cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopian Academic Staff Association

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
10 224
المشتركون
-424 ساعات
-127 أيام
-5330 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

03:05
Video unavailableShow in Telegram
#PmAbiy Speeches [ሊደመጥ የሚገባ] Share it on #TikTok #YouTube #Facebook and #Telegram #NoCopy-Right Issues in uploading @EUASAs
إظهار الكل...
💯 3👍 2😢 1
ጥያቄ????? 1. ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቃል ስለገቧቸው ጉዳይች በቅርቡ ምን አሉ? 2. ኢመማ እና በቅርቡ የተመረጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር አመራሮች በሁለት ወራት ምን ተግባራትን አከናወኑ ? ——————————————————————- የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ምላሽ እና እይታዉን በቅርቡ የምናቀርብ ይሆናል። @EUASAs
إظهار الكل...
🔥 15👍 7
ትዉስታ 1... ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የመኖሪያ ቤትን በሚመለከት ‹‹ጥሩ እንቅስቃሴ›› እንዳለ ተናገሩ ‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፣ ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን፤›› "የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መግለጻቸውን የማኅበሩ አመራሮች ተናገሩ፡፡ ማኅበሩ የዚህ ጥያቄ ምላሽ ውጤታማ ይሆናል ብሎ እንደሚያስብና ‹‹ጥሩ እንቅስቃሴ›› ላይ ነው ብሎ እንደሚያምን የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዮሐንስ (ዶ/ር) የተመራና ሰባት አባላትን የያዘ የማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ ቡድን በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በመገኘት፣ ለሰዓታት የፈጀ በመምህራንና በአገር ጉዳይ ውይይት አድርገው ነበር፡፡ ከማኅበሩ አመራሮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)፣ የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ እንዲሁም ከሁለት የጽሕፈት ቤታቸው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ነው፡፡ የመምህራኑን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ በሚመለከት የተወሰኑት ተጨባጭ ውሳኔዎች ምን እንደሆኑ ከሪፖርተር ለተነሳላቸው ጥያቄ ዮሐንስ (ዶ/ር) መልስ ሲሰጡ፣ እንደተለመደው አሠራር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን በሚሠሩበት አካባቢ የመኖሪያ ቦታ የማግኘት አሠራሩ የሚቀጥል ሆኖ፣ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን መኖሪያ ቤት በሚመለከት ግን ውይይት እየተደረገበትና ጥሩ ምላሽ ሊገኝ እንደሚችል እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን፣ ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን፤›› ሲሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላገኙት ምላሽ አስረድተዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከዚህ በፊት ሲያነሱት ስለነበረው የደመወዝ ጥያቄን በሚመለከት ማኅበሩ አንደኛው ይዞት የሄደው ጉዳይና የተወያየበት ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለደመወዝና መሰል ጥያቄዎች በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዳደረጉባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል፡፡ የደመወዝ ጭማሪውን በሚመለከት፣ የኑሮ ውድነትን በአጠቃላይ የማቅለል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው፣ ይህንንም ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ በውይይታቸው ላይ እንደተነሳ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ የማኅበሩ አመራሮችም ስለ ደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለማግኘት ጠብቀው እንዳልሄዱም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ማናችንም ደመወዝ በሚመለከት ‹ከዛሬ ጀምሮ ይህን ያህል ጨምረናል› የሚል መልስ አንጠብቅም፡፡ ችግሩ እንዳለና ትኩረት ተሰጥቶ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ነው ያነሳነው፤›› ሲሉ ዮሐንስ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የማኅበሩ አመራሮች ከመምህራን ጥያቄዎች በተጨማሪ የሙያ ጥያቄና የመምህርነት ሙያ ምንነትን በሚመለከት፣ የትምህርት ቤቶች አቅምና ግብዓት በሚመለከት፣ እንዲሁም ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠርንና የተለያዩ ጉዳዮችን አንስተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ‹‹በቶሎ ይሄ ነው የሚሆነው ወይም ያ ነው የሚሆነው ሳይሆን፣ ጊዜ ተወስዶ በአቅምና በፕሮግራም የሚሠራ ነው የሚሆነው፤›› ሲሉ የጥያቄዎቹ ምላሾች ስለሚወስዱት ጊዜ ተናግረዋል፡፡ የማኅበሩ አመራሮች ስለ ማኅበራቸውና ማኅበሩ ለማስገንባት ስላቀደው ሕንፃም ከተወያዩባቸው ጉዳዮች አንደኛ መሆኑን ሪፖርተር መረዳት ችሏል፡፡ @EUASAs
إظهار الكل...
👍 11
በ24/7/2016 ዓ/ም የተከናወነው ስብሰባ ሪፖርት "የዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር አመራሮች ከኢትዮጵያ መምህራን ማህበር(ኢመማ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ምክክር በማድረግ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበርን ለማጠናከር እንዲቻል አምስት አባላት ያሉት አስተባባሪ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቋቋመ በአዲስ አበባ ከተማ በ24/7/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ማዕከላዊ ፅ/ቤት በተካሄደው ምክክር ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ 18 የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር አመራሮች ተሳትፈዋል። የምክክሩ ዋነኛ አጀንዳዎች በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በተሟላ ሁኔታ የመምህራን ማህበርን ማጠናከር፣ እያጋጠሙ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው፦ ለምሣሌ የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በቶሎ ያለመከፈል፣ የትምህርት ጥራት ችግር እና የተማሪዎች የስነምግባር ችግር ( ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባጋጠመ የሲስተም ችግር ጥቂት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያሳዩት ያልተገባ ድርጊት) የሚጠቀሱ ናቸው። ከምንም በላይ የመምህራን ደሞዝ፣ መብትና የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በበቂ ሁኔታ ካለመኖር ጋር ተያይዞ የምሁራን ፍልሰት ...ወዘተ ነበሩ። የምክክር መድረኩን ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕረዚዳንት እና ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት የመሩት ሲሆን ከለይ በተገለፁት አጀንዳዎች ዙሪያ ከፍተኛ ዉይይት ተካሂዷል። ለችግሮች ሁሉ መፍትሄው መደራጀት፣ በሰላማዊ ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዛላቂ የሀገሪቱ ጥቅም ሲባል ምላሽ እንዲገኝ ከፍተኛ ሥራ መከናወን እንዳለበት መግባባት የተደረሰበት ሲሆን ተወያዮቹ ኢመማ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዉ ምስጋና አቅርበዋል። በመጨረሻም በሚቀጥለው ዓመት የማህበሩ ጠቅላላ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር አስተባባሪ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በመምረጥ ምክክሩ ተጠናቋል። በዚህም መሠረት፦ 1. ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ ከአ.አ.ዩ ፕሬዚዳንት 2.ዶ/ር ደመላሽ መንግሥቱ ከጅማ ዩ. ም/ፕሬዚዳንት 3.መ/ር ዉቤ እንግዳው ከባህርዳር ዮ. ፀሀፊ 4.መ/ር ሲሳይ በቀለ ከሰላሌ ዩ. አባል 5.መ/ር ፍቅረስላሴ አካሉ ከአሶሳ ዩ. አባል ናቸው። " ይህ ዉይይት ከተከናወነ ሁለት ወራትን አስቆጥሯል ። @EUASAs
إظهار الكل...
👍 12
01:22
Video unavailableShow in Telegram
ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ አሊ (ዶ/ር) ከጥር 16/2015 ዓ.ም በኋላ የገቡት ቃል ለህዝብ ይፋ ያደረጉበት ቀን ለትዉስታ ነው። የተደረገዉን ዉይይት ለሪፖርተር ገለጻ ያደረጉት ዮሃንስ በንቲ (ዶ/ር) ሲሆኑ ክወራት በፊት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳቶችን በአዲስ አበባ ስብሰባ ጠርተው ማወያየታቸው ይታወቃል። @EUASAs
إظهار الكل...
👍 2😁 1
ሰላም፣ ሰላም! እንዴት ሰነበታችሁ? መረጃዎች መቅረባቸውን ይቀጥላሉ። @EUASAs
إظهار الكل...
👍 12
ኢመማ የሐውልት ስብስብ ነውዮሐንስ ባንቴ ከ30 ዓመታት በላይ እራሱን በእራሱ በመሾም ለውጥ መካች በመሆን ዕድሜውን አስቆጥሯል። ከአጠቃላይና ከ2ኛ ደረጃ መ/ራን በሚዋጣው የአባልነት መዋጮ ላይ ከፍተኛውን % የያዘውን ፈሰስ ከተወሰኑ ዩኒቨርስቲ መ/ራን በስተቀር በመውሰድ 1. ት/ቱን ውጪ ሀገር 2ቱንም ተማረበት 2. ልጆቹ ከፍተኛ ተካፋይ ከሆኑ የአዳሪ ት/ቤቶች አስተማረበት፣ እያስተማረም ይገኛል። 3. አ/አ መሀል ከተማ ላይ 20 ሚሊዮን የጨረሰ ቤላ ቤት ሰራበት 4. የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራትን ተንሸራሽሮባታል 5. የዩኒቨርስቲ መምህራን እኔ አልወቅልም በማለት ሐምሌ 2011 ጄጄ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ በማድረግ ከሌሎች ያነሰ ክፍያ እንዲከፈላቸው አደረጎል 6. 75% በላይ የዩኒቨርስቲ መ/ራን በማህበር አልተደራጁም ። ሌሎችንም የተደራጁት እርስ በእርሳቸው ቀድሞ ከተደራጁት ልምድ በማስፋፋትና በመቀያየር የተደራጁ ሲሆን ጉዑዝ ኢመማ ምንም ተዋፅኦ የለውም።በስራ አድማ ወቅት ከህዳር 26_30 ቀን 2015 ዓ ም ይህ የፅንፈኞች አድማ ነው ኢመማን ዕወቅና አልሰጠውም በማለት መንግስታዊ ወገንተኝነቱን 100% ያሳየ ሐውልት ነው። ዛሬ ላይ ለኢመማ 36% ፈሰስ ክፈሉና አብርን እንሁን እያለ የወንዜ ሴራ አየሰራ ይገኛል። የሚከፍል ዩኒቨርስቲ መ/ማ ካለ መ/ራን ይጠይቃሉ? ለኛ ምን ታሪካዊ ለውጥ ለአመጣ ነው የሚከፈለው? አሳልፎ ሰለሸጠን? # ለ30 አመታት እንዴት ቀጠለ? እኛ የዩኒቨርስቲ መ/ራን የዩኒቨርስቲዎች መምህራን ማህበር (ዩ መማ) በአንቀጽ 39 መሰረት እናቋቁማለን ። የዩኒቨርስቲ መምህራን ማህበር ተጠሪነቱ ለመረጠው መምህራንና መ/ራን ብቻ ነው!!!
إظهار الكل...
👍 51💯 3 1
እጅግ በጣም በጣም የሚያሳዝነው ነገር አሮጌ የሴራ ፖለቲከኛ traditional policial thought ኢመማ በምንም ሁናቴ የዩኒቨርስቲ መ/ራንን አይወክልም ፣ በየትኛው ዘመናትም ወክሎ አያውቅም ። ሳይኖር ለሞተው ሙትቻ ስርዓት እኛን ከምድር ገዝግዘው እስከ መጨረሻ ለመጣል የሚሰራ አሮጌ አቆማዳ ነው። ይህንን አፋኝና ሴሬኛ ስርዓት ለመገርሰስ አሁን ላይ ጫፍ ደርሰናል። የተጠየቁ መሠረታዊ የዩኒቨርስቲ ጥያቄዎችን ካልመለሰ በመዋቅሩ የሚመራ ምሁር ነው። ህዝባችን ሀይላችን ነው። ዘረኛ ና ሰፈረኛ ያልሆንህ ምሁር ይህንን የኮስሞቲክስ ሲስተም ውስጥ የሚቃጀውን ስርዓት ለመገርሰስ ና ለራስህ ለመሆን ከጩኸት በመውጣት ዛሬም እንደ ትላንቱ ተነሳ ። ያሊያ የአንድ ሰሞን ጩኸት ውጤት የለውም አቀጣጥል
إظهار الكل...
👍 47 4🙏 1
"በኦሮሚያ ክልል መሬት ያልወሰዱ መምህራን ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው ታዘዘ" "በኦሮሚያ ክልል የመኖሪያ ቤት የሚሰሩበት መሬት ላልወሰዱ የክልሉ መምህራን ቦታ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ትእዛዝ መስጠታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። የክልሉ የትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት አድርጎ 8 የውሳኔ ሀሳቦችን ያስተላለፈ ሲሆን ከ8ቱ ነጥቦች አንዱ በከተማ ቤት መስሪያ ቦታ ላልወሰዱ መምህራን በአስቸኳይ ሊሰጣቸው ይገባል የሚል እንደሆነ ተጠቅሷል። ከዚህ ቀደም መምህራኑ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መመሪያ ወጥቶ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ከቆይታ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች እገዳ ተጥሎ እንደነበርና በክልሉ ት/ት ቢሮ ጥያቄ መሰረት ዳግም የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ለመምህራኑ  እንዲሰጣቸው ትእዛዝ መሰጠቱ ተጠቁሟል። ጉዳዩም ተፈፃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ለተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ትዕዛዝ መስጠቱም ተገልጿል። " ምንጭ @Ethiopian_Digital_Library @EUASAs
إظهار الكل...
👍 36 7
NEVER DEAL WITH THE CROOKS AND CRUELS.
إظهار الكل...
👍 3