ግጥም
الذهاب إلى القناة على Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
إظهار المزيد4 810
المشتركون
+1124 ساعات
+537 أيام
+23230 أيام
أرشيف المشاركات
4 812
#ፍቅር_ወረተኛ
ፍቅር እንደሞት ጥላ በድን አደረገኝ
አጥንቴን ሰበረው ከቶ አዝለፈለፈኝ
ፍቅር በአበባው መዓዛው ጣፈጠኝ
አሁን ግን ጠውልጎ ሽታው አሰለቸኝ
የፍቅር ክፋቱ ትዝታ ነው ሲሉ
አላመንኩም ነበር ውሸት በመምሰሉ
አሁን ግን አወቅሁት ይሰማኛል ቁስሉ
የነደፈኝ መርዙ የወጋኝ ሾተሉ
ይህ ጣፋጭ እንደማር መራር እንደኮሶ
ልፍስፍስ እንደጥጥ ጥብቅ ከምሰሶ
ዛሬ ህይወት አለው ነገ ይቀራል ፈርሶ
ፍቅርን አትመኑት ቢታይ ድርብ ለብሶ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
4 812
#የተቃርኖ_ሕግ
ከመኖር ጎረቢት ሞት ድግሱን ጥሎ
በየተራ እየጠራ ተረኛን ነጥሎ
ወረፋ አሰልፎ ዳሱ እንዳይጠብበት
የይለፍ ቃል ይዞ ተስማምቶ ከህይወት
ተረኛውን ብቻ ነጥሎ ይጠራል
እሱ መች ሊሰለች ሁሌም ይደግሳል
ከፅድቅ ጎረቢት ኩነኔም ተሹሟል
ከደግነት ማዶ ክፋት ይጠብቃል
ተቃርኖ የሌለው በክፉም በደጉም
ተፈጥሮን መርምሩ አንድ አቅጣጫ የለም
እንኳን በኛ ህይወት በሞት ለሚገታ
አለው ተቃራኒ ሰይጣንም ለጌታ
ለንጋት ጨለማ ለፀሃይ ዝናብን
ለተራራ ሜዳን ለወንድ ልጅ ሴትን
በበጎ በክፉ ተቃርኖ ሕግ ነው
ያልተመሳሰለ ግን የሚሳሳብ ነው
ተመሳሳይ ቁሶች የሚገፋፉትም
በተፈጥሮ ቀመር ታጥረው የቆሙትም
የነበሩ ናቸው አዲስ ነገር የለም
ያለ ተቃራኒ ህይወት አትቀጥልም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#Tearline (1$ price in premarket 🔥)
✅|| tearline ይባላል። ይህ ኤርድሮፕ ብዙ ተጠቃሚ የለውም።
✅|| ለዛም በpre market ለአንድ የtearline ቶከን እስከ 1$ ዋጋ ደርሰዋል። 😱
✅|| በ Gate.io exchange ዋሌት የፕሪማርኬቱ ዋጋ መመልከት ትችላላችሁ።
✅|| ሊስት የሚደረግበት ጊዜ በቅርቡ ነው ተብሏል።
እጅግ ቀላል ነው። ሙሉ አሰራሩ አሳያችኋለሁ። በርግጥ ከባድ ነገር የለውም። ለጊዜው ታስኮችን እየሰራችሁ ጠብቁኝ። ከታች ባለው ሊንክ ጀምሩት 🏃♂
https://t.me/TearlineAI_Bot/app?startapp=8m9IQBTh_0
4 812
#ችግር
ችግርና አደጋ ይደርሳል በቅጽበት
ችግርን ለመቅረፍ ያለፋል ዘመናት
ይህን ለመሰለ እክል ላጋጠመው
ፈጥኖ የደረሰ አለሁልህ ያለው
የሰማይ ቤቱን ጽድቅ የምድሩን ክብር
ይጎናጸፈዋል ከራስ እስከ እግር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
4 812
Nodepay
Download Nodepay App Download & Login
ሁሉንም ታስክ ጨርሱ 600ፖይንት ይሰጣቿል ክሌም አድርጉ
Browser ላይ ማይም ማድረግ ለተቸገራቹ በ Android App ስለጀመረ አውርዳቹ ከፍታቹ ማስቀመጥ ብቻ ነው።
Join 👉 Start
4 812
ዓለም ቅንዝረኛ ብዙ ባል አግብታ
ውሽማዋ ጉቦ ከቤቷ አስተኝታ
ከሳሽ አዘንተኛ ተከሳሽ ሰርገኛ
እንግዲህ ዶሲዬ ተከናንበህ ተኛ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ድምጻዊ ፍሬው ሀይሉ
4 812
Bums በጣም በብዙ ነገር ከ X-empire ተመሳሳይ የሆነ Project ነው።
በTwitter በጣም መነጋገርያ ሆኖ ነበረ በዚህም trend ሆነው በ social media ብዙ ከተነገረላቸው መሀል አንዱ ነው።
ከሁሉም በላይ በ ቴሌግራም መስራች Pavel Durove ጭምር ስማቸው ተነስቷል።
ይሄም ጥሩ Airdrop መሆኑ ማሳያ ነው እንደምታውቁት X empire ከበፊት ጀምሮ ሲሰሩ የነበሩ ልጆች በብዙ አትርፈዋል።
አሁንም ይሄን ከመጀመርያው ጀምሮ መስራት ያዋጣል። ምን አልባት ትልቅ project ይሆናል። who knows?
ለመጀመር 👉 Start
4 812
Bums በጣም በብዙ ነገር ከ X-empire ተመሳሳይ የሆነ Project ነው።
በTwitter በጣም መነጋገርያ ሆኖ ነበረ በዚህም trend ሆነው በ social media ብዙ ከተነገረላቸው መሀል አንዱ ነው።
ከሁሉም በላይ በ ቴሌግራም መስራች Pavel Durove ጭምር ስማቸው ተነስቷል።
ይሄም ጥሩ Airdrop መሆኑ ማሳያ ነው እንደምታውቁት X empire ከበፊት ጀምሮ ሲሰሩ የነበሩ ልጆች በብዙ አትርፈዋል።
አሁንም ይሄን ከመጀመርያው ጀምሮ መስራት ያዋጣል። ምን አልባት ትልቅ project ይሆናል። who knows?
ለመጀመር 👉 Start
4 812
#የምጡ_ጅማሬ
ነፍሴ ሆይ ልንገርሽ ስሚኝ በዝምታ
ግዜው ተገባዷል ይቅርብሽ ጨዋታ
ተግተሽ በንስሐ በርቺ በፆም ጸሎት
ዘመን ተገባዷል አጭር ሆኗል ህይወት
የምጡ ጅማሬ የመከራው ዘመን
ዛሬ እያሳሳቀ ጨርሶ ሊወስደን
ሀጢያትን ለምደነው ልብሳችን ከሆነ
በዙ ዓመታት አልፏል ልብም ደነደነ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#ኮረዳ
መልኳ ጠየም ያለ ፊቷ የረቀቀ
አንገቷ ብርሌ ዳሌዋ የላቀ
ጉንጮቿ የፈኩ የመሰሉ እንኮይ
ዓይኖቿ ገራፊ ከሩቅ ሰውን ጣይ
ቅንድቦቿ መሳይ የተከረከሙ
ሽፍሽፍቷ ረጃጅም ሰው የሚያስገርሙ
ከንፈሮቿ ለጋ ሳሙኝ ሳሙኝ ባይ
ፀጉሯ አረፍ ያለ ከወገቧ ላይ
ከንፈሯ ሲገለጥ ለመሳቅ አንድአፍታ
የጥርሷ ንጣቱ ምች የሚያስመታ
አጎጠጎጤዋ መሳይ የባህር ቅል
ሰው የማያስጠጋ ገፍትሮ የሚጥል
ባቷን ተረከዟን ወገቧን ጭምር
ፈጥሮታል ፈጣሪ ምንም ሳያስቀር
በእንዲህ ያለ ውበት ወጣቱ ተነድፎ
ማሰብም አልቻለ ቀረ ተዝለፍልፎ
ዓመሏን ሞያዋን መርምሮ ሳያውቅ
ላግባሽ አግቢኝ ብሎ ሄደ ሊጠይቅ
እሱም በበኩሉ ሸጋ በመሆኑ
ወደድኩህ አለችው እዚያው ወዲያውኑ
ታጥቦ የማይጠጣ መሆኑን ቁንጅና
ያወቁም አይመስሉም የሰሙ በዝና
ሳይተዋወቁ እንዲያው በችኮላ
ተጋቡ ሰሞኑን ቃልኪዳን ተሞላ
ወርም አልሞላቸው እውነቱን ሲረዱ
ትዳር በቁንጅና ብቻ አለመሄዱ
ኋላ እንደሰማሁት ሰው እንደነገረኝ
ትዳራቸው ፈርሶ ተፋቱ ብሎ አለኝ
ሳይመራመሩ አግብቶ ከመፍታት
ይሻላል መላመድ ነገሩን ማጣራት
ባሳብ በሕሊና ደግሞም በመንፈስ
ያሻል መግባባቱ እስከሞት ድረስ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
4 812
ሳቅ እንኳን ባትፈቅዱ ማልቀስ አትከልክሉ
ግዜን ተማምናችሁ ከላይ ነን አትበሉ
አላያችሁም ወይ የጊዜን ስብራት
ከላይ አሽቀንጥሮ ሲያዛምድ ከመሬት።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#ፋኖስ_እና_ብርጭቆ
አንድ የፋኖስ መብራት በግብሩ የኮራ
እንዲህ ሲል ተጣላ - ከብርጭቆ ጋራ።
እኔ ነኝ መብራቱ ብርሀን የምሰጥ
ጨለማን አጥፉቼ የምገላልጥ
አንተ ግን ተፊቴ እንዲህ ተደንቅረህ፣
ዙሪያየን ከበኸኝ እንዲያው ተገትረህ።
አልገባኝም ከቶ የምትሰራው ስራ
ብርሀኔ እርቆ ደምቆ እንዳያበራ
አንተን ፈጠረብኝ መንገድ የምትዘጋ።
እንቅፋት እየሆንክ ስራየን አታጥፋ፣
ገለል በል ከፊቴ ብርሀኔ ይስፋ።
''እውነትማ ለንተ ከሆንኩኝ እንቅፋት፣ ልሂድልህ ብሎ ቢለቅለት ቦታ፣
ከጎን የነፈሰው የንፋስ ሽውታ
መጣና መብራቱን አጠፋው ባንድ አፉታ።
አጭር እየሆነ ተመልካችነቱ
መለየት አቅቶት ጥቅሙን ከጉዳቱ፣
እወቁኝ እወቁኝ እያለ ሲነሳ
ሰውም እንዲሁ ነው ያመጣል አበሳ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ዶ/ር ከበደ ሚካኤል
4 812
#ተራርቆ_ከእውነት
ነፃነትን ሸጦ ገንዘብን ፍለጋ
በረከሰ ስደት በረከሰ ዋጋ
ህሊናን ለውጦ በሆድ አቆማዳ
እውነትን አስይዞ መግባት ትልቅ እዳ
ጎተራው ላይሞላ መሶቡ ላይፋፋ
ለኩርማን እንጀራ በውሸት ሲለፋ
አወይ ሰው ምስኪኑ ከትላንት አይማር
ውዱን እየሸጠ ለርካሽ የሚኖር
እርካታ ሳይኖረው ባለው ሳይደሰት
ሆዱ ይመራዋል ተራርቆ ከእውነት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#ትዝታ
ወደሽኝ ወድጄሽ ትዳር መሥርተን
ከእኛ አብራክ የወጡ ልጆች አፍርተን
ሰላምና ፍቅር እየተጎናጸፍን
በደራው ቤታችን በምቾት ኑረን
የእኛን ኑሮ ማማር የምቾት ሁኔታ
እያዩ የቀኑ ነዝተው አሉባልታ
በትዳራችን ውስጥ በነዙት ሐሜታ
አጉል ተበጣብጠን ደረስን ልንፋታ
ደስ ብሎን የኖርነው በሳቅ በጨዋታ
አይዋሽ አይነቅዝ ያለፈው ትዝታ
የሰው ወሬ ንቀን የሰውን ሐሜታ
በሰላም እንኑር በፈጠረሽ ጌታ
ዕጣችን ከሆነ ተለያይተን መኖር
ላንቺም ለኔ ደስታ ለልጆቹ ክብር
ትዝ ይበለንና የኖርነው በፍቅር
እንድንጠያየቅ መኮራረፍ ይቅር
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ደራሲ ታደለ ብጡል
4 812
#መንፈሴን_አመመኝ!!
ሰምቶ ለሚያሰማ ችግሬን ነግሬ
ስሜ አደባባይ ነው የሚውለው ዛሬ
ይረዳኛል ያልኩት ያመንኩት ቢከዳኝ
አልቅስ አልቅስ አለኝ በድንገት ሆድ ባሰኝ
ለካስ እህ እያለ ችግሬን መስማቱ
ሊረዳኝ አይደለም አቤት ሰው ከፋቱ
ደግፈኝ ያልኩት ሰው ገፍትሮ ቢጥለኝ
ከስጋዬ በላይ መንፈሴን አመመኝ።
ከአረገልኝ በላይ ያደረገኝ ብሶ
ሆዴን እየባሰው ይቀናኛል ለቅሶ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#ሀገርህ_ናት_በቃ
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ ክበብ፤
አይምሽ እንጅ መሽቶ ፥ ማታው ከጠረቃ፤
የነቃም አይተኛ የተኛም አይንቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ ፥ ብቻዋን የተኛች
ከዓለም ተደብቃ!
አኪሯ ቀዝቅዞ ፥ "ያንቀላፋች ውበት"
ያንተው የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ ፥ ወይ አብረሃት ንቃ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ነብዩ መኮንን
4 812
#ይመሻል_ይነጋል!!!
የከፋው ሰው እንጂ ህግን ያጓደለ፣
ከእግዚአብሔር እርቆ አድሮ የቀለለ፣
ግዜማ ቁጥር ነው ይመሻል ይነጋል፣
የተፈጥሮ ህጉን ጠብቆ ይጓዛል።
ጥፋቱ የሰው ነው ህግ የተላለፈ፣
በደልን በጉያው ደጋግሞ ያቀፈ።
ግዜ ነው አትበሉ ግዜ ምን አጠፋ?
ሰው እኮ ነው ዛሬም በቢጤው የከፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ገጣሚ_ስንታየሁ ሀብታሙ
4 812
#አንችን_አይጠጋ
ያንጎራጎርሽልኝ በመረዋ ድምጽሽ
ሲያውደኝ የነበር ያ ሽቶ ጠረንሽ
ትራስ የነበሩኝ መክዳ ጡቶችሽ
እማኝ እንዲሆኑኝ ላድርጋቸው ነቃሽ
በዕውነት ላፈቀሩት መሆን መስዋዕት
የቆዬ ነውና ከአያት ቅድመ አያት
በወረት መደሰት እስኪያልፍ ወረት
ምኞትሽ መሆኑን አሁን አወቅሁት
ሕይወቴን አጋልጠሽ ለሕመም ለአደጋ
ፍቅሬን ቸል ብለሽ ከሔድሽ እሌላጋ
የኔውስ የኔነው ምንም አያሰጋ
ብቻ የኔ ሐዘን አንችን አይጠጋ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ደራሲ ታደለ ብጡል
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
