cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

The Voice of Amhara የአማራ ድምፅ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
9 035
المشتركون
+8324 ساعات
+5757 أيام
+1 32230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የአማራ ክልል መንግስት ክዶናል፡ ለዳግመኛ ወረራ ዳርጎናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ! ክልሉን እየመራሁ ነው የሚለው የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያን ሕዝብ ክዷል፡ የደም ዋጋ ከፍለን ያስመለስነውን ማንነታችንን ለማስነጠቅ ዳግመኛ ወረራ አስከፍቶብናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ሚድያ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ይሄን የተናገሩ የሕወሓት ታጣቂዎች ከሳምንታት በፊት ጀምሮ በተፈናቃይ ስም ከነ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቆቻቸው በሰሜን ወሎ ዞን ስር በነበሩ በአራት ወረዳዎችና በሁለት ከተማ መስተዳድሮች በመግባት ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ድብደባ እንዲሁም ንብረት ዘረፋ እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ነው። ታጣቂዎቹ ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በመግባት በሰሜን ወሎ ዞን ስር በሚገኙ ራያ ባላ፣ ራያ ኦፍላ፣ ራያ ዘቦ፣ ራያ አላማጣ በተባሉ አራት ወረዳዎች እንዲሁም በአላማጣ ከተማ አስተዳደርና ኮረም ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ግድያ እየፈፀሙ ሲሆን፡ ለአብነትም ሰኔ 01/2016 ዓ/ም በአላማጣ ከተማ የተገደለው ወጣት ያሬድ መልካሙን ጨምሮ አስር የሚደርሱ ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ታውቋል። ከአማራ ድምፅ ሚዲያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው ቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች "አማራ ክልልን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው የብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያ አከባቢ አማራዎችን ክዶናል" ያሉ ሲሆን ቀጠናው ለዳግመኛ ወረራ እንዲጋለጥ አድርጓል ብለዋል። ህዝቡ በከባድ መከራ ውስጥ ይገኛል የሚሉት ነዋሪዎቹ ከዚህ መከራ ሊታደገው የሚችል አካል ጠፍቷል ሲሉ ተናግረዋል። የአማራ ድምፅ ያነጋገራት አራት ታዳጊ ልጆችን እንደያዘች ስትኖርበት ከነበረው ከራያ ባላ አከባቢ ተፈናቅላ ቆቦ ከተማ ተጠልላ የምትገኝ አንዲት እናት" የሕወሓት ታጣቂዎች በባለፈው አመት ባለቤቴን ገድለውብኛል፡ መኖሪያ ቤታችን ተቃጥሏል ንብረታችን ተዘርፏል ያለች ሲሆን "ዘንድሮም የእርሻ ማሳየ እንዳይታረስ ዳግመኛ ወረራ ተፈፀመብን፡ ታጣቂዎቹ ሊገድሉን ልጆቼን እንደያዝኩ አምልጬ ወጣሁ" ስትል ቃል በቃል ተናግራለች። ሌላኛው የአማራ ድምፅ ያነጋገራቸው በራያ ኦፍላ ወረዳ ስር በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ሲያስተምሩ የነበሩ መምህር"በተለየ ሁኔታ ከአራት አመታት ወዲህ አርሶ አደሩ አርሶ መብላት አልቻለም፡ ነጋዴው ነግዶ ማደር አልቻለም ተማሪዎችም አልተማሩም፡ ይባስ ብሎ ትምህርት ቤቶችም የጦር ካምፕ ሁነዋል ያሉ ሲሆን ገዢው አካል የራያን ህዝብ ክዷል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ እኛ አማራ ነን አንጂ አማራ እንሁን አላልንም ያሉ ሲሆን የኛ ያልሆነውን ማንነት ተገደን ልንቀበል ወይንም ሊጫንብን አይችልም ብለዋል። አገዛዙ የራያን ሕዝብ ነፃ ለማውጣት ህይወታቸውን የገበሩ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን አፈረሰ አሁን ደግሞ አንድ አሉን የምንላቸውን ፋኖዎችን ለማጥፋት በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጦርነት ከፍቷል ይህ የሚያሳየው የራያን ህዝብ ማንነት ለማጥፋትና መሬቱን አሳልፎ ለመስጠት ቆርጦ መነሳቱን ነው ብለዋል። የክልሉ መንግስት እንድንወረር ወዶ ፈቅዶ ከሰጠ በኋላ አሁን ላይ በኛላይ የሚደርሰውን ግና መከራን ለፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያነት እያዋለው ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ከአማራ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጨምረው ገልፀዋል። በመጨረሻም ነዋሪዎቹ፡ ገዢው መንግስት ደምና አጥንት ገብረን ያስመለስነውን ማንነታችንን እና እርስታችንን በሕጋዊ መልኩ ያፀድቅልናል በሚል በሰላማዊ መንገድ በትዕግስት ስንጠብቅ ብንቆይም ነገር ግን ሊሆን ስላልቻለ ከዚህ በኋላ እንደ ህዝብ ተነስተን ከፋኖዎቻችን ጋር በመሰለፍ ወረራ ባስከፈተብን የአገዛዝ ስርዓት ላይ የኃይል አማራጮችን ለመጠቀም እንገደዳለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተጨማሪ ዝርዝር ይከታተሉ👉 https://www.youtube.com/watch?v=vJmFC-VCGc8
إظهار الكل...
ዜና ሕዝቡ የኃይል እርምጃ ሊጀምር ነው! ከወደ ራያ የተሰማው አዲስ መረጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 21
Photo unavailableShow in Telegram
ሰበር ዜና! የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ከሰራዊታቸው ጋር ግምገማ እያደረጉ ባለበት የከባድ መሳሪያ ድብደባ ተፈፀመባቸው። የከባድ መሣሪያ ድብደባውን የፈፀመው የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ ሜካናይዝድ ጦር መሆኑም ታውቋል። በዚህ ጥቃት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ሕይወታቸው ያለፈ መስመራዊ የጦር መኮነኖች መኖራቸው ተሰምቷል...ዝርዝሩን ይጠብቁን! እስከዚያው ዩቱዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ፣ላይክና ሼር አድርጉ! ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ቻናል ይወዳጁ👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8
إظهار الكل...
👍 47👏 7 4
Photo unavailableShow in Telegram
እንደምን አደራችሁ! ወሎ ቤተ አማራ! ### አዲሱን የአማራ ድምፅ ቻናል ይወዳጁ👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8 የቴሌግራም ገፃችን ነው https://t.me/realthevoiceofamhara
إظهار الكل...
👍 56
Photo unavailableShow in Telegram
"ሞት እና ስቃይ መዘገብ ሰለቸኝ፣ አሁን ደግሞ በጦርነት የተጎዱ ሰዎችን ለማገዝ እርዳታ ወደማሰባሰብ ለማተኮር እያሰብኩ ነው" ይህን ከመታሰሩ በፊት ያለኝ ብርቱው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ነበር። በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ቤታቸው ላይ በተወረወረ ከባድ መሳርያ ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ እና ቤታቸው ለተቃጠለባቸውን የሰሜን ወሎ ነዋሪዎች የዛን ሰሞን ወደ 800,000 ብር የሚጠጋ ድጋፍ በራሳቸው የባንክ አካውንት እንዲሰባሰብ አርገን ቤታቸው ታድሶ እንዲገቡ አደረግን። ሌላም፣ ሌላም በርካታ የበጎ አድራጎት ሀሳቦች ነበሩት። ነገር ግን ግድያ፣ ጥቃት እና ግፍ ከሚደርስባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከማንም ቀድሞ መረጃ እያሰባሰበ ለህዝብ የሚያቀርበው ስራው ያልተወደደለት ጎበዜ ሀገር ጥሎ ከሄደበት ጅቡቲ ታፍኖ መጥቶ ለእስር በቃ። እርግጠኛ ነኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ለእስር ያበቃውን የጋዜጠኝነት ስራውን በደንብ የሚረዳበት እና የሚያመሰግንበት ግዜ ይመጣል። via EliasMeseret #JournalismIsNotACrime
إظهار الكل...
👍 54😢 20 6
https://www.youtube.com/watch?v=vJmFC-VCGc8 የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ወይንም በቀድሞ ስሙ ብአዴን የራያን ሕዝብ ክዷል፡ የደም ዋጋ ከፍለን ያስመለስነውን ማንነታችንን ለማስነጠቅ ዳግመኛ ወረራ አስከፍቶብናል ሲሉ የራያ አከባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ፡ ገዢው መንግስት ደምና አጥንት ገብረን ያስመለስነውን ማንነታችንን እና እርስታችንን በሕጋዊ መልኩ ያፀድቅልናል በሚል በሰላማዊ መንገድ በትዕግስት ስንጠብቅ ብንቆይም ነገር ግን ሊሆን ስላልቻለ ከዚህ በኋላ እንደ ህዝብ ተነስተን ከፋኖዎቻችን ጋር በመሰለፍ የኃይል አማራጮችን ለመጠቀም እንገደዳለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዝርዝሩን ይከታተሉ!
إظهار الكل...
ዜና ሕዝቡ የኃይል እርምጃ ሊጀምር ነው! ከወደ ራያ የተሰማው አዲስ መረጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 25
የራያ ሕዝብ "ብልፅግና ከድቶናል፣ ለዳግም ባቤነት አሳልፎ ሰጥቶናል" ሲል ቃል በቃል ተናግሯል! ህዝቡ እንደ ሕዝብ በአንድነት ተነስቶ ለተደጋጋሚ ወረራ በዳረገው የአገዛዝ ስርዓት ላይ የኃይል እስምጃ ሊጠቀም ይችላል ተብሏል! ሞት፣ መፈናቀል፣ መሰደድ በቃን ብሏል።ባለስልጣናቱ ፈርተዋል https://www.youtube.com/watch?v=vJmFC-VCGc8
إظهار الكل...
ዜና ሕዝቡ የኃይል እርምጃ ሊጀምር ነው! ከወደ ራያ የተሰማው አዲስ መረጃ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 27
Photo unavailableShow in Telegram
👍 17🤣 4
የሕወሓት ታጣቂዎች በሰሜን ወሎ ዞን ራያ አላማጣና በዙሪያው ባሉ አከባቢዎች የሚያደርሱት ጥቃት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የክልሉ መንግስት ይሄንን ጥቃት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀመበት ነው ተባለ! የሕወሓት ታጣቂዎች ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ስር በሚገኙ ራያ ባላ፣ ራያ ኦፍላ፣ ራያ ዘቦ፣ ራያ አላማጣ በተባሉ አራት ወረዳዎች እንዲሁም በአላማጣ ከተማ አስተዳደርና ኮረም ከተማ አስተዳደር ላይ በተፈናቃይ ስም ከነሙሉ ትጥቃቸው በመግባት የሚፈፅሙት ማንነት ተኮር ግድያ፣ ንብረት ዘረፋና እገታ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ይሄንን የታጣቂዎቹን ድርጊት የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ከፋኖ ኃይሎች ጋር ያለውን ውጥረት ያረግብልኛል በሚል ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እየተጠቀመበት ነው ሲሉ በራያ ዩኒቨርስቲ፣ በወልድያና በደሴ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ለአማራ ድምፅ ሚዲያ ገልፀዋል። ታጣቂዎቹ በአላማጣ ከተማ እለተ ቅዳሜ ሰኔ 01/2016 ዓ/ም ያሬድ መልካሙ የተባለ ወጣትን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን ተከትሎ ቅዳሜ አመሻሽና እሁድ ሙሉ ቀን በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። በተጨማሪም እሁድ አመሻሹን አንድ ወጣት በስራ ላይ እንደነበረ በታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት ክፉኛ ቆስሎ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ጣቢያችን ለማረጋገጥ ችሏል። በተፈናቃይ ስም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በአማራ ክልል አራት ወረዳዎችና ሁለት ከተማ አስተዳደሮች ላይ ዘልቀው የገቡት ታጣቂዎቹ፡ ማንነት ተኮር ግድያ፣ ድብደባና አስገድዶ መድፈር እየፈፀሙ ሲሆን በተጨማሪም ሰዎችን በማገት ከሦስት መቶ ሺ ብር ጀምሮ እስከ አንድ ሚሊየን ብር እየጠየቁ መሆናቸውንም የአማራ ድምፅ ሚዲያ ተጎጂዎችን ዋቢ በማድረግ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው ዘገባው ለአድማጭ ተመልካቾቹ ማድረሱ አይዘነጋም። ታጣቂዎቹ በአላማጣ ከተማ ምስራቅ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ታዳጊዋ ኢትዮጵያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት ላይ በተፈናቃይ ስም ከነ ሙሉ ትጥቃቸው መስፈራቸውንም ጣቢያችን በዘገባው ማካተቱ ይታወሳል። በራያ አማራዎች ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ጥቃት የክልሉ መንግስት አሚኮ በተባለ እራሱ በሚዘውረው ሚድያ በኩል የአማራ እና የትግራይ ክልል ሕዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እንዲገባ የቅስቀሳ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራኑ ገልፀዋል። ከአማራ ድምፅ ሚዲያ ጋር የስልክ ቆይታ ያደረጉት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው ያልተጠቀሰ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራኑ፡ በእነ አረጋ ከበደ የሚመራው የክልሉ መንግስት በክልሉ ውስጥ ያለውን ውጥረት ለማርገብ እና የፋኖ ኃይሎች ወደ አራት ኪሎ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ያስተጓጉልልኛል በሚል እሳቤ የራያን መሬት አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ወረራ ተፈፀመብኝ በሚል የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ተጠምዷል ሲሉ ተናግረዋል። ዛሬም ከስህተቱ ያልተማረው የሕወሓት ቡድን የአማራ ሕዝብ ላይ ዳግም ወረራ ለመፈፀም እየሞከረ ነው፡ ይህን የሕወሓት ቡድን ትንኮሳን የአማራ ክልል መንግስት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፋኖ ኃይሎች ጋር ያለውን ጦርነት ያስቆምልኛል በሚል አቅጣጫ ለማስቀየር እየሰራ ነው ብለዋል። ቢሆንም ግን የፋኖ ኃይሎች በአሁን ሰዓት ጠላታቸው ማን እንደሆነ ጠንቅቀው በማወቃቸው፡ ችግሩን ከስሩ ለማጥፋት ወደፊት የሚያደርጉትን ግስጋሴ እንደቀጠሉ ናቸው ሲሉ ምሁራኖቹ አክለው ገልፀዋል። በመጨረሻም ምሁራኑ: የሕወሓት ኃይሎች ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ባደረጉት ትግል ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ወጣት ከማስጨረስ ውጭ ያተረፉት ነገር አለመኖሩን በመረዳት፡ አሁን እየፈፀሙት ያለውን ወረራ በአስቸኳይ አቁመው ከወንድም አማራ ህዝብና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ያጋጫቸውን ስርዓት ነቅሎ ለመጣል ከፋኖ ኃይሎች ጋር የጋራ ትግል ማድረግ እንዳለባቸው ምክረ ሀሳብ አስቀምጠዋል። ከሳምንታት በፊት በሰሜን ወሎ ዞን አንዳንድ አከባቢዎች ላይ የክልሉና የዞን አስተዳደር አካላት ከማሕበረሰቡ ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ላይ "ያ ስትተማመኑበት የነበረው ፋኖ ስትወረሩ ግን ምንም ምላሽ መስጠት አልፈለገም።ፋኖ ለሕዝቡ የሚያስብ ቢሆን የሕወሓት ታጣቂዎች የሚያደርጉትን ወረራ ለማስቆም ይሰራ ነበር።ስለዚህ ፋኖን አትደግፉ ከመንግስት ጎን ቁሙ" በሚል ፋኖን የሚያጥላላ መልዕክት አስተላልፈው እንደነበር የአማራ ድምፅ በስብሰባው የተሳተፉ ሰዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል። በወቅቱ በነበረው መድረክ "ግብር የምንከፍላችሁ እናንተ እያላችሁ ፋኖን አስወረርከን ብለን ለምን እንጠይቃለን? መንግስት ነን ብላችሁ የተቀመጣችሁት እናንተ አይደላችሁም እንዴ? የሚል ጥያቄ ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተነሳባቸው የክልሉ አስተዳደር አካላት፡ "በአሁን ሰዓት መንግስት ፅንፈኞችን ለማጥፋት ዘመቻ ላይ ነው፡ ተባበሩን እና እነዚህን የፋኖ ኃይሎች ካጠፋን በኋላ የሕወሓት ታጣቂዎች የከፈቱብንን ወረራ በአስቸኳይ እናስቆማለን" የሚል ምላሽ መስጠታቸውንም ጣቢያችን በዘገባው አካቶ እንደነበር አይዘነጋም። ### ይህ አዲሱ የአማራ ድምፅ ሚዲያ ቻናል ነው👉https://www.youtube.com/@TheVoiceofAmhara8 የቴሌግራም ገፃችን ነው https://t.me/realthevoiceofamhara
إظهار الكل...
The Voice of Amhara 8 - የአማራ ድምጽ 8

Share your videos with friends, family, and the world

9👍 5🔥 3🤣 3
Photo unavailableShow in Telegram
😭 44👍 7😢 1😡 1
የመንግስት ኃይሎች የአማራ ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ሆሮጉድሩ ወለጋ አከባቢ በፈፀሙት የከባድ መሣሪያ ድብደባ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አርሶ አደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰማ! የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ወታደሮች በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ልዩ ስሙ ውባንጭ በተባለ ቀበሌ ላይ የከባድ መሣሪያ ድብደባ እየፈፀሙ መሆናቸውን ህይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ያሉ ወገኖች ለአማራ ድምፅ ተናገሩ! በቀበሌዋ የከባድ መሣሪያ ድብደባው የተጀመረው ሰኔ 03/2016 ዓ/ም እኩለ ቀን ገደማ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ መዋሉ ነው የተገለፀው። የገዢው ቡድን ወታደሮች በሚወረውሩት ከባድ መሣሪያ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ህፃናትና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ በርካታ አርሶ አደሮች መገደላቸው የተገለፀ ሲሆን፡ መኖሪያ ቤቶችም መውደማቸውን ነው ህይወታቸውን ለማትረፍ እየሸሹ ያሉ ወገኖች ለጣቢያችን የገለፁት። በተጨማሪም በጥቃቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳቶች መገደላቸው ታውቋል። የአገዛዙ ኃይሎች "ትጥቃችሁን ለመንግስት አስረክቡ" በሚል ምክኒያት በአከባቢው ማሕበረሰብ ላይ የሚፈፅሙት የከባድ መሣሪያ ድብደባ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን ህዝቡም ህይወቱን ለማትረፍ ቤቱን ለቆ ወደ ጫካ እየሸሸ እንደሚገኝ ነው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ለማረጋገጥ የቻለው። በተመሳሳይ ከሳምንት በፊት በዚኸው በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የአገዛዙ ወታደሮች "የደበቃችሁትን መሣሪያ አምጡ" በሚል በወሰዱት እርምጃ የአማራ ተወላጅ የሆኑ በቁጥር ከ30 በላይ አርሶ አደሮች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል። በተጨማሪም የሀገር ሽማግሌዎች በገዢው ቡድን ወታደሮች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን የደረሱበት አለመታወቁም ተሰምቷል። በዚህ ጥቃት ከተገደሉና ከቆሰሉ የአማራ ተወላጆች በተጨማሪ በርካታ የቀንድ ከብቶች ተዘርፈው የተወሰዱ ሲሆን መኖሪያ ቤቶችም በእሳት መቃጠላቸውንም ነው ተገጂዎቹ ለጣቢያችን የገለፁት። መከላከያ ሰራዊቱ የሚሰጣቸውን ሽፋን በመጠቀም ቤት ለቤት እየዞሩ ንብረት የሚዘርፉ የተደራጁ ወጣቶች አሉ የሚሉት ተጎጂዎቹ፡ በርካታ የቀንድ ከብቶችን እና የተከዘነ እህል በተሽከርካሪ እየጫኑ ዘርፈው ወስደውብናል ብለዋል። ከሳምንት በፊት በጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ የተጀመረው ይህ የመንግስት ኃይሎች ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት አድማሱን በማስፋት በዞኑ ስር ባሉ በሌሎች ወረዳዎችም የቀጠለ ሲሆን የዞኑ መቀመጫ ከሆነችው ሻምቡ ከተማ በደንጎሮ በኩል ከድርጎ ወደ ቱሉጋና የሚወስደው መንገድ መዘጋቱ ታውቋል። የአገዛዙ ኃይሎች እስከ ዛሬ የኦነግ ሸኔን ጥቃት ስትከላከሉበት የነበረውን የጦር መሣሪያ ለመንግስት አስረክቡ በሚል በከባድ መሣሪያ የታገዘ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን፡  የዘር ማጥፋት የፈፀሙብን ታጣቂዎች ባልጠፉበትና መንግስት ነኝ የሚለው አካል የዜጎችን ህይወት በማይታደግበት ሁኔታ ያለ ምንም ዋስትና መሣሪያችንን አናስረክብም ያሉ አንዳንድ የአከባቢው ነዋሪዎችም መከላከያ ሰራዊቱ ትጥቅ ፍቱ በሚል የከፈተባቸውን ጥቃት እየተከላከሉ እንደሚገኙ ነው የአማራ ድምፅ ለማረጋገጥ የቻለው። https://www.youtube.com/watch?v=LT20VU8TTLo
إظهار الكل...
ዜና! ዛሬም ያላባራው የወለጋ አማራዎች ጥቃት! ወሎ አምባሰል፣ኡርጌሳ፣ሮቢት፣ ውጫሌ ዙሪያ! The Voice of Amhara

#thevoiceofamhara #የአማራድምጽ #amharafanonews #amhara #gobezesisay

👍 19🔥 2