cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ወግ እና ትረካ(መፅሀፍ)🇪🇹 All-in-one

በዚህ "channel" ✔የፈለጉትን መፅሀፍ የሚያገኙበት(Pdf) ✔የፈለጉትን ትረካ የሚያገኙበት ✔የፈለጉትን የወግ አይነት የሚያገኙበት እንዲሁም ግጥም እንዲሁም ጠቅላላ እውቀቶችን በተጨማሪም ፍልስፍና ፡፡"ጥበብ ና ጥበብ"✍" All-in-one

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
257
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+1430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ይህ poll ዛሬ ከቀኑ ⌚️11:00 ሠዓት ላይ ያበቃል! https://t.me/allinone196/656
إظهار الكل...
👍 2
ይህ poll ዛሬ ከቀኑ ⌚️11:00 ሠዓት ላይ ያበቃል!
إظهار الكل...
👍 1
ይህ poll ዛሬ ከቀኑ ⌚️11:00 ሠዓት ላይ ያበቃል!
إظهار الكل...
ህዳር -11/03/2016 ዓ/ም
إظهار الكل...
stoicism         በጥንቷ ግሪክ የተፈጠረ ሲሆን እና በኋላም(እንዲሁም) በጥንቷ ሮም የተፈጠረ የፍልስፍና ትምህርት ቤት ነው። በርካቶች አንተውታል በፍልስፍናው አለም ታዎቂ እንዲሁም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፎል:: ይህ ብቻ አይደለም ምርጥ ከሚባሉ 10 philosophy ውስጥ አንዱ አና ዎነኛው ይሄ ነው እንቀጥል.. መስራቹ zeno ይባላል ስቶይሲዝም የተመሰረተው በዜኖ በሲቲየም በ3ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ሲሆን ፍልስፍናውን በአቴንስ ማስተማር የጀመረው በ300BC አካባቢ ሲሆን በፍጥነት በጥንቶቹ ግሪኮች ዘንድ ተወዳጅነትን አገኘ። እንደ Seneca፣  Epictetus እና Marcus Aurelius( ስለ Marcus Aurelius በሌላ ጊዜ በሰፊው እናወራለን) ያሉ ታዋቂ ፈላስፋዎች stoicism መርሆቹን የበለጠ በማዳበር እና በማስተዋወቅ ለዘመናት ተፅዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል። የስቶይሲዝም ማዕከላዊ መርህ ለጥሩ ሕይወት ቁልፉ -በተፈጥሮ መኖር🏕 እና -ውስጣዊ ጥንካሬን💪 እና -በጎነትን ማጎልበት ነው የሚለው ሀሳብ ነው። ስቶይኮች ከውጫዊ ሁኔታዎች ወይም ሁኔታዎች ይልቅ በእኛ ቁጥጥር ውስጥ ባሉ እንደ ሀሳቦቻችን፣ ድርጊቶቻችን እና አመለካከቶቻችን ላይ ማተኮር እንዳለብን ያምናሉ። (ማለት ወጭውን ሳይሆን ውስጣችን ላይ ማተኮር ማለት ነው) - ራስን መገሰጽ፣ -ምክንያታዊነት እና የሞራል -ታማኝነትን ይደግፋሉ።  stoicism እንዲሁ የአጽናፈ ሰማይን ተፈጥሯዊ ስርዓት መቀበል እና ለውጥን እና አለመረጋጋትን መቀበል አስፈላጊ መሆኑን ያጎላል። ፍልስፍናው የሚያስተምረን ከቁሳዊ ነገሮች ወይም ከውጫዊ ስኬት ጋር መያያዝ ሳይሆን ባህሪያችንን በማዳበር እና በዙሪያችን ካለው አለም ጋር ተስማምተን በመኖር ላይ ነው። ሌላው  የstoicism ቁልፍ ገጽታ የማሰብ እና ራስን የማወቅ ልምምድ ነው። ስቶይኮች የራሳቸውን ሃሳቦች እና ስሜቶች በመመርመር, ለውጫዊ ክስተቶች ያላቸውን ምላሽ በመረዳት እና ለውስጣዊ ሰላም እና መረጋጋት በመሞከር ያምናሉ፡፡ በአጠቃላይ፣ ስቶይሲዝም ግለሰቦች አርኪ እና ትርጉም ያለው ሕይወት ለመኖር ጽናት፣ ጥበብ እና የሞራል ልቀት እንዲያዳብሩ ያበረታታል። በምዕራቡ ዓለም አስተሳሰብ ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ያሳደረ ሲሆን ዛሬም በብዙ ሰዎች እየተጠናና እየተተገበረ ይገኛል። በአጠቃላይ የዚ philosophy ሀሳብ:- self improvement,self control ላይ የሚሰራ ነው ማንም ሰው እኛን ለማሳዘን አለስ ፈላጊ ንግግሮችን ሊናገር ሊያደርግ ይችላል ይህ ደግሞ ውጫዊ ነገር ነው እ ያንን ነገር እንደ ተልቅ ነገር አትቁጠሩት so እናንተ ድክመትን አስወግዱ ውስጣዊ ገፅታቹ ላይ ስሩ.... በትንሽ ነገር ስሜታችሁ አይጎዳ ሳሜታችሁን መቆጣጠር ማለት ነው ፍልስፍናውን በዚ ብቻ አትገድቡት..... የ @allinone196 መልእክት:- ይህ philosophy በሂወታችን እንድትተገብሩ እመክራችሆለው ነገ መንገዳችሁ የፀዳ ይሆናል በማንም የጥላቻ ንግግር እንዲሁም ድርጊት አትጎዱም ምክንያቱም ውስጣችሁ በሀሴቴ እና በሰላም የታጀበ ስለሆነ ለዛሬ በዚ አበቃን ሀሳብ አስተያየት ካሎት @LijSeyfeMD ይጠቀሙ ስለማን ስለምን እናውጋችሁ comment ያርጉን @allinone196 ነበርን!! only on @allinone196@allinone196 ብቻ @allinone196 👈👈👈 ይቀላቀሉን
إظهار الكل...
👍 1🔥 1🫡 1
Photo unavailableShow in Telegram
The philosophy of stoicism ይጠብቁን!!🙏🙏
إظهار الكل...
- The philosophy of stoicism - ✍ዛሬ ማታ 2:00 ይጠብቁን @allinone196 ላይ በ @LijSeyfeMD @allinone196
إظهار الكل...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
ግጥሞች_#211 የኔ ብርሀን አየሽ ጭራቁ አስፈራርቶኝ ፤ ነበርና ሮጥኩ ከህሊናዬ ጀርባ ተደበኩ በሬን ፤ እስኪጨልም ዘጋሁ ከብቸኝነት ፤ ብቻዬን ተዋጋሁ። ተስፋ ደፍሮ ፤ በማይበራበት የህልሜ ጭስ ፤ መውጫውን ባጣበት በኔ ተለክቶ ፤ በጠበበ አዕምሮ ልብሽ ምርኩዝ ሆነኝ ፤ ለዚህ ስንኩል ኑሮ ተነሳሁኝ ባንቺ ፤ ጨበጥኩኝ ብዕሬን ተነፈስኩ ፤ ከፈትኩትም በሬን ልኬን ፤ ባንቺ ሳልኩኝ የነገዬን ችቦ ፤ በፍቅርሽ ለኮስኩኝ። ግና ፈራሁ ብርሀንሽን ሰረኩ እንጂ ፤ መች እኔ አበራሁ ጭራቁ ራቀ እንጂ ፤ መቼ ተቀበረ አደበዘዝኩሽ መሠል ፤ ልቤ ተሰበረ። እናም ብርሀኔ... መሮጤ ግድ ሆኗል ፤ ካንቺ ርቄ ጭለማዬ ውስጥ ፤ መደበቄ ጠላቴን በራሴ ... እስክረታ ለፍቅርሽ ልበቃም... ልበርታ። አንድ ቀን ፤ ዕድል ካገናኘን       አሳይሽ ይሆናል የፍቅርሽን ፍሬ ግን ጊዜ ፤ ጓደኛዬ አይደል       ጠብቂኝ አልልም ደፍሬ ከሄድሽ ጮራሽን የሚችል ፤ ሰማይም አግኝተሽ ቅር አይበልሽ ፤ አታስቢ መጥለቅ ከፍ ... ከፍ ስትዪ ነው ፤ ምሽቴም የሚርቅ። ✍🏽✍🏽✍🏽... E.Z(@EZpoemandfiction) @allinone196 @allinone196 @allinone196 👈👈👈 ይቀላቀሉን
إظهار الكل...
ወጎች_#59 ፖሊማጅ! (አሌክስ አብርሃም) ከአመታት በፊት ሽመልስ ሀብቴ  አካባቢ እኖር ነበር! አንድ ቀን ቤተሰቦቸን ለመጠየቅ ወደክፍለሐገር  ልሄድ ተነሳሁ! በሌሊት የልብስ 'ባጌን' በጀርባየ አዝየ ወደአውቶብስ ተራ የሚሄድ ታክሲ ለመያዝ ጠደፍ ጠደፍ ስል የገነት ሆቴል የግንብ አጥር  ስር የተቀመጡ ሁለት ፖሊሶች አጋጠሙኝ፤ አንዱ ክላሽንኮቩን ታፋው ላይ አጋድሟል ፣ሌላኛው ዝነኛውን ጥቁር ዱላ ይዟል! ብርድና የጧት  ጨለማ  ስለነበር ተጀቡነው መልካቸው እንኳን በወጉ አይታይም! ቦታዋ ጨለም ካለ ተደጋጋሚ ስርቆት የሚፈፀምባት በመሆኗ ፖሊስ በማየቴ ውስጤ ዘና አለ! "ሄይ ወደየት ነው?" አለኝ አንዱ ፖሊስ ...ርምጃየን ገታ አድርጌ "ወደአውቶብስ ተራ" አልኩ! "ና ጠጋ በል እስቲ ...መታወቂያ ይዘሀል?" ጠጋ ብየ መታወቂያ ለማውጣት ስንደፋደፍ "ያ ምንድነው?" አለኝ በጅንስ ሱሪየ ላይ ቅርፁ ጎልቶ ወደሚታየው ስልኬ በጥቁር ዱላው እየጠቆመ "ስልክ" አልኩ "እስቲ አምጣው " ብሎ እጁን ዘረጋ ...ሰጠሁት፤ ሳምሰንግ ጋላክሲ ኖት 6 (በወቅቱ የመጨረሻው የሳምሰንግ ዘመናዊ ስልክ የነበረ ነው)! እያገላበጡ ለሁለት ሲያዩት ቆዩና ...."እና የት እየሄድክ ነው? " "ወደክፍለ ሀገር " "የት" "ደሴ" "ይሄን ስልክ ይዘህ ደሴ?" ሁለቱም ተሳሳቁ! አሳሳቃቸው አላማረኝም! "ስትመለስ ጣቢያ መጥተህ ውሰድ " አለኝ ባለዱላው መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሠለኝ... ጥቁር ዱላውን አመቻችቶ "ምን ይገትርሀል ሂዳ ፤ ወይሰ እንሸኝህ?" ሲለኝና ከኋላችን  የአንዲት ፒካፕ መኪና መብራት ሲያርፍብን አንድ ሆነ! እዛው ሰፈር የሚያውቀኝ 'ታዋቂ ሰው' ነው ...(እግዜር ልኮት ይሁን እድሌ ጎትቶት እንጃ) መስተዋቱን ዝቅ አድርጎ አንድ ነገር ብቻ  አለ "ደህናደራችሁ?  ቤተሰብ ነው! " ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋውጠው .... ስልኬን በ"ስታይል" መለሱልኝና አጭር ምክር መከሩኝ ..."ለወደፊቱ ውድ እቃ ይዘህ ሌሊት ብቻህን አትሂድ ...ማጅራት መችዎች ሊጎዱህ ይችላሉ" አለና ከኋላየ ወደቆመችው መኪና እያዩ ስልኬን ላተረፋት ሰው ምን ቢሉት ጥሩ ነው ? " ምከረው! " 😀 አመስግኘ መንገዴን ቀጠልኩ! ከብዙ ግርምትና እስካሁን ልመልሰው ካልቻልኩት የዕምነት መፈራረስ ጋር! ፖሊማጅ "ፖሊስ" እና "ማጅራት መች"  ከሚሉት ቃላት አዳቅየ  የፈጠርኩት አዲስ ቃል ነው! ማጅራት መች ፖሊስ እንደማለት! "ምላጭ ከለገመ በምን ይበጣል...ውሃ ካነቀ በምን ይዋጣል" እንዲሉ! ማጅራት ከሚመታ ፖሊስ ይጠብቀን🙏 @allinone196 @allinone196 @allinone196 👈👈👈 ይቀላቀሉን
إظهار الكل...
ህዳር -9/03/2016 ዓ/ም
إظهار الكل...