ዶ/ር ቅድስት የ ፅንስ እና ማህፀን ስፔሻሊስት ሀኪም
الذهاب إلى القناة على Telegram
✳️✴️✳️ይህ ጠቅላላ የማህፀን እና ፅንስ ምክርአገልግሎቶችን ✅ የወርአበባ መዛባትን ✅የመካንነት👫👩❤️💋👩 ✅የማህፀን ኢንፌክሽን: ✅የካንሰር ምርመራዎች እና ህክምና 🤵♀️ ✅ የቅድመ እርግዝና ክትትልና ምክር ✅ስለ እርግዝና🤰🤰 ክትትል የሚያስተምር የሚያማክር ገፅ ነው። 🟩🥼🥼ዶር ቅድስትን ለማማከር https://t.me/DrKidist @DrKidistOBYGN
إظهار المزيد4 101
المشتركون
-324 ساعات
-217 أيام
-7330 أيام
أرشيف المشاركات
✳️✴️✳️ይህ ጠቅላላ የማህፀን እና ፅንስ ምክርአገልግሎቶችን
✅ የወርአበባ መዛባትን
✅የመካንነት👫👩❤️💋👩
✅የማህፀን ኢንፌክሽን:
✅የካንሰር ምርመራዎች እና ህክምና 🤵♀️
✅ የቅድመ እርግዝና ክትትልና ምክር
✅ስለ እርግዝና🤰🤰 ክትትል የሚያስተምር የሚያማክር ገፅ ነው።
🟩🥼🥼ዶር ቅድስትን ለማማከር
https://t.me/DrKidist
@DrKidistOBYGN @ 9394
🙏
"በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከእምብርቷ በላይ አልፈን ነው የሰራነው። በጣም ትልቅ እጢ ሲሆን ይጠማዘዛል ተብሎ ባይታሰብም ግን ሁለት ጊዜ ተጠማዞ ነው ያገኘነው" - 19Kg የማህጸን እጢ ያወጣው ዶክተር
ሙሉ የእርግዝና ክትትል ባለማድረጓ፣ ሳይታወቅ ከጽንስ ጋር ተሸክማው የነበረውን 19 ኪሎግራም የማህጸን እጢ ከአንዲት እናት በቀዶ ህክምና ማውጣቱን ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቀዶ ህክምናውን የሰሩት የማህጸንና ጽንስ ስፓሻሊት ሀኪም፣ በዩኒቨርሲቲው በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚያስተምሩት ዶክተር ጁሃር መሐመድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" እናታችን የመጣችው ከገጠር አካባቢ ነው። ከአንድ ወር በፊት ልጅ የወለደችው ሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ጤና ጣቢያ ነው። ግን ከወለደች በኋላ ሆዷ አልሟሸሸም፣ እርግዝና እንዳለ አይነት ሆኖ ተወጥሮ ነበር የሚታየው።
ነገር ግን አንዲት እናት ከወለደች በኋላ ማህጸን ተኮማትሮ ወደቦታው ይመለሳል፤ በእርግዝና ወቅት የተወጠረ ሆዷም እየቀነሰ ነው መሄድ ያለበት። የዚችኛዋ እናት ግን ከወለደች በኋላም 30 ቀናት እንዳለ ነው የነበረው።
አዋላጅ ነርሷም ሲያየውም ሆዷ አልቀነሰም። እርሷም ህመም ይሰማታል። የቀረ ነገር እንዳለም ተሰማት። ባለሙያውም ጥሩ ባለሙያ ነው ሳላመሰግነው አላልፍም፤ ማህጸኗ ሳይመለስ የቀረ ነው የመሰለው፣ የሚችለውን አድርጎ ካቅሙ በላይ ሲሆን ለወልዲያ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ጻፈ።
መጥታ ሳያት ነፍሰጡር ነበር የምትመስለው፤ ሆዷ እንደተወጠረ ነበር። ከዚያም አልትራሳውንድ ስካን ሰራሁላት። በአልትራሳውንድ ለመለካት የሚያስቸግር፣ ሙሉ ሆዷን ከማህጸን ማስቀመጫው እስከ ሳምባዋ ድረስ የተወጠረ ሆድ ነው የነበራት።
ምክንያቱም ከእርግዝናው ጋር አብሮ ያደገ የማህጸን እጢ ነበረባት። በጣም ትልቅ (19Kg) እጢ ነው። ሲታይ ከማህጸን ዘር ፍሬ ማምረቻ የተነሳ ውሃ የቋጠረ እጢ ነበር የሚመስለው።
እንደዚህ አይነት ኦፕሬሽኖች መሰራት ያለባቸው ስድስት ሳምንት ከሞላ በኋላ፤ የእርግዝና ጊዜው ካለፈ በኋላ፣ ማህጸን ወደቦታው ከተመለሰ በኋላ ቢሆን ይሻላል ተብሎ ነው የሚመከረው። ግን ሴትዮዋ ስመለከታት ከፍተኛ ህመም ነበራት፤ ሆዷ በጣም ተወጥሮ ነበር፤ የምትመገበው አይስማማትም፤ እስከ ሳምባዋ ስለያዛት ለመመገብም ትቸገር ነበር።
ህመም ካስከተለ እጢው የመጠምዘዝ እድል አለው። ግን ደግሞ እጢው የመጠማዘዝ እድል ይኖረዋል ተብሎ የሚታሰበው መጠኑ ከ5 እስከ 10cm ሲሆን ነው። ከዚያ በላይ ከሆነ ይጠመዘዛል ተብሎ አይጠበቅም።
ህመሙ ስላለ ስድስት ሳምንት መጠበቅ አልተቻለም። በወለደች በወሯ ኦፕሬሽን ተሰራላት " ብለዋል።
በቀዶ ህክምና ወቅት ስላጋጠማቸው ነገር ዶክተር ጁሃር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" እጢው በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከእምብርቷ በላይ አልፈን ነው የሰራነው። በጣም ትልቅ እጢ ሲሆን ይጠማዘዛል ተብሎ ባይታሰብም ውስጥ ስንገባ ግን ሁለት ጊዜ ተጠማዞ ነው ያገኘነው። ግን በጣም ጥብቅ ያለ መጠማዘዝ አይደለም። ህመሙን ያስከተለባት መጠማዘዙ ነበር።
ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ሴትዮዋ እድለኛ የሆነችው ነገር፦ እጢው ሳይፈነዳ ነጥለን ነው በኦፕሬሽን ያወጣንላት። ከወር በፊት ሦስተኛ ልጇን ነው የወለደችው፤ ገና በመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ነች፣ 28 ዓመቷ ነው።
በመውለድ እድሜ ያለን ሰው ማህጸኑ ይተዋል፤ ከ50 ዓመት በላይ ሲሆን ግን እንደዚህ አይነት ነገር ሲያጋጥም ወደ ካንሰር የመቀየር እድል ስለሚኖረው ማህጸን፣ የዘር ፍሬዎች፣ ቱቦዎችም አብረው ይወጣሉ። የሷን ግን እጢ ያለበትን ጎን የማህጸን ቱቦ ማስተላለፊያውን ጨምረን አወጣላት። ምንም ነገር ሳይፈስና ሳይሰራጭ ነው ያወጣንላት።
አብዛኛው ሰው እጢው ከወጣ በኋላ በፌስታል የተቋጠረ ነው የመሰለው። ግን የራሱ የእጢው ከረጢት ነው። በራሱ ከረጢት ነው ቋጥረን ያወጣነው። በጣም ትልቅ ስለሆነ ባንዴ አይወጣም፣ ቀስ እያልን እየገፋን አወጣነው። ስንመዝነው ማመን አልቻልንም፤ ሳፋውን ሞልቶ አልፏል። 19 ኪሎ ግራም ነው። እንደዚህ አይነት ገጠመኝ አጋጥሞን አያውቅም።
አሁን ታካሚዋ በሙሉ ጤንነት ላይ ነች። ልጇንም እያጠባች ነው። ታህሳስ 1/2018 ነው ቀዶ ጥገና የተሰራላት። ወደቤቷ ሄዳለች። በሁሉ ነገር ሰላም ነች" ብለዋል።
የተሰማቸውን ደስታ ስንጠይቃቸውም፦
" ሀኪም ሲኮን ብዙ ነገሮች ያጋጥማሉ፤ የአሁኑ ግን ከሁሉም እርካታው የተለዬ ነው። ስቃዩዋም ብዙ ነበር። ደስታዋን፣ ልጀዋን ስታጠባ፣ በጤና ስትንቀሳቀስ ከማየት የበለጠ ደስታ የለም። የሰው የሰውን ህመም ወደራሱ አምጥቶ አስተያየት የሚሰጠው አስተያየት ሲሰጥ ሲታይ ያስደስታል።
ለካ ከዚህም በላይ በመስራት፣ በተለይ የገጠሩን ማህበረሰብ መድረስ አለብን ያስብላል። የሰው ማበረታታት ጥሩ እንድንሆን ነው የሚያደርገው፤ ለወደፊት ከዚህ በላይ ለመስራት፣ ማህበረሰቡን ለማገልገል ነው የምዘጋጀው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አባበ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
👚💓🌸👉🏾💊⛑☝️ከወሊድ በሗላ እሚወጣ ፈሳሽ ምን ይመስላል??
#lochia
አንዲት ሴት ከወለደች በሗላ እሚወጣው ፈሳሽ እንደሚከተለው ነው
✓ ከወሊድ እስከ አራት ቀን (ወሊድ-4 ቀናት)red🔴🔴
💡ድምቅ ያለ ቀይ ፈሳሽ : የረጋ ደም የቀላቀለ ይወጣል: በቀን ከሶስት በላይ ሞዴስ ልትጨርሺ ትችያለሽ::
💡ይህ ጤነኛ ሂደት ነው :ማህፀን ወደቀደመ ቦታው እሚመለስበት: እሚሽርበት::
✓ ከአራት እስከ እስር ቀን ይቆያል (4-10 lochia rubura 👚🌸 ቡንኝ ይህ ፈዘዝ ያለ ሮዝ እየመሰለ እሚወጣ ፈሳሽ ነው:: የቡናማ ከለር ይኖረዋል::
✓ ቢጫማ አንዳንዴም ነጭ(10-28ቀናት ይኖራል)(lochia alba)
⛑🔴⛑💊🚒🥼እሚወጣው ፈሳሽ ከነዚህ ከተለየ (በመጠን :በቀለም)ወደወለድሽበት ህክምና ቦታ ሄዶ ማማከር ግድ ይላል ::
🙏🥼👩⚕️ ቤተሰብ እንሁን : ቻናሉ እንዲያድግ ለቤተሰብ ለወዳጅ እናጋራ ተሳተፉ፥ ጥያቄ ጠይቁ::🥼👩⚕️
https://t.me/DrKidisthttps://t.me/DrKidist/32
የሚጥል በሽታ በ እርግዝና ጊዜ
❓👩⚕️የሚጥል በሽታ ምንድን ነው?
የሚጥል በሽታ የአእምሮ ተግባርን በድንገት የሚያውክ ክስተት ነው፡፡ ክስተቱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ማንቀጥቀጥና (seizure) ራስን መሳት ( loss of consciousness)ያስከትላል፡፡
👉🏾ሆኖም አንድ ሰው የሚጥል በሽታ እንዳለበት የጤና ባለሙያዎች ሊለዩ የሚችሉት በደም ውስጥ ከፍተኛ ከሆነ የስኳርና የአልኮል ማነስ ጋር ባልተያያዘ ምክንያት የጤና ችግር ከ2 ጊዜ በላይ የማንቀጥቀጥና የመጣል ሁኔታ ሲገጥመው ነው፡፡
❓👩⚕️የሚጥል ህመም ያላት ሴት ማርገዝ ትችላለች?
✅አዎ።
✅ህክምናው እየዘመነ ሲሄድ ይህ ህመም ያላቸው ሴቶች ወልደው ልጅ ማቀፍ ችለዋል።
👩⚕️💊ከማርገዜ በፊት ምን ላድርግ?
👉🏾ክትትልሽ በሁለት ሀኪም ይሆናል( በነርቭ ስፔሻሊስት እና በማህፀንና ፅንስ )
👉🏾ከሀኪምሽ ጋር መመካከር ፣ለማርገዝ እንዳቀድሽ (ይህ በቂ ጊዜ /ለቅድመ እርግዝና ክትትል እንዲኖርሽ ይረዳል።
👉🏾ይህም ማለት ለፅንስ ጉዳት ያለው የሚጥል መድኃኒት ካለ እንዲቀየር:እንዲቀነስ ፣እንዲቆም በቂ ጊዜ ይሰጣል።
👌እርግጥ ነው ፎሊክ አሲድ ለሁሉም ሴት ይሰጣል።ነገር ግን የሚጥል ህመም ላላት ሴት መጠኑ ተጨምሮ ልትወስድ ይገባል።
👩⚕️✍🏼የሚጥል ህመም እና እርግዝና።
👉🏾ይህ ህመም ባንቺም በፅንሱም ላይ ገዳት ያመጣል ይህም የሚከሰተው ማንቀጥቀጡ(seizure) በአግባቡ በቁጥጥር ስር ውሎ ካልሆነ ያረገዝሽው፣በድንገት ብትወድቂ፣ ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች አደጋ ያስከትላሉ።
✅ነፍሰጡር ስለሆንሽ ማንቀጥቀጡ አይብስም።
❓👩⚕️ማንቀጥቀጡን ምን ሊያባብሰው ይችላል?
✅መዳኒትን ማቆም: ወይም መጠን መቀነስ ማንቀጥቀጡን ሊያባብሰው ይችላል
❓👩⚕️ማንቀጥቀጥ እንዳይኖር ምን ላድርግ ?
👉🏾ከሀኪምሽ ጋር በግልፅ መወያየት፣እናም መመካከር ።
👉🏾በፍፁም ሳታሳውቂ መድሃኒትሽን አለማቆም።
👉🏾በቂ እንቅልፍ መተኛት አለብሽ።(እንቅልፍ አለመተኛት ህመሙን ያብሰዋል።
👉🏾አግባብ ያለው የአመጋገብ ስርአት ይኑርሽ።
👉🏾ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ የምትወስጃቸውን መዳኒቶች (ባህላዊም :ዘመናዊም)ለሀኪምሽ ማሳየት።
❓❓👩⚕️ምን አይነት ምርመራ ይደረጋል❓
👉🏾ደም( የመዳኒቶቹን መጠን ለማወቅ)
👉🏾የአልትራሳውንድ ምርመራ( የፅንሱን ጤንነት፣ እድገት አቀማመጥ ይታይበታል)
👩⚕️❓የሚጥል ህመም ስላለኝ በምንድነው ❓እምወልደው?
👉🏾ማንቀጥቀጥ seizure)በምጥ ሰዐት አይጨምርም በምጥ መውለድ ትችያለሽ::
👉🏾👌በቂ ክትትል በምጥ ሰአት በማረግ ለፅንሱ ወይንም ላንቺ ችግር ካለ በኦፕራሲዮን(cesarean section) መውለድ ትችያለሽ።
❓👌ልጄስ ላይ ምን ያስከትላል?
ይህ ህመም በመዳኒት በቂ እና ጥሩ ቁጥጥር ስር ከነበረ ለልጅስ አያሰጋም።
❓👩⚕️ማጥባትስ እችላለው?
✍🏼አዎ ።ብዙ እናቶች ይህንን ህመም እየተከታተሉ ማጥባት ይችላሉ።
✍🏼አብሮሽ ሰው እንዲያግዝሽ ይኑር ፣
✍🏼በቂ እንቅልፍ ማግኘት እንዳለብሽ አትርሺ፣
✍🏼ዳይፐር ስትቀይሪ መሬት ላይ( ድንገት ቢያንቀጠቅጥሽ ልጅሽ ከአልጋ ላይ ወይንም ከመቀየሪያ ጠረጴዛ እንዳይወድቅ )
✍🏼ገላውን ስታጥቢ እሚያግዝሽ ሰው ይኑር::
ይህ ጠቅላላ የማህፀን እና ፅንስ ምክር አገልግሎቶችን ፣ የወርአበባ መዛባት ፣ የካንሰር ምርመራዎች እና ህክምና ፣ የወሊድ ቅድመ እርግዝ እና ስለ እርግዝና ክትትል የሚያስተምር ገፅ ነው።
ዶር ቅድስትን ለማማከር
https://t.me/DrKidist
@DrKidistOBYGN
ሰላም ዶ/ር ልጄ 3 ወሩ ነው። እምብርቱ ላይ ያበጠ ነገር አለው! አንዳንዴ ይቀንሳል፣ የሆነ ጊዜ ደግሞ በጣም ይጠነክራል። የሰፈር ሰዎች ብዙ ነገር ይሉኛል( ሳንቱም አድርጊበት፣ በፕላስተር እሰሪው ...ወዘተ) ። እባክህ ያንተን ምክር እፈልጋለሁ።
(የወላጅ ጥያቄ)
👉ሰላም ጠያቂያችን ስለጥያቄው በጣም እናመሰግናለን።
👉እንደርሶ አገላለጽ ከሆነ ይህ ችግር Umbilical Hernia ይባላል!
👉ይህ ችግር በጣም የተለመደ እና በብዙ ህጻናት ላይ የሚከሰት ችግር ስለሆነ ለብዙ ወላጆች ይጠቅማል ብለን ስላሰብን ለማብራራት እንሞክራለን!
✍ጥያቄ- 1፡ የእምብርት ሄርኒያ(umbilical Hernia) ምንድን ነው?
🌡የእምብርት ሄርኒያ ማለት የሆድ እቃ ግድግዳ እምብርት ላይ የጡንቻ ክፍተት ሲኖረው የሚፈጠር ችግር ነው።
🌡በዚህ ክፍተት ማንኛውም የሆድ እቃ አካላት በተለይ ስብ እና አንጀት በክፍተቱ ሊወጣ ይችላል
🌡በዚህም ምክንያቱ እንደ እብጠት ሆኖ ይታያል።
🌡ይህ ችግር umbilical Hernia ይባላል!
✍ጥያቄ-2 : ይህ ችግር ምን ያህል የተለመደ ነው?
💊በሕፃናት ላይ በጣም የተለመደ ችግር ነው።
💊 100 አዲስ ከሚወለዱ ህጻናት ከ10-20 የሚሆኑት ሕፃናት በተለይም ያለጊዜአቸው የተወለዱ ወይም ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ይህ ችግር ይኖራቸዋል።
✍ጥያቄ-3: መንስኤው ምንድን ነው?
🌡በሆድ እቃ ግድግዳ አፈጣጠር ከአራቱም አቅጣጫ በማደግ እምብርት ላይ ይገናኛል።
🌡 ስለዚህ እድገቱን ካልጨረሰ እምብርት አካባቢ ትንሽ ቀዳዳ ወይም ክፍተት ይቀራል!
🌡ስለሆነም ህጻናት ከተወለዱ በኋላ እምብርት ላይ ሙሉ በሙሉ መዝጋት መዘጋት ካልቻለ ይህ ችግር ይከሰታል።
✍ጥያቄ- 4፡ ይህ ችግር በብዛት የሚከሰተው የትኞቹ ላይ ነው?
💊ይህ ችግር በማንኛውም ህጻናት ላይ የመከሰት እድል አለው!
💊በብዛት የሚከሰተው ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተያያዥ ችግሮች ያሉባቸው ህጻናት ላይ ነው!
🌡🌡ያለጊዜአቸው የተወለዱ ሕፃናት
🌡🌡ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሕፃናት
🌡🌡አንዳንድ ተያያዥ የአፈጣጠር ችግር ያሏቸው ሕፃናት
✍ጥያቄ-5: ይህ ችግር ያለባቸው ህጻናት ምን አይነት ምልክት ያሳያሉ?
🌡እምብርት ላይ በቆዳ የተሸፈነ ለስለስ ያለ እብጠት
🌡 ሲያለቅሱ፣ ሲያስሉ ወይም ሲወጣጠሩ የበለጠ የሚታይ ከሆነ
🌡ብዙውን ጊዜ ህመም አይሰማቸውም
🌡ብዙውን ጊዜ ዘና በሚሉበት ጊዜ እብጠቱ ተመልሶ ይቀንሳል።
✍ጥያቄ-6: ምን አይነት ችግር ሊያስከትል ይችላል?
📍አብዛኛውን ጊዜ ምንም አይነት ጉዳት የለውም።
📍 ነገር ግን አልፎ አልፎ ሄርኒያ ሊታሰር ይችላል (አንጀት ክፍተቱ ውስጥ በመግባት ሊታሰር ይችላል)።
💊ይህ ችግር መከሰቱን የሚያመላክት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች፡-
💉💉ጠንከር ያለ ህመም ያለው እብጠት
💉💉እብጠቱ ላይ ያለው ቆዳ መቅላት ወይም መጥቆር
💉💉ማስታወክ ካለው ወይም መጥባት ወይም ምግብ መውሰድ ካቆሙ
➡ ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ ቢያንስ አንዱን ካሳዩ አስቸኳይ እና ድንገተኛ ህክምና የሚስፈልገው ችግር ስለሆነ ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል መሄድ አለባቸው!
✍ጥያቄ-7: እንዴት ይታከማል?
🌡አብዛኛውን ጊዜ እስከ 2 አመት እድሜ ድረስ በራሱ የሚዘጋ ችግር ነው።
🌡ቀበቶ ማድረግ ፣ ሳንቲም ወይም የቤት ውስጥ መድሃኒቶችን ማድረግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው
💉💉ይህን ማድረግ ቁስለት በመፍጠር ልጅዎን ሊጎዱ የሚችሉ ተግባራት ናቸው።
🌡ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች እስከሌላቸው ድረስ ተፈጥሮ በራሱ ክፍተቱ እንዲዘጋ ያደርጋል።
✍ጥያቄ-8: ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው መቼ ነው?
🌡ችግሩ ከ3-4 ዓመታት በኋላ ከቀጠለ
🌡ክፍተቱ በጣም ትልቅ ከሆነ እና በክትትል የሚቀንስ ካልሆነ
🌡ድንገተኛ ችግር ካስከተለ
🩺ስለዚህ ለቀዶ ህክምና የሚያስችል ምክንያት ከሌለው በክትትል መታየት ይቻላል!
✍ጥያቄ-9: በቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን?
🌡ቦታውን ንጹህ እና ደረቅ ማድረግ
🌡በላዩ ላይ ሳንቲም ወይም ሌላ ነገር አለማድረግ
🌡ማሰር ወይም በማንኛውም ነገር መጫን አንጀት እንዲጎዳ እና እንዲቆስል አልፎ ተርፎም እንዲበሳ ስለሚያደርግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው!
👁 በዚህ ጉዳይ ወይም በሌሎች ጉዳዬች በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል።
👇👇👇👇👇👇
📲+251911441651
💻ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የtelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ:
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/DrSaleamlakT
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
እናመሰግናለን
አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:
የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር
Dr. Saleamlak Tigabie:
MD, Consultant Pediatric Surgeon, FCS-ECSA
ልጄ የዘር ፍሬው ላይ ውሀ ቋጥራል ተባልኩ። ምንድነው ምክኒያቱ? መቼስ ይጠፋል?(የወላጅ ጥያቄ)
👉ህፃናት ላይ ከሚታዩ የተለመዱ ችግሮች ውስጥ የዘር ፍሬ ከረጢት እብጠት አንዱ ነው።
👉 ከነዚህ ችግሮች አንዱ የዘር ፍሬ ከረጢት ውሃ መቋጠር(Hydrocele) በጣም የተለመደ ችግር ነው።
✍ ጥያቄ-1: Hydrocele ምንድን ነው?
👉Hydrocele በአንድ ወይም በሁለቱም በኩል ሊከሰት የሚችል በዘር ፍሬ ዙሪያ በዘር ፍሬ ከረጢት ውስጥ የፈሳሽ ስብስብ ነው።
👉ፈሳሹ የዘር ፍሬ ከረጢት እንዲያብጥ ያደርጋል።
👉 ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የህመም ስሜት የለውም።
👉በጨቅላ ሕፃናት በተለይም ያለጊዜው የተወለዱ ሕፃናት በብዛት ይከሰታል
👉 ነገር ግን በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል።
✍ጥያቄ-2: መንስኤው ምንድን ነው?
👉በፅንስ እድገት ወቅት ሁሉም ህጻናት ከሆዳቸው ወደ ብልት የሚሄድ ቱቦ አላቸው።
👉በወንዶች ይህ ቱቦ የወንድ የዘር ፍሬ (በሆድ ውስጥ የሚፈጠር) ወደ የዘር ፍሬ ከረጢት(Scrotum) እንዲወርድ የሚያስችል ቦይ ነው።
👉የቦዩ ሽፋን ከዘር ፍሬ ጋር የሚወርድ ከረጢት(Sac) ይፈጥራል።
👉ከጊዜ በኋላ ቦዩ ብዙውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይዘጋል።
👉 ነገር ግን ይህ ካልሆነ የውሃ መቋጠር ችግር(Hydrocele) ሊፈጠር ይችላል።
✍ጥያቄ -3: ዓይነቶቹ ምን ምን ናቸው?
👉1) የማይገናኝ
👉👉ቦይ እና ከረጢቱ ከተዘጉ በኋላ በዘር ፍሬ ከረጢት ውስጥ ፈሳሽ በመያዙ ምክንያት የማይገናኝ hydrocele ይፈጥራል።
👉ከሆድ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ስለሌለ ፈሳሹ በቦይ በኩል ወደ ሆድ መመለስ አይችልም።
👉2) የሚገናኝ hydrocele
👉👉በፅንሱ እድገት ወቅት ቦይው ሙሉ በሙሉ መዝጋት ሲያቅተው የሚፈጠር ችግር ነው፣
👉👉ይህም ፈሳሽ ወደ የዘር ፍሬ ከረጢት ለመግባት ክፍት ይሆናል።
👉👉ፈሳሹ በቦይ በኩል ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መፍሰስ ይችላል።
👉👉በዚህ ምክንያት የእብጠቱ መጠን ሊለዋወጥ ይችላል።
👉👉ፈሳሹ በዘር ፍሬ ከረጢት ውስጥ ሲሆን እብጠቱ የጨመረ ይመስላል
👉👉ነገር ግን ፈሳሹ በቦይ በኩል ወደ ኋላ ሲንቀሳቀስ እብጠቱ ትንሽ ይሆናል።
👉👉መክፈቻው ደግሞ ሰፊ ከሆነ የሆድ ዕቃዎች (እንደ አንጀት ያሉ) ወደ የዘር ፍሬ ከረጢት ውስጥ ሊገባ ይችላል።
👉👉 በዚህም ምክንያት(inguinal hernia) ያስከትላል(ማብራሪያውን በሌላ ጽሁፍ ያገኙታል)
👉3) የዘር ፍሬ ገመዱ ሃይድሮሴል
👉👉ይህ የሚከሰተው ከረጢቱ በሚዘጋበት ጊዜ ነው ነገር ግን ፈሳሹ በወንድ ዘር (spermatic) ገመድ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።
✍ጥያቄ -4: ምርመራው ምን ይመስላል?
👉በቀላሉ በአካል ምርመራ የሚታወቅ ነገር ነው።
👉 ፈሳሹ ብርሃን ስለሚያስተላልፍ ከለሌች ችግሮች በቀላሉ መለየት ይቻላል።
✍ጥያቄ-5: ሕክምናው ምን ይመስላል?
👉የሚደረገው ሕክምና እንደ ችግሩ ዓይነት ይወሰናል።
1) የማይገናኝ hydrocele፡-
👉👉በብዙ አጋጣሚዎች እነዚህ አይነት ችግር በህይወት የመጀመሪው አመት የመጥፋት እድል አለው።
👉👉ስለዚህ እድሜው ከ1 አመት በታች ከሆነ መከታተል ይመክራል።
👉👉ከ1 አመት በላይ ከቀጠለ የቀዶ ጥገና ጥገና አስፈላጊ ይሆናል።
👉👉ምክንያቱም ከአንድ አመት በላይ ሲቆይ የዘር ፍሬ ላይ ጫና ስለሚያሳድር የፍሬ መቀጨጭ ወይም መሳሳት(testicular atrophy) ሊያስከትል ስለሚችል ከ1 በላይ መቆየት የለበትም።
2) የሚገናኝ hydrocele፡-
👉ይህ ችግር በራሱ የመጥፋት እድሉ በጣም ዝቅተኛ ነው።
👉ስለዚህ በቀዶ ህክምና መስተካከል ያስፈልገዋል።
3) የዘር ፍሬ ገመዱ hydrocele፡-
👉በራሳቸው የመጥተፋት እድላቸው አነስተኛ ነውና የቀዶ ጥገና ህክምና ይጠይቃሉ።
✍ጥያቄ-6: ክትትል እና የሚደረግላቸው እንክብካቤ ምን ይመስላል?
👉ከቀዶ ህክምና በኋላ የዘር ፍሬ ከረጢት በትንሹ ያበጠ ሊመስል ይችላል።
👉ይህም በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል።
👉 ከ4 እስከ 6 ሳምንታት በአካላዊ እንቅስቃሴ ወይም በስፖርታዊ እንቅስቃሴ መሳተፍ የለባቸውም።
✍ጥያቄ -7: ወደ ሐኪም መሔድ ያለባቸው መቼ ነው?
👉ከቀዶ ህክምና በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶች ካጋጠማቸው:
• ትኩሳት
• አካባቢው ቀይ ከሆነ
•እብጠት ከጨመረ ወይም
•ህመም ከጨምረ
•ማንኛውም የኢንፌክሽን ምልክቶች ካለው ቶሎ ወደ ሆስፒታል በመሄድ መታዬት ይኖርባቸዋል።
📘በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወይም ለሌሎች ጥያቄዎች ከስር ባለው አድራሻ ማግኘት ይቻላል!
📲📲0911441651
💻ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የtelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ:
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/DrSaleamlakT
ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!
እናመሰግናለን
አዘጋጅ:
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:
የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም
Dr. Saleamlak Tigabie:
MD, Consultant Pediatric Surgeon, FCS-ECSA
☀️☀️☀️☀️ዶር ቅድስትን በ wecare በስልክ ማግኘት፣ መመካከር ፣ይችላሉ።
👇👇👇👇👇👇ለበለጠ መረጃ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ።☎️
በመተግበሪያው ከፈለጉ ከፕሌይ ስቶር ላይ በሚከተለው ሊንክ ገብተው በመጫን ዶርን ያግኙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
👚💓🌸👉🏾💊⛑☝️ከወሊድ በሗላ እሚወጣ ፈሳሽ ምን ይመስላል??
#lochia
አንዲት ሴት ከወለደች በሗላ እሚወጣው ፈሳሽ እንደሚከተለው ነው
✓ ከወሊድ እስከ አራት ቀን (ወሊድ-4 ቀናት)red🔴🔴
💡ድምቅ ያለ ቀይ ፈሳሽ : የረጋ ደም የቀላቀለ ይወጣል: በቀን ከሶስት በላይ ሞዴስ ልትጨርሺ ትችያለሽ::
💡ይህ ጤነኛ ሂደት ነው :ማህፀን ወደቀደመ ቦታው እሚመለስበት: እሚሽርበት::
✓ ከአራት እስከ እስር ቀን ይቆያል (4-10 lochia rubura 👚🌸 ቡንኝ ይህ ፈዘዝ ያለ ሮዝ እየመሰለ እሚወጣ ፈሳሽ ነው:: የቡናማ ከለር ይኖረዋል::
✓ ቢጫማ አንዳንዴም ነጭ(10-28ቀናት ይኖራል)(lochia alba)
⛑🔴⛑💊🚒🥼እሚወጣው ፈሳሽ ከነዚህ ከተለየ (በመጠን :በቀለም)ወደወለድሽበት ህክምና ቦታ ሄዶ ማማከር ግድ ይላል ::
🙏🥼👩⚕️ ቤተሰብ እንሁን : ቻናሉ እንዲያድግ ለቤተሰብ ለወዳጅ እናጋራ ተሳተፉ፥ ጥያቄ ጠይቁ::🥼👩⚕️
https://t.me/DrKidist
✳️✴️✳️ይህ ጠቅላላ የማህፀን እና ፅንስ ምክርአገልግሎቶችን
✅️ የወርአበባ መዛባትን
✅️የመካንነት👫👩❤️💋👩
✅️የማህፀን ኢንፌክሽን:
✅️የካንሰር ምርመራዎች እና ህክምና 🤵♀️
✅️ የቅድመ እርግዝና ክትትልና ምክር
✅️ስለ እርግዝና🤰🤰 ክትትል የሚያስተምር የሚያማክር ገፅ ነው።
🟩🥼🥼ዶር ቅድስትን ለማማከር
https://t.me/DrKidist
@DrKidistOBYGN
👉👉የማህፀን ጫፍ (አንገት ) በር ካንሰር ገዳይ በሽታ ነው ፣በጊዜው ከታወቀ ደግሞ ብዙ ሳይሰራጭ ማግኘት ፣ማከም ፣ማዳን ይቻላል።
🥼📝❤️❤️❤️ቀድሞ በማወቅ ፣ሳይሰራጭ በፊት ፣ በተለያዩ ህክምናዎች፣ እድገቱን ፣ስርጭቱን መግታት ነው አላማው።
❓❓❓እንዴት ነው እሚሰራው? ፣
በማህፀን ውስጥ መሳሪያ በማስገባት ፣ ናሙናውን ከ ማህፀን አንገት መውሰድ ነው።
ከመሄዳችን በፊት ምን ማድረግ አለብን ?
1⃣ግንኑኝነት አለማድረግ፣
2⃣አለመታጠብ ፣።
3⃣በማህፀን እሚወሰድ መድኃኒት አለመውሰድ ።
ናሙናው በስነደዌ ሀኪሞች ተጠንቶ ፣ እንደተገኘው ምላሽ ህክምና ይሰጣል።
⏩⏩⏩በቀጣይ ማን ማን ማሰራት አለበት ?
የት ይገኛል ?
እናም ፣ እናንተ እምታነሱትን ጥያቄ አይቼ አዘጋጃለው።
መልካም ቀን ።🙏🙏🙏
✳️✴️✳️ይህ ጠቅላላ የማህፀን እና ፅንስ ምክርአገልግሎቶችን
✅️ የወርአበባ መዛባትን
✅️የመካንነት👫👩❤️💋👩
✅️የማህፀን ኢንፌክሽን:
✅️የካንሰር ምርመራዎች እና ህክምና 🤵♀️
✅️ የቅድመ እርግዝና ክትትልና ምክር
✅️ስለ እርግዝና🤰🤰 ክትትል የሚያስተምር የሚያማክር ገፅ ነው።
🟩🥼🥼ዶር ቅድስትን ለማማከር
https://t.me/DrKidist
@DrKidistOBYGN
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
