cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Werabe university muslim students jemeà center

ይህ ቻናል ትክክለኛው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሲሆን፣ በቻናሉም፦ ➲ ሙስሊም ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ➲ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መስጂድ ስለሚደረጉ የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች የሚለቀቁ ይሆናል። ኢንሻ አሏህ 👇 https://t.me/WRU_MSJ_Official_channel ማንኛውም comment ካላቹ በዚ link ያስቀምጡልንን!! @WRU_MSTUDENT

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
617
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+37 أيام
+1130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ዓሹራን የመጾም ትሩፋት 🔅ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለ እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! ) ብለዋል ነቢዩም፥ ( የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ ) ብለዋል። 🔅አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም! 🔅የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የሚያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን፤አዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር፤ አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞች የሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6 ☄የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው?... የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል ምክንያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል፤ ( አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን ) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል። 🔅ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክንያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል፤ ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ሲያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል! 🔅ይህ በእንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል፤በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል።እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል። 🔅ጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ቀንን ለብቻው (ከፊት ወይም ከኋላ አንድ ቀን ሳይጾሙ) ነጥሎ መጾም እንደማይቻል በሐዲሶች የተገለጸ ሲሆን አጋጣሚ ዓሹራ ጾም በጁሙዓ ወይም ቅዳሜ ዕለት ቢሆን መጾም አይከለከልም። 🔅ዓሹራ ጾም ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደ ቀዷ ወይም የነዝር (ስለት) እና መሰል ምክንያት ያላቸው ጾሞችንም መጾም አይከለከልም። ☄ዓሹራን መጾም የቱን ወንጀል ነው የሚያስምረው? ዓሹራን መጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንደሚያሠርዝ ጠቅሰናል ይህ ምህረት ጥቃቅን ወንጀሎችን ነው የሚመለከተው ወይስ ከባባዶችንም ጭምር? ይህን አስመልክተው ኢማም አንነወዊይ የሚከተለውን ብለዋል፤ " የዓረፋ ጾምም ይሁን የዓሹራ ሌሎችም ወንጀልን ያስምራሉ የተባሉ ኢባዳዎች ጥቃቅን የሚባሉ ወንጀሎችን በሙሉ ያሰርዛሉ ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት እንደሆነ በምትኩ መልካም ስራዎች ይመዘገቡለታል አላህ ዘንድም ያለው ደረጃ ይጨምራል ጥቃቅን ወንጀሎች የሌሉበት ሆኖ አንድ ወይም ከዛ በላይ ከባድ ወንጀል ያለበት እንደሆነ ወንጀሉን ያቀለዋል ብለን አሏህ ላይ ተስፋ እናደርጋለን" ☄ቀዷ ያለበት ሰው ዓሹራ መጾም ይችላልን? እንደ ዓሹራ ያሉ ሱና ጾሞችን ያለምንም ጥርጣሬ ለመጾም ያለብንን ቀዷ ፈጠን ብለን ማውጣቱ ይመረጣል።ቀዳውን ሳይጾም ወቅቱ የሚያልፍ የሱና ጾም የደረሰበት ሰው በቀጣይ ለቀዳ ሰፊ ጊዜ እስካለው ድረስ ፈርዱን ቀዳ ሳያወጣ ሱና ቢጾም ችግር አይኖረውም። 🔅ከዓሹራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ቢድዓዎች  ታላቁ የዲን መሪ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠየቁ "በዓሹራ ቀን ሰዎች ገላቸውን ሲታጠቡ፤ ሲኳኳሉ፤ሂና ሲቀቡ፤ልዩ ሰላምታ ሲለዋወጡና ሲጨባበጡ፤ልዩ ምግብም ሲሰሩ እና ልዩ ደስታ ሲደሰቱ ይታያል ይህ ነገር በሸሪዓችን መሰረት አለውን?" እሳቸውም ሲመልሱ {{ ይህን አስመልክቶ ከነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተገኘ አንድም ሷሒሕ ሐዲስ የለም ሷሓቦቻቸውም ይህን አስመልክተው ያሉት ነገር የለም ቀደምት የዲን መሪዎችም አራቱም መሪዎች (ኢማም፥አቡ ሐኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዒ እና አሕመድ) ይሁን ሌሎችም ከነሱም ውጪ ያሉት ታዋቂ የሸሪዓ እውቀት ምንጭ የሚባሉ መጻህፍት ባለቤቶችም በዚህ ጉዳይ ከነቢዩም ይሁን ከሷሓቦች ወይም ከተከታዮቻቸው ምንም የዘገቡት ነገር የለም) ብለው መልሰዋል። 💥ከቢድዓ በመጠንቀቅ በዲኑ የተፈቀዱ ነገሮችን ብቻ በመስራት ወደ አላህ እንቃረብ! 💥የዘንድሮ (የ1445ዓ.ሂ) ዓሹራ የሚሆነው የፊታችን ጁሙዓህ (ከነገ ወዲያ) ሙሐረም 10 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 21 /2015) ሲሆን ከፊቱ ሐሙስን ወይም ከኋላው ቅዳሜን መጾም ተገቢ ነው። ከ11ኛው ቀን ይልቅ ከፊት ያለውን 9ኛውን ቀን መጾሙ ተመራጭ ነው። በተለይ ዘንድሮ 9ኛው ቀን ዕለቱም ሐሙስ ስለሆነ ሐሙስ ቀን የመጾምን ትሩፋትም ያስገኛል። ሁለት ቀን መጾም የሚከብደው ሰው 10ኛውን ቀን ብቻ መጾምም ይችላል። አላህ ይወፍቀን! ✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም @ዛዱል መዓድ 🔸 🔹 🔸🔹 🔸🔹🔸 🌐https://telegram.me/ahmedadem
إظهار الكل...
"زاد المعاد" ዛዱልመዓድ- የነገው ስንቅ

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም የሚዘጋጁ ተከታታይ ቋሚ ትምህርቶች፣ ፈትዋዎች፣ ሙሓደራዎችና አጫጭር ምክሮች የሚቀርቡበት ቻናል القناة التعليمية الرسمية لأبي عبد الله أحمد بن آدم الشراري دروس في القرآن والعقيدة والفقه وفتاوى ومقالات متنوعة باللغة الأمهرية http://www.youtube.com/c/ZadulMaad

👍 1
ሰኔ 27 /2016 እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን! ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት እያስመረቀ ነው! ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም መላው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን!
إظهار الكل...
👍 1
👍 5
بسم الله الرحمان الرحيم እንኳን አሏህ በሰላም አደረሳቹህ!!!! የተከበራቹህ እና የተወደዳቹህ የሱና ወንድምና እህቶች: እንኳን ለዚህ ለአመታት ስትለፉለት,ስትናፍቁት,ዱኣ ስታረጉለት, በሱ ምክንያት ብዙ መሷትነትን(የአካል,የሀሳብ,የግዜ) የከፈላቹለትና ብዙ ውጣውረዶችንየ ተጋፈጣቹበት የምረቃ(congratulation)(يوم التخرج)ቀናቹህ በሁሉ ነገር ቻይ የሆነውና ህልማቹህን እውን ለማድረግ የፈቀደው አሏህ በሰላምና በአፍያ አ.......ደ .......ረ..... ...ሳ........ቹ....ህ!! ደስታቹህ ደስታዬ እንደሆነ በፈጠረኝ በአሏህ ስም አስረግጬ እነግራቹዋለሁ!!! هنيئا لكم Congratulations! ሀበይ ተስ ባለሙ Congratulation Baga gammachiisa ቦሄ ደስ ባረናሁም اخوكم رضوان
إظهار الكل...
👍 15
بسم الله الرحمن الرحيم أما بعد التخرج هو شعور رائع لا يشعر بقيمته إلا من تعب وثابر في تحقيق هدفه وحلمه،أهنئكم من قلب مشتاق لفرحكم، أهنئكم و أسعد أوقات الهناء بقربكم، أهنئ كلّ قلب يحمل الحب لكم، وأشهد أنّكم على قدر الثقة كل شخص ينال ما يريد من نجاح وتفوق وأنتم وصلتم إلى أعلى المراكز بالاجتهاد والمذاكرة، فهنيئا لكم الحصول على درجة الماجستير. لا يمكن معرفة قدر النجاح الذي حققه الشخص سوى بمعرفة قدر الصعاب التي استطاع التغلب عليها، لذا نود أن نهنئكم بما وصلتم له من درجات النجاح والحصول على الماجستير الدرجة العالية من التقدير العلمي، ونتمنى لكم دوما النجاح والإشراق. بقلوب فخورة نتمنّى التّهاني الصّادقة على التّخرّج، فكلُّ الأحلام لا يُمكن تحقيقها إلّا بالشّجاعة لمتابعتها، لذلك يجب دائمًا التّعلّم والنّموّ وتحقيق الأفضل مبارك لكم النجاح والتميز والتقدم، ومن نجاح إلى نجاح بإذن الله تعالى. مبارك لكم التخرج كنتم اكثر من أصدقاء🥹 كنتم اخوه تشاركنا معظم اللحظات في الجامعة لعبنا وضحكنا واستمتعنا معكم سنوات مرت وها أنتم الان خريجي🥺 نفتخر بكم💪 جميعا كل التوفيق لكم.🥰 أسأل الله لكم التوفيق والسداد وان يعينكم على خدمة دينكم ووطنكم.🤲 من أختكم بنت أبرار
إظهار الكل...
👌 5👍 1
ግልፅ የደስታ ደብዳቤ 💌 ከወራቤ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ውድ ተመራቂ እህቶች ና ወንድሞች.... 👉 በእምነትና በሂጃባችሁ ፀንታችሁ 👉 ክብራችሁን ማንነታችሁን ጠብቃችሁ 👉 በሙስሊም ጠል አስተማሪ እና ተማሪዎች ተንኮል ሳትሸነፉ 👉 ህልማችሁንና የኡማውን አደራ ጠብቃችሁ 👉 የመንግስትን anti- ሙስሊም  ህጎች ተቋቁማችሁ 👉 ጦርነቱን : ችግሩን : ናፍቆቱን: ከቤተሰብ መራቁን በትዕግስት ችላችሁ 👉 Exit Exam ን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን በብቃት አልፋችሁ ----ለምርቃት ለደረሳችሁልን ውድ ሙስሊም እህቶቻችን ና ወንድሞቻችን ሁሉ ከአመታት ልፋት በኋላ በጉጉት ለምትጠብቁት የምርቃት ጊዜ እንኳን አላህ በሰላም አደረሳችሁ። ኢንሻአላህ ቀሪ ዘመናችሁም በመልካም ስራ: በስኬትና በደስታ የተሞላ እንዲሆን ምኞታችን ነው። እንኳን ደስ አላችሁ 🎓🎓🎓🎓 Congratulations!! 💝🎉🎉🎉🎈🎁 🎈🎈 🎉 🎊🎊هنيئا لكم🎓🎓🎓🎓 Congratulations!! 🎉🎉🎉🎈🎁 ቦሄ ደስ ባረናሁም🎓🎓🎓🎓 ሀበይ ተስ ባለሙ🎉🎉🎉🎈🎁🎓🎓🎓 Congratulation Baga gammachiisa🎈🎁🎓🎓🎓
إظهار الكل...
🎉 17 6👍 2
እንግዲያውስ ግዜውም የእረፍት ግዜ ነው እንዳያመልጣቹህ በታላቁ ፈዲለቱ አሸይኽ መሀመድ ዘይን ኣደም
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
ማስታወሻ ~~ የ ''القواعد الحسان المتعلقة بتفسير القرآن" ኪታብ ደርስ ዛሬ በኢትዮጲያ አቋጣጠር ከረፋዱ 4:00 የሚጀመር ይሆናል ኢን ሻኣ ላህ። 🕌 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ:- ፉሪ (በፉሪ ሜዳ ፊት ለፊት ባለው ቅያስ ገባ ብሎ) አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ Google Map - http://maps.google.com/?cid=9777129393835294663&hl=en&gl=gb የኪታቡ Pdf - https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/8593 ትምህርቱን በቴሌግራም ለመከታተል ፦ https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam
إظهار الكل...
3👍 1
EXIT የወሰዳችሁ እህት ወንድሞች አላህ መልካም ውጤትን ይወፍቃችሁ:: አልፏልና ሀምዲን ብቻ አከታትሉ:: ውጤቱ ያምር ዘንድ ጌታችሁን አብዝታችሁ ጠይቁ:: ከሁሉም ነገር ጀርባ ጥበቡ የላቀ ነውና እሱ የሚወስንላችሁን ውደዱ:: በመውሰድ ላይ ያላችሁን ብርታቱን ይስጣችሁ:: በብቃት ጀምራችሁ የምታጠናቅቁ ያድርጋችሁ:: መልካም ውጤት! መልካም ፈተና!
إظهار الكل...
20
09:35
Video unavailableShow in Telegram
የሳዳት  እና  የስፖርተኛዉ  ሙሐመድ  ልብ  የሚነካ  አሳዛኝ  ገጠመኝ  በኡስታዝ  ሳዳት  ከማል (ለወንድማችን  ሙሐመድ  ዱዐ  እናድርግለት)
إظهار الكل...
54.82 MB
3
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.