ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

ግጥም

ግጥም

الذهاب إلى القناة على Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

إظهار المزيد
5 633
المشتركون
+1024 ساعات
+187 أيام
+12730 أيام
أرشيف المشاركات
#ሳብድ_ለምን_መጣሽ? ከሄድሽ ጀምሮ ••• ትዝታና ናፍቆት አቅም እያሳጡ ሲጥሉ ሲያነሱኝ ወራቶች ሲሮጡ በሞት መኖር መሀል ጎኔ ተሰንቅሮ በምኞት  በማየት  ስለነገ  አሻግሮ በግድ ስላለፍኩት ወራት አመታቱ ብታውቂም አልመጣሽ ተይዤ በብርቱ            እሺ ይሄም ይቅር ዕልፍ የሆኑ ወቅቶች በተስፋ ማለሙ የመጠበቅ ደዌ ጠንቶብኝ ህመሙ እድሜን ያህል ነገር ስላንቺ መስጠቴ የዘመኔን ክፋይ ላንቺው መሰዋቴ ስሜቱ እየገባሽ ከእንቅልፍ መኳረፍ ገላን ብቻ አንጋሎ በሀሳብ መንሳፈፍ እንደው እንዴት ሆነ ብለሽ ሳጠይቂ ዕልፍ አሳልፈሻል ለብቻሽ ስትስቂ                     ከአይኖቼ በመፍለቅ ትራሴን ያራሱት ዘለላ እምባዎቼ ስላንቺ ያነቡት በዋዛ ተቆጥረው ሁነውብሽ ተራ እንዲያ በመሆኔም ልብሽም ሳይራራ             ቀርተሻል በዘበት እግርሽ አረገጠም እኔም ካለሁበት                     የሳቅ ደስታ ትርጉም እስኪጠፋኝ ድረስ ሌተቀን በማዘን እድሌንም ስወቅስ ትመጫለሽ በሚል ሰርክ በመጠበቅ ደጁን እያማተርኩ ሳጣሽም ስሳቀቅ ብስቁልቁል ብዬ ስላዩ ባክኜ ባላፊው አግዳሚው በሰው ተኮንኜ እኔው በታመምኩት እኔው ብንገላታ አላስቀምጥ ብሎኝ የሰው አሉባልታ ማንም ከማያቀኝ ከአዲስ ቦታ መንደር ከሰው ተገልዬ ሁኜ እንደ ባይተዋር በጣር ስለኖርኩት ስላለፍኩት ስቃይ እያወቀሽ ሁሉንም መጥተሽ አይኔን ሳታይ እኔን ለኔው ትተሽ ስላንቺው ኑረሻል መቼም አትክጂውም ሁሉን ልብሽ ያውቃል                  ታዲያ •                               •                                 ለምን                                 •                               •                        ይሆን ?              ዛሬ ሁሉ ረፍዶ ጎኔ እንደናፈቀሽ ግዜው ሄዶ ሄዶ ከለየልኝ   ዃላ  ጨርቄ   ተቀዳዶ ሰዎች ሲያወሩልሽ የማበዴን መርዶ ልታዪኝ  መምጣትሽ ካለሽበት ማዶ አዝነሽ ነው ፀፅቶሽ ፣ ወይስ ደስ ብሎሽ ? ንገሪኝ  እውነቱን ሳብድ ለምን  መጣሽ ?         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢʰᵃʳᵉ

#የመሸበት_የለም የመሸ ቢመስለኝ የጨለመ በእኔ ነገ ጤዛ ሆኖ ይረግፋል ሀዘኔ በእኔ የምትሰራው ገና ሆኖ ግዜው አንተ እኮ ጌታዬ መምጫህ በድንገት ነው የተውከኝ ቢመስለኝ የረሳኸኝ ዛሬ ነገም ያንተ ቀን ነው ይመለሳል ክብሬ እጠብቅሃለሁ በተስፋ ቃል ኪዳን አንተን ተስፋ አድርጎ የመሸበት የለም ወድቆ ቀረው ሲሉ አንሳኝና ልቁም አምላክ ባንተ ስራ ጠላትም ይደመም።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

ቤተሰብ አንድ ነገር ላስቸግራችሁ እኔን ለማገዝ ፍቃደኛ የሆናችሁ 700 ሰዎች ይኸን የቴሌግራም ቻናል join እያደረጋችሁ screenshot ላኩልኝ የ5 ቀን ቻሌንጅ ሰተውኝ ነው ስለትብብራችሁ ከወዲሁ ከልብ አመሰግናለሁ 🙏

please support me by join this channel

#የእብደቴ_መነሻ        ፀሐይን አግብቼ ጨረቃን ስወሽም፣        "ይኼ ሰው ምን ነካው?" ትያለሽ ሁልሽም፤                   በተስፈኛ ምድር......        ደራሲ ገጣሚ አድርጎ ሲፈጥረኝ፣        በዚያች ዕለት ነበር እብደት የጀመረኝ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ምኞትሽ_ላይ_በርቺ! አንፖልን ለማብራት ይቃጣሉ ጣቶች ጨለማ ም ነበረ ፋኖስ የሚያደምቁ ... ባይኖሩ ለኳሾች ። እመኚኝ እታለም! በምታይው ዓለም.. . አምፖልም ፋኖስም ድምቀቶች አይደሉም ብርሀን ለማፍለቅ እንደሚገለጥ ህልም ፈፅሞ አይፈኩም! መፍካት በመሻት ነው  በምኞት ነው መንቃት ጨለማን ለመስበር ... ከፋኖሱ ቀድመሽ... ልብሽን ነው ማብራት።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ   ✍ ሚካኤል አስጨናቂ

#በቃልሽ_ታስሬ የልቤ ላይ ንግስት አንቺ ውቧ ፍቅሬ ቀናትን በመቁጠር ወራትን ደምሬ ከጎንሽ ባልሆንም ከአንቺው ጋር አብሬ በፍቅርሽ ሰንሰለት በፅናት ታስሬ አሜን ይሁን ብዬ ቃልሽን አክብሬ ለልቤ ትርታ ለደም ዝውውሬ ለመንፈሴ እርካታ ብታመም ዶክተሬ ደስታን ለማጣጣም ፍቅርሽን ዘምሬ እስትንፋሴ ነብሴ ሆነሽ ለእኔ ጤና ለመኖሬ ትርጉም የሂወቴ ቃና አዛኝ እንደ ሄዋን ሩህሩህ ነሽና አለም አስር ትሙላ ከቤቴ ግቢና         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#መንደር_ላይ_አትከክ!!! አንተ ብቻ ጽና ፣ በሀገር ውሃ ልክ፤ ወርደህ በዝቅታ፣ መንደር ላይ አትከክ! በሰውኛ ሚዛን ፣ በእውነት ስሌት ትጋ! ሀገር ከማይጠቅም ፣ በደቦ አትንጋጋ! ሰፋ! ብለህ ብረር ! በከፍታ! ሀሳብ ፤ በግፊያው መሀከል ገብተህ አትጣበብ! በዛሬ ግርግር ፣ ነገን አታበላሽ ፤ በሰውኛ ፈረስ ፣ ሁን ለብቻ ገስጋሽ! ትውልዱ ሲነቃ ፣ በእውነት ተቀስቅሶ፤ መጠየቅ ሲጀምር ፣ ታሪክን አጣቅሶ፤ ያኔ! አንተ ኮራ በል ፣ ሌላው ሲሸማቀቅ፤ በሀገርህ ምድር ፣ ሰንደቅ ሆነህ ድመቅ! ከፍ! በል! ለነገ ፣ በአዲስ ህብረ ቅኔ! ይኸን ነው ዛሬ ላይ ፣ የምመክርህ እኔ!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

ያለቀኔ አፍቅሬሽ፥ ገፍተሽኝ ሄደሻል፣ አቻሽን ፍለጋ፥ ብዙ ተጉዘሻል፤ መቼም አይሰምርልሽ፥ልብ ሰብረሽ ሄደሽ፣ ምንጊዜ ቢረዝም፥ አይቀር መመለስሽ፣ ብዬሽ እንደነበር፥ ቆየሁ ስጠብቅሽ። ባ'ይኔ ላይ ተስለሽ፥ ዓመታት አልፈዋል፣ በልቤ እንደታተምሽ፥ ልጅነት ኰብልሏል። ባልተሳካው መሻት፥ በዛለው መንፈስሽ፣ ዓይንሽን ስትገልጪ፥ እርቃን ቀርታ ነፍስሽ፤ ክፍቱን እንደተውሽው፥ ቤቴን አግኝተሻል፣ ስጠብቅሽ ነበር፥ ለ'ኔ ግን ረፍዷል። መምጫ መንገድሽን ሲያይ፥ ሲባጅ የከረመው፣ በሰለለ ተስፋ፥ ታስሮልሽ የኖረው፤ ማፍቀሩን ሳይቀንስ፥ አንቺን በጠበቀ፣ ናፍቆትሽ ያሳሳው፥ የኔ ገላ አለቀ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ተመልሼ_አልመጣም ከወንጌል ቃል ሁሉ እግዜር ካስተማረው ነብስያዬን ገዝቶ ቀልቤን የማረከው ከልቡ የሆነ ይድናል የሚለው !! ምክንያቱም አለሜ ምክንያቱም ህመሜ የእውነትን ካልኖርኩ እኔ አልድንም ፆሜ ፀሎትም አይሰምር አይፈይድም ስግደት ሰደቃም አያርግ ይስሙላ ካለበት እናልሽ አለሜ ከወንጌል ቃል ሁሉ እግዜር ካስተማረው ነብስያዬን ገዝቶ ቀልቤን የማረከው ከልቡ የሆነ ይድናል የሚለው!!! ስለዚህ መሻትሽ ከልብሽ ከሆነ በፍቅራችን ቅጠል አንቺም ትድኛለሽ የኔም ነብስ ዳነ!! ግና ነብስያዬን ፍፁም ካልወደድሻት ውዴ ቀረሽብኝ አንቺም ቀረሽባት! ደግሞ ካንቺ  እርቄ ከሸሸሁኝ በጣም ውዴ ካለሽበት ተመልሼ  አልመጣም።        @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ዳዊት ጥዑማይ

#አድገናል ¡ የዘንድሮ ኑሮ ውሉም አልተያዘኝ፤ እንዴት እንዳደግነ መለኪያው አልገባኝ፤ ብቻ ግን አድገናል፤ በሁለት ዲጅት ወደ ላይ መጥቀናል¡፤ እቤታችን ድረስ ትቦ ተዘርግቷል፤ መብራት ገብቶልናል፤ ሲምም ተሰጦናል፤ ግና ውሀ የለም አንፖሉም አልበራ፤ ባዶ "ሲም" ነው እንጅ "ኔትወርኩም" አልሰራ፤ ብቻ ግን አድገናል፤ በሁለት "ዲጅት" ወደላይ መጥቀናል፤ አፍ ቀላጤ ፈርተን ሳናምነው አምነናል፤ ይህ ነው እድገታችን?፤ በሁለት ዲጅት ላይ ላይ መውጣታችን?፤ እኛም እንጮሀለን፤ እናስተጋባለን፤ ሀሰት እየሰማን አሜን እንላለን፤ እኔን እንደገባኝ.... ወደላይ ወደላይ ወደላይ መለፈፍ፤ ፍሬ ማያፈራው አበባው እስኪረግፍ፤ መና ካምላካችን ወድቆ እስኪዘረገፍ፤ ዝም አለማለት ነው መጮህ ነው ወደላይ፤ መብራቱ፣ ኔትወርኩ ውሃው የሞላላት ኢትዬጵያን እስክናይ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#መጪውን_ማን_አውቆ?! የኖረውን እንጂ ፣ የፊቱን ማን? አውቆ? እድሜው ላይ፣ ጨመር አብዝቶ ተጨንቆ? በአለፍነው ካልሆነ ፣ ህይወት የሚለካ፤ የመጪው ባለቤት ፣ እግዚአብሔር ነው ለካ፤ ትላንትን ተሻግሮ ፣ ዛሬን በእጁ ይዞ፤ የእርሱ ባልሆነ ነገ ፣ ያለቅጥ ተክዞ፤ የሚጨናነቀው ፣ ሰው በከንቱ እርቆ ፣ ያለፈውን እንጂ ፤ መጪውን ማን አውቆ? እንኳንስ ዓመታት ፣ አልፎ ለመገመት ፤ የፈት ለፊት ነገ ፣ የእኛ አይደለም ህይወት ፤ እናም ልቤ አስተውል ፣ በዛሬ ላይ ትጋ፤ ከትላንት ተምረህ ፣ በአምላክ ሀሳብ እርጋ፤ ነገማ ማን አውቆ ፣ መድረሻውን ቆጥሮ፤ ከአምላኩ በስተቀር ፣ ዛሬውን ተሻግሮ ? እንኳን ዓመታቱን ፣ እሩቅ! ቀድሞ ማየት ፤ በእግዚአብሔር እጅ ነው ፣ የዛሬው ሰአታት! በከንቱ መጨነቅ ፣ ልባችን ታውሮ ፤ ዛሬያችን ከነፈ ፣ ትላንት ሆኖ በሮ!!!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#ስጠብቅሽ_ልኑር! ቀናቶች ቢረዝሙ ቢቆጠሩ አመታት ግዜ ቢለያየን ቢያልፉብን ዘመናት ከልብሽ ባልጠፋም ከትዉስታሽ ጓዳ በስቃይ ታስሬ በናፍቆት ጎዳና ህልሜም ባይሳካ የሆዴን ባላገኝ በደስታየ ዘመን ባይተዋር ቢያረገኝ ግዴለም ችላለሁ ሁሉን ነገር ችዬ እጠብቅሻለሁ ልቤን አባብየ የሀሳብ በረዶ ይጥለቅ በአናቴ ይደንዝዝ አካሌ ይድከሙ ጉልበቴ አንገናኛለን እያልኩ በተስፋ ልጠብቅ እልፍ ግዜ ይለፍ ወዜ ሁሉ ይድቀቅ ምን ያደርግልኛል ካንች ወድያ ንሮ ፍቅርሽ ይበቃኛል የስንቅሽ ቋጠሮ በትዝታሽ ዋሻ እራሴን ደብቄ በምናቤ ስየ ፍቅርሽን ሰንቄ እጠብቅሻለሁ በተሰጠኝ እድሜ ባንች ናፍቆት ፍቅር ካልሞትኩኝ ታምሜ አዎ...ስጠብቅሽ ልኑር ሳለሁ በህይዎቴ ፍቅርም ባንች ይብቃኝ ይምከን ፍላጎቴ፡፡         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ቢታነፅ_ቢወቀር! እኔም አንድ ሰሞን ልክ እንደ ሰለሞን "ሁሉም ከንቱ ከንቱ ንፋስን መከተል ላይጥሉ መታገል: ላይከብሩ መባተል" እያልሁ አጨልሜ በራሴ ለግሜ: እፈላሰፍ ነበር! ከዚያ አንቺን አገኘሁ በጓሮ በር በኩል: ሰለሞኔን ሸኘሁ መፈጠሬን ወደድሁ ንፋስ አሳድጄ እንደ ቆቅ አጠመድሁ ከፀሀይዋ በታች: ግልገል ፀሀይ ፈጠርሁ ለኦናው አምፖሌ: ብርሀን አበደርሁ ማቅ የነበረው ጨርቅ: ሸማ ሆኖ ቆየኝ "ከንቱ የነበረው: "አንቱ" ሆኖ ታየኝ! ለካስ... ጠቢብ ቢያስተምረው መከራ ቢመክረው አካሉና ልቡ: ቢታነፅ ቢወቀር ሰው አቅሙን አያውቅም: ካልወደደ በቀር!         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ በእውቀቱ ስዩም

መልካም በዓል! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለገና በዓል በሠላም አደረሳችሁ።         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ቃና.... ከዉበት እስረኞች... ጥቁር ፍቅር ይዞኝ በንስር አይኖቼ... ፍለጋ ጀመርኩኝ የጠፋዉን ስሜን... ልመልስ አልኩና ማጣጣም ስጀምር.. የህይወቴን ቃና ለኔ ወጥመድ ሁነዉ... ዛራና ቻንድራ ሚስቴ ጋር አጣሉኝ... ማን ያቅርብ እንጀራ.....         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#አንተም_እኔም_ተጓዥ አትግፋኝ ወንድሜ ፣ በከንቱ ጥላቻ፤ ለየትኛው እድሜ ? እንኑር በጡንቻ? ለኮንትራት ዓለም ፣ ባለቤት ለሌላት፤ ከፍቅር ቀንሰን የምን? መገፋፋት ? አንተም እኔም ተጓዥ ፣ በተራ ለጣቂ፤ ማን እንደሚቀድም ፣ አምላክ ነው አዋቂ ። ስትገፋኝ ስገፋህ ፣ አንዱ ላያሸንፍ፤ መጓተት ብቻ ነው ፣ ሌላ የለንም ትርፍ ። ለፍቅርም አይበቃ ፣ የተሰጠን አድሜ፤ እኔም ነኝ ወንድምህ ፣ አንተም ነህ ወንድሜ።          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ

#ልቤን_መልስልኝ ልትሄድ  ከሆነ  ላይቀር  መለየቱ ቢበቃኝ  ይሻላል  ባንተ  መጎዳቱ። ቀልብህ  ካላረፈ  እግረኛ  ሆነህ መጓዝህ  ካልቀረ  ከእኔ  መራቅህ ለምን  አስፈለገ  ልቤን  መስረቅህ?         @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ

#ወዴት_ተሰወሩ? በሳቃችን ዘመን አብረውን የሳቁ፣ ከእናንተ ውጪ ብለው ትላንት ያደነቁ፣ ሳቃችን ሲጠፋ መከራችን ነግሶ፣ በእህ! እህ! ሲተካ በሀዘን በለቅሶ፣ ወዴት ተሰወሩ? ምንስ ከለላቸው? የትኛው ተራራ የትኛውስ እርቀት ገዝፎ ጋረዳቸው ? በዙሪያችን ከበው በክብር ሸልመው፣ በንግግራችን ፣ በማያስቅ ስቀው! ለጥቅማቸው ሲሉ ትላንት ያገጠጡ መካራ ሲገጥመን ወዴት? ፈረጠጡ?! የሉም፣ አይታዩም! ምን ጉድጓድ ዋጣቸው?! የትኛውስ እርቀት ከእኛ ሰውራቸው? የሉም! የሉም! በቃ ዛሬ የሉም! ሳቃችን ከጠፋ ከቶ አይመለሱም!!          @gitm_post     ♡ ㅤ     ❍ㅤ        ⌲                ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ     ˢʰᵃʳᵉ     ✍ ስንታየሁ ሀብታሙ