cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopian Passport Service(ICS)

مشاركات الإعلانات
45 942
المشتركون
+10324 ساعات
+5467 أيام
+2 43230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የውጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡ የተገልጋዮች/ደንበኞች አያያዝ፣ የውጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች ልየታ ላይ ያተኮረ በስልጠናና ስርፀት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በአደማ ከተማ ካኔት ሆቴል ከግንቦት 10-11/2016 ዓ.ም መሰጠቱ  የተገለጸ። በስልጠናው መክፈቻ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የዉጭ ዜጎች ቁጥጥርና ቆንስላ ጉዳዮች  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ስልጠናው ተቋሙ የጀመረው የሪፎርም ሂደት የተቋሙ የሰው  ኃይል በአቅም መገንባት ቁልፍ አካል እንደሆነና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁ ሲሆን በተመሳሳይ  በተቋሙ የሚስተዋሉ የደምበኛ አያያዝ ክፍተት ከሞምላትና ሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች በመጠቀም በህገውጥ መንገድ አገር ውስጥ የሚንቀሳሱ የውጭ አገር ዜጎች በመቆጣጠርና ህጋዊ የውጭ ዜጎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ትልቅ ሚና እንደሚነረው ገልጿል። በመጨረሻም ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙት አቅም ወደ ተግባር በመለወጥ ተቋሙ የጀመረው የለውጥና ሪፎሩም ትግበራ የበኩላችው እንዲወጡ አሳስቧል። የስልጠናና ስርጸት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከተማ አለሙ   እንደ ተቋም የሚነሱብንን የደንበኞች/ተገልጋዮች አያያዝ ውስንነቶች በአግባቡ በመረዳትና ትርጉም በመስጠት የሚስተካከሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጣችን እርካታ እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ የበኩላችንን አስተዋጾ መወጣት እንዳለብን ተነገሩ። ስልጠናው የደምበኛ አያያዝ፣ የውጭ ዜጎችና ቆንስላ ጉዳዮች ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም ሃሰተኛና የተጭበረበሩ ሰነዶች ልየታ በሚሉ የስልጠና ሰነዶች ቀርበው  በመድረኩ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ስልጠናው ተጠናቋል። __ Telegram: https://t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
Ethiopian Passport Service(ICS)

ICS Facebook:-

https://www.facebook.com/EthiopianPassportServiceAgency

👍 96 22👏 6🔥 4😢 3👎 1
👍 9
Photo unavailableShow in Telegram
➖ፓስፖርት ኦላይን መመዝገብ ለምትፈልጉ ፦ 1. አዲስ ፓስፖርት ለመሙላት፦ - የልደት ካርድ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌ መታወቂያ 2. ፓስፖርት ለማሳደስ፦ - የፓስፖርት የመጀመሪያው ገጽ ፎቶ እና - አንድ ጉርድ ፎቶ 3. የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርት፦ - መጥፋቱን የሚያረጋግጥ የፖሊስ ጣቢያ ወረቀት፣ - ፓስፖርት ኮፒ/ የፓስፖርት መረጃ፣ - ጉርድ ፎቶ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌመታወቂያ 4. የተበላሸ/ የተቀደደ ፓስፖርት፦ - የፓስፖርቱ የመጀመሪያ ገጽ ፎቶ፣ - አንድ ጉርድ ፎቶ እና - መታወቂያ ማሳሰቢያ፦ የየትኛውም አይነት አገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ የምትፈልጉ ክፍያ ቅድሚያ ነው። ቀጠሮ ለማስያዝ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን 📥 @Passport_Agency ✅Share and Join✅ @EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
👍 131 30👎 22😁 5🥰 1🍓 1
106👍 93😭 54👏 16🎉 10🤩 8
Photo unavailableShow in Telegram
በ11/09/2016 ዓ.ም ፓስፓርት የምትወስዱ ደንበኞቻችን በ 7876 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የላክን ሲሆን እሁድ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-06:00 ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት We've sent a text message to our customers scheduled for passport collection on May 19, 2024. If you've received a text message from us via 7876, please visit our Gotera Office in Addis Ababa on Sunday, May 19, 2024. Our offices will be open from 9:00 AM to 12:00 PM for passport collection. Remember to bring a printout of your online application form when you visit us. Immigration And Citizenship Service __ Telegram: https://t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
👍 71 15👎 9
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የቻይና ብሔራዊ የኢምግሪሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ። የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅንጅት አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች በተለይም የኢሚግሬሽን ዘርፉን ከማዘመን፣ የድንበር ቁጥጥር ስርዓቶችን ማሻሻል እንዲሁም የአቅም ግንባታ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን በተለይ ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች (forged documents) መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ የቻይና ብሔራዊ የኢምግሬሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማቸው ጋብዘዋል። ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልዩ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተው ዘርፉን ማዘመንና ማሻሻል በዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናግረዋል። Telegram :- t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
👍 137 39🔥 15👎 14😁 8🥰 4
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባቀረባቸው 3 ረቂቅ አዋጆች እና 1 ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቷል። ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ የመጀመሪያው የኢሚግሬሽን አዋጅ ቁጥር 354/1995ን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን መሰረታዊ ከሆኑ መብቶች አንዱ የሆነውን የመዘዋወር ነፃነትን ለማስከበር፣ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶችን ለኢትዮጵያዊንና ለውጭ አገር ዜጎች በተሻለ ጥራትና ቅልጥፍና መስጠት እንዲቻል፣ የተቀናጀ የድንበር ቁጥጥር እና አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት የተሟላ የመንገደኛ ቅድመ ጉዞ መረጃ መያዝ አስፈላጊ በመሆኑ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ሁለተኛው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን በድጋሚ ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ተቋሙ በሚሰጠው አገልግሎት የዜጎችን ፍላጎት የሚያሟላ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት ስርዓት የሰፈነበት እንዲሆን፣ የአገራችንን ብሄራዊ ጥቅምና ደህንነት በሚገባ የሚያስጠብቅ ስልጣንና አደረጃጀት እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ሶስተኛው የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ሲሆን የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን በማሻሻል አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ግልጽና ውጤታማ ማድረግ፣ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መሰረታዊ የዜጎችን መብትና ነፃነት ለማክበርና ለማስከበር ሁሉን አቀፍ የምዝገባ ስርዓት መዘርጋት የሚገባ በመሆኑ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረቡት 3 ረቂቅ አዋጆች ላይ በሰፊው ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ አራተኛው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚያስከፍለውን ክፍያ ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ማስፋት፣ የአገልግሎቶቹን የጥራት ደረጃ ማሻሻል፣ ብሎም የተጠቃሚውን ማህበረሰብ አቅም ባገናዘበ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያወጡትን ወጪ መሸፈን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ ረቂቅ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ Telegram: https://t.me/EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
Ethiopian Passport Service(ICS)

ICS Facebook:-

https://www.facebook.com/EthiopianPassportServiceAgency

👍 118 32👎 5🥰 1
👍 16 5
Photo unavailableShow in Telegram
➖ፓስፖርት ኦላይን መመዝገብ ለምትፈልጉ ፦ 1. አዲስ ፓስፖርት ለመሙላት፦ - የልደት ካርድ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌ መታወቂያ 2. ፓስፖርት ለማሳደስ፦ - የፓስፖርት የመጀመሪያው ገጽ ፎቶ እና - አንድ ጉርድ ፎቶ 3. የጠፋ ወይም የተሰረቀ ፓስፖርት፦ - መጥፋቱን የሚያረጋግጥ የፖሊስ ጣቢያ ወረቀት፣ - ፓስፖርት ኮፒ/ የፓስፖርት መረጃ፣ - ጉርድ ፎቶ እና - ግዜው ያላለፈ የቀበሌመታወቂያ 4. የተበላሸ/ የተቀደደ ፓስፖርት፦ - የፓስፖርቱ የመጀመሪያ ገጽ ፎቶ፣ - አንድ ጉርድ ፎቶ እና - መታወቂያ ማሳሰቢያ፦ የየትኛውም አይነት አገልግሎት ቀጠሮ ማስያዝ የምትፈልጉ ክፍያ ቅድሚያ ነው። ቀጠሮ ለማስያዝ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን 📥 @Passport_Agency ✅Share and Join✅ @EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
👍 149 34🥰 24👎 17🔥 14
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ተወያዩ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ሁለቱ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው። በዚህም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ላይ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ በዘረጋው የጋራ የአሰራር ስርዓት የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለመሻገር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግልጽና የተቀላጠፈ አሰራር ስርዓትን በማስፈን የተጀመሩትን ዜጎችን በህጋዊ መንገድ  ለስራ ወደ ውጭ የመላክ ስራ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ አፈፃፀሙን ከፍ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅበት ሁኔታ ላይም ውይይት በማካሄድ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል:: Telegram: t.me/@EthiopianPassportServiceICSETH
إظهار الكل...
👍 169 29👏 13🤯 11🤔 4