cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 306
المشتركون
+124 ساعات
+267 أيام
+8230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
#በአዲስ አበባ የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፀዳጃ ቤቶች ንፅህና ጉድለትና ለተላላፊ በሽታዎች ምክንያት ነው ተባለ‼️ በአዲስ አበባ ያለው የውሃ አቅርቦት ችግር ለመፀዳጃ ቤቶች ንፅህና ጉድለትና ለተላላፊ በሽታዎች ምክንያት መሆኑን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የውሃ አቅርቦት በሌለበት ሁኔታ መፀዳጃ ቤቶች ለጤና ጠንቅ ይሆናሉ ያለው ቢሮው፥ እንደ ኮሌራ እና መሰል በሽታዎች መዛመት መንስኤ እንደሚሆንም ነው የገለጸው። የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ በቀን ከ500 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ በላይ የመልቀቅ አቅም እንደሌለው የገለፀው ቢሮው ይህም ለመፀዳጃ ቤቶች ፅዳት አስቸጋሪ ሁኔታን እየፈጠረ መሆኑን አመላክቷል። አያይዞም በመዲናዋ ከሚገኙ ወደ 1 ሚሊየን አባወራዎች 40 በመቶ የሚሆኑት ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት እንደሌላቸው እና አምሥት በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም አይነት መፀዳጃ ቤት እንደሌላቸው ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል። For more upcoming news Join now and invite others👇👇👇 https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
👍 3👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ቀይ ባህር… የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች ቡድን በቀይ ባህር እና በህንድ ወቅያኖስ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚን፣ ዩኤ ዲስትሮየርን እና ሶሰት እቃ ጫኝ መርከቦችን ኢላማ ያደረጉ ስድስት ጥቃቶች መፈጸማቸውን በኢራን የሚደገፈው ቡድን ቃል አቀባይ ያህያ ሳርኤ በትናንትናው እለት ተናግሯል። አብዛኛው ህዝብ የሚኖርበትን የየመን ክፍል የተቆጣጠረው እና በኢራን የሚደገፈው የሀውቲ ሚሊሻ በመርከቦች ላይ ጥቃት የሚያደርሰው ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርቱን ለማሳየት እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል። ቡድኑ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የሆነችውን ኢሰንሀወርን በቀይ ባህር ሰማናዊ ክፍል በበርካታ ሚሳይሎች እና ድሮኖች አድርገናል ያለው ሳርኤ ይህ ጥቃት በ24 ሰአታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#GreatDam ‼️ "ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው…" ✔የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ግንባታ በተሳተፉት ኮንትራክተሮች ላይ ግድቡን በሚቃወሙ አካላት ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው መሆኑ ተገለፀ! ✔ከዛሬ 13 ዓመታት በፊት የተጀመረውና በመሃል  የግንባታ ሂደቱ ተቋረጦ የነበረዉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ በተሳተፉት ኮንትራክተሮች ላይ ከፕሮጀክቱ እንዲወጡ የማስፈራራት እና የማባበል ዛቻዎች እየተደረገባቸው መሆኑ ተገልጿል። ✔ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚገኙ ተቋራጭ ኮንትራክተሮች ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ እንደቀጠለ መሆኑን የገለፁት የፕሮጀክቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ይህም ቢሆን ግን ግንባታው በታቀደለት ጊዜ ይጠናቀቃል በማለት ተናግረዋል ሲል ካፒታል አስነብቧል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
👍 1👎 1
#" በሃይማኖት ጉዳዮች ረቂቅ አዋጅ " ላይ የመጨረሻ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ረቂቁ ከባለፈው መጠነኛ ማሻሻያዎች ተደርጎበት መቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። በመጀመሪያው ረቂቅ አዋጅ ያልነበረና የመንግሥትንና የክልሎችን ግዴታና ኃላፊነት በመዘርዘር የተቀመጠው ክፍል አንዱ ነው። በዚህ ክፍል ላይ መንግሥት በሃይማኖት አስተምህሮና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ተደንግጓል፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ከውጭ አገር የሚላክለትን የገንዘብ ዕርዳታ፣ ስጦታ ወይም ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን በሕግ ሥልጣን ለተሰጠው አካል ማሳወቅ እንደሚኖርበት ተደንግጎ የነበረው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ከተሻሻለው ረቂቅ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን ማንኛውም የሃይማኖት ተቋም ፦ ✔ የሃይማኖት ተቋሙን ኦዲት ሪፖርት ለሰላም ሚኒስቴር እንዲያቀርብ፣ ✔ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ #በ3_ወራት የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በገለልተኛ ኦዲተር ማስመርመር እንደሚኖርበት የተቀመጠው የረቂቁ ክፍል በተሻሻለው ላይ #ተካቷል፡፡ ሌላኛው ተሻሽሎ የቀረበው የረቂቅ ክፍል አለባበስን እና የተማሪዎች አመጋገብን ጨምሮ በማንኛውም የትምህርት ተቋም ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ተግባር የመንግሥትና ሃይማኖት መለያየት መርህንና የሃይማኖት ነፃነትንም በጠበቀ መንገድ መከናወን አለበት የሚለው ነው፡፡ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ የመጨረሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በመንግሥት እና በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት ምን ድረስ እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቷል ብለዋል። አዋጁን ማዘጋጀትም ያስፈለገው ይህን ጉዳይ በግልጽ ለማስቀመጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት በሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ውስጥ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው  ፤ ነገር ግን አብረው በሚሠሩባቸው ጉዳዮች በሕግ የተቀመጠ አሠራር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የተነሱ ሐሳቦችን በግብዓትነት ወስዶ ለሚመለከተው አካል የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ እንደሚያዘጋጅ ተገልጿል፡፡ (Reporter Newspaper) ቤተሰብ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

👍 3 2
Photo unavailableShow in Telegram
#Ethaopia ‼️🥲 ትልልቅ ስብሰባዎችን እና ኮንፈረንሶችን በማዘጋጀት ኢትዮጵያ ከጥቂት አመታት በፊት አንዳንዴ 2ኛ፣ ሌላ ግዜ 3ኛ እና 4ኛ ሆና ትታወቅ ነበር። ከኒውዮርክ እና ጄኔቫ በመቀጠል የአለም ሶስተኛዋ የዲፕሎማቲክ ካፒታል የምትባለው አዲስ አበባ እንደ አፍሪካ ህብረት እና ECA ያሉ ትላልቅ ድርጅቶች መቀመጫ ሆና ሳለ በቅርብ አመታት ኢኮኖሚያቸውን ባዘመኑት እነ ርዋንዳ እና ኬንያ ቦታዋን ተነጥቃለች። እነዚህ ኮንፈረንሶች ሲካሄዱ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የውጭ ምንዛሬ እንዲሁም ሀገርን በማስተዋወቅ በኩል ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው። በትኩረት ሊሰራበት ይገባል። Via:EliasMeseret https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
👍 5
Photo unavailableShow in Telegram
#ቅምሻ ልዩ መረጃዎች! በዐማራ ክልል ማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በመንግሥት የፀጥ ኃይሎች እየወደሙ ነው። 1)  ለጤና ተቋማት የተመደቡ 587 በላይ አምቡላሶች ለወታደራዊ አገልገሎት ለወታደራዊ ቁሳቁሶች ማመላለሻ እየዋሉ ነው። ሕክምና ተቋማት መድረስ የነበረባቸው 1731 እናቶች ባለፉት 9 ወራት ከወሊድ እና ከአምቡላስ እጥረት ጋር በተያያዘ ደም ፈሷቸው ሕይወታቸው አልፏል። 15,607 ሕፃናት ከሕክምና አገልግሎት ባለማግኘታቸው ህይወታቸው አልፏል። 2) በዐማራ "ክልል" 184 ትምህርት ቤቶች 42 ሞያና ቴክኒክ ኮሌጆች  ወታደራዊ ጣቢያ (ካምፕ ሆነዋል) የትምህርት ቤቶቹ መገልገያ መሣሪያዎች ተዘርፈዋል። ወድመዋል። ወንበሮች እየተፈለጡ ለምግ ማብሰያ ሆነዋል። አምስት ሚሊየን ሁለት መቶ ሽህ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ አልሄዱም። 3) ጤና  ተቋማትን በተመለከተ 116 ጤና ተቋማት አገልግሎት አቁመዋል። 94 የጤና ባለሞያዎች ድብደባ እስራት ተፈጽሞባቸዋል። መረጃዎችን ከዐማራ ክልል ቢሮዎች ነው የተገኙት! ግንቦት 25/2016 ዓ.ም https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
👍 2
#Oromiya ‼️ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከክልሉ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ እየመከሩ ነው።ውይይቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
#MoE የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተናን በኦንላይን የሚወስዱ ተፈታኞች በክላስተር የተዘጋጀ ማስፈንጠሪያ (URL) ላይ በመግባት እንዲለማመዱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል። ከስር የተቀመጡት ማስፈንጠሪያዎች ተፈታኝ ተማሪዎች የሚለማመዱበት ሲሆን የፈተናው ዕለት ደግሞ መፈተኛ ይሆናሉ። Note: እስካሁን Username እና Password ያለገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ➧ ክላስተር አንድ አዲስ አበባ፦ https://c2.exam.et ሲዳማ ክልል፦ https://c2.exam.et ትግራይ ክልል፦ https://c2.exam.et ➧ ክላስተር ሁለት ደቡብ ም/ኢ/ክልል፦ https://c3.exam.et ጋምቤላ ክልል፦ https://c3.exam.et አማራ ክልል፦ https://c3.exam.et ➧ ክላስተር ሦስት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፦ https://c4.exam.et ሀረሪ ክልል፦ https://c4.exam.et አፋር ክልል፦ https://c4.exam.et ኦሮሚያ ክልል - 1 • አዳማ ከተማ፦ https://c4.exam.et • አጋሮ ከተማ፦ https://c4.exam.et • አምቦ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ አርሲ፦ https://c4.exam.et • ምዕራብ አርሲ፦ https://c4.exam.et • አሰላ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ባሌ፦ https://c4.exam.et • ባቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቤሾፍቱ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቦረና፦ https://c4.exam.et • ቡሌ ሆራ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ቡኖ በደሌ፦ https://c4.exam.et • ዶዶላ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ባሌ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ቦረና፦ https://c4.exam.et • ጉጂ፦ https://c4.exam.et • ምሥራቅ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et • ምዕራብ ሐረርጌ፦ https://c4.exam.et • ሆለታ ከተማ፦ https://c4.exam.et • ሆሮ ጉዱሩ፦ https://c4.exam.et • ኢሉባቦር፦ https://c4.exam.et ➧ክላስተር አራት ድሬዳዋ ከተማ፦ https://c5.exam.et ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል - 2 • ጅማ፦ https://c5.exam.et • ጅማ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ቄለም ወለጋ፦ https://c5.exam.et • ማያ ከተማ፦ https://c5.exam.et • መቱ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሞጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሞያሌ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ነጆ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ነቀምት ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሮቤ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሰንዳፋ በኬ፦ https://c5.exam.et • ሻኪሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሻሸመኔ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሸገር ከተማ፦ https://c5.exam.et • ሸኖ ከተማ፦ https://c5.exam.et • ምስራቅ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ)፦ https://c5.exam.et • ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ሸዋ፦ https://c5.exam.et • ምስራቅ ወለጋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ወለጋ፦ https://c5.exam.et • መዕራብ ጉጂ፦ https://c5.exam.et • ወሊሶ ከተማ፦ https://c5.exam.et https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja

Photo unavailableShow in Telegram
#አማራ ‼️ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኤፍራታና  ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አልብስ አደፍራሽ ትናንት ግንቦት 24/2016 ዓ.ም ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በቤታቸው እያሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው ይከታተሉ https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
“ ይህ የሪያል ማድሪድ ታሪክ ነው “ አስራ አምስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ድላቸውን የተጎናፀፉት ሪያል ማድሪድ የቡድን አባላት ከድሉ በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ከተሰጡ አስተያየቶች መካከልም ፡- - “ አስራ ስድስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ስለማሸነፍ ከአሁኑ እያሰብን እንገኛለን “ ናቾ - “ ይህ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሪያል ማድሪድ ታሪክ ነው “ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ - “ እድለኛ ከሆንኩኝ ከሪያል ማድሪድ ጋር ስድስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን አነሳለሁ “ ካማቪንጋ - “ ይህ ቡድን ቤተሰብ ነው ፣ የስኬታችን ዋነኛ ሚስጥር ይህ ነው። አስራ ስድስተኛው የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ቀጣይ አመት ማሸነፍ እንፈልጋለን። “ ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ - “ ወደ ሪያል ማድሪድ ስመጣ አንድ ህልም ነበረኝ ቢያንስ አንድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ማሸነፍ ነበር።” ሉካ ሞድሪች - “ ይህ ቀን በህይወቴ ከተደሰትኩባቸው ቀናቶች መካከል አንዱ ነው ፣ ህልሜ እውን ሆኗል “ ሲል አምበሉ ናቾ ተናግሯል። ቶኒ ክሩስ ፣ ሉካ ሞድሪች ፣ ናቾ እና ዳኒ ካርቫሀል በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት ስድስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል። https://t.me/Satenawmedia1
إظهار الكل...
ሳተናው ሚዲያ / Satenaw Media

ትክክለኛ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ! #Ethiopia #Ethiopianews #Addismereja