ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
925
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+47 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም 👉🏼‎ፅንፈኞች ከሚያሰራጩት የተዛባና የዞናችን ህዝብን ከማይወክሉ መረጃዎች ህዝቡ ሊጠነቀቅ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ገለፀ!! ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ዘመን ነባርና አዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በነፃ ለማሰልጠን ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የህብረተሠቡን የመንገድ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀዲያ እና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ የሞዴል የገጠር መንደሮችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል፤ የርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ (በምሥል) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ የአፋልጉኝ ማስታወቂያ!!! መረጃውን share በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው እናገናኛቸው!!! ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም መድረክ ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃ በማግኘት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጎነት ለጉራጌ ማህበረሰብ ባህል በመሆኑ በቀጣይም የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልእክት ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪና አከፋፈልን አስመልክቶ በዛሬው እለት ውይይት ተደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ለውዝ፣በርበሬ እና ነጭ ሽንኩርት አሁናዊ ቁምና በምስል በከፊሉ፦ 👉🏼‎ የሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሷል- ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን አበሰሩ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ለውዝ፣በርበሬ እና ነጭ ሽንኩርት አሁናዊ ቁምና በምስል በከፊሉ፦ 👉🏼‎ አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የቀን ውሎ አበል አከፋፈል ይፋ ሆነ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ መንግስት በትምህርት ዘርፉ የመደመር ፍልስፍናን ተከትሎ እየሰራ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሸው ጣሰው (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

የሰንደቅ ዓላማ ክብር ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ሉዓላዊነት መገለጫ ነው። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ሰንደቅ ዓላማ አባት እናቶች ለሀገር የከፈሉት መስዋዕትነት ማንፀባረቂያ ነው። ሰንደቅ ዓላማ የሀገር ኅብረ-ብሔራዊነት መገለጫ ዓርማ ነው። የሰንደቅ ዓላማ ክብር ከሚንፀባረቅባቸው፣ የሀገር ፍቅርም ከሚገለፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀልም ሆነ ሲወርድ በክብር እና በሥነ-ሥርዓት ቆሞ ብሔራዊ መዝሙር መዘመር ነው። በድሬዳዋ ከተማ ዘወትር ጠዋት እና ማታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ሰንደቅ ዓላማ ጠዋት ይሰቀላል፤ ማታ ደግሞ ይወርዳል። በድሬዳዋ የሰንደቅ ዓላማ መስቀል እና ማውረድ ሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት በዙሪያው የሚካሄዱ ማንኛውም እንቅሰቃሴዎች የሚቆሙ ሲሆን፤ ሁሉም ሰው ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ለባንዲራው ያለውን ክብር እና ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ይገልጻል። ይህ ልምድ የሰንደቅ ዓላማ ክብርን ለትውልድ ማስተማሪያ አንዱ መንገድ መሆኑን የድሬዳዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የሰንደቅ ዓላማ ሥነ-ሥርዓት በዚህ መልኩ በመከናወኑ ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህ ተግባር አዲሱ ትውልድ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርም እንደሚያሳድገው ተናግረዋል። የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ በወርሃ ጥቅምት የመጀመሪያው ሰኞ ይከበራል። #ebc

መስከረም 30/2018 ዓ.ም የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ዘመን ነባርና አዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በነፃ ለማሰልጠን ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመሆኑም እውቅና ባገኘንባቸው የሙያ መስኮች፡- 1/ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ( ict ) ከደረጃ 1 - 4 2/ በሜታል ማኑፋክቸሪንግ ከደረጃ 1 - 4 3/ በኮንስትራክሽን ከደረጃ 1 - 4 4/ በጋርመንት ( ጨርቃ ጨርቅ ቴክኖሎጂ ) ከደረጃ 1 - 4 5/ በፈርኒቸር ስራ ከደረጃ 1 - 4 6/ በአውቶሞቲቭ ሰርቪንግ ከደረጃ 1 - 4 ባሉን የሙያ ዘርፎች በመደበኛ ( በቀን ) ፕሮግራም በማታ ፕሮግራም በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራሞች አስተምረንና አሠልጥነን ወቅቱ የሚጠይቀው የሙያ ባለቤት እናደርጎታለን። ለምዝገባ ሲመጡ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ ዋናና አንድ ኮፒ፣ትራንስክሪፕት የ12ኛ ክፍል፣ ከ9-12ኛ ዋናና አንድ ኮፒ፣ ኢንትራንስ ውጤት ዋናና አንድ ኮፒ፣ የሰልጣኙ 3በ4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ብዛት 2 በመያዝ 03/02/2018 ዓ.ም እስከ 15/02/2018 መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ይገልጻል።

መስከረም 30/2018 ዓ.ም የህብረተሠቡን የመንገድ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በወረዳው ት/መ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሰበሰበውን የህዝብ አስተያየት መነሻ በማድረግ ከተቋሙ ማኔጅመንት አባላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄዷል። የውይይቱ አላማ ለህዝብ አስተያየት ክብርና ምላሽ በመስጠት መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች በማረም በተቻለ መጠን የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተገቢው ለመመለስ ነው። በውይይቱ ወቅት የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባስ ለሙ ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተሠበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱ የህብረተሰቡን የመንገድ ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ ተቋሙ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ቀበሌን ከወረዳና ከሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ጋር ለማስተሳሰር በወረዳ መንግስት፣ ተወላጅ ባለሃብቶችን ጨምሮ ህብረተሰቡን በማስተባበር የገጠር መንገድ ግንባታ፣ የተለያዩ ስትራክቸሮች ስራ፣ የድልድይ ግንባታ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ማከናወኑ በአውንታ ተገለጿል። በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ትርፍ ከመጫን፣ከታሪፍ በላይ ከማስከፈልና ከሚገባ ፍጥነት በላይ ከማሽከርከር ጋር ተያይዞ ማስተካከል እንደሚገባ እንዲሁም አዳዲስ ስምሪት ከመሃል አምባ ቱሉ ቦሎ፣ከመሃል አምባ አረዳ፣ከመሃል አምባ ቡትጅራ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር ተጀመረው ያልተጠናቀቁ የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች ከማጠናቀቅ አንጻር እና የሚሰሩ መሠረተ ልማቶች ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በአሉታ የተገለጹ የህዝብ አስተያየቶች ናቸው። የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሽብር ረጋ የቀረበውን የህዝብ አስተያየት ትክክለኛና ተገቢ መሆኑን ጠቅሠው በተቋም ደረጃ የተነሱ ግብዓቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘንድሮ አመት በቁርጠኝነት እንዲሚሠሩ አስገንዝበዋል። አቶ አሸብር አክለውም የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተገቢው ምላሽ ለመስጠት ህብረተሠቡና ባለሃብቶች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸው የተገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ህዝቡ በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባው አስታውቀዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። ዘገባው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

የአፍልጎኝ ማስታወቂያ!!! መረጃውን share በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው እናገናኛቸው!!! በምሰሉ ላይ የምትመለከቷት እናትችን ወ/ሮ ሙሉ ረጋሳ ይባላሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል በዱከም ከተማ በያቱ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን በዚህ ቀበሌ ቤተሰቦቻቸውና ወንድማቸው እውነቱ ረጋሳ የሚባል ወንድም እንዳላቸው እናታችን ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ሙሉ ረጋሳ ከቤተሰቦቻቸው ጠፍተው በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ ላይ መኖር ከጀመሩ ከአመታት በላይ አሰቆጥረዋል፡፡ እናታችን ወ/ሮ ሙሉ ረጋሳ የመሀል አምባ ከተማ ማህበረሰብ ከተማው ላይ ቆርቆሮ ቤት በመሰራት በክብር እያኖሯት ይገኛል፡፡ ሆኖም ወ/ሮ ሙሉ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመገናኝት ፈላጎት ሰላላቸው የዱከም ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም እናታችንን የሚያውቅ ሠው በሙሉ ቤተሰቦቿን በማፈላለግ እንድናገናኛት በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ 0910527616 መደወል ማሳወቅ እንችላለን። የመሀል አምባ ከተማ ህዝብ ለእናታችን እያደረገ ላለው ጥበቃና እንክብካቤ የሚደነቅ ነውና ክበሩልን፡፡ መረጃውን share በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው እናገናኛቸው!!!

እንኳን ደስ አለን የጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም መድረክ ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃ በማግኘት የዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!!

ወንድ 4 ሴት 6 ድምር 10

በጎነት ለጉራጌ ማህበረሰብ ባህል በመሆኑ በቀጣይም የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ ተግባራት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የ2017 የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያ፣የ2018 የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መክፈቻ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል። የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ በጉራጌ ዞን በክረምት ወራት የተሰሩ ስራዎች የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እንደነበር አስታውቀዋል። በመሆኑም እነዚህ አበረታች ስራዎች በማጠናከር ክፍተቶች በማረም በበጋ ወራትም ለሚሰሩ ተግባራት በትጋት መፈጸም እንደሚገባ መክረዋል። የወጣቶች የስብእና ማእከላት በመገንባት ያልተጠናቀቁ ቤቶች በማጠናቀቅ፣የተያዙ የበጎ ፍቃድ ተግባራት በላቀ ደረጃ እንዲፈጸሙ አቶ ኸይሩ አሳስበዋል። የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ በጎነት ለጉራጌ ማህበረሰብ ባህል በመሆኑ በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል። በበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 102 ሺህ ወጣቶች በማሳተፍ ከ2መቶ 72ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በማስጠቀም ከ92 ሚሊየን ብር በላይ ላማዳን ታቅዷል ብለዋል። በቀጣይም 158 አዲስ ቤቶች ግንባታ እና 158 ቤቶች ደግሞ በእድሳት መልክ ይሰራሉ ነው ያሉት። ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ቤቶች በአፋጣኝ ማጠናቀቅ ይገባል ያሉት አቶ ሙራድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቤት ከመገንባትና ልዩ ልዩ ድጋፎች ማድረግ ላይ አጽንኦት እንዲሰጠው አስገንዝበዋል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ወጣቶችና እስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የእስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰይፈ አለሙ እንደገለፁት የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ተቋማትን ማስፋፋትና ማዘመን ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል በማለት፣ ወጣቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ብቻ ሳይሆን በብዙሃ የኢኮኖሚ ዘርፎችም ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ብለዋል!! በውይይቱ የተሳተፉ አካላት በየ መዋቅራቸው በ17 ዘርፎች ለአብነትም በትምህርት፣በደም ልገሳ፣እርሻ በማረስ፣ቤቶች በመገንባት፣በመጠገን እና በአካባቢ ጽዳትና ውበት አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው አስታውቀዋል። በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች እንደተናገሩት በጎነት መንፈሳዊም አለማዊ እርካታ ያለው በመሆኑ ያለምንም ክፍያ በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ መሆኑን ገልጸው በቀጣይም በበጋ ወራትም በትኩረት እንደሚሰሩ አመላክቷል። በእለቱም በበጎ ፍቃድ ተግባር ትብብር ላደረጉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶችና መምሪያዎች እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

መስከረም 28/2018 ዓ.ም አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በወረዳው  ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለጤና ጣቢያ እና ለሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽኖች በጉበት በሽታ እና በኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል። በዚህ ወቅትም የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባረክ ሰይፉ እንዳሉት ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በጉበት እና በኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት የግንዛቤ ስልጠና በበቂ ሁኔታ መሰጠቱን ተናግረዋል። ህጻናት በተወለዱ በ24 ሰአት ውስጥ የሚሰጥ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት አዲስና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ እንደሆነም አመላክተዋል። ይህ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱና ወደ ጤና ተቋማት ሲገባ አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት በ24 ሰአት ውስጥ እንዲከተቡ ይደረጋል ብለዋል። ስልጠና የወሰዱ ባለሙያዎኞች በተግባር ቀበሌ ድረስ በመውረድ ለማህበረሰቡ ተወካዮች የግንዛቤ ስልጠና የሚሰጡም እንደሆነ ተናግረዋል። የኩፍኝ ክትባት ቀደም ሲል ለጥቂት ህጻናት ተብሎ የማይከፈት እንደነበረና በዚህ ምክንያት  ክትባቱ ሳይከተቡ የሚያመልጣቸው በርካታ ህጻናቶች እንደነበሩ አስታውሰው። አሁን ላይ ክትባቱ ይቀርብበት የነበረው ብልቃጥ የተቀየረ ሲሆን ብልቃጡም ለአምስት ህጻናት ተደርጎ መቅረቡና ወደ ጤና ጣቢያ አንድ ህጻን ለክትባት ቢመጣ እንኳን ክትባቱ ተከፍቶ እንደሚሰጥም አመላክተዋል። ሁሉም ህጻናቶች ዘጠኝ ወር ወይም አንድ አመት ከሶስት ወር የሞላቸው ህጻናት ወደ ጤና ተቋም በማምጣት ክትባት እንዲከተቡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና እንደሆነም ተጠቁሟል። በቀጣይ ክትባቱ በሚቀርብበት ጊዜ ጽ/ቤቱ የክትትልና የድጋፍ ስራ አጠናክሮ እንደሚሰራም አስታውቀዋል። ስልጠናው ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች፣ ለክትባት ፕሮግራም ሙያተኞች ፣ ለእናቶችና ህጻናት ጤና አስተባባሪዎችና ለጤና መረጃ ባለሙያዎኞች፣ ለጤና ኤክስቴንሽኖች እንዲሁም ለጤና ጽ/ቤት ለቴክኒካል ወርኪንግ ግሩፕ አባላት ስልጠናው ተሰጥቷል።