LEARN TECH ||ethiopia ®
الذهاب إلى القناة على Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
إظهار المزيد1 495
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-107 أيام
-5530 أيام
أرشيف المشاركات
📚በ5 ዓመቱ አባቱ ሞተ
📚በ16 ዓመቱ ትምህርቱን አቋረጠ
📚በ17 ዓመቱ 4 የተለያዩ ስራዎቹን አጣ።
📚ከ18 እስከ 22 ዓመቱ የባቡር ትኬት ቆራጭ ሆኖ ቢሰራም አልተሳካለትም
📚የሀገሩን መከላከያ ቢቀላቀልም ተባረረ
📚ለአንድ ኢንሹራንስ ድርጂት ግብይት ሰራተኛ ሆነ..ይህም አልተሣካለትም፡፡
📚በ19 ዓመቱ ደግሞ ልጅ ወልዶ ነበር።ነገር ግን በ 2ዐ ዓመቱ ሚስቱ ልጃቸዉን ይዛ ጥላዉ ሄደች፡፡
📚በአንዲት ትንሽየ ካፌ ምግብ አብሳይና ሰሃን አጣቢነት መስራት ጀመረ
📚የራሱን ልጅ አግቶ ሚስቱን ወደ ቤት እንድትመለስ ለማግባባት ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀረ።
📚65 ዓመት ሲሞላዉ ጡረታ ወጣ።ጡረታ በወጣ በመጀመሪያዉ ቀን የ105 ዶላር ቼክ ከመንግስት ደረሠዉ..እሱ ግን የተረዳዉ መንግስት "ራስህን መመገብ አትችልም" እንዳለዉ ነበርና ከዚህ በኋላ መኖሩ ጥቅም እንደሌለዉ ራሱን አሣምኖ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አደረግ ይህም ሳይሆን ቀረ፡፡
📚አንድ እለት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ ምኞቶቹን ወረቀት ላይ ማስፈር ፈለገ የፃፈዉ ግን በህይወቱ ሊያደርጋቸዉ እየቻለ ሳያደርጋቸዉ ስለቀሩ ነገሮች ነበር...ከዝያም በእርግጠኝነት ማድረግ እንደሚችለዉ የሚያዉቀዉን አንድ ነገር አሰበ...ምግብ ማብሰል፡፡
📚ወዲያዉም የመንግስትን የውለታ ቼክ መልሶ 87 ዶላር ተበደረ፡፡በዚያች ብድርም ቅመሞቹን ሸምቶ ፍራይድ ችክን አዘጋጀ።እናም በኬንታኬይ ለሚኖሩ ጎረቤቶቹ በራቸዉ ድረስ እየሄደ መሸጥ ጀመረ፡፡
📚አስታዉሱ ይህ ሰዉ በ65 ዓመቱ ራሱን የማጥፋት ሙከራ አድርጎ ነበር።
📚ግን በ68 ዓመቱ ኮሎኔል ሳንደርስ የኬንታኬይ ፍራይድ ችክን KFC ኢምፓየር መስራች ቢሊየነር ሆነ
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
➖➖➖➖➖ ➖➖ ➖➖
📖 @abyssinianwisdom
በአንድ ወቅት ሶቅራጦስ በግሪክ ደልፊን ቤተመቅደስ ላይ "know thyself" ወይም "ራስህን እወቅ" ብሎ ተናግሮ ነበር።
ራስን ማወቅ ሌሎችንም ለማወቅ መሠረት ነው።ራስን ማንበብ ደግሞ አለምን ለማንበብ ወሳኝ ነው ይባላል
📚ብዙዎች መጽሐፍ ያነባሉ።
📚አዎንታዊ አስተሳሰብንም ይጎናፀፋሉ።
📚ዕውቀታቸውንም ያጋራሉ፡፡
ይሄ በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ራስን አንብቦ፣ራስን መርምሮ፣ራስ ላይ ጥናት አድርጎ ራስን አብጠርጥሮ ማወቅ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ በርካታ ምሁራኖች ይናገራሉ።ስለዚህ ራሳችንን ለማወቅ እራሳችንን እናንብብ ለማለት ነው። ከበእምነት ላይብረሪ ጋር መልካም ቆይታ እንዲሆንላችሁ ተመኘው...
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
➖➖➖➖➖ ➖➖ ➖➖
💪 @abyssinianwisdom
የፍቅር_አይነቶች
1. #ኤሮስ ፦ ተክለ ቁመናን አይተው
የሚያፈቅሩ ናቸው ።
2. #ሉደስ ፦ ፍቅርን እንደ ጨዋታ የሚመለከቱ ናቸው።
3. #እስቶስ ፦ ፍቅርን ለህይወታቸው ንሮ መሰረት አድርገው የሚያስቡ ናቸው ።
4. #ማንያ ፦ ፍቅራቸውን እስከ ሞት ድረስ እማይረሱ አንዴ ልባቸውን ከሰጡ መቼም ተስፋ የማይቆርጡ ፍቅራቸውን መቼም
እንደማያገኙ እያወቁ እንኩአን የሚያፈቅሩ ናቸው።
5. #ፕራግማ ፦ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መጣጣም እና ተመሳሳይነትን የሚፈልጉ ናቸው ።
6. #አጋፔ፦ በፍቅር ለመውደቅ ብዙ የሚቆዩ ግን በፍቅር ከወደቁ በሆላ ሁሉ ነገራቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው
እናንተ ኬትኛዉ ናችዉ ?
👇Join our channel👇
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
የፍቅር_አይነቶች
1. #ኤሮስ ፦ ተክለ ቁመናን አይተው
የሚያፈቅሩ ናቸው ።
2. #ሉደስ ፦ ፍቅርን እንደ ጨዋታ የሚመለከቱ ናቸው።
3. #እስቶስ ፦ ፍቅርን ለህይወታቸው ንሮ መሰረት አድርገው የሚያስቡ ናቸው ።
4. #ማንያ ፦ ፍቅራቸውን እስከ ሞት ድረስ እማይረሱ አንዴ ልባቸውን ከሰጡ መቼም ተስፋ የማይቆርጡ ፍቅራቸውን መቼም
እንደማያገኙ እያወቁ እንኩአን የሚያፈቅሩ ናቸው።
5. #ፕራግማ ፦ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መጣጣም እና ተመሳሳይነትን የሚፈልጉ ናቸው ።
6. #አጋፔ፦ በፍቅር ለመውደቅ ብዙ የሚቆዩ ግን በፍቅር ከወደቁ በሆላ ሁሉ ነገራቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው
እናንተ ኬትኛዉ ናችዉ ?
👇Join our channel👇
@Abyssinianwisdom
የፍቅር_አይነቶች
1. #ኤሮስ ፦ ተክለ ቁመናን አይተው
የሚያፈቅሩ ናቸው ።
2. #ሉደስ ፦ ፍቅርን እንደ ጨዋታ የሚመለከቱ ናቸው።
3. #እስቶስ ፦ ፍቅርን ለህይወታቸው ንሮ መሰረት አድርገው የሚያስቡ ናቸው ።
4. #ማንያ ፦ ፍቅራቸውን እስከ ሞት ድረስ እማይረሱ አንዴ ልባቸውን ከሰጡ መቼም ተስፋ የማይቆርጡ ፍቅራቸውን መቼም
እንደማያገኙ እያወቁ እንኩአን የሚያፈቅሩ ናቸው።
5. #ፕራግማ ፦ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መጣጣም እና ተመሳሳይነትን የሚፈልጉ ናቸው ።
6. #አጋፔ፦ በፍቅር ለመውደቅ ብዙ የሚቆዩ ግን በፍቅር ከወደቁ በሆላ ሁሉ ነገራቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ናቸው
እናንተ ኬትኛዉ ናችዉ ?
👇Join our channel👇
@Abyssinianwisdom
ለፈገግታ😁
አያቴ ከሰው በላይ ያድርግህ ብላ መርቃኝ ይሀው አሁን በየሰፈሩ ጣራ ላይ ዲሽ እየሰራሁ ነው 😂😂😂😂😂😂😂😂
@Abyssiniawisdom
#ውስጥህን_ብቻ_አድምጠው
ለትንሽ ጊዜ የምታውቀውን ሁሉ እርሳው፡፡ ህብረተሰቡ የነገረህን ተወው። ሌሎች ከአንተ የሚጠብቁትን ችላ በለው። ወደራስህ ውስጥ ተመልክትና “ለእኔ ተፈጥሮአዊ ስሜት ምን አይነት ስሜት ነው? መቼ ነው በሕይወት እንዳለሁ የተሰማኝ? እውነተኛው እኔ እንደሆንኩ የተሰማኝ መቼ ነው?” የሚሉ ጥያቄዎችን ለራስህ ጠይቅ፡፡
ራስን መፈረጅ ወይም ሌሎችን ማስደሰት አይኑር፡፡ ራስን የመተቸትም ይሁን ውሳኔዎችን የማጤን ጥንቃቄም እንዲሁ፡፡ ያለውን ነገር ማጣጣም ብቻ! በዚህ ሂደት ውስጥ አልፈህ እውነተኛና ትክክለኛ ስሜት የሚሰማህ ከሆነ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ እየሄድክ ነው!
ውስጥህ መሆን ያለብህንና እውነቱን ይነግርሀል፡፡ ሁሌም በጸጥታ ውስጥ ሆነህ አድምጠው!
#የልማድ_ኃይል_ATOMIC_HABITS መጽሐፍ
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom. @Abyssinianwisdom
እኛኮ እንዲህ ነን
ሙስናን ከመስቀል ሙሾን ከዘፈን፤
መሳ ለ መሳ የቃረምን፤
ስድብን ከውዳሴ በአንድ እልፍኝ ያኖርን፤
በብርሃን የምንለግስ በጨለማ ዘርፈን፤
ከአንገት በላይ መልአክ ታች ታቹን ሰይጣን፤
ሆነን የከረምን እኛኮ እንዲህ ነን።
እውነቱን ከሆነ ጻድቅም ርኩስም ነን።
@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
በአለም ላይ ያለውን እያንዳንዱን ሰው ታገኛላችሁ ግን በጭራሽ
ከራሳችሁ ጋር ተገናኝታችሁ አታውቁም፡፡
ልትናደዱ ትችላላችሁ ግን ለዘላለም ተናዳችሁ አትቆዩም፤በጣም ንዴተኛ ሰው እንኳን አንዳንድ ጊዜ ይስቃል፤መሣቅም አለበት።ንዴት ቋሚ ሁኔታ ሊሆን አይችልም።በጣም የከፋው ሰው እንኳን
ፈገግ ይላል።የሚስቀው ሰው እንኳን አንዳንድ ጊዜ ያለቅሳል። በሚስቀው ሰው አይኖች ላይ እንባዎች ይመጣሉ።
ስሜቶች ቋሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ለዚያ ነው emotions ብለን የምንጠራቸው።emotion የሚለው ቃል የመጣው "motion" "እንቅስቃሴ" ከሚለው ቃል ነው።ስሜቶች ይንቀሳቀሳሉ።ለዚያ ነው emotions ተብለው የተጠሩት።
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @abyssinianwisdom@abyssinianwisdom@abyssinianwisdom@abyssinianwisdom
አፈር ብላ አለችኝ አሜን ይሁን አልኳት
ዘላ ስትነክሰኝ ይቅር ብዬ ሳምኳት
ዛሬ ወይም ነገ ብትለወጥ ብዬ
እሽሩሩ እያልኩኝ ከጀርባ አዝዬ
እንኳን ልትለወጥ ልትራራልኝ ቀርቶ
ታሯሩጠኝ ጀመር በእራሴ ቀበቶ
ማነው ባል😕
በ ኪሩቤል አሰፋ
@Cher7ub
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
#ኡቡንቱ!
አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።
ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-
"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "
ጨዋታው ተጀመረ።
ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።
ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::
የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።
ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።
በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው:-
"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"
"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-
“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።
Light house academy
❤️❤️❤️
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
አንዳንዴ ዋጋህን ስለሚያውቁ ሊያሳንሱህ ይሞክራሉ! የማይገዛስ ገዢ አንዳንዴ ይከራከር የለ!!! ክርክር ማሳነስ ብቻ ሌላ አቅም የለም ምንም መፍጠር አይችሉም!!!
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
#መናገር ወይስ ማሰብ የቱ ይቅደም?
በድሮ ጊዜ አንድ ሰው ጥፋት ያጠፋና ዳኛ ፊት ይቀርባል፤ ታድያ ዳኛው ሦስት ዓይነት የቅጣት ምርጫ አቀረቡለት...፡፡
1. አንድ ኪሎ ሽንኩርት እየላጠ መብላት፣
2. አንድ መቶ ጅራፍ መገረፍ፣
3. አምስት መቶ ብር መክፈል፡፡
ሰውዬው ለማሰብ የሚሆን ልቡና የሌለው ነበርና የመጀመርያ ምርጫ ሆኖ ስላየው ብቻ ሽንኩርቱን እበላለሁ» አላቸው...፡፡
ከቀረበለት አንድ ኪሎ ሽንኩርት ገና አንድ ሁለት መብላት ሲጀምር ጊዜ ዓይኑ ማልቀስ ለሐጩም መዝረብረብ ጀመረ አልቻለም። ከመቀመጫው ተስፈንጥሮ ተነሣና «መቶ ጅራፍ መገረፍ ይሻለኛል» አላቸው፡፡
ወዲያው ኃይለኛ ገራፊዎች ተጠሩና እየተፈራረቁ ይለበልቡት ጀመር፡፡ ግማሽ እንደደረሰ አልቻለም ፤ እጁን ወደ ላይ አነሣ፡፡ «እህሳ» አሉት ዳኛው፡፡
«አልቻልኩም» አላቸው፡፡
«ታድያ ምን ይሻላል» አሉት እየሳቁ፡፡
«በቃ አምስት መቶ ብሩን እከፍላለሁ» አለ ከተኛበት እየተነሣ፡፡
**«ያንተ ትልቁ ጥፋት መጀመርያ ወንጀል መሥራትህ ብቻ አይደለም፡፡ ማሰብ አለመቻልህ እንጂ፡፡ ምናለ አስበህ ከሦስቱ አንዱን ብትመርጥ ኖሮ፡፡ እኔ ከሦስቱ አንዱን እንድትቀጣ ነበር የወሰንኩት፡፡ አንተ
ግን መናገር እንጂ ማሰብ ባለመቻልህ ሦስቱንም ተቀጣህ፡፡» አሉት ይባላል።
© ዳንኤል ክብረት
#ከመናገር ይልቅ ማሰብ ይቅደም!!!**
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
“የእለት እንጀራዬን ስላገኘሁ አመሰግናለሁ፡፡ በህይወት የምቀጥልበት ተጨማሪ ቀን ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ፡፡ ዛሬ ጠዋት ህያው ሆኜ ዳግም ነቅቻለሁ፤ ፀሐይ በድጋሚ ብርሃኗን ሰጥታኛለች፤ ጨረቃንም ዳግም ለማየት እችላለሁ፤ ዛሬ ዳግም ህያው ነኝ፡፡ ዛሬ ህያው ሆኜ መቀጠሌ አስፈላጊ አልነበረም፤ ዛሬ መቃብር ውስጥ እሆን ነበር፡፡ ሆኖም ግን በድጋሚ ህይወት ተሰጥቶኛል፡፡ የተሰጠኝ በስራዬ ሳይሆን እንዲሁ በነፃ ነው፡፡” የሚል የምስጋና ስሜት በልብ ውስጥ ሊኖር ይገባል፡፡ ምግብ እየተመገብን፣ ውሃ እየጠጣን፡ እየተነፈስን ነው ያለነው፡፡ ለዚህ ሁሉ የምስጋና ስሜት ሊኖረን ይገባል፡፡ ለመላው ህይወት፣ ለመላው ዓለም፤ ለመላው አፅናፈ ዓለም፤ ለመላው ተፈጥሮ፤ ለመለኮት የምስጋና ስሜት ሊኖረን ይገባል፡፡
@Abyssinianwisdom
ግን እኔ ማነኝ? ምንድን ነኝ ብሎ ራሱን ጠየቀ።ልክ ይሄን በጠየቀበት ቅፅበት፤ፊቱ አንድ የማይረባ ቀልድ እንደሰማ ሰው ፈገግ አለ።«አሁን መቼም ይሄን ጥያቄ ጮክ ብዬ ብጠይቅ፤“አይ በቃ እሱም ጀመረው"፤"ድሮም እኮ" የሚሉ ወዳጆቹ ፊቱ ላይ ታዩት።ሃኪሞቹን ደግሞ ይህንኑ «እኔ ማን ነኝ» የሚል ጥያቄ ቢጠይቃቸው "አይ! ህመሙ ጭንቅላቱ ላይ ወጣ" ብለው ሲቲ ስካን እንደሚያስነሱት ትዝ ሲለው "የሰይጣን ጆሮ ይደፈን" አለ ለራሱ፤በሲቲ ስካን የተመረመረበትን ዋጋ መክፈል እንደሚመረው እያሰበ።
ግን "ቤተሰቦቼን ብጠይቃቸውስ" እንዳለ አንዳች ነገር እንደሰማ ሰው ሰውነቱን ዘገነነውና እንደመባነን አለ።እጆቹና እግሮቹ ተጠፍረው አጃና ሚካኤል ሁለት ሰባት ሲጠመቅ ታየው።"አቤት! አቤት! አቤት! እንዴት ይቀዘቅዛል።"
ገረመው።በርግጥም ይህን ጥያቄ ከራሱ ሌላ የሚጠይቀው፣ቢጠይቀውም ሊመልስለትና ሊያስረዳው የሚችል አንዳችም ነገር የለም።«ሌላ ነገር አለመኖሩ በራሱ መልስ ነው» ብሎ አሰበ።«እዚህ ሆስፒታል ውስጥ የአእምሮ ሃኪም አለ» ብለው ነርሶቹ ሲያወሩ የሰማው ትዝ አለውና "እሱን ብጠይቀውስ?" አለ።ወዲያው ዘገነነው።አንቲሳይኮቲክ የተባለ መድሀኒት ውጦ ሰውነቱ ሲደክምበት ተሰማው።"እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም......." አለ
📓አለመኖር
✍️ዳዊት ወንድማገኝ(ዶ/ር)
ዛሬና መጪው ሳምንት የሰላም ውሎ እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ እነዚህን ሶስት ነገሮች ላቀብላችሁ . . .
1. ምንም ብታደርጉም ፈጽሞ ለውጥ የማታመጡትን ነገር ስታሰላስሉ አትዋሉ፡፡ መለወጥና ማስተካከል በማንችለው ነገር ላይ ጊዜያችንንና ስሜታችንን ካባከንን ሰላማችን ይናጋል፡፡
2. እጃችሁ ከገባና እናንተ ጋር ከደረሰ በኋላ የት እንደምትወስዱትና ምን ነገር ላይ እንደምታውሉት የማታውቁትን መረጃ ለመስማት ከመሞከር ተቆጠቡ፡፡ ከቀንደኛው የሰላም ጸሮች መካከል አንዱ፣ እጃችን ከገባ በኋላ ለምንም ነገር የማይጠቅም መረጃን የመስበስብ ልማድ ነው፡፡ ስራ ላይ የማናውለው መረጃ ውስጣችንን ታምቆ ሰላም ይነሳል፡፡
3. ማስታወስ በሚገባችሁና በመይገባችሁ ያለፉ ልምምዶች መካከል ለመለየት ሞክሩ፡፡ ጤና-ቢስ ልምምዶቻችሁን አንድ ጊዜ ትምህርታችሁን ካገኛችሁባቸውና ወደፊት ከተራመዳችሁ በኋላ እንደገና ላለማስታወስ ሞክሩ፡፡ ያለፉትን ጤና-ቢስ ልምምዶች ማሰላሰል ልምምዱን እንደገና እንደመኖር ያህል ነው፤ ውስጥም ያደክማል፤ ሰላም ይነሳል፡፡
የሰላም ቀን ይሁንላችሁ፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ
@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
ሳቅ ሲበዛ የሐዘንን ያህል እንምባ ያስፈስሳል፤መቀመጥ ሲበዛ የመስራትን ያህል ያደክማል፤ደግነት ሲበዛም እንዲሁ የክፋትን ያህል ይጎዳል እንጂ አይጠቅምም።
ሁሉን ነገር በመጠን ከያዙት ግን እንኳንስ መልካሙ ክፋውም ይጠቅማል ።
#ከበደ_ሚካኤል
@Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
📚መፅሐፍ አንብቦ ያልተለወጠ ሠው ካላነበበው ሠው ምንም የሚለየውና የሚሻለው ነገር የለም
ወዳጄ ሆይ…. መፅሐፍት የሚያስተምሩህ በሠውነትህ ላይ ሌላ ሠዋዊ ተፈጥሮ እንድትጨምር ሳይሆን ትክክለኛ፣ ዓላማ ያለው፣ ዕውቀት ያለው፣ ምግባርና ንግግሩ አንድ የሆነና መልካም ማንነት ያለው ሠው መሆን እንዴት እንደምትችል ነው፡፡፡
መፅሐፍት ዓላማና ራዕይ እንዲኖርህ የዕውቀት ስንቅ ያዘጋጁልሃል፡፡ ለራስህና ለዓለም በጎ ታሪክ ጥለህ ማለፍ እንድትችል ብርታትና ጥንካሬ፣ መልካም አመለካከትና ቅንነት እንዲኖርህ ያግዙሃል፡፡ ይሄ የሚሆነው ግን ጎበዝ ተማሪ ከሆንክ ብቻ ነው፡፡ ጎበዝ ተማሪ መሆን ብቻውን ዋጋ የለውም፡፡ የተማረውን በተግባር መሞከር የሚችል ብልህ የተግባር ሠው መሆንም ይጠበቅብሃል፡፡
መፅሐፍ አንብቦ ያልተለወጠ ሠው ካላነበበው ሠው ምንም የሚለየውና የሚሻለው ነገር የለም፡፡ እንደው ለወሬ ፍጆታ ብቻ ካልሆነ በስተቀር! መፅሐፍት ዓለምን እንደቴሌቪዥን ያሳዩሃል፡፡ ዓለም ውስጥ ገብተህ በዕውቀት እንድትንቦራጨቅና የጥበብ ባህሩ ላይ መዋኘት እንደትችል አማካሪህ ሆነው ያገለግሉሃል፡፡ ነገር ግን እንደአንተ አይተውኑልህም፡፡ ተዋኙ ወይ ተዋንያኑ አንተው ራስህ ነህ፡፡ ተውኔቱ ደግሞ ሕይወትህ ነው፡፡ መቼቱ ኑሮህ ነው፡፡ መድረኩ ዓለምህ ነው፡፡
ያነበብከውን በአዕምሮህ አመላልሠህ፣ ሃሳብ ጨምረህና ተንትነህ መሬት አውርደህ በተግባር አስመስክረህ የምትኖርበት አንተ ነህ፡፡ ካንተ ሌላ ላንተ ማንም አይመጣም፡፡ መፅሐፍት መነሳሳት፣ እውቀትና ክህሎት እንዲኖርህ ከጀርባ ሆነው ይገፉሃል፡፡ መንገዱን የምትጀምረው ግን አንተው ራስህ ነው፡፡ ያላንተ ያንተን መንገድ የሚሄድ ማንም የለም፡፡
በዙሪያህ ያሉ ሠዎች ልክ እንደመፃሕፍቱ ለዓላማህ እንድትቆም ይመክሩህ፣ ይዘክሩህ፣ ያነሳሱህ ይሆናል እንጂ መንገድህን አይራመዱልህም፡፡ ሠው’ነትህ ላይ በጎ ምግባርና መልካም ዕውቀት እንድትጨምር መፅሐፍት ይረዱሃል እንጂ ራሳቸው ወደውስጥህ አይገቡም፡፡ ጨማሪውም ሆነ አስገቢው አንተው ራስህ ነህ፡፡ በምንነትህ ላይ ማንነትህን እንድትገነባ የመጽሐፍት ገፆቹ እንደመስታወት ሆነው ዓለሙን ያሳዩሃል፡፡
አንባቢ ሁሉ ባነበበው አይታነፅም፡፡ ብልህ አንባቢም መሆን ይጠበቅብሃል፡፡ ትንሽ አንብበህ ብዙ ማሠላሠል ግድ ይልሃል፡፡ ያነበብካቸውን ቁምነገሮች ከራስህ ሃሳብ ጋር እያስተሳሰርክና እያዋሃድክ የራስህ አዲስ ሃሳብ እንዲኖርህ መፅሐፍት መንገዱን ይጠርጉልሃል፡፡ የሁሉም ነገር ቁልፍ ያለው አንተው እጅ ላይ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ አስተሳሰብህ ነው፡፡ የቁልፉ ጋን ምግባርና ተግባርህ ነው፡፡ ያነበብከውን በተግባር ካላረጋገጥክ መረጃ እንጂ ዕውቀት አልያዝክም ማለት ነው፡፡ ዕውቀት ማለት በማንበብ የሠበሰብከውን መረጃን በመጠቀም ለበጎ ዓላማ በተግባር በስራ ላይ ማዋል ነው፡፡ ዕውቀት በተግባር የሚገለፅ እንጂ በወሬ ላይ ብቻ የተንጠላጠለ አይደለም፡፡ ተማሪ የሚማረው ሊሠራበት ነውና ያነበብከውን አመዛዝነህ፣ ከራስህ ሃሳብ ጋር አዛምደህ፣ ከዘመኑ አዋጅተህ፣ የራስህን ሃሳብ ፈጥረህና አሳድገህ በገቢር ታውለው ዘንድ በርታ፡፡
መፅሐፍት ጌጥ ሳይሆን የነፍሳችን ምግብ ነው፡፡ ምግቡን አላምጦና አጣጥሞ መዋጥ ግድ ይላል፡፡ መዋጫ ውሃው አመለካከት ነው፡፡ አመለካከትህ መልካም ካልሆነ ጣፋጩ እሬት ይሆንብሃል፡፡
ወዳጄ መፅሐፍት ውስጥ የምታገኛቸውን ቁምነገሮች እንደ ማስቲካ አላምጠህ ከመትፋት ይልቅ አጣጥመህ ዋጣቸው፡፡ ማጣጣም ማለት ከራስ ሃሳብ ጋር ማስታረቅ ነው፡፡ ማጣጣም ማለት በሌሎች ሃሳብ ምሣሌነት የራስን ሃሳብ ማግኘት ነው፡፡ የሌሎችን ሃሳብ እንዳለ መገልበጥ ሳይሆን የራስን ሃሳብ በሌሎች መስታወትነት መስራት ነው፡፡ አበቃሁ!
ቸር ጊዜ!
©እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
