cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ማኅበረ ቅዱስ ፋኑኤል

مشاركات الإعلانات
198
المشتركون
-224 ساعات
-27 أيام
-230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🕊 [ † እንኳን ለቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊  † ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ  †  🕊 † አናንያ : አዛርያና ሚሳኤልን እንዲያው በቀድሞው አጠራር ሠለስቱ ደቂቅ [ሦስቱ ሕጻናት] እንላቸዋለን እንጂ ለእኛስ በእድሜም : በጸጋም : በትሩፋትም አባቶቻችን ናቸው:: ቅዱሳኑ የወቅቱ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጆች ናቸው:: ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ ሕዝቡን ሲማርክ አብረው ተማርከው ባቢሎን ወርደዋል:: ንጉሡ ከምርኮ ወጣቶች ለቤተ መንግስት ሲመርጥ ሦስቱ ቅዱሳንና ዳንኤል ተመርጠው የምቾት ሕይወት ተዘጋጅቶላቸው ነበር:: ነገር ግን በምግብና በአምልኮ ከአሕዛብ ጋር መተባበርን አልፈለጉምና ምርጫቸው ጾምና ጸሎት ከቆሎ ጋር ሆነ:: ምንም እንኳ በቤተ መንግስት ውስጥ ቢኖሩ : ምንም የነገሥታት ልጆች ቢሆኑ ለእነርሱ ከእግዚአብሔር ፍቅር የተሻለ አልነበረምና በጥሬ ቆሎ ተወስነው ኖሩ:: አምላካቸው ከሃሊ ነውና በውበትም ሆነ በጥበብ በባቢሎን ምድር ከነርሱ የሚደርስ አልተገኘም:: ንጉሡም በባቢሎንና በአውራጃዋ ላይ ሾማቸው:: ስማቸውንም በአማልክቱ ስም ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ አላቸው:: ከነገር ሁሉ በኋላ አሕዛብ ቀንተውባቸዋልና የክፋት አዋጅን አሳወጁ:: ናቡከደነጾር ፷ [60] ክንድ ቁመት ያለውን የወርቅ ምስል አቁሞ "ስገዱ" ቢላቸው አይሆንም በማለታቸው ተቃጥለው እንዲሞቱ እሳት ተፈረደባቸው:: ነበልባሉ ከጉድጓዱ ወደ ላይ ፵፱ [49] ክንድ ቢነድም ቅንጣት ያህል ፍርሃት አልጎበኛቸውም:: ወደ እሳቱም ሲጥሏቸው መልዐከ አድኅኖ ቅዱስ ገብርኤል ደርሶ አዳናቸው:: ከሆነው ነገር የተነሳ አሕዛብ አፈሩ:: ናቡከደነጾር ግን ከዙፋኑ ተነስቶ የቅዱሳኑን አምላክ እግዚአብሔርን ባረከ:: ከዚያች ቀን በኋላ አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል በአት አጽንተው : በጾምና በጸሎት ተወስነው ኑረዋል:: ነፍሳቸው ከሥጋቸው ስትለይ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆኗል:: ቅዱስ ዳንኤልና ናቡከደነጾር ተሯሩጠው ቢሄዱ ሦስቱም በአንድነት ዐርፈው ተገኝተዋል:: ንጉሡ በእጅጉ ይወዳቸው ነበርና በወርቅ በተለበጠ ሳጥን ቀብሯቸዋል:: ስሞት ከመካከላቸው ቅበሩኝ በማለቱ ዛሬ ድረስ ለበቁ አባቶች የአራቱ መቃብር ባቢሎን ውስጥ ይታያል:: ቅዱሳን አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል [ሲድራቅ : ሚሳቅና አብደናጐ] ያረፉት ግንቦት ፲ [10] ቀን ሲሆን ዘመኑም ከክርስቶስ ፭፻ [500] ዓመት በፊት ነው:: † አምላካቸው ከእሳት ባወጣቸው ቀንም :- "ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ:: ስቡሕኒ ውዕቱ ወልዑልኒ ውዕቱ ለዓለም::" የሚለውን ምስጋና ፈጣሪ ገልጾላቸው ደርሰውታል:: [በእሳቱ ውስጥ ሆነው ተናግረውታል::] ድርሰታቸው ፪ [2] ወገን ሲሆን ባለ ስድስት አንቀጹ ምስጋናቸው ከ፮፻ [600] ዓመት በኋላ ክርስቶስ እንደሚወለድ የሚያሳይ ነው:: ሌላኛውና ፴፫ [33] አንቀጾች ያሉት ምስጋናቸው ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ለ፴፫ [33] ዓመታት እንደሚመላለስ ያጠይቃል:: ቅዱሳን ሠለስቱ ደቂቅ ካረፉ ከ፱፻ [900] ዓመታት በኋላ [ማለትም ከክርስቶስ ልደት በ፬፻ [400] ዓመታት] ታላቁ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ቤተ ክርስቲያንን አንጾላቸው ነበርና አጽማቸውን ሊያገኝ ተመኘ:: ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ጠርቶ "አባ! አጽመ ቅዱሳንን ባቢሎን ወርደህ አምጣልኝ?" አለው:: ቅዱሱ ሐጺር ዮሐንስም በደመና ተጭኖ ባቢሎን ገባ:: በቅዱሳኑ መቃብር ፊትም ሰግዶ አለቀሰ:: ሠለስቱ ደቂቅም "ወዳጃችን! ምን ሆንክ?" አሉት:: ቅዱሱም መልሶ "ወደ ግብጽ እንሒድ:: አባ ቴዎፍሎስ ይፈልጋቹሃል" አላቸው:: እነሱም "ለቅዱሱ ቴዎፍሎስ እንዲህ በለው:: እግዚአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ:: ግን አጽማችን እስከ ዓለም ፍጻሜ ባቢሎንን አይለቅም:: ለክብርህ ግን እንመጣለን::" "ለምልክትም ይሆን ዘንድ መብራት ሳታበራ በሌሊት ጠብቀን በለው" ብለው ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ባርከው ሸኙት:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርም መጥቶ መልእክቱን አደረሰ:: በዕለተ ቅዳሴ ቤታቸው ቅዱሳን:- ቴዎፍሎስ : ቄርሎስ : ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና ሌሎችም ከምዕመናን ጋር በጨለማ ሳሉ ቤተ ክርስቲያኑ ቦግ ብሎ በራ:: እጅግ የሚደነቅ ብርሃንም ከበባቸው:: በብርሃኑ መካከል ሠለስቱ ደቂቅ ሲያልፉ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ሕዝቡም በደስታና በዝማሬ የቅዱሳኑን ቅዳሴ ቤት አክብሯል:: † በረከታቸው ይደርብን:: 🕊 [ † ግንቦት ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ] ፩. ሠለስቱ ደቂቅ ቅዱሳን [አናንያ : አዛርያና ሚሳኤል] ፪. ቅዱስ አብርሃም ጸራቢ [ሰማዕት] ፫. አባ ሚካኤል ገዳማዊ ፬. አባ ይስሐቅ ግብጻዊ [ †  ወርሐዊ በዓላት ] ፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ ፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ ፫. ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ጻድቅ ንጉሥ ፬. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ ፭. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ] ፮. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት ፯. ቅዱስ ዕፀ መስቀል † " ናቡከደነፆርም መልሶ:- መልአኩን የላከ : ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን : የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን : በእርሱ የታመኑትን ባርያዎቹን ያዳነ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ:: " † [ዳን.፫፥፳፰] (3:28) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
01:45
Video unavailableShow in Telegram
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬             [  ፍ ኖ ተ አ በ ው ! ] የእውነተኞቹ አባቶቻችን የተጋድሎ ሕይወት ይህ ነው ! ❝ የቀደሙ አባቶቻችን ጻድቃን ቅዱሳን በእምነታቸው የእሳቱን እቶን አቀዘቀዙት፡፡ በዚያም በባዕድ ሀገር ባርነቱን ፣ መከራውን ፣ ሥቃዩን ሁሉ ታግሠው ኖሩ፡፡ እኛ ጥቂቱን መከራ እንኳ ያለመታገሣችን ምክንያቱ እምነታችን ጎዶሎ ስለሆነ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ትዕግሥት ከእኛ ዘንድ የራቀ ሆነ፡፡ ❞ [  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  ] ❝ ቅዱሳን በጾምና በጸሎት በልመናና በስግደት በሰላም ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገሩ ፤ በመስቀሉም ታምነው ወደ ርስታቸው ገቡ  ፤ እኛም በታላቋ ዕለት በዚያች ሰዓት ይምረን ዘንድ እርሱን እንታመን። ❞ [ ቅዱስ ያሬድ ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬
إظهار الكل...
إظهار الكل...
ክርስትና ለኔ ሕይወቴ ነው።መሪማ እንድሪስ ከእስልምና ወደ ክርስትና ምስክርነት

#ethiopia #orthodox #fnoteabriham

إظهار الكل...
የዝንጅብል አስደናቂ ጥቅሞች | dryonas | ዶ/ር ዮናስ | janomedia | ጃኖ ሚዲያ | newmedia

#dryonas #janomedia #yonas