LEARN TECH ||ethiopia ®
الذهاب إلى القناة على Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
إظهار المزيد1 495
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-107 أيام
-5530 أيام
أرشيف المشاركات
#5ቱ_መልካም_ቃላት
ትናንት፣ የዛሬ አመት ወይም የዛሬ አስር አመት ምንም ይከሰት ምን ዛሬ ላይ እንደ አዲስ ቀንህን መጀመር ትችላለህ።
እያንዳንዱ ንጋት ከትናንትናህ የምትሻልበት አዲስ እድል ነው፤ አዲስ ታሪክ የምትጽፍበት፣ የጎደለ ብርጭቆህን የምትሞላበት ነው።
እያንዳንዱን ቀንህን አለምን ለመቆጣጠር አስበህ ጀምር፤ አምስት መልካም ቃላትን ምረጥና ለራስህ ደጋግመህ ንገረው። የኔ አምስቱ መልካም ቃላት እነዚህ ናቸው፦
🤗 በራሴ እተማመናለሁ
💎 ዋጋ አለኝ
✅ ለውጥ እያመጣሁ ነው
👑 ስኬታማ ነኝ
💕 ተወዳጅ ነኝ
እናንተስ አዲሱን ቀናችሁን እንዴት ለመጀመር አስባችኋል?
Join our channel
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ውብ ጊዜያትን ለማሳለፍ!
🔴ሁለት ነገር ቀናችንን ያበላሽብናል
1. ስለ ትናንት ማሰብና
2. ከሰው ጋር ውድድር
🟡ሁለት ነገር ቀናችንን ያስተካክልልናል
1. ያለንን ማመስገንና
2. ዛሬን መኖር
🟢ሁለት ነገር ነጋችንን ያሳምርልናል
1. እቅድ ማውጣትና
2. በቂ ምክንያት ማስቀመጥ
ይቀላቀሉ Join Now
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አምላክ ይክፈልልኝ
አንቺ እማምዬ ...እስቲ ልጠይቅሽ
ስንት ነው መጠኑ ስንት ያወጣል ፍቅርሽ
ማሰብ አቅቶኛል እንኳንስ ልክስሽ
እንኳንስ ልክስሽ አቅቶኛል ማሰብ
በስንት ይታመናል ልጆችን መሰብሰብ
በምን ይከፈላል ከራስ ቆርሶ ማጉረስ
ስንት ያወጣልና ለልጅ ህመም ማልቀስ
ንገሪኝ ልክፈለው ስንት ነው ሚበቃሽ
እድሜሽ ስንት ያወጣል ለኔ ስትይ ኖረሽ
ልከፍልሽ ባልችልም ያዢ ልመርቅሽ
የዘላለም ጌታ አንቺን ያኑርልኝ
መሶብሽ ሙሉ ይሁን ጎሎሽ አያሳየኝ
በረከትሽ ይብዛ
ሳቅሽ ድርብ ይሁን አንቺን አይክፋብኝ
እኔ ምን አቅም አለኝ አምላክ ይክፈልልኝ።
ከ ናቲ የሳራ ልጅ
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@Abyssinianwisdom
''...እኔ የምመኘው ዛሬ አርጄ ነገ ልታረድ፤ ዛሬ ቀምቼ ነገ ልቀማ የሚለዉ የልበደንዳናነት እምነት ተወግዶ እንዲሁም ዛሬ እንደተጠቃሁ ነገ ማጥቃት አለብኝ የሚለዉ የተጠቁት ሰዎች የመበቀል ስሜት ተወግዶ ታላቅ እርቅና ሰላም ወርዶ የነገዋ ዓለማችን ለሁሉም መልካምና ሰላማዊ ኑሮ እንድትሰጥ ነዉ።...''
~~
፠ ''በፍጹም አልወለድም'' አልሁ ጮኽ ብዬ ነገሩ ግራ ሆነባት ወዲያና ወዲህ ፊቷን እያዞረች ሰው እንዳለ ማየት ጀመረች። ወይ ግሩም! ሰይጣን ጠራኝ ልበል? አለች።
አዬ ደግሞ የምን ሰይጣን ? እኔ ነኝ አልወለድም" ያልኳት ወደ ሆዷ አንገቷን ዝቅ አደረገችና " አንተ ማን ነህ? አለች በታላቅ ፍርሀትና ጭንቀት። እንግዳው ነገር የተሰራው ሆዷ ውስጥ ሆነና የምታመልጥበት ዘዴ ባይኖራት እንጂ በዚህ ጊዜ ልቧ እስኪፈርስ ብትሮጥ በወደደች
" እኔ በሆድሽ ውስጥ ያለሁት ልጅ ነኝ" አልኳት...
አልወለድም
ከአቤ ጉቤኛ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
🔴ከአንድ ሀይማኖታዊ ጉሩፕ ያገኘሁት ጽሑፍ ነው አንብቡት ይጠቅማቹሀል።
✍ከዕለታት አንድ ቀን ሁለት ጓደኛሞች መንገድ በአንድ እየተጓዙ ሳለ በትልቅ እንሰራ ሙሉ ወርቅ ያገኛሉ፡፡
ከዚያም እየተደሰቱ ወርቁን ይዘው ሄዱ፡፡
ከሁለተኛው አንደኛው ሆዱን ታማሚ ስለ ነበር ሁሌ ለሆዱ የሚጠጣ መድሃኒት የሚአዘጋጅለት ጓደኛው ነበር፡፡
ወርቁን በአገኙበት ዕለት ግን ሁለቱም የተለያዬ ክፉ ሃሳብ አሰቡ፡፡
,
☜☞ሆዱን ይታመም የነበረውም <<ይህ ወርቅ ለሁለት ከተከፈለ አይበቃንም ስለዚህ ይህ ጓደኛዬ እኔ የምጠጣውን መድኃኒት አዘጋጅቶ በጥብጦ ሊሰጠኝ ጎንበስ ሲልልኝ በሰይፍ አንገቱን ብዬ ገድዬ ወርቁን እኔ ብቻ እወሰዳለሁ>> ሲል አሰበ፡፡
፡
☜☞ሁለተኛውም እንድሁ ለብቻው << ለጓደኛዬ መድኃኒቱን ሳዘጋጅለት መርዝ ጨምሬ ልስጠውና እርሱ ሲሞት የአገኘነውን ወርቅ እኔ ብቻ እወስዳለሁ>> ሲል አሰበ፡፡
ከዚያም አንደኛው የሆዱን ህመም መድኃኒት ከመርዝ ጋር በጥብጦ ጓደኛውን <<መድኃኒቱ ደርሶልሃል ና ጠጣ>> አለው፡፡
ያኔ ሆዱን ይታመም የነበረው ሰውም እሺ ጓደኛዬ አንሳና ስጠኝ አለው፡፡
ጓደኛውም አንስቶ ሊሰጠው ጎንበስ ሲል በሰይፍ አንገቱን አለና ጓደኛውን ገደለው፡፡
፡
✿ከዚያም ጓደኛውን የገደለ ይህ ሰው<< አሁን ወርቄን እኔ ብቻ እወስዳለሁ መድኃኒቴንም እጠጣለሁ>> አለና መድኃኒቱን አንስቶ ጠጣው፡፡ነገር ግን መድኃኒቱ መርዝ ሟቹ ስለጨመረበት ይህም ወዲያው ሞተ፡፡
፡
ይህ ተገኝቶ የነበረ ወርቅም ለሁለቱም ሳይሆን ቀረ፡፡
,
አይ የሰው ልጅ........!!!
ይገርማል .!!!
፡
♥ተወዳጆች እነዚህ ጓደኛሞች የተጣሉት እነርሱ ላልደከሙበት ወርቅ ነበር፡፡
ወርቁ ለሁለቱም ሊሆናቸው ሲችል በመስገብገባቸው እና እርስ በርሳቸው ክፉ አሳብ በማሰባቸው ሁለቱም ሞቱ ወርቁም ለአንዳቸውም ሳይሆን ቀረ፡፡
፡
✔እነዚህ የእነርሱ ባልሆነ ወርቅ እንደ ተጣሉ እኛም ዛሬ እኛ ላልሠራናት ዓለም፦
የእኛ ባልሆነች ዓለም ስንጣላ እንውላለን፡፡
ፍቅር ቢኖረን ለሁላችን ለምትበቃን ዓለም የእኔ አገር የእኔ ብሄር ብቻ ናት በማለት ስንጋደል አንዳችን ለአንዳችን ሞትን ስንመኝ እንኖራለን፡፡
፡
☞ይህንን ክፉ ሃሳብም ለማሳካት ከመድኃኒት ጋር መርዝ የሚጨምር እራሱን ዝቅ የሚአደርገውንም ዝቅ ካለበት የሚገድሉ በዓለማችን ላይ እየበዙ መጥተዋል፡፡
፡
♦እየመሰለን እንጂ ይችን እየተጋደልን ወደናት የኖርነውን ዓለም ሁለችንም ጥለናት እንሞታለን፡፡
✝ያኔ ይህች የተጋደልንባት ዓለም ለማንም ሳትሆን ትቀራለቾ፡፡
አዎን ዓለም የእኛ አይደለችም፡፡የማንምም አትሆንም፡፡
✔የእኛ ካልሆነች ያእኛ ያልሆነን ነገር መውደድ ደግሞ ሌብነት ነው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስም እንድህ ይላል፡፡
♥"ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን((ወርቁን ፣ብሩን ፣ሥልጣኑን)) አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።"ይላል፡፡
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:15-16)
✈ቅዱስ ጳውሎስም
<< አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤"ይላል፡፡
(ወደ ዕብራውያን 13:5)
፡
#ተወዳጆች ሆይ፦ እንግዳውስ ስለ ገንዘብም ስሌላም ሳንጣላ እርስ በእርሳችን እየተዋደድን በፍቅር እንኑር፡፡
ብቼዬን ይድላኝ አንበል
የእኛ እንጀራ ላይ ወጥ ለማድረግ ከሌላው እንጀራ ላይ አሸዋ አናፍስስ፡፡
፡
እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ማስተዋሉን ያድለን፡፡
T.me/Bekirstos_kassa
,
#ኢትዮጵያዊ _ነኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
ኑሮ ቢገፋኝ ፥ የማልወድቅለት
እንዳክሱም ድንጋይ ፥ እንደሮሐ አለት
የጊዜ ሞገድ ፥ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ፥ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ፥ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ ፥ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ፤
ከዋርካ ባጥር ፥ ከምቧይ ተልቄ
ከፀሀይ ባንስም ፥ ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ፥ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ ፥ በፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵ ያዊ ነኝ፤
ግትር ጠላቴን ፥ ባጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን ፥ በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር ፥ የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ ፥ ዓደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ፥ ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ፥ ተራራ መራጭ
ልክ እንዳሞራ ፥ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵ ያዊ ነኝ፤
እንደመሀረብ ፥ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ፥ ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ ፥ የማልገታ
ኢትዮጵ ያዊ ነኝ።
Join & share
👇👇👇👇
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩ
እንዲሁም ለተጨማሪ የግጥም አልፎም ለሁሉ አቀፍ የብእር ውጤቶች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን....
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አምስቱ ታላላቅ ሀሳቦች
1,ከፍተኛ የአፈፃፀም እና የምርታማነት ደረጃ ላይ ለመድረስ ቁልፉ ነገር በየማለዳው ነቅተህ ዋና ስራንን የመፍታት ልምምድ ማዳበር ነው።
2,የወጠንከውን ግብህን በየቀኑ ገምግብ።በጣም አስፈላጊ የሆነውን ግብህን ለማሳካትና ልታሳካው በምትችለው በጣም ወሳኙ ተግባር ላይ እርምጃ ውሰድ።
3,እቅዶችን በወረቀት ላይ ንደፍ
4,የስራህን ቅደም ተከተል በግልፅ ዘርዝር
5,በሕይወትህና በስራህ ውስጥ ስኬትህን ወሳኝና አስፈላጊ ከሆነው መካከል የመምረጥ ችሎታህ ቁልፍ ነው።
📓 ኢላማህን ምታ
✍🏻 ብርያን ትራሲ
📚 @abyssinianwisdom
እንግሊዛዊው አንቶኒ በርገስ በ42 ዓመቱ በጭንቅላት ካንሰር ምከንያት በህይወት የሚቆየው ለአንድ አመት ብቻ እንደሆነ ዶክተሮች ይነገሩታል ።
በጊዜው በጣም ያዝናል፣ ይሁን እንጂ ሚስቴ ከሞትኩ በኋላ እንዳትቸገር በማለት በቀረችኝ ጊዜ ስራ መስራት አለብኝ፣ ለሚስቴ ጥሪት ማስቀመጥ አለብኝ ብሎ ወሰነ።
አንቶኒ በርገስ ኘሮፌሽናል ደራሲ አልነበረም። ነገር ግን በዉስጡ የተዳፈነ የመፃፍ ችሎታ እንደነበረዉ ያዉቅ ነበርና ወረቀቱን ከጽሕፈት ማሽኑ ጋር አወዳጅቶ መፃፍ ጀመረ።
በሚገርም ሁኔታ በቀረችዉ አንድ አመት ውስጥ 5 መፃሕፍትን አሰናድቶ ጨረሰ። ይህም ታዋቂዉ ደራሲ 'Em foster' በህይወቱ ሙሉ ከፃፈዉ በላይ እሱ በአንድ አመት ዉስጥ የፃፈዉ ይበልጥ ነበር ። እንዲሁም 'J.D.stelenger' የተባለዉ ደራሲ በህይወት ዘመኑ ከፃፈዉ መፅሐፍ በላይ በእጥፍ ፃፈ።
በካንሰር ለመሞት አንድ አመት ቀረህ የተባለው አንቶኒ በርገስ ይህን የአንድ አመት ጊዜ በለንደን ሆስፒታል ውስጥ አሳልፏል። ነገር ግን ከበርካታ የሴሬብራል ምርመራዎች በኋላ ምንም አይነት በሽታ ወይም ዕጢ አልተገኘበትም። በዚህ ጊዜ ነበር የሙሉ ጊዜ ጸሐፊ ለመሆን የወሰነው።
በኖረበት ቀሪ እድሜ (በ76 ዓመቱ ይችን አለም እስከተሰናበተበት ጊዜ ድረስ) 70 መፅሃፍቶችን ለአንባቢያን አበረከተ ። በተለይ 'clock work orange' በሚል ያሳተመዉ መፅሐፍ ታላቅ እዉቅናን ያስገኘለት ስራው ነበር ።
አንቶኒ በርገስ ‘ለመሞት አንድ አመት ነዉ ያለህ’ ባይባልና ሚስቱ እንዳትቸገር 'ጥሪት አስቀምጬ ልሙት' በሚል ሀሳብ ባይነሳ ፣ ይህን ያህል ቁጥር ያለው መፅሐፍ ባልፃፈ ነበር።
ከዚህ ታሪክ የምንማረው:-
የተሰጠን ዛሬ እንደሆነ አውቀን የተዳፈነውን ችሎታችንን አውጥተን ለሌሎች የብርሃን ችቦን እንለኩስ።
@abyssinianwisdom
ብርጭቆው ከባድ ነው ወይስ ቀላል?
አንድ አሰልጣኝ እንዲህ ሲል ለሰልጣኞቹ በመጠየቅ አንዲትን ቀላል የምትመስል፣ ነገር ግን እጅግ ወሳኝ ቁምነገር አስተላለፈ፡- “አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጃችሁ ብትይዙት ከባድ ነው ወይስ ቀላል?”
ሁላችንም እንደምንጠብቀው ሰልጣኞቹ በአብዛኛው ቀላል እንደሆነ በመስማማት ገለጹ፡፡ አሰልጣኙም በመመለስ፣ “መልሳችሁ ትክክልም፣ ስህተትም ነው” በማለት ሲያብራራ፣ “ይህንን ውኃ የተሞላ ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ ከያዛችሁት ቀላል ነው፡፡ ለአንድ ሰዓት ከያዛችሁት ደግሞ እየከበዳችሁ ይሄድና እጃችሁን የሕመም ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሙሉ ከያዛችሁት እጃችሁ ይደነዝዛል፣ ይዝላል፣ እንዲያውም ብርጭቆውን ልትለቁት እስከምትደርሱ ድረስ ልትደክሙና ሊከብዳችሁ ሁሉ ትችላላችሁ”፡፡
መልእክቱ ይሄ ነው፡- የዚህ ብርጭቆ ክብደት ልክ በመጀመሪያ እንደነበረ፣ ከአንድ ደቂቃ በኋላ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላና፣ ከአንድ ቀን በኋላ ያው ነው፡፡ እዚህ ጋር ልዩነት ያመጣው ብርጭቆውን በእጃችን የያዝንበት የጊዜ ርዝመት ነው፡፡ የስሜትም ጉዳይ እንዲሁ ነው!
ማንኛውም እንደ ጭንቀት፣ መረበሽና ፍርሃት የመሳሰለ ቀላል የተባለ የስሜት ሁኔታ ለጊዜው ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል፣ ሆኖም ስሜቱን ለረጅም ጊዜ ስንይዘው ግን መዛላችን፣ መድከማችን፣ መታመማችንና ሕይወት ከአቅማችን በላይ እየሆነ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ምናልባት የመኖር ጣእም ያጣችሁት፣ ድብርት የሚጫጫናችሁና የውስጥ (የስሜት) ህመም የሚሰማችሁ አንዳንድ ስሜቶችን ለረጅም ጊዜ እየያዛችሁ ሊሆን ይችላልና አላስፈላጊ ስሜቶችን ገና በትንሽነታቸው ቶሎ ቶሎ ለማራገፍ ሞክሩ!
ዶክተር እዮብ ማሞ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ሌሎችን የሚያስከፋ ሰው በመጨረሻ ራሱ ይከፋል። ሌሎችን የሚያስደስት ሰው ደግሞ በመጨረሻ የደስታ ከፍታዎች ላይ ይደርሳል፡፡ ለዚያ ነው ደስታን ለመስጠት የሚሞከር ሰው በውስጡ ያለውን የደስታ ማእከል ያበለጽጋል የምለው፡፡ እናም ሌሎችን የሚያስከፋ ሰው ደግሞ በውስጡ የሚገኘውን የመከራ ማእከል የሚያሳድግ ይሆናል፡፡
ፍሬው ከውጭ አይመጣም፤ ፍሬው
የሚፈጠረው በውስጣችሁ ነው፡፡ የትኛውንም ነገር አድርጉ በውስጣችሁ
ተቀባይነትን ታበለጽጋላችሁ፤ ፍቅርን የሚፈልግ ሰው ፍቅሩን መስጠት አለበት፡፡ ቡራኬን የሚሻ ሰው የራሱን ቡራኬ መስጠት ይኖርበታል፡፡ እሱ ቤት ውስጥ አበቦች ይዘንቡ ዘንዳ ሚፈልግ ሰው ሌሎች ስዎች ቤት ውስጥ አበቦች ይዘንቡ ዘንዳ ማድረግ አለበት።ሌላ መንገድ የለም፡፡
📓 ነፃ ስሜቶች
✍🏻 ኦሾ
📚 @abyssinianwisdom
🔥በፈተናዎች ተስፋን አትጣ። ፈተና ብቁ ከሆንክ ልታልፈው፣ ብቁ ካልሆንክ ለዛ ደረጃ እንድትበቃ ራስህን እንድታሻሽልበት እና እንድትማርበት ተፈጠረ እንጂ እንድታቆም አልተፈጠረም። በፈተና ወቅት በርታ፤ አሸንፍ። ከወደቅክ ራስህን አሻሽለህ እስክታልፍ ደጋግመህ ሞክር።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
#ውሸት
ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??
ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡– ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡
ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡
ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-
ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡
ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡
ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡
ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡
ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡
ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡
ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity) እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡
የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡
ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ………..
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
#አሳ_ጎርጓሪ
አዛኝ እሩህሩህ ያንች ደግነት የተለመደ፣
በአንዲት እርጉም ቀን ያኔ ተናደ፣
ዘንዶ የሚያዎጣ አሳ ጎርጓሪ፣
አርሂቡ ብለሽ ስታሳድሪ፣
ስትቀበይው አንጥፈሽ መደብ፣
አጉል ስሜቱ ሲያሳጣው አደብ፣
ብቸኝነትሽን አይቶ ገምቶ፣
በተኛሽወት በቆጡ ወቶ፣
ስጋ እንዳዬ ጅብ ሲያቅበዘብዘው፣
ሁለቱ እጆችሽ አንገቱን ይዘው፣
ሲጠባበቁ ነብሱ እስኪረታ፣
የእርሱም ጉልበቱ እየበረታ፣
እውር አድርጎት አጉል ስሜቱ፣
ስትታገሉ
ጩኸት ተሰማ ለጎረቤቱ፣
ሰሚ ሲመጣ ምነው ለማለት፣
ተዘርሮ እርሱ ወድቆ ከመሬት፣
ቢላሽን ይዘሽ አንችም ደም በደም፣
ያንች አይነት ዎኔ አልተለመደም፣
ያኔ ስታይው ተጎርቶ ኮሶ፣
በደግነትሽ ሆድሽ ተላውሶ፣
እያሳዘነሽ ዘመድ ማጣቱ፣
መአድ ሞልተሽ በአይነት በአይነቱ፣
እስኪ ጠነክር ካዛለው ድካም፣
ሽር ጉድ ብትይ ቅንጣት አልረካም፣
ክብር ዝናሽን የትም አርክሶ፣
ለአንድ ቀን አዳር ህግ አጥሩን ጥሶ፣
በረከት ባለው በቤትሽ ውሎ፣
ሰዋዊነቱን ሀቅ አቅሉን ጥሎ፣
ከራሱ አልፎ ካንች ሲጣላ
ብታነሽበት የቢላ ስለት፣
ማንም አልራራም ገዳይ ለማለት፣
መልካምነትሽ ጥላሸት ለብሳ፣
ገዳይ ስትባይ በኖረ እሬሳ፣
እቴ ሚስኪኗ
ምን ልበልልሽ ያንን እንግዳ
ያንን አስጋሪ፣
ዘንዶ 'ሚያወጣ አሳ ጎርጓሪ።
✍ኤዶምገነት ፃፈችው
@Edom_Ge
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
Umbrella can't stop the rain but can make us stand in the rain.
Confidence may not bring success but gives us power to face any challenge in life.
💭@abyssinianwisdom
✊ ኩርኩም ✊
እልፍ ኩርኩሞችን
የቀመሱ ራሶች፣
ዳሳሽ እጆች እንጂ
አይሹም ትራሶች።
ይስማዕከ ወርቁ
ከ የወንድ ምጥ መጽሐፍ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
🌿" ግን ፈራለው "
ፍራትን ወደ ስኬት ሚያደርስ ሀይል ማድረግ ይቻላል!
ደፋር መሆን ማለት አለመፍራት አይደለም! ነገር ግን ደፋር መሆን ማለት ከፍራቻ በላይ መሆን ማለት ነው ፡፡ በሂወት ውስጥ ከሞከርናቸዉ ይልቅ በፍራቻ ምክንያት የተዉናቸዉ ነገሮች ይበዛሉ ፡፡ የፍራቻ ስሜት ከሁለት ሃሳቦች ሊመጣ ይችላል
1, ይህን ነገር ከዚህ በፊት አልሞከርከዉምኮ እንዴት አድርገህ ትችለዋለህ ? የሚልና
2,ከዚህ በፊት ሞክረህ አልቻልከውም ነበር የሚል ይሆናል ፡፡ ታዲያ ይህ ስሜት ሲሰማን ምን እናርግ ?
ከዚህ በፊት አታዉቀዉም ሲልህ እኮ አሁን ልወቀዋ በለው ፡፡
ደግሞ ሞክረህ አልቻልከዉም ሲልህ ደግሞ አሁን ከበፊት የተሻልኩ ነኝ ስለዚህ አሁን እችላለሁ በል ።
ከዛም ምትሰራዉን ስራ ይህችን አጭር ሂወት በፍራቻ ምክንያት ማግኘት ያለባትን አታሳጣት ፡፡ ያላፈቀራችሁ አፍቅሩ አፍቅራችሁ የተጣላችሁ ደግማችሁ አፍቅሩ ፣ ያልነገዳችሁ ነግዱ ነግዳችሁ የከሰራችሁም ደግማችሁ ነግዱ ፣ ያላመናችሁ እመኑ አምናችሁ የተከዳችሁ ደግማችሁ እመኑ ።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
Repost from የድሮ መፅሐፎች በPDF
ዩፎስ ( በራሪ ዲስኮች )
ድርሰት - ጆን ዊልዶን ዊት ሌቪቴት
ትርጉም - ጋሽ ማሞ ውድነህ
ይዘት - ልዩ ዘገባ
የመጀመሪያ ዕትም - 1987 ዓ.ም
የገፅ ብዛት - 195
ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👉 @OLDBOOKSPDF
#ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት
(Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!
2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!
3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።
4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።
5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============
6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።
7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።
8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።
10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================
11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።
12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።
13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።
14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።
15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================
16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።
17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!
18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።
19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።
20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።
21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ኬቨን ሃርት የተባለው ኮሜዲያን። እዚህ የስኬት ጫፍ ላይ ከመድረሱ በፊት ብዙ መከራ ያሳለፈና አትችልም ተብሎ የተገፋ ሰው ሲሆን፣ ከሲንግል እናቱ ቤት ሥራ ፍለጋ ሲወጣ እናቱ የሰጡት ስጦታ መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። ኬቨን አንድ ቀን የሚመገበው አጥቶ በጣም ቸግሮት ለእናቱ ይደውላል፣ ማሚ ስራ ማግኘት አልቻልኩም እባክሽ እርጂኝ አላቸው? እናቱም የሰጠሁህን መጽሐፍ ቅዱስ አንበብክ ወይ ? እርሱም ራበኝ እያልኩሽ የምን መጻሕፍ ነው የምትይው አላቸው። ልጄ አሉት የሰጠሁህን መጻሕፍ ቅዱስን አንብበህ ቢሆን ኖሮ እኮ አይርብህም ነበር አሉት።
ኬቨን እናቱ አንብብ ያሉትን መጻሕፍ ቅዱስ ሳያነብ እናቱ በማኅፀን በር ካንሰር ያርፋሉ፣ እርሱም በዓለም ምርጡ ኮሜዲያን ውዱ አከተርም ከሆነ በኃላ፣ አንድ ቀን የልጅነት ፎቶግራፎቹን ለፊልም ፈልጎ ሲበረብር ያንን እናቱ የሰጡትን መጻሕፍ ቅዱስንም ገለጠው፣ ውስጡ እናቱ ለስራ መፈለጊያና መጠነኛ ቤት መከራያ እንዲሆነው የተውለትን 1ሺ ዶላር አገኘ። ገንዘቡ ለአሁኑ ኬቨን ምንም ብትሆንም እናቱ ግን ንብረታቸውን ሸጠው ነበር ለልጃቸው የሰጡት። መጻሕፍት ውስጥ ብዙ መልሶች አሉና መጻሕፍትን እናንብብ። ቀና ብሎ በዕውቀት ለማውራት ብዙ አጎንብሶ ማንበብን ይጠይቃል።
ፍፁም አብርሃም✍️✍️
📚@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዜአብሔር "ማስታዎሻ" በሚለው ግለታሪኩ ላይ ለጋሽ ዘነበ ወላ እንዲህ ሲል አጫውቶታል። "መማር ስትጀምር ከሰፈር ትዎጣለህ በቃ ዓለም ውስጥ ትገባና ዓለም ሁሉ ያንተ ትሆናለች" ብሎታል። ይህን ሀሳብ ወስደን የሀገራችንን ወቅታዊ የማህበረሰብ የባህልና ስነ ልቦና ብንመለከትበት አሁን ሀገራችን ላይ እየታየ ያለው ጠቅላላ የማህበረሰብ ትስስርና ሰነ ልቦና በመላሸቅ ላይ ሆኖ እናገኘዋለን። ተማረ የምንለው ሰው ከዓለም አቀፋዊነት ይልቅ መንደርተኝነትና ወንዜነት ሲያጠቀው፣ በብሔር ተደራጅቶ በዝባዥና ተበዝባዥ ጎራ ለይቶ ሲዋጋና ሲያዋጋ የሚውለው ተማረ ብለን የምንጠራው የህብረተሰብ ክፍል ሆኖ እናገኘዋለን። መማር ቀስበቀስ ወደ ሙሉዕነት የሚወስደን የህይወት መሠላል እንጂ በሰፈር፣ በወንዝ እና በመንደር መካከል ውስጥ መወሸቅ አይደለም። መማር እራስን በሰነ ልቦና ችሎ መቆም ነው። እራስን በራስ የመወሰንና የማድረግ እርግጠኝነትን መጨመር ካልቻልና የሞዴል እንስሳት (conditioned animal) ነን ማለት ነው።
የአንድ ማህበረሰብ በአስተሳሰብ እያደገ ሲመጣ የማደረግና የመወሰን እርግጠኝነቱ እየጨመረ ይመጣል፣ ተፈጥሮን የማሰስና የማሸነፍ ክህሎቱ እየጨመረ ይመጣል። በዚህም ስንፍንና ማሸነፍ ይችላል ማለት ነው። በአስተሳሰብ ማደግ ያልቻለ ማህበረሰብ የማድረግ ፍላጎቱ ዝቅተኛ ስለሚሆን የራሱን ሀይል ለጥቅም የማዋል አቅም ስለሌው የመንፈስና የቁስ እጥረት ይገጥመዋል።በዚህም አማራጩ የመንፈስና የቁስ ፍላጎቱን የሚሞላለት የቅርብ አካል ይፈልጋል። ዘመድ፣ የአገር ልጅ፣ የወንዝ ልጅ፣ ከፍ ሲል የብሔር ጥላ ይፈልጋል። ለምንድ ነው እነዚህን ጥላዎች የሚፈልጋቸው ብንል አነዚህ ነገርሮች ወደ ቀደመው እናታዊ ውህደት ስለሚሄድ ነው። እናታዊ ውህደት (mother archetype) ያልተላቀቀ ማህበረሰብ ሁሉንም ነገር ተበስሎ እንዲቆየው የመሆን ፍላጎት ነው። የዚህ ማህበረሰብ ጠቅላላ ህላዌ (collective ego) አልዳበረም ማለትም እራሱን ከእውነታ ጋር አላዋሀደም ማለት ነው። ጠቅላላ ህላዌ እራሱን እንዲችል ህይዎት በእውቀትና በክህሎት የምትሸነፍ መሆኗን ማዎቅ ብሎም የማድረግ ሀይሉ ማደግ መቻል አለበት። ለዚህ ደግሞ ሁነኛ መፍትሄ መማር ነው። መማራችን ደግሞ ሙሉነትን ሊያጎናጽፈን መቻል አለበት።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
