cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ጥበብ በሰንበት ትምህርት ቤት

በፌስቡክ ግሩፕ https://facebook.com/groups/555256809815508/ በፌስቡክ ፔጅ https://www.facebook.com/profile.php?id=100090253324883 በቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/senbet_tmhrt_bet

إظهار المزيد
Ethiopia11 036Amharic9 240الفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
198
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

#የካቲት_፳፫ #አድዋ በሚያቃጥል ንፋስ ወበቅ በሚበዛው         ሽው ብትን ሲል ፊትን በሚገርፈው አሸዋ ደባልቆ አይን በሚያጠፋው      የትሳለ ድንጋይ  እግር በሚቆርጠው ጫማ በሌለበት መንገድ ሳይሰራ       እያቆራረጡ ጫካ እና ተራራ ምንም ሳይደክማቸው       ተቋጥሮ ወኒያቸው እልክ ተናንቋቸው        በዚህ ውስጥም ሆነው ተስፋ ባለመቁረጥ እጅግ ተፈትነው ቆዳቸውም ቢላጥ አላማ ነውና ማሸነፍ የነሱ       አርደው አጋደሙት እነ ገድል ሱሱ። እሱም ፈረጠጠ እግሩ ወደመራው        እግሬ አውጭኝም አለ ደብቁኝ ከጉሪያው ጥቁር ድል አረገ  ሀበሻው ፎከረ      አደዋ ሰማዩኣ በሀሴት ታጠረ ነጭ ተሸነፈ      ለአለም ተለፈፈ የመስፋፋት ህልሙ በወኔ ተገታ      በአርበኛው ሀበሻ አናቱን ተመታ አለም ደንገጠች     በፍራት ተናጠች ታሪክ ተቀየረ      ነጭ አቀረቀረ ጥቁር ቀና ብሎ ወንድነት አሳየ       እያጋላበጠ እያንከባለለ ነጭን አበራየ።       ቪቫ አጼ ምኒልክ ሮም ተናወጠች       እምየ ጣይቱ ጀግና ሴት ተባለች በጥቁር ድል ብስራት ኢትዮጵያን አስጠራች ። @tibebezesenbet @tibebezesenbet
إظهار الكل...
ሁለተኛው ሰውዬ ደግሞ «እዚያ ከፍተኛ የጫማ ገበያ አለ፤ ምክንያቱም አንድም ጫማ ያለው ሰው የለምና´ ብሎ ሪፖርት አቀረበ፡፡ አያችሁ ሁለቱም በአንድ እውነታ ላይ ተስማምተዋል፡፡ የሄዱበት ቦታ ጫማ ያደረገ ሰው የለም፡፡ በመርሐቸው ግን ተለየይተዋል፡፡ አንዱ እንደ ችግር የቆጠረውን ሌላው እንደ ዕድል ቆጥሮታል፡፡ ስለዚህ በሕይወታችሁ ውስጥ አምነትና መርሕ ካለ ሕይወትን ሙሉ ያደርጋታል፡፡ ያ ማለት ግን ለሌሎች ነገሮች ቦታ አይኖራችሁም ማለት አይደለም፡፡ አሉ ሌሎች ነገሮች፡፡ ትምህርት፣ ሥራ፣ ዕድገት፣ ትዳር፣ ልጆች፣ ሌሎችም ነገሮች፡፡ በእምነትና በመርሕ አስቀድሞ ሕይወቱ የተሞላ ሰው ለእነዚህ ነገሮች በቂ ቦታ አለው፡፡ ሳይጎድ ልበት መሙላት የሚችል ቦታ አለው፡፡ የዚያኛውን ቦታ ሳያስለቅቅ ነገር ግን ለእነዚህም ቦታ ይኖረዋል፡፡ አለ ደግሞ ሦስተኛው ነገር፡፡ ስኳሩ፡፡ እንደምታውቁት ዛሬ ዛሬ ብዙ ሰዎች ስኳር እየተው ነው፡፡ ካልሆነም ደግሞ እየቀነሱ ነው፡፡ በሕይወታችንም እንደ ስኳር ያሉ ነገሮች አሉ፡፡ ለእነርሱም ቢሆን ግን ሕይወታችን ቦታ አላት፡፡ ግን መጀመርያ ድንጋዩና የከበሩት ድንጋዮች ከገቡ ነው፡፡ አስቀድማችሁ ስኳሩን ቦታ ካስያዛችሁት ለሌላ ነገር የሚሆን ቦታ አታገኙም፡፡እንዲህ ያደረጉ ሰዎች አሉ፡፡ መጀመርያ ሕይወታቸውን በትርኪ ምርኪ ነገር የሞሉ፡፡ በመዝናናት፤ በክብርና ዝና፤ በቧልትና ቀልድ፤ የሞሉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በኋላ ለሌሎች የሚሆኑ ቦታ አያገኙም፡፡ ካልሆነም የግድ የእነዚያን ቦታ ማስለቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የገባን ማስወጣት ደግሞ ቀላል አይደለም፡፡ አንዳንዶች ከትዳር በፊት የለመዱትን ስኳር በትዳር ወቅት ማስለቀቅ አቅቷቸው መከራ ያያሉ፡፡ አንዳንዶች ከሥልጣን በፊት የለመዱትን ስኳር መላቀቅ አቅቷቸው ለመርሕና እምነት ቦታ አጥተዋል፡፡ አንዳንዶች ከትምህርት በፊት የለመዱትን ክፉ ስኳር በዕውቀት መተካት አቅቷቸው ይሰቃያሉ፡፡ ለመሆኑ በገንዘብ፣ በሥልጣን፣ በቆንጆ ወንዶችና ሴቶች፣ በግብዣና በስጦታ በቀላ የሚደለሉ ሰዎች አላያችሁም? ለምን ይመስላችኋል? እነዚህ ሰዎች ሕይወታቸው በስኳሩ ብቻ የተሞላ ስለሆነ ነው፡፡ በሕይወታቸው ውስጥ ምንም ዓይነት ጠንካራ ዐለት የለም፡፡ ምንም ዓይነት የከበረ ድንጋይ አልገባም፡፡ እነርሱ በስኳር ብቻ የተሞሉ ናቸው፡፡ ያንን ስኳር ደግሞ ማሟሟት ቀላል ነው፡፡ ዐለቱ ግን አይሟሟም፡፡ የለመዱትን ስኳር እያላሱ እንደፈለጉ እምነታቸውንም ሆነ አመለካከታቸውን መቀያየር ቀላል ነው፡፡ አያችሁ በዐለት የተሞሉ ሰዎች ውስጥ የተወሰነ ስኳር መክተት የምትችሉትን ያህል በስኳር የተሞሉ ሰዎች ውስጥ ግን የተወሰነ ዐለት መክተት አትችሉም፡፡ እናም እነዚህ ሰዎች ለሕይወት ርባና ያለው ምንም ዓይነት ፋይዳ የላቸውም፡፡ እነርሱ ገንዘብ እስከተከፈላቸው ድረስ ለየትኛውም ቡድን ይጫወታሉ፡፡ ዛሬ ገጥመውት ከእጁ ዋንጫ የነጠቁትን ቡድን ነገ ደግሞ አብረውት ሆነው ዋንጫውን ለማንሳት ዝግጁ ናቸው፡፡ ሥልጣንና ክብር እስካገኙ ድረስ ከመላእክት ወገን ወርደው ከሰይጣን ጋር ለመሰለፍ አይዳግታቸውም፡፡ ለእነዚህ ሰዎች በሕይወታቸው ሜዳ ላይ ምንም ዐይነት መሥመር የላቸውም፡፡ አረንጓዴም፤ ቢጫም ሆነ ቀይ መሥመር የላቸውም፡፡ ሁሉንም ይሻገሩታል፡፡ «ከዚህ በመለስ ከመጣማ ሕይወቴ ያልፋል እንጂ፤´ የሚሉት ነገር የለም፡፡ አካባቢያቸውን ለመለወጥ ሳይሆን እንደ እስስት ከአካባቢያቸው ጋር ለመለወጥ ዝግጁ ናቸው፡፡ እንደ ስኳር ለመድረቅም፤ ለመሟሟትም ይችላሉና፡፡ ሰው ሲፈጠር ለሁለቱ ነገሮች የተፈጠረ መሆኑን ተፈጥሮው ይነግረናል፡፡ አእምሮ፣ ልቡናና ኅሊና እንዲኖረን የተደረገው ለምን ይመስላችኋል? አእምሮ ለማወቂያ ነው፡፡ ዓለምን የምናውቅበት፡፡ በአምስቱ የስሜት ሕዋሳት በኩል በሚገባው ዕውቀት የምንረዳበት፡፡ ኅሊናስ? ኅሊናማ የሕይወት የምትባለው መርከብ ካፒቴኗ ነው፡፡ ሕይወት በዚህ ካፒቴን ካልተመራች በማዕበል መካከል እንደተተወች የነጋዴዎች መርከብ ትሆናለች፡፡ ኅሊና የተቀመጠው ሕይወት በመርሕ እንድትመራ ነው፡፡ አንድ ሰው እሺም እምቢም የሚላቸው፤ የሚያከብራቸውና የሚሞትላቸው፤ የሚታገልላቸውና፤ መሥዋዕትነት የሚከፍልላቸው መርሖች ከሌሉት እርሱ ሰው ሳይሆን ካልዕ ፍጥረት ነው ማለት ነው፡፡ ልቡናስ ምንድን ነው? ልቡና የእምነት ቦታ ነው። የሚያበረታና የሚያጠነክር፤ ኃይልና ብርታት የሚሆን፤ የማይታዩትን ነገሮች ልናይበት የምንችል፤ ከሞት ወዲያ ዓላማ እንዲኖረን የሚያደርግ፤ ሞትን ሊያሸንፍ የሚችል እምነት፡፡ እነዚህ ናቸው ዐለቶቹ፡፡ እነዚህም ናቸው የከበሩት ድንጋዮቹ፡፡ ከእነዚህ በመለስ ያለው ቢመጣ የማይጨምር፤ ቢቀርም የማያጎድል ስኳር ነው፡፡ ችግሩ አስቀድሞ ስኳሩ ከሞላ ለሌሎች ነገሮች ቦታ የለውም፡፡ @tibebezesenbet @tibebezesenbet
إظهار الكل...
#ወግ✞ ስኳር አንድ መምህር ሁለት ትልልቅ የመስተዋት ገንቦዎች ይዞ ወደ ክፍል መጣ፡፡ ሦስት ተማሪዎች ደግሞ በካርቶን ሌሎች ሦስት ነገሮችን ተሸክመውለታል፡፡ ተማሪዎቹ ከመቀመጫ ተነሥተው ተቀበሉት፡፡ መምህሩ ትልልቁን የመስተዋት ገንቦዎች በተማሪዎቹ ፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ ሦስቱን ካርቶኖቹን ደግሞ በጎን አደረጋቸው፡፡ መጀመርያ ትልልቅ ድንጋዮች አነሳና በአንደኛው የመስተዋት ገንቦ ውስጥ እስካፉ ድረስ ከተታቸው፡፡ ከዚያም ተማሪዎቹን አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ «ይህ የመስተዋት ገንቦ ሙሉ ነውን?´ ተማሪዎቹም በአዎንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡ ከዚያም ቀጠለና ትንንሽ የከበሩ ድንጋዮችን አንሥቶ ወደ መስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ከተታቸው፡፡ በድንጋዮችና በድንጋዮቹ መካከል በሚገኙ ባዶ ቦታዎች ወስጥ እየገቡ የከበሩት ድንጋዮች ገንቦውን ሞሉት፡፡ መምህሩም ተማሪዎቹን በድጋሚ ጠየቃቸው፡፡ «አሁንስ የመስተዋቱ ገንቦ ሙሉ ነውን?´ ተማሪዎቹም ሙሉ መሆኑን ተናገሩ፡፡ ቀጠለና መምህሩ ከሦስተኛው ካርቶን ስኳር እያፈሰ ወደ መስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ከተተ፡፡ በቀሪው ባዶ ቦታ ውስጥ እየገባ ስኳሩ ሞላ፡፡ መምህሩም የተለመደ ጥያቄውን ጠየቀ፡፡ «የመስተዋቱ ገንቦ ሙሉ ነውን?´ ተማሪዎቹም በአዎንታ መለሱ፡፡ እንደገና መምህሩ ሁለተኛውን የመስተዋት ገንቦ አቀረበ፡፡ ከዚያም በተቃራኒው ስኳሩን በመስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ሞላበት፡፡ ተማሪዎቹንም ገንቦው ሙሉ መሆንና አለመሆኑን ጠየቀ፡፡ ተማሪዎቹም ሙሉ መሆኑን መሰከሩ፡፡ በመቀጠል ድንጋዮቹን ለማስገባት ሞከረ፡፡ ነገር ግን ስኳሩ ሁሉንም ቦታ ስለያዘው ማስገባት አልቻለም፡፡ ለከበሩ ድንጋዮች የሚሆን ቦታም አላገኘም፡፡ መምህሩ ከሁለቱ የመስተዋት ገንቦዎች ፎት ቆመና ተማሪዎቹን ሃሳብ ጠየቃቸው፡፡ የመጀመርያው የመስተዋት ገንቦ ሦስቱንም ነገሮች ሲያስገባ ሁለተኛው ገንቦ ለምን አልቻለም? የመጀመርያው ገንቦ ድንጋዩን ሲያስገባ ሙሉ ነበረ፡፡ የከበሩ ድንጋዮች ሲጨመሩም ሙሉ ነበረ፡፡ ስኳሩም ሲጨመር ሙሉ ነበረ፡፡ ሁለተኛው ገንቦ ግን በስኳሩ ብቻ ሞላ፡፡ ለምን? በሕይወታችሁ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አለ መምህሩ፡፡ የመስተዋት ገንቦ ሕይወታችሁ ናት፡፡ ድንጋዩ፣ የከበሩት ድንጋዮችና ስኳሩ ደግሞ በሕይወታችሁ ውስጥ ቅድሚያ የምትሰጧቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሰው በሕይወቱ ውስጥ የሚያስፈልጉትም ሆኑ የሚፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የሚያገኙትም ሆኑ የሚያገኛቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የሚገጥማቸውም ሆኑ የሚያጋጥሙት ብዙ አማራጮች አሉ፡፡ ሁሉም ቦታ ይይዛሉ፡፡ አንዳንዶቹ ነገሮች እነርሱ በሕይወታችን ቀድመው ከገቡ ለሌሎቹ የሚሆን ቦታ የማይኖራቸው ናቸው፡፡ እነርሱ ብቻ ከሞሉ የሌሎችን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ለሌሎች ቦታ እንተው ካልን ደግሞ እነርሱ ይጎድላሉ፡፡ በሌላም በኩል አንዳንዶች እነርሱ በሕይወታችን ቢሞሉም ለሌሎች ቦታ ያላቸው ናቸው፡፡ በመጀመርያው ገንቦ ውስጥ ድንጋዩን ስናስገባው ገንቦው ሙሉ ነበረ፡፡ ነገር ግን ለሌሎች መግቢያ የሚሆን ቦታ ነበረው፡፡ ድንጋዩ ምንድን ነው? በሕይወታችን የመጀመርያ ቦታ ልንሰጣቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ እምነታችን፤የሕይወት መመርያዎቻችን፤ ማንነታችን፣ ቤተሰባችን፣ ሀገራችን፣ ለእውነት የምናደርገው ተጋድሎ እነዚህ መጀመርያ በሕይወት ገንቧችን ውስጥ ከገቡ ሕይወታችን ሙሉ ትሆናለች፡፡ ተመልከቱ መጀመርያ ድንጋዩ ከገባ በኋላ ብንተወው እንኳን ገንቦው ግን ሙሉ ነበር የሚሆነው፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው፡፡ ገንቦው ሙሉም ጎዶሎም ነበር ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ጎዶሎነቱ ሙላቱን አልቀነሰውም፡፡በቃ ገንቦው ሊይዘው የሚችለው የድንጋይ መጠን ያንን ብቻ ነበረ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ነበረ፡፡ ገንቦውን ሙሉ ለማድረግም እርሱ ብቻ በቂ ነበረ፡፡ ነገር ግን ቦታም ነበረው፡፡ ከላይ ያነሣናቸው ነገሮች በሕይወታችን ካሉ ሕይወታችን ሙሉ ትሆናለች፡፡ ነገር ግን ለሌሎችም ነገሮች ቦታ ይኖሯታል፡፡ ምናልባት ግን የከበሩ ድንጋዮችና ስኳሩ እንኳን ባይኖር ሙሉ እንደሆነች ትቀጥላለች፡፡ ሀብታም አንሆን ይሆናል፤ ታዋቂ አንሆን ይሆናል፤ ሁሉ ነገር የተሳካልን አንሆን ይሆናል፤ ከኛ ተርፎ ለሌለ የምንሰጥ አንሆን ይሆናል፤ ለመትረፍረፍና ለመዝናናት የሚበቃ ነገር አይኖረን ይሆናል፡፡ እንዲህም ሆኖ እንኳን ሕይወታችን ግን ሙሉ ትሆናለች፡፡ ሕይወትን የሚሞላት እንደ ድንጋዩ ጠንከርና ከፍ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እምነትና የሕይወት መመርያዎች ዋነኛ የሕይወት ሙላቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ካሉ የከበረው ድንጋይና ስኳሩ ባይኖሩ እንኳን ሕይወት ግን ሙሉ መሆንዋ አይቀርም፡፡ ሕይወትን በዋናነት የሚሞሏት እምነትና የሕይወት መመርያዎች ወይንም አቋሞች ናቸው፡፡ ችግር ችግር የሚሆነው በራሱ ችግር ስለሆነ አይደለም፡፡ ችግር ችግር የሚሆነው በችግር ዓይን ሲያዩት ነው፡፡ በኢንዱስትሪ አብዮት ዘመን ሁለት ሰዎች ከአንድ የጫማ ፋብሪካ ተልከው ወደ አፍሪካ መጡ፡፡ የጫማ ገበያን ጉዳይ ሊያጠኑ፡፡ ሁለቱም ሰዎች የተለያያ ሪፖርት ይዘው ተመለሱ፡፡ የመጀመርያው ሰው «እዚያ ለጫማ የሚሆን ገበያ የለም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰዎች በባዶ እግራቸው ነው የሚሄዱት´ አለ፡፡ #ይቀጥላል
إظهار الكل...
✞መንፈሳዊ_ወግ✞ #የልብን_ከሰይጣን ቀደምት አበው እና እማት የሰይጣንን ማንነት በሚገባ ከማወቃቸው የተነሣ ሰይጣን መዋጋት እና ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ራሱን ያታልሉት ነበር፡፡ ይህም መንፈሳዊ ብቃታቸው እና ዕውቀታቸው የቱን ያህል ይደርስ እነደነበረ ከሚመሰክሩት ነገሮች አንዱ ነው፡፡ የትምህርተ ኅቡዓት መተርጉማን «ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቀውም» ይላሉ፡፡ ሰይጣን የሚችለው በሰው ልቡና የታሰበውን መገመት ብቻ ነው፡፡ በሰው ልቡና የተመላለሰውን ማወቅ ስለማይችል ሰዎች የልባቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ይገፋፋቸዋል፡፡ ሔዋንን ስለ ዕጸ በለስ ያንን ሁሉ የጠየቃት ለማወቅ ወይንም ለመረዳት ፈልጎ ሳይሆን ሥላሴ በሔዋን ልቡና የጻፉትን ነገር ማወቅ ስላልቻለ ነው፡፡ ሔዋን ስትናገር ግን ሃሳቡን ዐወቀ፡፡ ዐውቆም ዝም አላለም ጠልፎ የሚጥልበትን ወጥመድ አዘጋጀ፡፡ እናቶቻችን ወደ ቅዱሳት መካናት ለመሳለም ሲሄዱ «ላሊበላ፣ አኩስም፣ ግሼን ልሄድ ነው» አይሉም ነበር፡፡ «እንጨት ልሰብር፣ ውኃ ልቀዳ፣ ዘመድ ልጠይቅ» እያሉ ነበር የሚጓዙት፡፡ ይህም ሰይጣን በልቡናቸው ያለውን ተረድቶ ዕንቅፋት እንዳያመጣባቸው ነው፡፡ ይህንን የሰይጣን ስንፍና ከሚያውቁ አበው መካከል አባ ሉቃ እና አባ ታድራ ያደረ ጉትን ከመጽሐፈ መነኮሳት አንዱ የሆነው መጽሐፈ ፊልክስዮስ በተስእሎ አንቀጽ 56 ላይ እንዲህ ይነግረናል፡፡ በአንድ ገዳም ውስጥ አባ ታድራ እና አባ ሉቃ የሚባሉ መነኮሳት ነበሩ፡፡ እንጸናለን ብለው የመጡ ብዙ መነኮሳትን ሰይጣን ከበኣታቸው ሲያስወጣቸው ተመለከቱና እንዲሁ ውስጥ ለውስጥ ተግባቡ፡፡ «በቀጣዩ ክረምት ከበኣታችን ወጥተን በበረሃ ለብቻችን እንጋ ደላለን፤ በዚያም ሰይጣንን ድል እናደርገዋለን» ተባባሉ፡፡ ሰይጣንም እውነት መስሎት እነርሱን ከበኣታቸው ለማውጣት የሚያደርገውን ፈተና ተወው፡፡ በበረሃም ይጠብቃቸው ጀመር፡፡ ክረምት በደረሰ ጊዜም «አሁንማ በክረምት እንዴት እንሄዳለን፤ በጋ ሲወጣ በረሃ ወርደን ሰይጣንን እንቀጠቅጠዋለን፣ እስከዚያ ዝም ብለን እንቀመጥ» ተባባሉ፡፡ ሰይጣንም እውነት መስሎት ፈተናውን ሁሉ ትቶ በጋ እስኪደርስ ጠበቃቸው፡፡ በጋም በደረሰ ጊዜ «ወደ በረሃ እንሄዳለን ተባብለንኮ ሰነፍን፣ ምን ይሻላል፤በቃ በክረምት እንሄዳለን» ተባባሉ፡፡ እንዲህ እያሉ ሰይጣንን ሃምሳ ስድስት ዓመት ዘበቱበት፡፡ በዚህም የተነሣ የመልክአ ሥላሴ ደራሲ እንዲህ የሚል አርኬ ደረሰላቸው:- ሰላም ለአክናፊክሙ እሳታውያን አክናፍ እለ በማእከል ሀለው ወእለ ሀለው በጽንፍ አለብወኒ ሥላሴ ቀትለ መስተጋድል መጽሐፍ ከመ ወትረ ይትዋሥአኒ ትምይንተ ሉቃ ትሩፍ ወጉሕልተ ታድራ ምስሌየ ይዛዋዕ በአፍ፡፡ በጎ ነገሮችን ከሰው ተማክሮ መሥራት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ቆራጥነትን የሚጠይቁ፣ ፈተናም የሚበዛባቸውን መልካም ነገሮችን ከመሥራት በፊት ማውራት ግን በራስ ፈቃድ መከራ መጋበዝ ነው፡፡ አበው እንዳሉት ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቅም፡፡ ስለዚህም ስለምናስበው ነገር ሁሉ በየአጋጣሚው እንድናወራ ያደርገናል፡፡ ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው፡፡ ብዙ እያወሩ ጥቂት ከመሥራት፣ ምንም ሳያወሩ ብዙ መሥራት እንዴት መልካም ነው፡፡ሞያ በልብ ነው ይላል የሀገሬ ሰው፡፡ በየትዳሩ፣ በየማኅበሩ፣ በየጉባኤው፣ በየአጥቢያው ፈተና ከሚበዛባቸው ምክንያቶች አንዱ ይኼ ሊሆንስ ከቻለ) ሁሉንም ነገር ለሰይጣን ስለምንነግረው፡፡ ባል እና ሚስት ተያይተው ብቻ የሚግባቡባቸውን መንገዶች ገንዘብ ማድረግ አለባቸው፡፡ የምናስበውን ሁሉ አናውራ፡፡ በልቡናችን ተቀምጦ በተግባር ብቻ መገለጥ ያለበትን እንለይ፡፡ ኮሚቴ ሲበዛ፣ ስበሰባ ሲበዛ፣ ውይይት ሲበዛ፣ ሰው ሲበዛ በዙ ጊዜ መንፈሳዊ ሥራ መሠራት ከባድ ይሆናል፡፡ መሰናክሉም ይበዛል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከተሰብሳቢዎቹ ጋር አጅሬም አብሮ ሳይሰበሰብ አይቀርም፡፡ ሴት የበዛበት ወጥ እና ወሬ የበዛበት መንፈሳዊ ሥራ ሁለቱም ይበላሻሉ፡፡ እስኪ ከወሬ ተግባር ይቅደም፡፡ የነ አባ ትዳራን እና የነ አባ ሉቃን ነገር ባንረሳው መልካም ነው፡፡ @tibebezesenbet @tibebezesenbet
إظهار الكل...
#ዘወረደ እንኳን ለ2015 ዓ.ም ጾመ ኢየሱስ በሰላም አደረሳችሁ። የዐብይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ዘወረደ ይባላል። ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡ ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የዓብይ ጾም የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤›› የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው፡፡ ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡ ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡ የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል፡፡ ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም ሳምንትን (ዘወረደን) ስያሜ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሐዋርያት ተቀብላ ታስተምራለች፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡ @tibebezesenbet @tibebezesenbet
إظهار الكل...
እንኳን ለ2015 ዓ.ም ጾመ ኢየሱስ በሰላም አደረሳችሁ!!! #ዐቢይ_ጾም ጾም ማለት ሰውነትን ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል፣ ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነዉ፡፡ ጌታችን መጾም ሳያስፈልገው የጾመው በጾም መሣሪያነት ዲያቢሎስን ድል ታደርጋላችሁ ሲለን ነው፡፡ እርሱ ድል አድርጎታል ካልጾሙ ካልጸለዩ ሰይጣንን ድል ማድረግ እንደማይቻል ጌታ አስተምሮናል፡፡ ጾም ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት እንደሆነ በሰብአ ነነዌ ታውቋል እነዚህ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የተመለሱት በጾም ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር በጾም በጸሎት የተመለሱ ድኅነትን እንዳገኙ ሁሉ ያልተመለሱ ደግሞ ጠፍተዋል፡፡ ለምሳሌ ሰብአ ሰዶም ገሞራ እንደ ነነዌ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ባለመመለሳቸዉ እሳት ከሰማይ ወርዶ አቃጥሎ አጥፍቶአቸዋል (ዘፍ ፲፱፡፳፫)፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከሚጾሙት 7ቱ አጽዋማት አንዱና ትልቁ ዐብይ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም ዐብይ ጾም ፣ ጾመ ኢየሱስ ፣ ጾመ ሁዳዴ ፣ አርባ ጾም በመባል ይታወቃል ፡፡ ዐብይ ጾም መባሉ ትልቅና ታላቅ ጾም መሆኑን ለማሳወቅና አምላካችን ለሰዎች በመጀመሪያ አብነት ለመሆን የጾመው ስለሆነና ቀኖቹም ከሌሎች አጽዋማት በቁጥርም ከፍ ስለሚል ነዉ፡፡ ጾመ ኢየሱስ መባሉ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጠቀሰ ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው በመሆኑ ጾመ ኢየሱስ ተብሏል (ማቴ ፬᎓፩)። ሁዳዴ ጾም መባሉ ይህ ስያሜ የወጣው ሁዳድ ከሚለው ሲሆን ሁዳድ ማለት ሰፊ የእርሻ ቦታ ማለት ሲሆን ዐብይ ጾምም የሥላሴን ልጅነት ያገኙ ክርስቲያኖች በሙሉ ሰፊና ትልቅ ወደሆነው ካገኙት የማያጡት ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያደርስ ሁሉም ምዕመን የሚጾመው ጾም በመሆኑ አባቶቻችን ጾመ ሁዳዴ ብለዉ ሰይመውታል፡፡ 40 / አርባ ጾም ይኸውም ጌታ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሔደ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ፣ ጸለየ ብሎ ቅዱስ መጽሐፍ በማቴዎስ ፬፤፪ እንደ ተጻፈ ጌታ አርባ ቀን የጾመው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ ዐብይ ጾም ሦስት ክፍሎችና ስምንት ሳምንታት ያሉት ሲሆን እነሱም ፡-ሦስቱ ክፍሎች የተባሉት እነዚህ ናቸዉ፡፡ ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል )፡-ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ ያለዉ ቀን ነዉ፡፡ የጌታ ጾም፡-ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣእና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው፡፡ ሕማማት ፡- ይህም ጌታችን በአልአዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሣዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሥዑር ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው፡፡ ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነዉ፡፡ የአብይ ጾም ስምንት ሳምንታት ፩- ዘወረደ ፪- ቅድስት ፫- ምኩራብ ፬- መጻጉዕ ፭- ደብረ ዘይት ፮- ገብርኄር ፯- ኒቆዲሞስ ፰- ሆሣዕና የሰው ልጆች ጠላት የጨለማ ገዢ የሆነው ዲያቢሎስን በጾም እንደምናሸንፈዉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል፡፡ ጾም ሥጋችንን ለነፍሳችን የምናስገዛበት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት የጽድቅ መንገድ ለሥጋ ጤንነትም ቢሆን አስፈላጊያችን የሆነ አንዱና ዋነኛዉ የጽድቅ እቃ ጦራችን ነው፡፡ሆኖም የጾም ወቀት ሲመጣ አቀበት የሚወጡ ይመስል የሚፈሩትና የሚያማርሩት ሳይሆን እንኳን መጣልን ተብሎ በጉጉት የሚናፈቅ መሆን አለበት፡፡ በተለይ አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ በሚታየዉ አስቸጋሪ ፈተና እያንዳንዳችን ልባዊ ጾም በመጾም ልዑል እግዚአብሔር የጸሎታችን ምላሽ እንዲሰጠን እንማጸናለን፡፡ ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን፡፡ @tibebezesenbet @tibebezesenbet
إظهار الكل...
በቅዱስ ሲኖዶስ እና በሕገ ወጥ መልኩ ሢመት በፈጸሙት መካከል የተደረሰው ስምምነት
إظهار الكل...
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሙሉ ቃል።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.