በተግባር እየሰራበት ይገኛል። ብዙ ሀገራት ተማሪዎችን በፈተና እና በቤት ስራዎች ሲያስጨንቁ፣ ፊንላንድ ግን ፍጹም የተለየና ሰላማዊ መንገድን ትከተላለች። የፊንላንድ የትምህርት ስርዓት 3 ዋና ዋና አስገራሚ ምስጢሮች፦
ብሄራዊ ፈተና የለም፦ በፊንላንድ ተማሪዎች እስከ 18 ዓመታቸው ድረስ ምንም አይነት አስገዳጅ ሀገር አቀፍ ወይም ክልላዊ ፈተና አይወስዱም። ተማሪዎች የሚመዘኑት በክፍል ውስጥ በሚያሳዩት ተሳትፎ እና በክህሎታቸው ላይ ተመስርቶ መምህራኖቻቸው በሚያደርጉት ቀጣይነት ያለው ግምገማ (Continuous Assessment) ብቻ ነው። 🛏 የቤት ስራ እና አሳይመንት ፈጽሞ ቀሏል፦ ትምህርት ቤት ከተጠናቀቀ በኋላ ተማሪዎች ደብተራቸውን ይዘው አይጨነቁም። የቤት ስራ ከተሰጠም ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ያልበለጠ እና ተማሪው ብቻውን በቀላሉ ሊሰራው የሚችለው ቀለል ያለ ንባብ ብቻ ነው። ምክንያቱም "ትምህርት በክፍል ውስጥ ያበቃል፤ ከቤት በኋላ ያለው ጊዜ ለመጫወት፣ ለቤተሰብ እና ለእረፍት ነው" ብለው ያምናሉ። 🏃‍♂️ ለየ45 ደቂቃው የ15 ደቂቃ እረፍት፦ ተማሪዎች በአንድ ክፍለ ጊዜ ለ45 ደቂቃ ከተማሩ በኋላ፣ ለ15 ደቂቃ አስገዳጅ የውጭ ጨዋታ እና እረፍት ያደርጋሉ። በረዶም ይሁን ዝናብ፣ ህጻናቱ ወደ ውጭ ወጥተው እንዲጫወቱ ይደረጋል፤ ይህም ጭንቅላታቸው ሁልጊዜ ንቁ እንዲሆን ይረዳዋል።
ባጭሩ፦ ፊንላንዶች "Less is More" (ማሳነስ ማብዛት ነው) በሚለው ፍልስፍና ያምናሉ። ተማሪዎቻቸውን ባለማስጨነቃቸው በአለም አቀፍ የትምህርት ደረጃዎች (እንደ PISA) በየአመቱ ከፍተኛውን ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛሉ። —————————————— 👉 @havanacademyofficial ——————————————

ለትልቅ ስኬት በትናንሽ እርምጃዎች መጀመር ግድ ነው። ዛሬ የገነባችሁት ማንነት የነገውን ማንነታችሁን ይወስነዋል። ሁልጊዜም ከትላንት የተሻለ ለመሆን መጣርን አታቁሙ። የምትፈልጉት ቦታ ላይ እስክትደርሱ ድረስ ጉዟችሁን በልበ ሙሉነት ቀጥሉበት! 💪✨ የሁልጊዜም ምርጫችሁ፣ ሀቫን አካዳሚ! #HavanAcademy #StayFocused #SuccessMindset —————————————— 👉 @havanacademyofficial ——————————————

ሐቫን ሚዲያ (Havanh Media) የሥራ ዕድል! ተማሪዎችን ያተኮሩ የቲክቶክ እና ዩቱብ ቪድዮችን ማዘጋጀትና በካሜራ ፊት ማቅረብ የሚችሉ ንቁ ወጣቶችን እንፈልጋለን። የሥራ መደብ፦ የቪዲዮ ይዘት አዘጋጅ (Educational Content Creator) ዋና ተግባር፦ ተማሪዎችን ማዕከል ያደረጉ አጫጭር፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የቪዲዮ ይዘቶችን ማመንጨትና በካሜራ ፊት ማቅረብ። ተፈላጊ ክህሎት፦ በካሜራ ፊት የመቆም ሙሉ በራስ መተማመን፣ ግልጽ የንግግር ችሎታ እና ለተማሪዎች የሚሆን ይዘት የመቅረጽ የፈጠራ ብቃት። ለመመዝገብ ይህንን የጉግል ፎርም (Google Form) አሁኑኑ ይሙሉ፦ 🔗 https://forms.gle/T4DhF6ivzUfeajLp7 —————————————— 👉 @havanacademyofficial ——————————————