cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Subi Time™ ሱቢ ታይም

Addisababa, Ethiopia🇪🇹

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
26 012
المشتركون
-3224 ساعات
-3127 أيام
+3 10030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#የቃለሕይወት ቤተ ክርስቲያን “ ሃያ (20) ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችንም እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” - ቤተክርስቲያኗ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን፣ 40 በመቶ የሚሆን የኩሪፍቱ ማዕከል ይዞታዋን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ‘ በጉልበት ሊወስደው ነው ’ ስትል ከሰሞኑን በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቷ ይታወቃል። ጉዳዩ ከምን ደረሰ ? ቤተ ክርስቲያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠችው ቃል ፣ “ 20 ሄክታሩን አጥረውታል። መጋዘኖችን እያፈረሷቸው ነው። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንገደዳለን ” ብላለች። “ ዛሬ (ሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ/ም) ግቢ ውስጥ ገብተው በጉልበት አጥረውታል። መሳሪያ በያዙ ሰዎች እያስጠበቁት ነው ያሉት ” ስትል ገልጻለች። ይህንን ያሉት አንድ የቤተ ክርስቲያኗ አካል ፣ “ እኛም ዛሬ ለጠቅላይ ሚኒስቴሩም፣ ለኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮችም ደብዳቤ እየላክን ነው ” ብለዋል። “ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጠዋት ነው የላከነው፣ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳም ልከናል። ገና ምንም የሰጡት ምላሽ የለም ” ሲሉ አክለዋል። “ 40 በመቶ ገደማ ይዞታችን ነው ይወሰዳል የተባለው ” ያሉት እኝሁ አካል፣ “ አሁን ግማሹን አጥረዋል። ለሁለት ግለሰቦች ነው ይሰጣል የተባለው ” ነው ያሉት። በተጨማሪ ፣ በፍርድ ቤትም እግድ እንዲያወርድላቸው እንደጠየቁ፣ የሚጠብቁት ያስገቡትን ደብዳቤ ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጸዋል። “ አስቸኳይ ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ወደ መጥራት የምናመራ ይሆናል። በሰላማዊ መንገድ ድምፃችንን እናሰማለን። ሁል ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የምትቆመው ከሰላም ጎን ነው። የመረበሽ የማስረበሽ ዓላማ የላትም ” ብለዋል። ቅሬታ የቀረበበት የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። ሆኖም በቀጣይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia @subitime
إظهار الكل...
إظهار الكل...
Subi Time | WhatsApp Channel

Subi Time WhatsApp Channel. ለተለያዩ መረጃዎች. 0 followers

በኦሮሚያ ክልል፤ በጅማ ዞን፤ የቡ ከተማ በቅርቡ ከሰማይ እንደመጣ የተነገረለትን ድንጋይ በተመለከተ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሰጠው መረጃ ================= አስትሮይድ (Asteroid) በህዋ ውስጥ የሚገኙ ድንጋያማ አካላት ናቸው፡፡ በዋነኛነት የስርዓተ ጸሐይ አካል በመሆን በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው ስፍራ የመቀነት ቅርጽ (Asteroid Belt) ፈጥረው ጸሐይን ይዞራሉ፡፡ እነዚህ የሰማይ አካላት ግዙፍ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹም በመቶ ኪሎሜትሮች የሚቆጠር ዲያሜትር ያላቸው ናቸው፡፡ በአንፃሩ ሜትሮይትስ (Meteorites) ወደ ምድር ከባቢ አየር የገቡ የአስትሮይዶች ወይም ኮሜት ቁርጥራጮች ናቸው። በሌሊት ሰማይ ላይ የምናያቸው የብርሀን ጅራቶች ሜትሮይድ (Meteoroid)፣ ትንሽ የጠፈር አለት ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገባና ሲቃጠል የሚፈጠር ነው በመጠን የገዘፉ እና ጠንካራ የሆኑት አለቶች ከእሳታማው መተላለፊያ እና የመሬት ከባቢ አየር ተርፈው መሬት ላይ ይደርሳሉ። ሜትሮይት በምድር ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ እና ጉዳት በአንፃራዊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ በየዓመቱ ወደ ምድር ገጽ የሚወርዱትም በቁጥር ጥቂት ናቸው፡፡ አብዛኛው አካላቸው በምድር ከባቢ አየር ውስጥ ሲያልፍ ተቃጥሎ ስለሚያልቅ፤ የሚያደርሱት ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያደርገዋል፡ በኢኖቬሽና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስትቲዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪና ምርምር ማዕከል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የአስትሮይድ እንቅስቃሴን ለመከታተል (Asteroid Tracking) የሚያስችል የቴሌስኮፕ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡ @subitime
إظهار الكل...
01:05
Video unavailableShow in Telegram
ለበለጠ መረጃ ደምበል ሲቲ ሴንተር በ4ኛ ሊፍት 4ኛ ፎቅ ወይም በ 0911243280 ይደውሉ
إظهار الكل...
22.85 MB
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም ክትትል እና ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን አመሰገኑ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት የኮሪደር ልማት ስራዎቻችን የእያንዳንዱ ቀን እና ምሽት ስራ እየተገመገመ የሚስራ ስራ መሆኑን ገልጸው ፤ ልማቱ ለመረጠን እና ቃል ለገባንለት የከተማችን ነዋሪ የኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ፤ከዘመናዊነት ጋር የተቃኘ አሰራርን በመዘርጋት እና በማሳለጥ ለከተማችን የኢኮኖሚ እድገት ወሳኙን ሚና እንድንወጣ ያስቻለን ነዉ ብለዋል፡፡ በሂደቱም በምታደርጉት ተሳትፎ በአዲስ አበባ ፈጣን ለውጥ ውስጥ ታሪካዊ አሻራችሁን እያሳረፋችሁ መሆናችሁን ተረድታችሁ ስራውን በፍጥነት ብቻ ሳይሆን በጥራት እንድትሰሩ አበረታታችኋለሁ ብለዋል። በታሪክ ሂደት የከተማዋን የሥራ ባህል በቀየርንበት ፤ ቀንና ለሊት በስራችሁበት ጎን ለሥራ ጥራት የምትሰጡት ትኩረት እንዲሁ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዲችል መስራት አለብን ሲሉ አበክረው ተናግረዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቦሌ ሳይት በየምሽቱ በሥራ ላይ ለነበሩ ሰራተኞችን የእራት ግብዣ እያደረጉ ያሉትን የአካባቢውን ነዋሪዎች ምስጋናና ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።
إظهار الكل...
በከተማችን በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ፣ ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማችንን አረንጏዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ:: በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል:: ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀም እና በመንከባከብ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ለማሳሰብ እንወዳለን::
إظهار الكل...
ከሃገራችን የተለያዩ ከተሞች የመጡ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.