ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)
الذهاب إلى القناة على Telegram
በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙር ሆነችኝ።መዝ-118:54 ሸር በማድረግ ተባበሩን👇👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21
إظهار المزيد7 106
المشتركون
+524 ساعات
+407 أيام
+11230 أيام
أرشيف المشاركات
1✞ የትንሣኤው ጌታ
የትንሣኤው ጌታ ሊያ_ነሳን ተነሳ /2/
ሙስና መቃብርን በኃይሉ ድል ነሳ/2/
ነብሱን በስልጣኑ ከስጋው የለየው
ዳግመኛም በኃይሉ ምት ድል አረገው
ሙታንን ያድን ዘንድ በፍቃዱ የሞተው
ከሙታን ተነስቷል እነሳለው ያለው
አዝ__
እንደ_ኃያሉ ሰው እንደ ተወው ስካር
ተነሳ ክርስቶስ ድል አርጎ መቃብር
እሱም ጠላቶቹን ከኋላ መታቸው
የዘላለም አሳር እነሆ ሰጣቸው
አዝ__
እንደተናገረው በአፈ ነቢያት
ከሙታን ተነሳ አምላከ አማልክት
ወዶን ከሰማያት እንደ ወረደልን
የሙታን በኩር ሆኖ ጌታ ተነሳልን
አዝ__
እንደተናገረው ተነስቷል ክርስቶስ
ሞትን አሰናብቶ ችንካሩን ሰበረው
ከሙታን ተነስቶ በሶስተኛው ቀን
እስራችን ተፈታ ሰላም ሆነልን
አዝ__
በእምነት ገሰገሰች ማልዳ ከመቃብሩ
እውነታው ቢከብዳት ባያስተኛት ፍቅሩ
የአምላኮን መነሳት ሰምታ ከመላእክት
አየች ትንሳኤውን ማርያም_መቅደላዊት
አዝ__
በእውነት አምነናል መቃብሩን አይተን
ነጭ የለበሱትን መላእክቱን ሰምተን
እግዚአብሔር ሲነሳ ጠላት ተበትኗል
በጌታ ትንሳኤ ትንሳኤያችን ሆኗል
ኢየሱስ ክርስቶስ በኃይሉ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጐ÷ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሥቷል፡፡ እርሱ የትንሣኤና የሕይወት ባለቤት ነውና፡፡
✤ ዮሐ ፲፩÷ ፳፭ ✤
11 25
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
https://t.me/OrtodoxMezmur121
https://t.me/OrtodoxMezmur121
https://t.me/OrtodoxMezmur121
✞ በይስሐቅ ፈንታ
በይስሀቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ /2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ /2/
ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የእኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደሞት
ንጹህ ኢየሱስ በደል የሌለበት
እርሱ ተሸክሞ የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙን እየተዘራ
ለሚገርፉት ሁሉ ምኅረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ
አዝ----------------
የሰማነዉ ስም ማን ሰዉ እንኳ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጾል
ባየነዉስ ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ
አዝ----------------
እጁ እየታሰረ ይስሐቅ ተፈታ
ኢየሱስ ቀረበ በሰዉ ልጆች ፈንታ
ንጹህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀል ተጭኖ
አዝ----------------
ተቆጠረ እንጂ እንደተቸገረ
በደዌ በህመም ማቆ እንደኖረ
አምላክ ለእኛ ብሎ ተናቀ በሰዎች
እየተጸየፉት ተፉበት ብዙዎች
አዝ----------------
በእዉነት ደዌያችንን እርሱ ተቀበለ
በሰዉ ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነዉ እንደ ወንጀለኛ
በእኛ ሲሰቀል ሰማያዊው ዳኛ
አዝ----------------
ለሰዉ ልጆች ሕይወት የታሰበዉ ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንጹሁ በግ በአርምሞ ይነዳል
መዝሙር
ሊቀ-መዘምራን ይልማ ኃይሉ
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
t.me/OrtodoxMezmur121
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞ ንሴብሆ ✞
ንሴብሆ /2/ለእግዚአብሔር /2/
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4
እናመስግነው/2/ እግዚአብሔርን/2/
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/
አዝ-----
ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ሕይወት የሚሰጥ መና ነው ምግባችን
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራ ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
አዝ-----
ከአለት ላይ ውሃ ፈልን ጠጣን
ይህን ታላቅ ጌታ ኑ እናመስግን
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል
አዝ-----
አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተና ቢበዛ
ኃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ
✝️ከወደዱት✝️ለወዳጆ ሼር ያድርጉት↗️
✨✨✨✨✨✨✨
✝️https://t.me/OrtodoxMezmur12 ✝️✨✨✨✨✨✨✨
👍 🔄 🙅♂️ ✍️
ˡᶦᵏᵉ ˢʰᵃʳᵉ ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
☦️መልካሙ ገበሬ☦️
ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ
ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ስርዓቱ
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ
አዝ=====
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ
አዝ=====
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት
ጠባቂ መልዐኳ ተማጸነላት
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት
ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት
አዝ=======
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች
ቀሲስ ዳዊት ፈንታዬ
✝️ከወደዱት✝️ሼር ያድርጉት↗️
https://t.me/OrtodoxMezmur121
متاح الآن! بحث تيليغرام 2025 — أهم رؤى العام 
