cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Marcel Planiol

Laws, law books, case discussions, cassation decisions, proclamations, regulations, directives, articles, law journals and commentaries!

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
197
المشتركون
-124 ساعات
-17 أيام
-830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

https://t.me/lawsocieties
#Alehig #አለሕግ
إظهار الكل...
የተሻሻለውን_የቤተሰብ_ህግ_ለመገንዘብ_የሚረዱ_አንዳንድ_ነጥቦች_ቅፅ_1_በመሓሪ_ረዳኢ_1995_ዓ_ም_1.pdf20.03 MB
የሰበር መ/ቁ 227978 የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር አከፋፈል በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የጦር መሣሪያ ጭኖ በመገኘቱ የተነሳ በጉምሩክ ኮሚሽን ሲወረስ የተሽከርካሪው ባለቤት (ተበዳሪው) የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት በመቃወም ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ጣልቃ በመግባት የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ ወይስ አይችሉም? የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር በመያዣነት የያዟቸው ተሽከርካሪዎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ለማዘዋወር ድርጊት መፈጸሚያነት ውለው ሲገኙ በጉምሩክ ኮሚሽን አስተዳደራዊ ውሳኔ ውርስ የሚደረጉ ሲሆን የፋይናንስ ተቋማቱም የውርስ ውሳኔው በተሽከርካሪዎቹ ላይ ያላቸውን የቀደምትነት መብት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው የሚል ክርክር ያቀርባሉ። በጉምሩክ አዋጅ ቁ. 859/06 አንቀጽ 153 መሠረት የጉምሩክ ጉዳዮች አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍል የውርስ ውሳኔውን በማጽናት በሰጠው ውሳኔ ላይ የተሽከርካሪው ባለቤት ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው ይግባኝ ላይ አበዳሪው ባንክ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የአሰራር መመሪያ ቁ. 02/11 አንቀጽ 16(1)(ሀ) መሠረት የጣልቃ ገብ አቤቱታ በማቅረብ የክርክሩ ተካፋይ መሆን ይችላል? ወይስ ጉዳዩ በቀጥታ ለመደበኛ ፍ/ቤቶች የሚቀርብ ነው? በሚለው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ባለመኖሩ ለክርክር በር ሲከፍት ቆይቷል። የታክስ ይግባኝ ኮሚሽኑ የፋይናንስ ተቋማቱ የሚያቀርቡትን የጣልቃ ገብ አቤቱታ ተቀብሎ የማየት ሥልጣን በሕግ ያልተሰጠው መሆኑን በመጥቀስ አቤቱታውን ውድቅ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ጉዳዩን በይግባኝ የሚመለከቱ መደበኛ ፍ/ቤቶች ደግሞ የጉምሩክ ጥፋት መፈጸሙን ተከትሎ የሚጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶችንና የውርስ ውሳኔዎችን ሕጋዊነት በመቃወም የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቀብሎ የማየትና መርምሮ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የመስጠት የመጀመሪያ ደረጃ የሥረ ነገር ሥልጣን ለጉምሩክ ኮሚሽን አቤቱታ አጣሪ የሥራ ክፍሎች የተሰጠ በመሆኑና በጉምሩክ አዋጁ የተዘረጋው የቅሬታ አቀራረብ ሥነ ሥርዓት በጉዳዩ ላይ ያገባናል የሚሉ ሦስተኛ ወገኖች ወደ ክርክሩ በመግባት መብትና ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚችሉበትን አሠራር ያልዘረጋ በመሆኑ ተበዳሪው (የተሽከርካሪው ባለቤት) ለታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚያቀርበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ የፋይናንስ ተቋሙ የክርክሩ ተካፋይ ሊሆን ይገባል የሚል አቋም ያንጸባርቃሉ። ይህንን በሚመለከት የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 227978 አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ሰ/ሰ/ችሎቱ - በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በሚካሄዱ ክርክሮች የሚያከራክረው ጉዳይ ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል? አልጫነም..ሊወረስ ይገባል? አይገባም የሚል ክርክር በመሆኑና የፋይናንስ ተቋማቱም የቀዳሚነት መብት ያላቸው ስለመሆኑ ከማንሳት በስተቀር ተሽከርካሪው የጦር መሣሪያ ጭኗል ወይስ አልጫነም በሚለው የክርክር ፍሬ ጉዳይ ላይ የሚያቀርቡት ክርክር አለመኖሩን፤ በመሆኑም ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ፍሬ ጉዳይ ላይ መብት ወይም ጥቅም የሌላቸው መሆኑን... - የቀዳሚ መብት ጥያቄ የሚነሳው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3059(1) መሠረት በመያዣ የተያዘው ንብረት በሌሎች ገንዘብ ጠያቂዎች ተይዞ ንብረቱ በሀራጅ ከተሸጠ በኋላ የተገኘው ገንዘብ የሁሉንም ዕዳ መሸፈን በማይችል ጊዜ መሆኑንና የቅድሚያ መብት አቤቱታ በዚህ ደረጃ የሚነሳ አለመሆኑን፤ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ክርክሩ እንዲገቡ በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የሚሰጥ ውሳኔ በባንኩና በተበዳሪው መካከል ያለውን የብድር/መያዣ ውል መሰረት ያደረገ አለመሆኑን በማንሳት ....ባንኩ የብድር ውሉን መሠረት በማድረግ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ ግን በመጠበቅ ውሳኔ ሰጥቷል።    በመሆኑም የፋይናንስ ተቋማት በመያዣነት የያዙት ተሽከርካሪ የውርስ ውሳኔ ሲተላለፍበት የመያዣ ውሉን መሠረት አድርገው በመደበኛ ፍ/ቤቶች ክስ ከሚመሰርቱ በስተቀር የውርስ ውሳኔውን ሕጋዊነት ብቻ በሚመለከተው በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን በተሽከርካሪው ባለቤትና በጉምሩክ ኮሚሽን መካከል በሚካሄድ ክርክር ጣልቃ ገብተው ለመከራከር አይችሉም። BY Tsegazeab Zerihun Gebeyehu, an Attorney for FDRE Customs
إظهار الكل...
🇪🇹የሕግ ጉዳይ

Legal matter, Ethiopia Legal Info, #ጠበቃና የሕግ አማካሪ We offer you Reliable services with a very high sense of responsibility. #ከጠበቃ ጋር ተነጋገሩ @TalkToLawyer [email protected]

👍 1
yihew ye dr. mehari leteyekachu
إظهار الكل...
Mehari Redai 2.pdf55.15 MB
የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ መግለጫ ወንጀል ለተለያየ ዓላማ ሊፈጸም የሚችል ቢሆንም ገንዘብ የሚያስገኙ ወንጀሎች የሚፈጸሙት ፈፃሚዎቹ በዋናነት ከወንጀል ድርጊታቸው የገንዘብ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ከሚፈጸሙ ወንጀሎች መካከል የሙስና ወንጀሎች በተለይም ጉቦ መቀበል ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፥ የተከለከሉ ዕፆችን ማዘዋወር፣ የሃሰት ገንዘብ ማተም፣ ሕገ ወጥ ሀዋላ፣ የታክስ እና የኮንትሮባንድ ወንጀሎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ እነዚህ እና መሰል ወንጀሎች በባህሪያቸው ለወንጀል ፈጻሚዎች ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ሲሆኑ በሀገር ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ የሚያሳርፉት አሉታዊ ተጽዕኖ ደግሞ በተቃራኒው እጅግ አደገኛና ውስብስብ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ወንጀልን ከመከላከል እና አጥፊዎች ላይ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ከማስተላለፍ አንፃር በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎችን በወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ በተጨማሪ የወንጀል ፍሬ ወይም ለወንጀል መፈጸሚያነት የዋለውን ንብረት መውረስ ተገቢ ነው፡፡ በወንጀል የተገኘ ሃብትን የማስመለስ ሂደት የተለያዩ ደረጃዎችን የሚያልፍ ሲሆን በዚህም የወንጀል ምርመራን መሰረት በማድረግ ንብረት የመለየት፣ ንብረት የማገድ፣ ንብረት የመያዝ እና በአስተዳደር ስር እንዲቆይ የማድረግ እንዲሁም ንብረት የመውረስ ተግባራት ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡ ይህንን ሂደት በአግባቡ ለመፈጸም ወጥና ራሱን የቻለ የንብረት ማስመለስና አስተዳደር ሕግ ሊኖር ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ራሱን የቻለ በወንጀል የተገኘ ሃብትን የሚመለከት ሕግ ባይኖራትም በተለያዩ አዋጆች ስር በወንጀል የተገኘ ሃብት ማስመለስን በተመለከተ ተፈጻሚነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ተካተው እናገኛለን፡፡ በእነኚህ አዋጆች ውስጥ ተካተው የሚገኙት የንብረት ማስመለስ ድንጋጌዎችም ተበታትነው ከመገኘታቸው ባሻገር ተፈፃሚነታቸውም በአዋጆቹ ስር ለተደነገጉት የወንጀል አይነቶች ብቻ እንደመሆኑ መጠን ወጥ የሆነ የንብረት ማስመለስ እና ማስተዳደር ሕግ አለመኖሩ በአዋጆቹ ባልተካተቱ እና ከፍተኛ የሆነ የንብረት ጥቅም ወይም ጉዳት በሚያስከትሉ ወንጀሎች ላይ የንብረት ማስመለስ ሂደት መሰረታዊ የሆነ የሕግ እና አፈፃፀም ክፍተት እንዲኖር አድርጓል፡፡ በመሆኑም እነዚህን በተለያዩ ሕጎች ውስጥ ተበታትነው ያሉትን የንብረት ማስመለስ እና አስተዳደር ድንጋጌዎች በአንድ ወጥ ሕግ ውስጥ በማካተት ለአፈጻጸም ምቹ የሆነ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ይህም ሁኔታ በወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ መርሆዎች መካከል አንዱ የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመለየት፣ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለማስተዳደር ወይም ለመውረስ የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እንደሚሆን እንዲሁም በዚሁ ፖሊሲ ተራ ቁጥር 3.16.3 ላይ ስለንብረት ማገድና መውረስ የተካተተ በመሆኑ በዚህ የፖሊሲ አቅጣጫ መሠረት አንድ ወጥ የሆነ ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ አዋጅ ተዘጋጅቷል። የዚህ አዋጅ ዋነኛ ዓላማ የወንጀል ፍሬ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመያዝ፣ ለማገድ፣ ለመውረስ ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ግልጽና ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ በማበጀት ማንም ሰው ከሕገ-ወጥ ድርጊት ማናቸውንም አይነት የኢኮኖሚ ጥቅም እንዳያገኝ ለማድረግ እና የንብረት ማስመለስ ሕግ ወንጀልን በመከላከል ሂደት ያለውን ከፍተኛ ሚና ለማሳካት የሚያስችል የንብረት ማስመለስና ማስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በአሁኑ ወቅት ከወንጀል ጋር ግንኙነት ያለውን ምንጩ ያልተወቀ ንብረትን ማስመለስ እንዲቻል እና በተለያዩ ሕጎች ውስጥ ተበታትነውና ለአፈጻጸም አስቸጋሪ ሆነው ያሉትን የንብረት ማስመለስ እና መውረስ መሠረታዊ ድንጋጌዎች እና የሥነ-ሥርዓት ሂደቶች የንብረት ማስመለስና መውረስ ሂደት ውስጥ ያሉትን ልዩ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም አይነት ወንጀሎች የሚያገለግል አንድ ወጥ የሆነ ዝርዝር የሕግ ማዕቀፍ በማውጣት በንብረት ማስመለስና መውረስ ሂደት ውስጥም ሆነ ንብረቱ ከተወረሰ በኋላ የንብረቱን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ማስጠበቅ የመንግስትና የሃገሪቱን ጥቅም ማስከበር ማዕከል በማድረግ የተዘጋጀ ሕግ ነው። ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን እና በወንጀል የተገኘ ሀብትን ከማስመለስ ጋር በተያያዘ ሰፋ ያለ ጽንሰ-ሐሳባዊ ጉዳዮችን እና የሀገራትን ልምድ በአግባቡ ለመረዳት ከዚህ በታች የተመላከቱተን ጽሁፎች ያግዛሉ። ፍትህ ሚኒስቴር
إظهار الكل...
የወንጀል ቅጣትን መገደብ - ሕጉና ተግባሩ ጸሐፊ፡- ዜና ሁነኛው https://t.me/EsubalewAmareLawOffice https://t.me/EsubalewAmareLawOffice
إظهار الكل...
የወንጀል_ቅጣትን_መገደብ_ሕጉና_ተግባሩ.pdf9.16 KB
👍 1
ሁከት ተፈጠረ በተባለበት ወቅት ንብረቱ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ንብረቱ በከሳሽ ይዞታ ስር የነበረ መሆን አለመሆኑ እና ተከሳሽ በክሱ የተጠቀሰውን ተግባር ለመፈፀም የሚያስችል መብት ያለው መሆን አለመሆኑን እንጂ ከዚህ በላይ በመሄድ በውርስ ይዞታ ባለቤትነት ላይ ተመስርቶ ውሳኔ መስጠት ተገቢነት የለውም፡፡( ሰበር መ/ቁ 186348፤ አንቀፅ 1140፣1149(1) እና 1149(3))                    =======
إظهار الكل...
ሁከት.pdf5.73 KB
👍 1
የወንጀል ሕግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራ መሆኑ (Non-Retroactivity of Criminal Law) ====================== በዚህ መርህ መሰረት ህግ ሊተገበር ወይም ሊፈፀም የሚችለው ህጉ ከፀደቀ በኋላ በተፈፀሙ ድርጊቶች ላይ ነው። ይህ ማለት አዲስ ህግ ሲወጣ ህጉ ከመውጣቱ በፊት የተፈፀሙት ድርጊቶች በአዲሱ ህግ ወንጀል መሆናቸው ቢደነገግም ለበፊቱ ድርጊት ተፈፃሚ አይሆንም። አንድ ሕግ የዜጎችን መብትና ግዴታ የሚወስን በመሆኑ ሰዎች ሕጉ እስከሚለወጥ ድረስ ድርጊቶቻቸውን ወይም ግንኙነታቸውን ሕጉ በሚፈቅደው ወሰን ውስጥ ያካሂዳሉ፡፡ አንድን ሁኔታ የሚለውጥ ወይም የሚያሻሻል ሕግ ቢወጣ ሕጉ ተፈፃሚ መሆን ያለበት ቢያንስ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ወደፊት መሆን አለበት፡፡ ይህ መርህ በወንጀል ህግ አንቀፅ 5 እና በህገ መንግስቱ አንቀፅ 22 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በአዲሱ ወይም በ1996 ዓ.ም በወጣው የወንጀል ህግ እና በተሻረው የወንጀል ህግ እንደወንጀል የተቆጠረ ድርጊት የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ፣ ጉዳዩ የሚታየው በተሻረው የወንጀል ህግ መሰረት ነው። ድርጊቱ በአዲሱ ህግ መሰረት ወንጀል ሆኖ በተሻረው ህግ ግን እንደወንጀል ካልተቆጠረና የተፈፀመው አዲሱ ህግ ከመፅናቱ በፊት ከሆነ ሊያስቀጣ አይችልም። እንዲሁም የተሻረው ህግ ይሰራ በነበረበት ጊዜ የተፈፀመ ወንጀል ሲኖር በአዲሱ ህግ ግን እንደወንጀል ያልተቆጠረ ሲሆን ሊያስከስስም ሆነ ሊያስቀጣ አይችልም፤ ክሱም ተጀምሮ እንደሆነ እንደሚቋረጥ በወንጀል ህጉ ተደንግጓል። የወንጀል ህግ ወደ ኋላ ሄዶ አይሰራም ሲባል በመሰረታዊ ሕጉ ላይ ሁለት ዓይነት ውጤቶችን ያስከትላል፡፡ አንደኛው አንድ ድርጊት በሚፈፀምበት ጊዜ ድርጊቱ በጊዜው የማያስቀጣ ከነበረ ይኸው ድርጊት ከጊዜ በኋላ በወጣ ሕግ ወንጀል ነው ሊባል አይችልም፡፡ ሁለተኛው ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ወንጀል ቢሆንም እንኳን ወንጀለኛው መቀጣት ያለበት ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት ተፈፃሚነት የነበረው የወንጀል ሕግ በደነገገው ጣሪያ መሆን አለበት የሚሉ ናቸው፡፡ ስለዚህም ከድርጊቱ በኋላ የወጣው ሕግ የቅጣት ጣሪያውን ከፍ ቢያደርገው ይህ ቅጣት ሕጉ ከመታወጁ በፊት ለተፈፀመ ወንጀል ተፈፃሚ መሆን የለበትም፡፡ ይሁንና አዲሱ ህግ ለተከሳሹ ወይም ለተቀጣው ሰው የሚጠቅም በሆነ ጊዜ ከድርጊቱ ኋላ የወጣው ህግ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 22(3) ይደነግጋል። በተጨማሪ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 6 ስር እንደተደነገገው አዲሱ የወንጀል ህግ እንዲፀና ከተደረገ በኋላ አድራጊው ህጉ ከመፅናቱ በፊት ላደረገው ወንጀል ሲፈረድበት፣ ወንጀሉን በፈፀመበት ጊዜ በሥራ ላይ ከነበረው ሕግ ይልቅ ይሄኛው ሕግ ቅጣት የሚያቀልለት ሲሆን በአዲሱ ህግ ላይ የተመለከተው ቅጣት ይፈፀምበታል። By Tsegaye D._Lawyer!
إظهار الكل...
👍 1
https://t.me/LegalAff በወንጀል ህግ ስልጣን በሌለው ፍርድ ቤት የተሰጠ የጥፋተኛነት እና ቅጣት ውሳኔ ሊጸና የማይችል ስለመሆኑ የሰ/መ/ቁ 243034/16        ጉዳዩ ለፌደራሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ሊቀርብ የቻለው አመልካቾች በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበባቸው የወንጀል ክስ በ1996 በየወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 32፣35 እና 539 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በአመልካቾች መሪነት በቁጥር 200 ከሚሆኑ የወንጀል ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ከባድ ሰው መግደል ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ ለቀረበ ክስ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ድርጊቱ ስለመፈጸሙ በማስረጃ በማረጋገጥ አመልካቾች እያንዳንዳቸው በ18 ዓመት እድሜ እስራት እንዲቀጡ ወስኖዋል፡፡ ጉዳዩ በክልሉ ባሉ የበላይ ፍርድ ቤቶች በይግባኝ ቀርቦ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በማጽናት መዝገብ በመዝጋት ቢወሰንም አመልካቾች ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን የይግባኝ መከራከርያ ሃሳብ ያደረጉት በኦሮምያ ክልል ዓቃቤ ህግ በቀረበ ክስ መሰረት ሰው ሊሞት የቻለው በኦሮሞ እና በአማራ ቢሄር መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት በመሆኑ ጉዳዩ የማየት ስልጣን የሚኖረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሲሆን የኦሮምያ ክልል ፍርድ ቤት በሌለው ስልጣን ጉዳዩን አይቶ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት ነው፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት መጥርያ ደርሶት ተጠሪ በበኩሉ ሟች እና አመልካቾች የተለያየ ብሄር አባላት ቢሆኑም በአንድ አከባቢ የሚኖሩ በመሆናቸው የክልሉ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አይቶ መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት መልስ አቅርቦዋል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮምያ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አይቶ የመወሰን ስልጣን የለውም በማለት ውሳኔውን በመሻር አመልካቾች ከማረምያ ቤት እንዲለቀቁ ሲወስን በፍርድ ሀተታው ላይ የሚከተለውን የውሳኔ ሃሳብ በማስፈር ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት አወቃቀር ፌደራላዊ ከመሆኑ አንፃር የዳኝነት አካሉም በፌደራል እና ክልል ደረጃ የተቋቋመ ቢሆንም፤ የፍርድ ቤቶቹ አደረጃጀት ትይዩ ባለመሆኑ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች በክልላቸው ከሚሰጣቸው የዳኝነት ሥልጣን በተጨማሪ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሥልጣን ደርበው የሚሰሩ ሲሆን፤የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችም በክልላቸው ከሚኖራቸው የዳኝነት ሥልጣን በተጨማሪ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚታዩ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን አላቸው፡፡(የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(2) እና 80(4) ይመለከቷል፡፡) የፌደራል መንግስቱም ሆነ የክልል መንግስት ሥልጣን ምንጭ ሕገ-መንግስት መሆኑን፤ ለፌደራሉ መንግስት የተሰጠው ሥልጣን በክልሎች መከበር ያለበት መሆኑን፤ በተመሳሳይ ለክልሎች የተሰጠውን ሥልጣን የፌደራል መንግስት ማክበር እንዳለበት የሕገመንግስቱ አንቀጽ 50(8) ያመለክታል፡፡ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን በሰበር አይቶ የማረም ሥልጣን በክልል ጉዳዮች ላይ ብቻ የተገደበ መሆኑን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987 አንቀጽ 80(3) (ለ) ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሕገ-መንግስቱ በተሰጣቸው የውክልና ሥልጣን አይተው የሰጡትን ውሳኔ በሰበር የማረም ሥልጣን በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 ቁጥር 10(1)(ሠ) ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት የተሰጠ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያፀደቀችው እና በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9(4) ድንጋጌ መሠረት የሀገሪቱ የህግ አካል የሆነው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን (international covenant on civil and political Rights) አንቀጽ 14(1) ማንኛውም ሰው በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሔር የቀረበበትን ክስ በሕግ በተቋቋመ፤ ስልጣን ባለው ነፃና ገለልተኛ አካል የመዳኘት መብት ያለው መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 የወንጀል የዳኝነት ሥልጣን የሚደነግገው ቁጥር 4(9) እንደሚያመለክተው በተለያዩ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦች፤ ጎሳዎች፤ሐይማኖት ተከታዮች፤ ወይም በፖለቲካ ቡድኖች መካከል ከተፈጠረ ግጭት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን የማየት ሥልጣን የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ሕገ-ምንግስታዊ ውክልና ባልተነሳባቸው ክልሎች ይህን ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ሥልጣን አይቶ የመዳኘት ሥልጣን በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 80(2) መሠረት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ናቸው፡፡ በፌደራል ፍርድ ቤት ሥልጣን ስር የሚወድቅ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር ማድረግ፤ የተጀመረ የወንጀል ምርመራ ላይ ክትትል ሪፖርት እንዲቀርብ ማድረግ እንዲሁም ምርመራው በአግባቡ ተከናውኖ እንዲጠናቀቅ፤ የህዝብ ጥቅም መነሻ አድርጎ ወይንም በወንጀል የማያስጠይቅ ሲሆን ምርመራው እንዲቋረጥ ወይንም የተቋረጠው ወንጀል ምርመራ እንዲቀጥል ማድረግ፤ ምርመራው በህጉ አግባብ መከናወኑን ማረጋገጥ፤ የፌደራል መንግስትን በመወከል በወንጀል ጉዳዮች ክስ መመስረት፤ መከራከር፤ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ክስ ማንሳት፤ የተነሳ ክስ እንዲቀጥል ማስደረግ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሥልጣን መሆኑን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 943/2008 ቁጥር 6(3)(ሀ) እና (ሠ) ይደነግጋል፡፡ በተያዘው ጉዳይ በአመልካቾች ላይ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1),(ሀ) (ለ)፣35 እና 539(1)(ሀ)ን በመተላለፍ በክሱ ላይ በተገለጸው ጊዜ በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ አባቦ ሞሌ በሚባል አካባቢ በአማራ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ዓይነቱ የማይታወቅ የጦር መሳሪያ በመያዝ ከሌሎች 200 ሰዎች ጋር በመሆን ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ነው፡፡ ክሱ የቀረበለት የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ለወንጀል ድርጊቱ መፈጸም መነሻው ምክንያቱ በአማራ ብሄር እና ኦሮሞ ብሄር መካከል በተፈጠረ ግጭት አመልካቾች ከሌሎች 200 በላይ ከሚሆኑ ሰዎች ጋር ወደ ግል ተበዳይ ቤት በመሄድ ወንጀሉን እንደፈፀሙ በማስረጃ ማረጋገጡን ውሳኔው ያመለክታል፡፡ አመልካቾች ለወንጀል ድርጊቱ መፈፀም ምክንያት የሆነው በአማራ እና ኦሮሞ ብሄር መካከል የተነሳ ግጭት በመሆኑ ወንጀሉን የመመርመር ሆነ ክስ ማቅረብ የፌደራል ዓቃቤ ህግ ሆኖ እያለ በክልል ፓሊስ እና ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ ተመርምሮ ክሱ ለክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረቡን በመቃወም ላቀረቡት አቤቱታ ተጠሪ በሰጠው መልስ አመልካቾችም ሆነ የግል ተበዳይ የሚኖሩት አንድ አካባቢ በመሆኑ ግጭቱ የብሄር አይደለም የሚል ክርክር አንሰቷል፡፡ ግጭቱ የብሄር መሆኑን በክስ ማመልከቻው ላይ የተመለከተው ፍሬ ነገር የሚያሳይ ሆኖ እያለና በማስረጃም ተረጋግጦ ባለበት አመልካቾች እና የግል ተበዳይ በአንድ አካባቢ መኖራቸው ግጭቱ የብሄር አይደለም ወደሚል ድምዳሜ ሊያደርስ አይችልም፡፡ By 21C legal affair
إظهار الكل...
21C Legal Affair

⚖️ 21C Law vs practice ⚖️. ነፃ የህግ የማማከር አገልግሎት፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች : አጫጭር ኖቶች እዚሁ ያገኛሉ። Here on our channel, we provide Free legal Aid. You could alsk get access to laws, cassation decisions, job opportunity updates.

ግሩም ውሳኔበሰባት ዳኞች ተለውጧል የሰበር መዝ/ቁ 191393 ሚያዚያ 30/2015 ~~~ ♦ካሁን በፊት በተለያዩ የሰበር ውሳኔዎች "ለውርስ ክርክር ተፈፃሚነት ያለው ሟች በሞተበትና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ ተፈፃሚነት የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በስራ ላይ ባለው ህግ መሰረት ሊሆን ይገባል" በሚል የተሰጡ ውሳኔዎች በሰባት ዳኞች ተለውጦ ተፈፃሚ የሚሆነው ህግ ሟች በሞተበትና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ ተፈፃሚነት ያለው ህግ ሊሆን ይገባል ተብሏል። ♦ይህ ውሳኔ ተገቢና አሳማኝ መሆኑን የምንቀበል ቢሆንም ለእኛ ጥያቄ የሆነብን ግን ካሁን በፊት በነበሩት የሰበር ውሳኔዎች መሰረት ዳኞች ህግን ተርጉመው እንዳይሰሩ በሰበር ችሎቱ አስገዳጅ ውሳኔ ተሰጥቶበታል በሚል መብታቸውን ያጡ ሰዎች በምን ይካሱ? ህጉ ሳይለወጥ ግን ሰበር ችሎቱ በሚሰጠው ተለዋዋጭ ውሳኔ ምክንያት የብዙዎች መብት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ ያለ መሆኑን ተረድተናል። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ድርሻ የሚወስደው የዳኞቹ አቅም ነው። JOIN በማድረግ ተጠቃሚ ይሁኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/ethiolawreviews https://t.me/ethiolawreview ✅ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩ ✅Share to families and friends
إظهار الكل...
የፌድራል_ጠቅላይ_ፍርድ_ቤት_ሰበር_ውሳኔ_የሰበር_መ_ቁጥር_191393_ሚያዚያ_30_ቀን_2015_.pdf5.36 KB
👍 1
Repost from MTU School of Law
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
  • File unavailable
Robert Allen Sendler Ethiopian Civil Procedure.pdf337.99 MB
Wondwosen on criminal procedure(1).pdf3.44 MB
A Handbook on Cr Law by Dejene G.docx6.23 KB
Ethiopian Tax Law New Text Book_.pdf2.54 MB
Principles of Ethiopian Criminal Law.pdf3.47 MB
Ethiopian Employment Law (1).pdf2.31 MB
Ethiopian Constitutional Law.pdf4.37 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.