cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም

በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
3 274
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+127 أيام
+4430 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
🚧 ስልጠናው የወሰዳችሁ የማህበሩ አባላቶች በመሉ! ➡️የሰልጣኝ ድርጅት ባለቤቶች ወይንም ስራ አስኪያጆች በዝግጅቱ ላይ እንድትገኙልን በማክበር እንጋብዛለን፡፡ ➡️ስልጠናውን ወስዳችሁ የሰርተፊኬት ብር 2,500 ክፍያን ያልፈፀማችሁ ጥቂት ድርጅቶች ክፍያውን ባምቢስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ በሚገኘው ኃይለ ገብርኤል ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ባለው የማህበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይንም በማኅበሩ የባንክ አካውንት 1000336931197 በማስተላለፍ እስከ ነገ ሐሙስ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ክፍያውን እንድትፈፅሙ ማህበሩ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 🔷 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭ ማህበር
إظهار الكل...
1
Photo unavailableShow in Telegram
3🥰 1
የፕሮጀክቶች መዘግየት ከ16 ቢሊዮን በላይ ብር ተጨማሪ ወጪ አስወጥቷል የመጀመሪያ ውለታቸው ሳይጠናቀቅ በሌላ ጨረታ ወደ ግንባታ የገቡ 13 ፕሮጀክቶች ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን ዋና ኦዲተር ይፋ አደረገ፡፡ የፕሮጀክቶች መቋረጥ የሚያስከትለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ሊቀንስ የሚችል አሠራር ባለመዘርጋቱ በናሙና ከታዩ 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ ውለታቸው ሳይጠናቀቁ በሌላ ጨረታ ወደ ግንባታ የገቡ 13 ፕሮጀክቶች በመንግሥት ላይ በድምሩ 16 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ ማስከተላቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ይፋ አድርጓል፡፡ የፕሮጀክቶች መቋረጥ በመንግሥት ሃብት ላይ እየፈጠረ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ብክነት ሊቀንስ የሚችል ሥራ አስቀድሞ እየተሠራ ባለመሆኑ የተፈጠረ ችግር መሆኑን ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ አመልክተዋል። የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ባቀረበው የ2015 ዓ.ም የፌዴል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ የምክር ቤት አባላት በፕሮጀክቶች መቋረጥ የሚደርሰውን የገንዘብ ብክነት የሚቀንስ አሠራር እንዲዘረጋ እንዲሁም ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሪፖርት ካካተታቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የፌዴራል መንግሥት የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የተቋረጡ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች አፈጻጸም አንዱ ነበር፡፡ በፌዴራል በጀት የሚሠሩ ፕሮጀክቶችን ያያዙ ሥራ ተቋራጮች የያዙትን ፕሮጀክት ሳያጠናቅቁ ወይም አፈጻጸማቸው ሳይታይ በሌላ ጨረታ ላይ እንዳይወዳደሩ የሚከለክል አሠራር ሥርዓት ተዘርግቶ ቁጥጥር እና ክትትል አለመደረጉን ሪፖርቱ አንስቷል፡፡ በዚህ ምክንያትም የውል ዋጋቸው በድምሩ 10 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ 12 ፕሮጀክቶች በሁለት ሥራ ተቋራጮች የተያዙ መሆናቸውንም ነው ያመለከተው፡፡ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በውስን ፕሮጀክቶች ክትትልና የቁጥጥር ሥራ የጀመረ ቢሆንም፤ ኢትዮጵያ በምትተገብረው የፕሮጀክት ልክ የተደራጀና የተቀናጀ የቁጥጥርና ክትትል ሥራ አለማከናወኑን ጠቁሟል፡፡ በዚህም ምክንያት በናሙና ከታዩ 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ የ38 ፕሮጀክቶች ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና በውለታቸው መሠረት ያልተወረሰ ወይም ገቢ ያልተደረገ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ዋና ኦዲተር በናሙና ከተመለከታቸው 41 የተቋረጡ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለ25 ፕሮጀክቶች ከተከፈለው የቅድመ ክፍያ ብር ሦስት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ውስጥ ሁለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ተመላሽ ተደርጎ ለሌላ የልማት ሥራዎች እንዲውል ያልተደረገ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ በሠራተኞችና በኅብረተሰቡ ጤንነትና ደኅንነት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ ባለመሆኑም በናሙና የታዩ ግንባታ ላይ ባሉ ሰባት ፕሮጀክቶች ላይ የሚሠሩ ተቋራጮች የቅድመ መከላከል ሥራዎችን አሟልተው እየሠሩ አለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ለ24 ሥራ ተቋራጮች መመሪያው የማይፈቅደው ደረጃ የተሰጠ መሆኑና ለልዩ ሥራ ተቋራጭ የተሰጠው የብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ እና በመመሪያው ላይ የተቀመጠው ዘርፍ የማይመሳሰል ሆኖ በኦዲት የተገኘ መሆኑንም አመልክቷል፡፡ በጠቅላላ፣ በሕንጻ፣ በመንገድና በልዩ ልዩ ሥራ ተቋራጭነት ዘርፍ ኢንቨስትመንት ወስደው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ 261 የውጭ ሀገር ሥራ ተቋራጮች እንዳሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡ ሆኖም ግን ከ11 ሥራ ተቋራጮች ውጭ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ሁሉንም የውጭ ሀገር ሥራ ተቋራጮች በምዝገባ መመሪያው ላይ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የብቃት ማረጋገጫ በመስጠት ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ አለመሆኑም ተጋልጧል፡፡ ከ11 ሥራ ተቋራጮች ውስጥም የተቀመጠውን አነስተኛ መስፈርት ሳያሟሉ የብቃት ማረጋገጫው የተሰጣቸው ሦስት ሥራ ተቋራጮች መኖራቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ ባለሥልጣኑ ጊዜያቸውን ጠብቀው በማያድሱ ሥራ ተቋራጮች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ዋና ኦዲተር በናሙና ከተመለከታቸው 40 ሥራ ተቋራጮች ማኅደር ውስጥ 36ቱ ጊዜያቸውን ጠብቀው አለማደሳቸውን መታዘቡን በሪፖርቱ አመልክቷል። ለባለሥልጣኑ በላከው ሪፖርትም የቁጥጥር ሥራው እንዲጠናከር ማሳሰቢያ መሰጠቱንም አመልክቷል፡፡ (ኢፕድ)
إظهار الكل...
👍 1 1
Photo unavailableShow in Telegram
The 5 most popular types of construction equipment.
إظهار الكل...
3
ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ካቢኔ 3ኛ ዓመት 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ካፀደቃቸው ጉዳዮች አንዱ የመንገድ ሴት ባክ (Set Back) አጠቃቀምን በተመለከተ ....
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ምሽት 2፡30 በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን!
إظهار الكل...
2
➡️ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከካም ሴራሚክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር  በመሆን ከ2 ቢሊዮን  በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት  የሴራሚክ አምራች ፋብሪካ አቋቋሙ። ⏺ የፋብሪካው ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ ምርት እንደሚገባ በስካይ ላይት ሆቴል  በተደረገው ይፋዊ የአክሲዮን  የመመስረቻ ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል። ⏺ በስምምነት የፊርማ ስነ-ስርአቱ የተከበሩ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሥራ መመሪያ እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ⏺ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ወ/ሮ  መልእክት ሳህሉ ተገኝተዋል።
إظهار الكل...
👍 3🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ፈሰስ ተደርጎበት ለሚገነባ ኩባንያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፣ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን የመሰረተ ድንጋዩን አስቀምጠዋል። የሚገነባው ማምረቻ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን የሚያመርት ሲሆን በፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ እና ትሬዲንግ ኩባንያ አማካኝነት ነው የሚገነባው። በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም÷ ወደ ኮርፖሬሽኑ ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻውን በ11 ሄክታር የለማ መሬት ላይ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ኩባንያ ከ1 ኘጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ የግንባታ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቶቹን ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት እንደሚልክ ተገልጿል። (FBC)
إظهار الكل...
👍 1👏 1
እንኳን ደስ አለን!!! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኔ 4/2016ዓ/ም ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ የባለስልጣኑን አዋጅ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በአፈጻጸም ትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለማረምና ከዘመነ አሰራር ጋር ለመራመድ የሚያሥችል፣ ብሎም የሃገር ዉስጥ ተወዳዳሪዎች ያላቸዉን ተሳትፎ ለማበረታታት የሚያስችል ድንጋጌ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በመንግስት ልማት ድርጅቶች  ጭምር ተፈጻሚ መሆኑንና የሚከሰቱ የሕግ ጥሰቶች የሚያስከትሉትን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ያካተተ አዋጅ መሆኑም ተነግሯል፡፡ የባለስልጣኑ ረቂቅ በአዋጅ ቁጥር 1333/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል፡፡ (መግንባ)
إظهار الكل...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
👉 የዛሬ የሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን 🚧 ይህ የሬድዮ ፕሮግራም የሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተለያዩ የግንባታ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ የግንባታ ግብዓት ችግር፣ የቴክኖሎጂ ዕጥረት፣ ብቁ የሆነ ባለሙያ አለመገኘትና የግንባታ ደህንነት ወይንም ሴፍቲ እና ሌሎችም ጉዳዮች የሚነሱበት ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ ⏺ ወቅታዊ በዛሬው ወቅታዊ ፕሮግራማችን ላይ የምንመለከተው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ያካሄደውን መድረክ በተመለከተ ወደ እናንተ የምናደርሰው መረጃ ይኖረናል፡፡ 👷የእንግዳ ሰዓት -  ኢ/ር ጀበል ጀማል የጀጀኮን ኮንስትራክሽን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ እና ኢ/ር ሀብታሙ ታደሰ የቲዌይ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋር በእንግዳ ሰዓት ፕሮግራማችን ላይ በቀጥታ ስርጭት የምናደርገው ቆይታ እንደተጠበቀ ነው፡፡ ዛሬም እንደተለመደው ስራ ተቋራጮች በተመለከተ የምናነሳቸው ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ በዚህ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ደግሞ ማንሳት የምትፈልጉት ጥያቄም ካለ እንደተለመደው አድርሱን፡፡ እንቀበላለን፡፡ 🥍📻 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችንን ትከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
إظهار الكل...
👍 2 1
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.