cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የህይወት ቅኔ🥀

🙏WELCOME TO OUR CHANNEL 🙏 In our channel we provide ✍️1መልካምና አስተማሪ የሆኑ ሀሳቦችን ማጋራት ✍️2 አንድነትን ማጠንከር ፍቅራችንን ያብዛው 🙏ሌሎችን ወደቻናሉ ውስጥ ማስገባት ቁም ነገር ያላቸውን ነገሮች ለሌሎች ሼር ማድረግ አንርሳ ያለንን እውቀት ማካፈል የሁል ግዜ ተግባራችን እናድርግ 📩For any comment, promotion @Lil_ezrael

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
22 143
المشتركون
-1624 ساعات
+1897 أيام
+3 01530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

💵ስልኳን በመጠቀም ብቻ ብር መስራት ይፈልጋሉ❓ እንግዲያውስ preton drop🤖 ይጫወቱ Coin ይሰብስቡ 🥳 START👇
إظهار الكل...
🎁 Start 🎁
🔑ዛሬ ምከር ምከር እያለኝ ነው 📌 የተረጋጋ ህይወት እንዲኖርህ… 📚 መፀሐፍትን አንብብ። 😶 ብዙ አታውራ (ማውራት ሲኖርብ ግን ዝም አትበል)። 🙇 ምክር እና አስተያየት ለመቀበል አትፍራ። 🙏 ለተደረገልህ ጥሩ ነገር አመስግን። ⛲ አዳዲስ ቦታዋች ሂድ። 😴 በቂ እንቅልፍ ተኛ። ❔ እማታውቀውን ጠይቅ። 💵  በየወሩ ከወር ገቢህ ላይ ቆጥብ (ትንሽም ብትሆን)። 💼  ዛሬ መስራት ያለብህን ዛሬውኑ ስራ። 4ተኛ ላይ የተናገርኩትን እንዳትረሱ‼️ @misteriouslife
إظهار الكل...
2👍 1👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
إظهار الكل...
💕መስከረም🌸
💕ጥቅምት🌸
💕ኅዳር🌸
💕ታህሳስ🌸
💕ጥር🌸
💕የካቲት🌸
💕መጋቢት🌸
💕ሚያዝያ🌸
💕ግንቦት🌸
💕ሰኔ🌸
💕ሀምሌ🌸
💕ነሀሴ🌸
💕🌸🌸ጷግሜ🌸🌸💕
إظهار الكل...
ሀ/ አሥራት
ለ/ ምፅዋት
ሐ/ መስጠት
መ/ ማካፈል
♥️የከንቲባው ልጅ♥️ 🥀ክፍል 39🥀 . . Notice :- እውነተኛ ታሪክ ነው! . . ━━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ አዘጋጅ እና አቅራቢ=-ከህይወት ቅኔ የቴሌግራም ቻናል ✍ . . የመጨረሻውን ክፍል እዲለቀቅ ላይክ ሼር በደንብ አርጉ ♥️♥️♥️ . . ትልና ድጋሜ ደግሞ ከተቀመጠችበት ተነስታ "በኛ ምክንያት ካለች ፡ በሷና በአባቴ ምክንያት ማለቷ ነው" አለችና ትንሽ እንደ ማሰብ ብላ "የኔ ህይወት እንደዚህ የመሆኑ ጉዳይ ላይ የአባቴም እጅ አለበት ለማለት ፈልጋ ብቻ እንዳይሆን ...?" አለች እኔ ላይ አፍጥጣ ። ለማረጋጋት ብዬ 'በቃ ተረጋጊ ፡ ለጊዜው ስለምንም ነገር በእርግጠኝነት ስለማናውቅ ምንም ማድረግ አንችልም' ስላት "የኔ ጌታ አንድ ነገር ብቻ ልለምንህ ፡ ከዚህ ቦታ ይዘህኝ ሂድ" ብላ ተማፀነችኝ ። ህይወት ለጊዜው ሆቴል ይዤ መረጋጋት ይኖርብኛል ብላኝ ነበር ። እኔ ግን ለብቻዋ እንድትሆን ስላልፈለኩኝ ከሷ ጋር ተቀራራቢ መልክ ካላት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ልጅ ID card ለምኜ ወደ ጊቢ ይዣት ገባሁ ። በር ላይ መታወቂያውን ልብ ብለው ስለማያዩት ማንም በማንም ሰው ID መግባት ይችላል ። በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ደንግጣ ነበር ። እንደ high school ጠባብ አይደለም ። በዛላይ ከ #15 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአንድ ጊቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዛታቸው ትንሽ ግር ይላል ። ሰዓቱም ወደ ምሽት እየተጠጋ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ ለእራት ከጊቢ እየወጣ ነበር ። ለተባበረችን ልጅ Id መልሼ ፡ እኛ እንደነገሩ ጊቢ ውስጥ ካለው ላውንጅ እራት በልተን ከዚህ በፊት ብቻዬን አዘውትሬ የምቀመጥባት ፣ ከማራኪዬ ጋርም ስልክ የማወራባት የነበረው ቦታ ወሰድኳት ። ቦታው ጨረቃን ወለል አድርጎ ከማሳየቱም በተጨማሪ ጭር ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ፣ በዛላይ ደግሞ እራስን ለማዳመጥ በጣም አመቺ ነው ። "ሳልማር ዩኒቨርሲቲ ገባሁ አይደል...?" አለችኝ ህይወት በተከፋ ድምፅ ። እንዳይሰማት ብዬ 'እኛ ተምረን ይመስልሻል እዚህ የደረስነው ...? ዩኒቨርስቲ ከገባ ውስጥ #10% አይሆንም ተምሮና በራሱ ጥረት እዚህ የገባው ። አብዛኛው ኮርጆ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ሳያስበው ነው እራሱን እዚህ ቦታ ላይ ያገኘው ። ዞረሽ ብትጠይቂያቸው "እኔ ለቤተሰቦቼ ብዬ ነው የምማረው ፡ እኔ ላይፉን ለማየት ነው የመጣሁት ፣ እኔ ከ famly ርቄ ነፃነቴን ለማግኘት ነው የመጣሁት ፣ ወዘተ ይሉሻል ። አላማ አለኝ ፣ ትምህርቴን ጠንክሬ ጨርሼ ለሀገሬና ለወገኔ እንደዚህ ላደርግ ነው የመጣሁት የሚልሽ በጣት የሚቆጠሩ ልጆች ብቻ ናቸው ። ታዲያ አንቺስ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለመግባትሽ ማመስገን እንጂ ማማረር ነበረብሽ ...?' አልኳት ። ደግሞም የምሬን ነው ። የከሰረ ትውልድ ይዛ ፣ ትርፍ ለማግኘት የምትሯሯጥ ሀገር ላይ ነን ። ይሄንን ትውልድ ማስተማር ያለብን physics ፣ chemistry ፣ biology ሳይሆን ትምህርት ምን እንደሆነ ፣ ምን ምን ጥቅም እንዳለው ፣ በወሬ ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር ማሳየት አለብን ። ከሁሉ ነገር መቅደም ያለበት ለትምህርት ያለን ፍቅርና ፍላጎት ነው ። እሱ ላይ ከተሰራ ሌላው ሁሉ በራሱ ጊዜ ይመጣል ። ይሄ ትውልድ ትምህርት የሚለውን ቃል እራሱ መስማት አይፈልግም ። በቃ ከሰይጣን በላይ ጠልቶታል ። ስለዚህ የጠላውን ነገር በግድ ተማር ከምንለው ፡ ለምን እንደጠላ መርምረን ፣ ምን ብናደርግ ደግሞ መውደድ እንደሚችል አስበን ወደ ቀልቡ መመለስ የተሻለ ይሆናል ። እንዲሁ ስለ ዩኒቨርስቲ እያወራን እያለ #01:30 ላይ የህይወት አባት እቤት ገብተው አጧት መሠለኝ ስልኳ ላይ ደወሉ ። አንስታው እንድሰማቸው ነው መሠለኝ loud speaker ላይ አደረገች ። "የኔ ህይወት ፡ የት ሄደሽ ነው ፣ ከቤት አጣውሽ እኮ ...?" ሲሏት "አያይ ብዙም አልራኩም ፡ ባሌንና ልጄን አይቼ ለመመለስ ብዬ ነው" አለቻቸው ፈርጠም ብላ ። "ስለምን ባልና ልጅ ነው የምታወሪው ልጄ ...?" አሏት መልሰው ። ህይወትም ትንሽ የፌዝ ሳቅ እንደመሳቅ አለችና "ለካ አልነገርኩህም ፡ ባል አለኝ እኮ ፣ ለዛውም አንድ ቆንጂዬ ህፃን ልጅ ከሶስት ዓመት በፊት ወልደናል" አለቻቸው ። ምንም መልስ የለም ፣ ፀጥ ፡ ሴኮንዱ ይቆጥራል ፡ አሁንም ግን ምንም አይነት መልስ ከህይወት አባት አልመጣም ። ህይወት ዝምታው ሲበዛባት "አየህ ፡ ምንም መልስ የለህም ። ቆይ ግን እስከመች ነበር እኔን ለመደበቅ ያሰብከው ፣ እስከዘላለም ...? ንገረኛ ...? ለማንኛውም ከኔጋር ከምታሳልፈው ቅዳሜና እሁድ ይልቅ ከነሱ ጋር የምታሳልፋቸው አምስት ቀናት የተሻሉ ስለሆኑ እነሱ ይሻሉሀል ። ቆይ ግን ልጅ አለኝ ፣ ሚስት አለኝ ብትል የምቃወምህ መስሎህ ነበር ...?" ስትላቸው "የኔ ልጅ እቤት ተመለሺና እናውራ" ብለው ይማፀኗት ጀመር ። "ሶስት ዓመት ሙሉ እኮ እቤት ነበርኩ ። ያኔ የት ነበርክ ። ለማንኛውም አትፈልገኝ ፣ የተሻለ ቦታ ላይ ነው ያለሁት ። መገናኘት ሲያስፈልገን እራሴው እቤት እመጣለሁ" ብላ ስልኩን ዘጋችው ።ምንድነው ሰው ሁሉ ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ መላክ የመሰለው ፣ እንዴት ነው ሰማዩ እንዲህ ተጠቅልሎ በእጄ የምይዘው መሀረብ ያከለው ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው ፡ መሬት መዞር ትታ በእፎይታ ያቆማት ፣ ምንድነው ጨረቃን ከሰማይ አውርዶ ምድር ያሳረፋት...? እያልኩ አስባለሁ ። ደግሞም አላቆምም መልሼ መላልሼ አሁንም አስባለሁ ። ማነው በመንገዴ ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ ፣ ማንስ ነው ግማሽ ልቤን ሸርፎ የወሰደው ፡ በትልቁ ቆርሶ ፣ መንገደኛው ሁሉ የተከፋ ፊቱን በማን ተነጠቀ ፣ ከጨፍጋጋ ፊት ላይ እንዲህ ያለ ብርሃን እንዴት ፈነጠቀ ፣ ሚሊዮን ህፃናት ከልብ በሚነሳ ስርቅርቅ ድምፃቸው ፡ የት ቢዘምሩ ነው ልቤ ሚሰማቸው ፣ እኮ በምን ምክንያት ይህ ሁሉ ተቀየረ ፣ ያልነበረ ወደነበረ እንዴት ተመለሰ ...? እያልኩ አስባለሁ ። አሁንም አስባለሁ ። ምንድነው እንደዚህ ፊቴን በብርሃን ፡ ከንፈሬን በውብ ሳቅ የሚያጥለቀልቀው ፣ እንዴትስ ነው ከልቤ ኮለል ያለ ሰላም በጠዋት የሚፈልቀው ፣ የጠሉኝን ሁሉ ድንገት መውደዴ ፡ መሬቱን ለቅቄ አየር ላይ መንጎዴ ፡ ምንድነው ምስጢሩ ፣ ቆይ ውስጤን ምን ነካው ...? አለም እንዲህ ጠቦ በእርምጃ የሚለካው ፣ ውቅያኖስ በእፍኝ ተጨልፎ የሚደርቅ ፣ ተራራው በክንዴ ተጎሽሞ የሚደቅ ፣ ኧረ ምን ተዓምር ነው እያልኩ አስባለሁ ። እኔ ደግሞ ቤሳቤስቲን ሳንቲም ኪሴ ሳይጨመር ፣ ዓመት የለበስኩት ልብሴ ሳይቀየር ፣ የዘውትር ጉርሴ ጣዕሙ ሳይነካ ፣ እኔነት እኔ ውስጥ ተቀይሯል ለካ ። እኮ በምን ምክንያት እኔ ተቀየርኩኝ ፣ እንዴት እኔ ነኝ ስል ፡ እኔ ሌላ ሆንኩኝ እያልኩ አስባለሁ ። ለካስ ከህይወት ጋር ስለሆንኩኝ ነው ። ያውም ከአባቷ ተለይታ ከድሬዳዋ ለቃ ከዩኒቨርስቲ የዚህን ዓመት ትምህርት ጨርሼ ስመለስ አብራኝ ወደ ትውልድ ቦታዬ ወደ ሙገር መጥታ ። አሜሪካ እንደማትሄድ ለአባቷ አሳውቃ በሰላምና በዕንባ ተለያይተዋል . ከ 150 ላይክ ቡኋላየመጨረሻው ክፍል 40 ይለቀቃል🌹             𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ አንብባችሁ ስጨርሱ ላይክ ለወዳጆ ሼር ያርጉ ♥️🫶
إظهار الكل...
👍 38 10🥰 2🎉 2
የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና፣ ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?? ▸ ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም፤ ተበድሎ ይቅር ማለት ግን ይበልጥ ይከብዳል። በድለን መርሳቱ ላይከብደን ይችላል፤ ተበድለን መርሳት መቻል ግን ጥንካሬን ይሻል። እየተጠሉ መውደድ፤ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል። ▸ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን። ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው። ▸ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። 🔹እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ?
إظهار الكل...
👍 6👏 2