cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር ግጥሞች

ይህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምህርትን የምንማማርበት Channel ነው !  ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇 ➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF ➲ስንክሳር ትምህርቶች ➲ መዝሙራትን ➲ ግጥሞች ➲ ፊልሞችን ➲ ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ"   ( 2ኛቆሮ -13 ፥ 5)👇 Group ገጽ👇👇 https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
9 118
المشتركون
-424 ساعات
+2557 أيام
+44630 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
የዘማሪ ዲያቆን ይገረም ፀጋዬ የአቀባበል እና ሽኝት መርኃ ግብር 👉አስክሬኑ ካለበት ከደቡብ አፍሪካ አርብ ከቀኑ 8:35 ይነሳል። 👉አርብ ማታ ከምሽቱ 3:00 ሰአት ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳል ። 👉አስክሬኑ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፣በአድባራት እና በገዳማት አስተዳዳሪዎች፣በመምህራን በዘማሪያን እና በወዳጆቹ ታጅቦ ቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል ይገባል። 👉ከለሊቱ 10:00 እስከ ከጠዋቱ 1:00 ሰአት በሊቃነ ጳጳሳት እየተመራ ጸሎት እና ስርአተ ቅዳሴ ይደረጋል። 👉ቅዳሜ ከጠዋቱ ከ1:00 ሰአት እስከ 2:30 የሽኝት መርኃ ግብር ይሆናል። 👉ከከጠዋቱ 3:00 ሰአት ጀምሮ ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ሆሳዕና በአገልጋይ አባቶች፣በመምህራን፣ዘማሪያን እና በወዳጅ ቤተሰቦቹ ታጅቦ ይሄዳል። 👉እሁድ ከቅዳሴ ቡኃላ ስርአተ ቀብሩ በሆሳዕና ደብረ ምህረት ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን ስርአተ ቀብሩ ይፈፀማል። ከአስተባባሪ ኮሚቴ
إظهار الكل...
በስመዓብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "በቀራንዮ የተከፈለውን ዋጋ ባሰብኩ ግዜ አንደበቴ ዝም ይል ዘንድ ልተወው አልችልም መንፈሴም እመሰክር ዘንድ ያነሳሳኛል።" ተናገር አለኝ መስክር ተናገር አለኝ ዘምር ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ ሰላም አውጥቶ ካስገባ ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ ሆሳዕና ልበል መድኃኒት ከፍ በልልኝ የኔ አባት ተጠምተኸ እኔ ረካሁ ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ አዝ_ እጆቹን እዩት በእምነት ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት በዚያ ታትሞ ውበቴ እየሱስ ለኔ ብርታቴ ከማንም በላይ ከምንም ለኔ ልዩ ነው ዘላለም ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ እኔስ በረታሁ በአምላኬ አዝ_ የእሾህ አክሊሉ በራሱ ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ ሞቴን ገድሎታል አባቴ ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ ሰው የመሆኔ ምስጢሩ የማይለወጥ ነው ፍቅሩ የገባኝ እውነት በምድር ላይ ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ አዝ_ ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ ተራበ ውዴ መድኃኔ ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ ወሰን የሌለው ምሕረቱ ለዚህ ደግነት ውለታ ምን ይከፈላል ለጌታ 👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
✞ የከበረ ስሙን ✞ የከበረ ሥሙን እንድታስከብር ጠላት ዲያብሎስን እንድታሳፍር አንተን የመረጠ እግዚአብሔር ይክበር የከሃዲን ትዕቢት ምንም ሳትፈራ የእግዚአብሔር ሰማዕት ተቀበልክ መከራ በመከራው ብዛት ደከመኝ ሳትል ጸንተህ ተጋደልክ ጊዮርጊስ ኃያል      አዝ= = = = = በፈጣሪ ሥም ድካም ያላገኘህ በብርቱ ተጋደልክ ጽናትን አሳየህ ገድልህን ልናገር ጊዮርጊስ አባቴ ጽናትህ አስቀናኝ እኔም በሃይማኖቴ       አዝ= = = = = የሄድክበት መንገድ ቢሆንም ጠባብ ልቤን ማሳረፊያ ሆኖኛል ወደብ መንፈሳዊ ጀግና ጠላት ያልገዛህ ሰይጣንን ተዋጋህ ጸናህ በእምነትህ      አዝ= = = = = ፈጥኖ የሚያልፈው የዚህ ዓለም ክብር ሊለየኝ አይችልም ከጌታዬ ፍቅር ብለህ የዘመትከው የጽድቅ ወታደር የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ምስክር       አዝ= = = = = በኃይሉ እግዚአብሔር ጸንቼ አምናለሁ ሁሉን ለፈጠረ አምላክ እሰግዳለሁ የሥቃይ መሳሪያው አያስፈራራኝም እኔ ክርስቲያን ነኝ ወደ ኋላ አልልም ብለህ ስትመሰክር ብቻህን ሆነህ በመንፈስቅዱስ ፍቅር በረታ ልብህ       አዝ= = = = = ጽናትህን አይቶ ዱድያኖስ ቢቆጣ በትዕቢት ተነሳ ሥጋህን ሊቀጣ የልዳው ሰማዕት ቅዱስ መምህር ገድልህን ልናገር እንዲሆነኝ ክብር        አዝ= = = = = መከራው ቢጸና ጊዮርጊስ ታግሶ ቀራንዮ ሄደ በልቡ ገሥግሶ እረዳቱን አውቆ ታምኖ የተሰማራ ጊዮርጊስ በጸሎቱ ፈጣሪውን ጠራ            መዝሙር|             ፋንቱ ወልዴ https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
ማመስገን ብቻ ነው ስራዬ መዘመር ተግባሬ አንተ እማ አትለይም ከአንደበቴ አንተ እማ አትነጥፍም ከከንፈሬ ውለታህ ነው ውዴ የሚቀሰቅሰኝ ማለዳ ማለዳ አዚመው የሚለኝ የቀመስኩህ ውዴ ያጣጣምኩት ፍቅር እንዴት ያስችለኛል በአፌ ሳልናገር                       ልናገር ያንተን ነገር ላምልክህ ላውጅህ በአዲስ መዝሙር አልጠግብህ ባወራህ አንተ እማ ልዩ ነህ    ኢየሱስ ልዩ ነህ ወዳጄ ልዩ ነህ                       ከቋንቋ ይልቃል ከቃላቴ በላይ ምድር አትወስነው አይከልለው ሰማይ የፍቅርህን መጠን አለካውምና እፁብ እፁብ ብዬ ላንሳልህ ምስጋና                       ማረፍ ሆኖልኛል ስምህን ስጠራ አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ በናቁኝ ሰዎች ፊት ያማረው ነገሬ ኢየሱስ ሆነህ ነው አዲሱ መዝሙሬ                        በሞገስ ያቆምከኝ በጠላት ከተማ አሜን ነው መዝሙሬ ስኖር ካንተ ጋራ ማጉረምረም አይኖርም ማመስገን ብቻ ነው ሲሞላም ሲጎድል ኢየሱስ ጌታ ነው 🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ━━━━━━━━━━━━ ዘማሪ ዘላለም ይንገስ https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
ትምክተ ዘመድነ /2/ ማርያም እምነ ማርያም ትምክተ ዘመድነ አዝ የድነታችን አርማ የነፃነታችን የህይወት መሠረት ነሽ ድንግል እናታችን አንቺ ለኛ ዘርን ባያስቀር እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶ ምድር ሁላችን በጠፋን ነበር /አዝ/ የአብርሀም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ የጌዲዮን ፀምር ለይቶ ያከበረሽ የኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ የዋህ ርግብ ከአበው ስር የተገኘሽ እፀሳቤት የህይወት ሀረግ ነሽ /አዝ/ አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይቺን አለም ሲቃኝ ንፅይት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንቺን ቢያገኝ ትህትናሽን ህይወትሽን ወዶ ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ አከበረሽ በፍፁም ተዋህዶ /አዝ/ የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም ከሀጢያት ከመርገም የዳነብሽ አለም አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በሲኦል ውስጥ ተግዘን የኖርን ድንግል ባንቺ ነፃነት አገኘን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
የለውም ደም ግባት አይተን እንድንወደው በሰው የተናቀ ሆነ የሕማም ሰው በወዳጆቹ ቤት የቆሰለው ቁስል ይታያል በእጆቹ በገነት መካከል የተመላለሱት ደምተዋል እግሮቹ ንጉስ ሆይ እያሉ ይዘብቱ ነበር የእሾህ አክሊል ደፍተው ሁሉን የሚያየውን የአማኑኤልን ዓይኑን በጨርቅ አስረው በሚሸልቱት ፊት እንደማይናገር እንደ የዋሁ በግ ዝም አለ እግዚአብሔር ለማህበረ አይሁድ አሳልፎ ሊሰጥ ጌታውን በብር ህዝቡ በሌለበት ምቹ ጊዜ ይሁዳ ይፈልግ ነበር ወርቅ ወይም ብር ነሐስ አትያዙ ብሎ እንዳላስተማረው ጨካኙ ይሁዳ የዘላለም ምግቡን በገንዘብ ቀየረው ሊቀ ካሕናቱ በካህናቱ ፊት ቀረበ ለፍርድ ንጹህ መስዋዕት ሆኖ መስዋዕት ተቀበለ ሞትን ሊያስወግድ ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ስቦት እስከ ሞት ደረሰ ወራሽ እንድንሆን ስጋውን ቆረሰ ደሙን አፈሰሰ ሁሉን የሚመግብ ሁሉን የሚያረካ ለሁሉ የሚያዝነው በወንበዴ መሐል በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ አላቸው ሐሞት ለመብሉ ሆምጣጤ ለጥሙ አይሁድ አቀረቡ የተጨነቀች ነፍስ የተራቆተች ነፍስ ነበር ጥም ርሃቡ ├─────────── │ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም │አልከፈተም፤ ለመታረድ │እንደሚነዳ ጠቦት፥ │በሸላቶቹም ፊት ዝም │እንደሚል በግ፥ እንዲሁ │አፉን አልከፈተም። │ ❏ ኢሳይያስ 53፥7 ├─────────── ├⊙ዲ/ን አቤል መክብብ ├─────────── https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
በስመዓብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን "በቀራንዮ የተከፈለውን ዋጋ ባሰብኩ ግዜ አንደበቴ ዝም ይል ዘንድ ልተወው አልችልም መንፈሴም እመሰክር ዘንድ ያነሳሳኛል።" ተናገር አለኝ መስክር ተናገር አለኝ ዘምር ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ ኑሮዬን ባርኮት ሕመሙ ሰላም አውጥቶ ካስገባ ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ ሆሳዕና ልበል መድኃኒት ከፍ በልልኝ የኔ አባት ተጠምተኸ እኔ ረካሁ ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ አዝ_ እጆቹን እዩት በእምነት ቆሰለ ሊሰጠኝ ሕይወት በዚያ ታትሞ ውበቴ እየሱስ ለኔ ብርታቴ ከማንም በላይ ከምንም ለኔ ልዩ ነው ዘላለም ሕይወቴን ለእርሱ አስማርኬ እኔስ በረታሁ በአምላኬ አዝ_ የእሾህ አክሊሉ በራሱ ለእኔ ቤዛ ነው ሞገሱ ሞቴን ገድሎታል አባቴ ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ ሰው የመሆኔ ምስጢሩ የማይለወጥ ነው ፍቅሩ የገባኝ እውነት በምድር ላይ ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ አዝ_ ክብሩን ለማወጅ ተነሳሁ ሲያድነኝ ከሞት እያየሁ ገመና ሸፋኝ ኪዳኔ ተራበ ውዴ መድኃኔ ይሄ ነው የቆመኝ በፊቱ ወሰን የሌለው ምሕረቱ ለዚህ ደግነት ውለታ ምን ይከፈላል ለጌታ 👉ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
🌼 እመኑ በእርሱ 🌼 እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደርጋል ጌታ    በረዶ አዝንቦ ጠላት እየመታ ውቅያኖስ ጥልቁን ፈጥኖ እያተነነ    ነገር ለወጠ ሁሉ በእርሱ ሆነ ፪                 አዝ እመኑ በርሱ.... ተራራው ነደደ እመኑ በርሱ.... ሸለቆው ታወከ እመኑ በርሱ.... ዝግባው ተሰባብሮ እመኑ በርሱ.... አለቱ ደቀቀ እመኑ በርሱ.... የአሕዛብ ጣኦታት እመኑ በርሱ.... በፊቱ ረገፉ እመኑ በርሱ.... በስሙ የታመኑ እመኑ በርሱ.... ወጀቡን ቀዘፎ                 አዝ  እመኑ በርሱ.... የማይነጋ ለሊት እመኑ በርሱ.... የማያልፍ ቀን የለም እመኑ በርሱ.... ሁሉም ይቻለዋል እመኑ በርሱ.... ጌታ መድሃኒአለም እመኑ በርሱ.... ፍቅር ነው ዘላለም እመኑ በርሱ.... ደግ አባት ለልጁ እመኑ በርሱ.... ሁሌ ተዘርግታ እመኑ በርሱ.... ትኖራለች እጁ                   አዝ እመኑ በርሱ..... ሞገድ የማይሰብረው እመኑ በርሱ..... ፅኑ መርከብ አለን እመኑ በርሱ.... አንፈራም አንሰጋም እመኑ በርሱ..... ከሱጋር እያለን እመኑ በርሱ..... ጠላት ተሸንፏል እመኑ በርሱ.... ሰይጣን አፍሯል ዛሬ እመኑ በርሱ ..... ውህኒው ይነዋወፅ እመኑ በርሱ.... በታላቅ ዝማሪ                  አዝ እመኑ በርሱ.... ባዶ ነው አይሰራም እመኑ በርሱ.... የጠላት ፉከራ እመኑ በርሱ.... የማይተወን ጌታ እመኑ በርሱ.... አለ ከኛ ጋራ እመኑ በርሱ.... እጅግ አትረፍርፎ እመኑ በርሱ.... ፀጋ ከበዛልን እመኑ በርሱ.... በሞት ጀርባ ቆመን እመኑ በርሱ.... ገና እንዘምራለን https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
✞ማር ሊቀ ሰማዕት✞ ማር ሊቀ ሰማዕት ገባሬ መንክር ጊዮርጊስ ኃያል(፪) የዱድያኖስ አምላክ - - ጊዮርጊስ ኃያል ያንን ደራጎን - - ጊዮርጊስ ኃያል አምላክ እንዳልሆነ - - ጊዮርጊስ ኃያል ገድለህ አሳየኸን - - ጊዮርጊስ ኃያል የቤሩት ኮከብ ነህ - - ጊዮርጊስ ኃያል የልዳ ፀሐይ - - ጊዮርጊስ ኃያል ለባሴ ሞገስ ነህ መክብበ ሰማዕት(፪) አዝ= = = = = መከራና ስቃይ - - ጊዮርጊስ ኃያል እያጸኑብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ትናገር ነበረ - - ጊዮርጊስ ኃያል ስለ አምላክህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሥጋህን ፈጭተው - - ጊዮርጊስ ኃያል ይድራስ ሲበትኑት - - ጊዮርጊስ ኃያል ዳግመኛ አስነሳህ አምላከ ምሕረት(፪) አዝ= = = = = አንገትህ ሲታረድ - - ጊዮርጊስ ኃያል ምድር ተናወጠች - - ጊዮርጊስ ኃያል ወተትና ውሃ - - ጊዮርጊስ ኃያል ደምም አፈለቀ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰብዐ ነገሥታት - - ጊዮርጊስ ኃያል እስኪደነቁብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰባት አክሊላትን ጌታ አቀዳጀህ(፪) አዝ= = = = = የዚህን ዓለም ጣዕም - - ጊዮርጊስ ኃያል ንቀኸው ጥቅሙን - - ጊዮርጊስ ኃያል በፍቅር ተቀበልክ - - ጊዮርጊስ ኃያል መራራ ሞትን - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰማይና ምድር - - ጊዮርጊስ ኃያል ሳርና ቅጠሉ - - ጊዮርጊስ ኃያል ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሉ(፪) https://t.me/qidus_Michael_abate12
إظهار الكل...
ጊዮርጊስ ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር ህያውን ነው በሰማይ ብፁዕ ነው በምድር ደራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና ከሞት አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና የሀዘን ማዕበል እንዳያንገላታኝ ታምር ሰሪው ሰማዕት ፈጥኖ አረጋጋኜ በእግዚአብሔር ጣዕም በፍቅሩተጠምዷል ይህን አለም ንቆ በክብር አጊጧል አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ እርሱ ለምጠራው ሲመሽም ሲነጋ ዋስ ጠበቃዬ ነው በነፍስም በስጋ ድንቅ የሚፈፅም ሀያል ሰማዕት ነው በቅድመ እግዚአብሔር ለእኔ የሚቆመው አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ የምስጋናን አውታር የታጠቀ ሰማዕት ስሙን ተሸክሞ የታመነ እስከሞት ሙታንን የሚያስነሳ ስልጣን ተቀብሏል በአባቱ መንግስት እንደ ፀሐይ ደምቋል አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ https://t.me/qidus_Michael_abate12 ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
إظهار الكل...