cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እወድሻለሁ

Etio_Ortodocks

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
193
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

f2a239aafe6b9882582b93702ae7e8fb.mp44.54 MB
12eacb8da320fd78ce38702ee5bdf963.mp46.21 MB
544f5cca04189792a6bc0a716d1b9fb9.mp43.46 MB
3f5b8a847247426772414d9440631ea9.mp42.46 MB
ea8ba8607390101955d10b3b83b49ced.mp48.22 KB
9bc86cf3fc176708166bd332a64f266b.mp46.04 MB
7a1ee2fb18157dd37c39d047c1826e11.mp44.98 MB
2022-05-06-182657580.mp446.68 MB
2022-05-06-182915210.mp423.56 MB
Like,follow,share አድርጉ
إظهار الكل...
06:50
Video unavailableShow in Telegram
_የመስቀሉ_ነገር_ሲገባን_ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኃይሉ1080p.mp438.75 MB
2.94 MB
5.46 MB
01-ምዕናም አንቲ.amr0.87 KB
01-መኣዛ ጣዕሙ ለተአምርኪ.amr0.62 KB
01-ርዕይዎ ኖሎት-1.amr0.79 KB
01-ሰላም ለክሙ-1.amr0.67 KB
​​† እንኳን ለታላቁ ኮከበ ገዳም አባ እንጦንስ እና ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! #አባ_እንጦንስ በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ / ዓቢይ / THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው:: አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው:: በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን:: ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው:: ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት:: ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል:: ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ:: ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ:: እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል:: አባ እንጦንስ የመነኮሳት ሁሉ አባታቸው: ለገዳማውያን ሁሉም ሞገሳቸው ናቸው:: እንዲያውም ብዙ ጊዜ "ኮከበ ገዳም: ማኅቶተ ገድል (የበርሃው ኮከብ: የተጋድሎ መብራት)" ተብለውም ይጠራሉ:: ቤተ ክርስቲያን ለጀማሪዎች ትልቅ ትኩረት ትሰጣለች:: ለምሳሌ:- አባ ዻውሊን (የካቲት 2 የሚከበሩ) ለብሕትውና መሠረትን ስለ ጣሉ "አበ ባሕታውያን" ብላ ታከብራለች:: አባ እንጦንስን ደግሞ "አበ መነኮሳት (የመነኮሳት አባት): ቀዳሚሆሙ ለመነኮሳት (ለመነኮሳት ቀዳሚና ጀማሪ) ስትል ትጠራቸዋለች:: አባ እንጦንስ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚነሱ ቅዱሳን መነኮሳት ሁሉ መንገድን ይጠርጉ ዘንድ ብዙ መከራን በትዕግስትና በአኮቴት ተቀብለዋል:: ላለፉት 1,700 ዓመታት እንደ ሻማ እየቀለጡ ያበሩ አበው ቅዱሳን ሁሉ የአባ እንጦንስ ልጆች ናቸው:: ከምጥ የከፋ የዲያብሎስ ፈተናን ተቀብለው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ቅዱሳኑን ወልደዋል:: የመነኮሳት አለቃ የሆኑትን ታላቁን መቃርዮስን ጨምሮ በርካቶችን አመንኩሰው ለቅድስና አብቅተዋል:: አባ እንጦንስ ግብጻዊ ሲሆኑ የተወለዱት አቅማን በምትባል ቦታ አካባቢ ነው:: ጊዜውም በ252 ዓ/ም ነው:: የተባረኩ ወላጆች ለቅዱሱ እንጦንስና አስከትለው ለወለዷት ሴት ልጃቸው : አስቀድመው ፍቅረ ክርስቶስን: አስከትለውም ሃብት ንብረታቸውን አውርሰው ዐርፈዋል:: በዚህ ጊዜ የአባ እንጦንስ እድሜ አፍላ ወጣትነት ላይ ነበር:: በልጅነት ጊዜአቸውም አባ እንጦንስን ሲስቁ: ሲጫወቱ: አልያም ሲቀልዱ አየሁ የሚል ሰው አልነበረም:: ፍጹም ቁም ነገረኛና ታዛዥ: በዚያ ላይም አስተዋይ ነበሩና ሙሉ ጊዜአቸውንም ከቅዱስ ቃሉ በመመገብ: በትምሕርትና በማስቀደስ ያሳልፉ ነበር:: ዘወትርም ዜና ሐዋርያትን እያነበቡ በመንፈሳዊ ቅናት ይቃጠሉ ነበር:: በጊዜው የምናኔ ሕይወት ጐልቶ ባለ መገለጡ አባ እንጦንስ የሚያደርጉት ይጨንቃቸው ነበር:: ሲጸልዩም "አበው ሐዋርያት ይሕንን ክፉ ዓለም ንቃችሁ ጌታችሁን የተከተላችሁበት ጥበብ እንደ ምን ያለ ነው!" እያሉ ይደነቁ ነበር:: መሻታቸውን ያወቀ ጌታም ምሥጢርን ገለጠላቸው:: አንድ ቀን በቅዳሴ ላይ ወንጌል ሲነበብ ካህኑ ስለ ምናኔ የሚጠቅሰውን ክፍል አነበበ:: ለአንድ ባለ ጠጋ ሕግጋትን ከነገረው በሁዋላ "ፍጹም ልትሆን ከወደድክስ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ተከተለኝ" (ማር. 10:17) የሚለውን ጥቅስ ሲሰሙ ተገርመው "ጌታ ሆይ! ይህንን የተናገርኸው ለእኔ ነው" ሲሉ አሰቡ:: በቀጥታም ሃብታቸውን ለአካባቢው ሰው አካፍለው: እህታቸውን ከደናግል ማሕበር ደምረው እርሳቸው ወደ ዱር ሔዱ:: ከዚህች ቀን ጀምረው አባ እንጦንስ ከ80 እስከ መቶ ለሚገመቱ ዓመታት ከአጋንንት ጋር በጦርነት ነበር የኖሩት:: በንጹሕ አምልኮታቸውና በቅድስናቸው የቀና ጠላት ሰይጣን በብዙ ጐዳና ፈተናቸው:: አቅም ቢያጥረው አራዊትን መስሎ ታገላቸው:: በዚህ አልሳካ ቢለው የእሳት ሰንሰለትን አምጥቶ ገረፋቸው:: በሞትና በሕይወት መካከል ጥሏቸው ሔደ:: ወድቀው ያገኟቸው ሰዎች ለዘመዶቻቸው ሰጥተዋቸው አገገሙ:: ልክ ሲነቁ ግን ፈጥነው ወደ በርሃ ተመለሱ:: ሰይጣን በርሃው የቅዱሳን ማደሪያ እንዳይሆን ሰግቷልና ጨክኖ ታገላቸው:: ግን አልቻላቸውምና ተረታ:: አምላከ ኃያላን ክርስቶስ ከቅዱሱ ጋር ነበርና:: ከዚህ በሁዋላ ግን ጸጋው በዝቶላቸው ድውያንን የሚፈውሱና ሰይጣን የማይቀርባቸው ሰው ሆኑ:: በረዥም ዘመነ ቅድስናቸውም:- 1. ብዙ አርድእትን ከመላው ዓለም ሰብስበው: አስተምረው: ምናኔን ከግብጽ ማዶ በመላው ዓለም አስፋፉ:: 2. በደመና እየተጫኑ ብዙ አሕጉራትንም እየዞሩ ሰበኩ:: በዚህም አሕዛብን ወደ እምነት: ኃጥአንን ወደ ንስሃ መለሱ:: 3. ጊዜው ዘመነ ሰማዕታት ነበርና ወደ አደባባይ ሒደው ከሃዲዎችን ገሠጹ:: ማንም ደፍሮ ግን አልገደላቸውም:: እነዚህንና ሌሎች ተግባራትን እየሠሩ በቅዱስ ሚካኤል እጅ መነኮሱ:: እርሳቸውም ብዙዎችን አመነኮሱ:: አርጅተው እንኩዋ ከተጋድሎ ያላረፉት አባታችን የጣመ ነገር ቀምሰው: ገላቸውን ታጥበው አያውቁም:: በ372 ዓ/ም በዚህች ቀን ሲያርፉም ዕድሜአቸው 120 ደርሶ ነበር:: የአባ እንጦንስን በዓል ለማክበር የምትሹ ቤተ ክርስቲያናቸው ጎንደር ከተማ ከቀሃ ኢየሱስ በላይ ይገኛል:: ለአባታችን እንጦንዮስ /እንጦንስ/ እንጦኒ ክብር ይገባል! ዝክረ ቅዱሳን 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
إظهار الكل...

በቅድሚያ በያላቹሁበት ሰላማቹሁን ያብዛላቹሁ🙏 👆 👆👆👆👆👆👆👆👆👇 👍የእለቱ መልእክት ነዉ✍ 👆👆👆👆👆👆 ለምን ይሆን? አንተበውድ ሆስፒታል ተወልደህ ይሆናል፣ እኔ በቤት ውስጥ ተወልጄአለሁ፤ ሁለታችንም በህይወት እየኖርን ነው። አንተ በግል ትምህርት ቤት ተምረህ ይሆናል፣ እኔ በመንግስት ትምህርት ቤት ተምሬአለሁ፤ ሁለታችንም በአንድ ዩንቨርስቲ ጨርሰናል። አንተ ከምቹ አልጋ ላይ ከእንቅልፍህ ነቅተህ ይሆናል፣ እኔ ከመሬት ላይ፤ ሁለታችንም የሰላም ሌሊት አሳልፈናል። አንተ የለበስካቸው ልብሶች ውብና ውድ ይሆናሉ፣ የኔ ቀላልና ርካሽ ናቸው፤ ሁለታችንም ራቁትነታችንን ሸፍነናል። አንተ ብዙ የምግብ ዐይነቶችን ከጥሩ መስተንግዶ ጋር አማርጠህ በልተህ ይሆናል፣ እኔ ቤት ያፈራውን ወስጄ በልቻለሁ፤ ሁለታችንም ግን የምግብ ፍላጎታችንን ለማርካት ስንል ተመግበናል። አንተ Land Cruser TurboV8፣ Range Rover፣ Lexus Jeep፣ Hummer Jeep ወይንም G Wagon...መኪናትነዳ ይሆናል፣ እኔ የህዝብ ትራንስፓርት እጠቀማለሁ፤ ሁለታችንም ግን ወደፈለግንበት መዳረሻ ደርሰናል። ምናልባት ይሄንን ልጥፍ (post)እያነበብክ ያለኸው፤ በSamsung Galaxy 8Edge፣ በiPhone7s+፣ በSony Xperia፣ በGoldvish Le Million ወይንም በVertu Signature Cobra...ስልክህታግዘህ ይሆናል፣ እኔ ይህንን የምፅፈው ስክሪኑ በተሰበረ ስልኬ ቢሆን እንኳ ሁለታችንም መልእክቱ እኩል ይታየናል። ይሀውልህ፤ ህይወት የፉክክር መድረክ አይደለም። ነገሮችን ለማሳካት ብዙ መንገዶች ቢኖሩ እንኳ ሁሉም የህይወት መስመሮች የሚመሩን ወደ አንድ አቅጣጫ ነው። ይኸውም- ሞት። ደግሞ ደስታ ሁሉንም ነገር በማግኘት ውስጥ አይመጣም፣ ካለህ ነገር ውስጥ መልካሙን በማውጣት እንጂ። ትልቁ ቁምነገር ያለው ራስህን የምታይበት መነጽር ነው። ደስታ ማለት የምትወደውን ማግኘትም አይደለም፣ ደስታ ማለት ያገኘኸውን በቂ ነገር መውደድ ነው። ልብ በል፤ ያንተ በዚህ አለም መኖር የሚያስደስተው ሌላውን ሲሆን አንተን የሚያስደስትህም የሌላው መኖር ነው። የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም፤ ምንም ሳትይዝ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው፤ ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ። ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ። ከሞትክ በኋላስ? ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ። ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ። ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል፤ መቀመጫህ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል። ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል። ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiateማድረግ)ይጀምራል። ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ። ታዲያ፤ • ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት? • ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት? •ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር፣ ጭቅጭቅና ንትርክ? • ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት? •ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ? •እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ? ጥለህ ለምትሄደው አለም?!።እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር። ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...ሁሉንምበሰው'ነቱ እኩል- ተመልከት፣ ስማ፣ እርዳ፣ አድንቅ፣ አመስግንም። ምክንያቱም የሁላችንም ፍጻሜ አንድ ሥፍራ- መቃብር ነውና!።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። ራስህንም በዚህ ምድር ብቻ አትለካው፣ ከዚህ አለም ወዲያ ያለውን ህይወት አስብ። ሁለቴ የተወለደ አንድን ሞት፣ አንዴ የተወለደ ግን ሁለት ሞት ይሞታልና ቀን ሳለ በየእምነታቹሁ ወደ ፈጣሪህ ተጠጉ። ሁልጊዜም በፈጣሪ ደስ ይበልህ!! ሽ 👆👆👆👇 😎 👕👍LIKE 👖 👇👇👇👇👇👇👇 ❤️ሌሎችም join እዲያደርጉ ❤️Share 😘 Share 😘 ️@Ewnetawoch11 @Ewnetawoch11 @Ewnetawoch11
إظهار الكل...
"ሰው እና መላዕክት በዚያች ዕለት አበረው ጮኹ" ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ኢትዮጵያ ርዕሰ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ በዚቁ " ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላዕክት " "እረኞች አዩት መላዕክትም አመሰገኑት " ብሎ ያስቀመጠው ሀይለ ቃል ይዘን ወደ ኃላ እንመለስ ዘንድ እሻለው። መጽሐፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሸክላ ሰሪ የሚሰራው የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ። ፈጥሮ አልቀረም መንክር በሆነ ምሥጢር ተወለደ። ይህን ድንቅ ነገር ያዩ ሰዎች(እረኞች) እንዲሁም መላዕክት በታላቅ ደስታ ሆነው በዚህች ዕለት አብረው በምስጋና ጮኹ። ይህ ዛሬ ሊደገም ግድ ሆነ። " መኑ የሐዩ እሞት ወእይሬእያ" "ሕያው ሆኖ የሚኖር፥ሞትንስ የማያይ ማን ነው? "መዝ 89፥48 እንዲል ሞት በማሕፀንዋ ፍሬ ተሰባብሮዋልና እየተብረከረከ ወደ ድንግል ቀረበ። ነፍሷ ከስጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሃንን እያየች ነበር። ልጅዋንም ልመናዬን ትሰማ ዘንድ እለምንሀለው ብላ እንድንድንባት ዘንድ ቃል ኪዳን ከተቀበለች በኃላ አረፈች። በዚህ ጊዜ ሰው እና መላዕክት አብረው ጮኹ። ዳሩ ግን ጨኻታቸው እንደቀደመው አልነበረም። አርያም በጣፋጭ የመላዕክት ዝማሬ ተሞላ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች።ስለዚህ ሊገልጹት በማይችሉት በተለያየ ዜማ ሰውና መላዕክት በዚህች ዕለት አብረው ጮኹ። ገብሩ ለሐዲስ ሐዋርያ እንኳን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.