925
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+67 أيام
+1130 أيام
أرشيف المشاركات
#የምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች ቅጥር ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማከናወን በርካታ የቅድመ ምርጫ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። በመሆኑም ቦርዱ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ገለልተኛ የምርጫ ክልል ሠራተኞችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል።
በዚኽም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የምታሟሉ በሁሉም ክልሎች ላይ “በምርጫ ክልል በአስፈጻሚነት” ማገልገል የምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፤ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ https://nebe-election.org/registration_co በመጠቀም ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የሥራ ቦታ፦ በሁሉም ክልሎች፣
• የሥራ ቆይታ ፦ ለሰባት ወር፣
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
National Election Board of Ethiopia NEBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በወረዳው ያለውን ፀጋ አሟጠ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው በወረዳው ግብርና ጽ/ቤት "የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት፣ የ2018 ዋና ዋና ግቦች እና የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት የንቅናቄ መድረክ በመሀል አምባ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው።
በወረዳው በ2018 በጋ መስኖ ከ1 ሺህ 735 ሄክታር መሬት በላይ እንደሚለማ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ኡስማን
የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት የንቅናቄ ሠነድ አቅርበው ጥልቀት ያለው ግምገማ ነክ ውይይት ተካሄዷል።
የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዳሉት በወረዳው ያለውን ፀጋ አሟጠን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለመስኖ ልማት ስራ ምቹ የውሃ አማራጭ ባለባቸው አካባቢዎች ባህር ዛፎችን በማንሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት የሚሰጡ ሰብሎችን ለማልማት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ጠቅሠው
የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በልዩ ትኩረት መስራት በተለይም የማር ምርት የወረዳው ብራንድ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ መስራት ይገባል ብለዋል።
የበጋ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ አስፍቶ በመስራት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የተቀናጀ ግብርና ልማት ስራዎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ዉጤት መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ከድር መርጋ አክለውም በወረዳው የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻልና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በዘርፉ ያለውን የሰው ኃይል በአግባቡ መጠቀምና የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን በማጠናከር የዘንድሮ የበጋ የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ በውጤታማነት ለመስራት የባለድርሻ አካላት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።
በጉባኤው ላይ የወረዳ አመራሮች፣የ፣የቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ስራስኪያጆች፣ የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች፣የጽ/ቤት ባለሙያዎች፣የህዝብ ክንፍ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክት ያስተላልፉ ሲሆን
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ኡስማን
የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ሪፖርት፣ የ2018 ዋና ዋና ግቦች እና የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት የንቅናቄ ሠነድ አቅርበዋል።
በጉባኤው ላይ የወረዳ አመራሮች፣የ፣የቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ስራስኪያጆች፣ የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች፣የጽ/ቤት ባለሙያዎች፣የህዝብ ክንፍ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን!!!
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እያስገነባ የሚገኘው የአዞ ተንጠልጣይ ድልድይ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የአዞ ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር በወረዳው ከሲብ ማራንቶ እና ጎምራ ቀበሌዎች በቀላሉ የሚያገናኝ ነው።
የአዞ ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እስከሚደረግ ድረስ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ህብረተሠቡ መጠቀም እንደሌለበት የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የጥንቃቄ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮች በወቅታዊ ፓለቲካዊና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በወቅታዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ትኩረት ያደረገ የአመራር የውይይት መድረክ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም ወረዳ አቀፍ የዳልጋ ከብቶችን በሆርሞን ማድራት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመሀል አምባ ከተማ ማስጀመሩን ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በደነብ ቀበሌ የ2ኛ ዙር የሴቶች የልማት ህብረት ሞዴል ቀበሌ መመረቁን የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በተለያዩ ምክንያቶች ክትባት ጀምረው ያቋረጡ እና ምንም ያልጀመሩ ህፃናትን በመለየት ተገቢው የክትባት አገልግሎት እንዲያገኙ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼መንግስት በሚያወርዳቸው ህዝብን ተጠቃሚ በሚያደርጉ አሰራሮች ሴቶች መሪ ተዋናይ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የተቋማትና የፈጻሚዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም የህዝብ ክንፍና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ ማካሄድ ጀመረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እሬሶ ቀበሌ በሴቶች ልማት ህብረት በመደራጀት ለብረተሠቡ የናፍጣ ወፍጮ አግልግሎት እየሰጡ የሚገኙ እናቶች፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ሊያካሂድ ነው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ በምስል፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት ከ50 ሚሊዮን 717 ሺህ ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 76 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታወቀ።
፨፨፨፨///፨፨፨፨
👉🏼የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመራሩን አቅም ማሳደግ ይገባል :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የመሀል አምባ ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የወረዳው መንግስት ከከተማው ማዘጋጃ ቤትና ከከተማው ነዋሪ በቅንጅት እንደሚሰራ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስታወቁ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመጎራጉር ቀበሌ በገጠር ስራ እድል ፈጠራ በተደራጁ ወጣቶች ከ20 ሄ/ር በላይ በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝ ስንዴ እና ገብስ አሁናዊ ቁመና በምስል በከ በከፊሉ፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቤት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመት በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ከከተማው ህዝብ ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የ2018 ትምህርት ዘመን የቴክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየደረጃው አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም በመሀል አምባ ከተማ እየገመገመ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር እድሪስ ህልፈትን በማስመልከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የህብረተሰቡን የጤና ባለቤትነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስገነዘቡ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ የሚኖሩ የከሲብ ወንጀላ መረዳጃ ማህበር ከ550 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍቶችና የተማሪዎች ወንበር ከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ለሚገኙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የጤና ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በመሀል አምባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
