ar
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

الذهاب إلى القناة على Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

إظهار المزيد
213
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
-430 أيام
أرشيف المشاركات
ሸኽ አልመጋሚስ እንዲህ ይላሉ "ወፍ ውሃ ሲጠጣ በአጠገቡ አትለፍ ታስደነግጡታላችሁ'ና። በዚህ የአላህን ውዴታ ፈልጉ።" የትኛው ኸይር ስራ መጥፎ ነገር እንደሚመልስ አይታወቅምና በኸይር ስራ ላይ እንበርታ!

አትመፃደቅ! አትማል! አታስረዝም! ከአቡ ዘር (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ثَلاثَةٌ لا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَومَ القِيامَةِ: المَنّا
አትመፃደቅ! አትማል! አታስረዝም! ከአቡ ዘር (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ثَلاثَةٌ لا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَومَ القِيامَةِ: المَنّانُ الذي لا يُعْطِي شيئًا إلَّا مَنَّهُ، والْمُنَفِّقُ سِلْعَتَهُ بالحَلِفِ الفاجِرِ، والْمُسْبِلُ إزارَهُ﴾ “ሶስት አይነት ሰዎች አላህ በዕለተ ትንሳዔ አያናግራቸውም። ተመፃዳቂ! አንድን ነገር አይሰጥም ከሰጠም ለመመፃደቅ ቢሆን እንጂ። እቃውን ሲሸጥ በውሸት መሃላ የሚሸጥና ልብሱን ከቁርጭምጭሚት አሳልፎ የሚለብስ ናቸው።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 106

የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ፣ ለንግስህናህ ተጋሪ የሌለህ ብቸኛው ጌታችን ሆይ የእድሜ በረካን ለግሰን::ለአካላችን ጤንነትን ወፍቀን፣ እርዝቃችንንም ሰፊ አድርግልን:: ጌታችን ሆይ በምንሞትበት ወቅት ለምላሳችን ሸሃዳን ግጠመን:: ከሞትንም ቡሃላ ምህረትን ለግሰን:: በምርመራህ ሰዓትም አውፍ. በለን:: አላህ ሆይ ለኛም፣ለወላጆቻችንም ለመላው ሙስሊም ከጀነትህ ከፊርዶስ የላይኛውን ክፍል እንድትለግሰን እንናማፀንሃለን:: አሚን

ይህ ያልፋል ይሁን⁉️ 🇵🇸 እህት ወንድሞቻችን መልካም የሆኑ ጊዜያቶች ያሳልፋሉ ይሁን⁉️ የአላህ.......!
+3
ይህ ያልፋል ይሁን⁉️ 🇵🇸 እህት ወንድሞቻችን መልካም የሆኑ ጊዜያቶች ያሳልፋሉ ይሁን⁉️ የአላህ.......!

The Palestinian Ministry of Health says a total of 107 individuals were killed and 176 others injured by Israeli occupation f
The Palestinian Ministry of Health says a total of 107 individuals were killed and 176 others injured by Israeli occupation forces in the Gaza Strip during the last 24 hours.

ረመዿን 15 بكاء الشيخ سعود الشريم في موعظة مؤثرة من خطبة الجمعة اليوم ١٤ رمضان ١٤٤٣هـ ከዛሬ 2 ዓመት በፊት በ መስጅደል ሀረም የተደረገ ገሳጭ ምክር .................................................. እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩት ይኸው የረመዷን ወራችሁ ተጋምሷል ልክ ወሩ ሲገባ እንደዛ እንኳን አደረሳችሁ እንዳላልን አሁን ላይ ግማሹን አጥተነዋል ቀሪው ቀንም እንደ መጀመሪያዎቹ በቀስታ የሚጓዙ አይደሉም። ዛሬ ላይ ቀዳሚ ሰው ማለት ስራውን ያስቀደመ ሰው ነው ተቅዋው ወደ ፈጣሪው የወሰደችው ሰው ነው ወደ እሱ የሚወስድ  ዘርም ፣ስልጣንም ገንዘብም አይደለም ። አላህ እንዲህ ይላል لَن تَنفَعَكُمْ أَرْحَامُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ ۚ يَوْمَ الْقِيَامَةِ يَفْصِلُ بَيْنَكُمْ ۚ ዘመዶቻችሁም፣ ልጆቻችሁም በትንሣኤ ቀን አይጠቅሟችሁም፤ (አላህ) በመካከላችሁ ይለያል፡፡ ተቻኮሉ! ፍጠኑ! ይህ ወር እኮ በፍጥነት አላፊ ነው ያለፈው ደግሞ መቼም አይመለስም የቀረው ደግሞ በፍጥነት የሚያፈተልክ ነው። .............................................. አደራ በደንብ እንጠቀምበት ወሏሂ ይህን ዕድል ማግኘት በራሱ ትልቅ ዕድለኝነት ነው ። ቀሪ ቀኖቹን በመልካም ስራዎች ላይ እንበርታ! 🔈 ሸይኽ ሱዑድ ሹረይም

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙 =============== 🖌 በኢልያስ አሕመድ በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።               ››››› ‹‹‹‹‹ በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦ 1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው። ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል። ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው። 2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል። በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦ 👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!) 👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣ 👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣ 👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣ እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው። 📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦ «“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው። በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦ እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ። በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ.... “ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።» [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)] 📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦ «ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)] 📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦ «ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)] ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል። አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ። 📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ «የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)] 👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነውበተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ! ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦ ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም። 📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?» እርሳቸውም፦ «مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا» = «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!» 📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል። «ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል! [“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣ “አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)] 👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው። ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው። ረመዳን 15/1445 ____ @ustazilyas

የጎዳና ላይ እፍጣርን በተመለከተ ፈትዋ (የሸሪዓ ብይን ተሰጠ):: 《《《《《《●》》》》》》 የጎዳና ላይ እፍጣር በሸሪዓ እንደለለና በአንዳንድ ሀገሮች ላይ ተጀምረው ዛሬ ልማድ ሆኖ ማስቆም እንዳልተቻለ የሀገራችንና የምስራቅ አፍሪካ ሙቲ የሆኑት ታላቁ ዓሊም ዶ/ር ጀይላን ከድር ገመዳ የፈትዋ ብይን ሰጡ:: ዶ/ሩ አክለውም ሽሪዓ ውስጥ የለለ ብደዓ (እስልምና ውስጥ አዲስ ፈጠራ) መሆኑን በማስገንዘብ ነገ ማስቆም ወደማይችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት በአስቾካይ መቆም እንዳለበት አሳስቧል:: ========***========= በሌላ በኩል ታላቁ ዓሊም ዶ/ር ሸህ ሙሐመድ ሓሚዲንም በተመሳሳይ አቋም በመያዝ ታላቁ የጎዳና ላይ እፍጣር ብደዓ ከመሆኑ በተጨማሪ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይመዝናል በማለት ማስቆሙ የተሻለ መሆኑን አስረድቷል:: የጋራ እፍጣሮችን በየመስጅዱ ደጅ ላይ በማድረግ በጋራ በማፍጠር እና አቅም የለላቸውንም ማስፈጠር ይቻላል ብለዋል:: ======*======= ሁለቱም ተላላቅ ዶ/ሮች አብዮት አደባባይን በተመለከተ ሜዳው የሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ሙስሊሙ እስላማዊ ትዕይንቶችን ከእፍጣር ውጭ በሌሎች ፕሮግራሞች ማሳየት ይቻላል ብሏል:: አመሻሽ ላይ በጨለማ ጎዳና ላይ እፍጣር ከማድረግ ወጣ ብለን በቀን በየአመቱ ሀገረአቀፍ የረመዳን አቀባበል እና የደዓዋ ፕሮግራም በአብዬት አደባባይ ማካሄድ ይቻላል በማለት አቅጣጫ ሰጥተዋል:: የጎዳና ላይ እፍጣርን በሸሪዓ ብይን ስከለከል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ታሳቢ በማድረግ ነው:: 1. የጎዳና ላይ እፍጣር ፕሮግራሙ የሚካሄደው አመሻሽ ላይ በመሆኑ ከእፍጣር በኃላ ወንዶች እና ሴቶች በጨለማ በመቀላቀላቸው በተለይ ከቤተሰብ ክትትል ዉጭ ሆኖ ከሁሉም አቅጣጫ ከሩቅ ወደ አደባባይ የተመሙ ወጣቶች መካከል ጨለማን ተገን አድርገው ብዙ ችግሮች ልፈጠሩ ይችላሉ ተብሏል:: 2. በአደባባዩ እፍጣር ላይ ባለፈው አመት የተከሰተው ሴት እህቶቻችን ላይ በዱርዬዎች የደረሰው ልብሶቻቸውን በምግብ: በእርጎ: በወተት: በለስላሳና በመሳሰሉት ለእፍጣር በቀረቡ ምግቦች እና መጠጦች የለበሱትን ሂጃቦቻቸውን አውቀው በማጨመላለቅ ተበለሻሽተውባቸው ክብራቸው ተነክቷል:: ካደባባዩ ከወጡ በኃላም ጨለማን ተገን አድርገው ጎዳናዎች ላይ በየመንገዱ ትንኮሳዎች እና መተናኮሎች ተስተውሏል:: 3. እንደሚታወቀው በአገራችን አንፃራዊ የፀጥታ ችግሮች ይከሰታሉ:: ጨለማን ተገን አድርገው በሁከት ፈጣሪዎች የፀጥታ ችግር ካጋጠመ በፀጥታ አስከባሪዎች ለመቆጣጠር ያስቸግራል:: 4. እስካሁን የተካሄደው የአብዮት አደባበባይ የጎዳና ላይ እፍጣር ፕሮግራሞች አብዛኛው በመደበኛ የስራ ቀናት ላይ በመሆኑ ከቀኑ 5:00 ጀምሮ መንገዶችን በማዘጋጋት ሰፊ ህብረተሰብን መተላለፊያ መንገድ በማሳጣት ከፍተኛ የትራፍክ መጨናነቅን አስከትሏል:: ህብረተሰብን ማስቸገር እና ጎዳናዎችን ማዘጋጋት ከሙስሊም በተለይ ከፆመኛ አይጠበቅም:: 5. ለዚህ እፍጣር ፕሮግራም ላይ ያለ በቂ ቁጥጥር እና ክትትል የሚባክኑ ንብረቶች እና የሰው ጉልበት ከፍተኛ በመሆኑ እንደማህበረሰብ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይመዝናል:: ~¤¤¤~ በመጨረሻም በጨለማ ጎዳና ላይ እፍጣር ከማድረግ ወደየመስጅዶች መልሰን አቅም ከለላቸው ከደሃ ማህበረሰብ ጋር ብናፈጥር የተሻለ መሆኑን ዑለማዎች አስረድቷል:: በየአመቱ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጭ ሆኖ በእረፍት ቀን ላይ አገር አቀፍ የረመዳን አቀባበል እና ሰፊ የደዓዋ ፕሮግራም በአብዮት አደባባይ ላይ ማካሄድ እንደሚቻል አስገንዝበዋል:: መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇 https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Israeli occupation forces are preventing ambulances from reaching injured Palestinians shot by their fire in Beit Furik town,
Israeli occupation forces are preventing ambulances from reaching injured Palestinians shot by their fire in Beit Furik town, east of Nablus.

BREAKING: Israeli drones target a vehicle with missiles near the village of Souairi in east-central Lebanon.
BREAKING: Israeli drones target a vehicle with missiles near the village of Souairi in east-central Lebanon.

እስኪ ሁላችሁም አዳምጡት🥺 ወሏሂ በጣም ከበድ ነው። አዳምጡት!!! ©ሁዛፈህ ኡመር...ኢስላማዊ ምክር በ ቴሌግራም t.me//huzafeh_umer በ ቲክ ቶክ tiktok.com/@huzafeh_umer ሼር በማድረግ አዳርሱ

ረመዿን 14 🌙 *الحكمة من الصوم*🌙 የፆም ጥበቡ ከፆም ጥበብ ውስጥ አንድ ሰው አላህ ፈቅዶለት ከነበሩት ነገራቶች ብቻ ሳይሆን ክልክል ከተደረገበት ነገራቶችም መፆም እንደሚገባው ነው ለዚህም ማስረጃው እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ ከናንተ በፊት በነበሩት ላይ ፆም እንደተደነገገ ሁሉ በናንተ ላይም ተደነገገ የሚለው የጌታችን ንግግር ነው። ለምንድነው የተደነገገው? እሱን ልትፈሩት ይከጀላልና ለዚህ ነው እንጂ እንድትራቡ ወይም እንድትጠሙ አይደለም፤  አላህን እንድትፈሩት የሚከጀለው ደግሞ ግድ ያደረገባቹን በመተግበር እና እርም ያደረገባቹን ነገሮች በመተው ነው። የአላህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ይላሉ የሐሰት ንግግርን ፣ በሐሰት መስራትን እንዲሁም መሀይምነትን (የመሐይማንን ተግባር) ያልተወ ሰው ምግቡንና መጠጡን ከመተዉ አላህ ጉዳይ የለውም፡፡›› አላህ በዋናነት ከእኛ የሚፈልገው ተፈቅደው የነበሩትን ምግብና መጠጥ እንድንተው አይደለም ይልቁንም  ሐሰትን በሐሰት መስራትን እና የመሃይም ስራዎችን ከመስራት እንድንቆጠብ ነው ሐሰት ንግግር ሲባል ክልክል የሆኑ ማንኛውም ንግግሮችን ያካታል የውሸት ንግግሮች ክልክል ናቸው ። ወንድሜ ሆይ! ከሙናፊቆች ጋር መመሳሰል ትፈልጋለህን? 🔈 ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሠይሚን አላህ ይዘንላቸውና

► ስለ ስቃይና መከራ ባሰብኩ ሰዓት፣ ► ስለ ቤተሰብ የጅምላ ጭፍጨፋ ባሰብኩ ቁጥር፣ ► ስለ መስጂድ መውደም ባሰብኩ ቁጥር፣ ► ስለ ህፃናት መግፍ መገደልና መጨፍጨፍ ባሰብኩ ቁጥር፣ ► ስለ « ይችህ እናቴ ናት፣ ፀጉሯን አውቀዋለሁ » አይነት በቦምብና በሚሳኤል የሰውነት መበጣጠስ ባሰብኩ ቁጥር...... ትዝ የሚሉኝ ፈለስጢናዊያን ናቸው‼️ ⭕️ ........የሚገርመው ነገር ይህ ሁሉ በደልና ስቆቃ እየተፈፀመባቸው እነሱ ግን ፈገግ እያሉ ነው‼️ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ► Whenever I think about pain and suffering, ► Every time I think about the family massacre, ► Every time I think about destroying the mosque, ► Every time I think about the killing and killing of children, ► Every time I think about "this is my mother, I know her hair" like being torn apart by bombs and missiles...... I remember the Palestinians‼️ ⭕️ ........ the surprising thing;  All this injustice and misery is being done to them, but they are smiling ‼️ Rashad Ibn Muzamil Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil