ar
Feedback

لا تقع ضحية للمخادعين! تيليمتريو يكتشف ويُميّز هذه القنوات 👉 إذا كنت تريد رؤية العلامة، اشترك

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
925
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
+930 أيام
أرشيف المشاركات
ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ ኩታገጠም የመኸር ድንች ማሳ በምስል፦

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መርጃ ቁሳቁስ ለመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከመስፈንጠር ከፍታ፣ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ምዘና መጠናቀቁ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል በወረዳው ርዕሰ- ከተማ መሃል አምባ ላይ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የ2017 በጀት አመት ግምገማና ምዘና መድረክ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከመስፈንጠር ከፍታ፣ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ መካሄድ ጀመረ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ህብረተሰቡን በመንገድ ልማት መስክ የማስጠቀሙ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎"ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና የተሟላ ክብር'' " በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ደሳ ቀበሌ ከ36 ሄክታር በላይ በክላስተር በተዘጋጀ መሬት ላይ የመኸር የስንዴ ዘር ተዘርቷል። 👉🏼‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ለ2018 በጀት ዓመት 43 ቢሊየን 252ሚሊየን 509ሺ 909 ብር አጸደቀ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር በመሆኑ የዘውትር ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት አፈጻጸሞች፣በ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የአመራር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የወልቂጤ ግብርና ምርምር ማዕከል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም ‌‎የጉራጌ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት በአጠቃላይ የፖለቲካና ንቅናቄ ስራዎች የአንደኝነት ደረጃን አገኘ‼ ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎

ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መርጃ ቁሳቁስ ለመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዚህ ወቅትም የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን መንግስት ልዩ ትኩረት ሠጥቶ ከሚሰራባቸው መስኮች አንዱና ዋነኛው የጤናው ዘርፍ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ጤናው የተጠበቀ ሁለንተናዊ  ምርትና ምርታማነቱን ማረጋገጥ የቻለ ዜጋ ማፍራት የፖሊሲው አንዱ አካል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው መንግስት በሚጠበቀው ልክ ተደራሽ ያልሆነባቸውን ልማታዊ ስራዎች ለማልማት የመንግስትን፣ የህዝቡን፣ የተወላጅ ባለሀብቶችና መሠል አቅም በማስተባበር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አፅንኦት ሠጥቶ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሠው ከዚህ አኳያ የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግብዓት እጥረት ምክንያት ለህብረተሠቡ መስጠት የሚገባውን የጤና አገልግሎት መስጠት ሳይችል መቆየቱን ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አህመድ ዶ/ር አማካኝነት "አንድ ፕሮጀክት በአንድ ወረዳ" በሚል የተያዘውን ውጥን ለማሳካት የተቋሙን ችግሮች ለመፍታት ሠፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራስኪያጅና ተወላጅ ባለሃብት የሆኑት አቶ ጀማል አህመድ በሌሎች ከሚያደርጓቸው ልማታዊ ተሳትፎዎች በተጨማሪ የመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን የግብዓት ችግሮች በመረዳት ችግሩን መቅረፍ እንዲቻል ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የሆስፒታሉን የግብዓት ችግር ለመቅረፍ የሠሩት ስራ ትውልድ የማይረሳውና ዘመን ተሻጋሪ ተግባር መሆኑን ገልፀው በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተወካይ አቶ ሙህዲን መኪ እንዳሉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አህመድ የመ/አ/የመ/ደ/ሆስፒታል ያሉበትን የግብዓት ችግሮች በመፍታት የህብረተሰቡ ጤና ባለቤትነት ለማረጋገጥ  ሠብዓዊ ሃላፍትናቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ባለሃብቱ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን በመግለፅ X-ray ማሽን፣ ባክአፕ ጄኔሬተር፣ራዲያተር፣ላውንደረያ ማሽን ሌሎች 9 አይነት የህክምና ማሽኖች ድጋፍ መደረጉን በመግለፅ ባለሃብቱ እያደረጉት ያለውን ሁለንተናዊ እገዛ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ አስታዉቀዋል።  የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበኩላቸዉ ድጋፉ የተሟላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ወሳኝ ሚናን ይጫወታል ብለዋል። ድጋፉ የተሟላ የጤና አገልግሎት መስጠት ያስችላልም ብለዋል። አክለውም ባለሃብቱ ላደረጉት ድጋፍ በዞኑ መንግስት ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ አየለ ፈቀደ "በሽታን አስቀድሞ መከላከልና አክሞ ማዳን" ፖሊሲያችንን በተጨባጭ ተግባራዊ እናደርጋለን ያሉ ሲሆን የቀረቡ ግብዓቶችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሃመድ አሚን ጀማል ባስተላለፉት መልዕክት የወረዳው መንግስት የጤና ሴክተሩን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ከተቋማቸው ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ተከትሎ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጨባጭ ለውጥ መኖሩን ገልፀዋል። መንግስት የዜጎች ጤና ተደራሽነት ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ መሃመድ አሚን የመ/አ/የመ/ደ/ሆስፒታል ከ500 ሺህ በላይ ለሚጠጉ በወረዳው ውስጥና በወረዳው ዙሪያ ለሚገኙ ዜጎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህንን አገልግሎት በተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ድጋፉ መደረግ የአንበሳውን ድርሻ ይጫወታልም ብለዋል። አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በሠጡት አስተያየት ቀደም ሲል ተፈላጊዉን የጤና አገልግሎት ለመስጠት የግብዓት አለመሟላት ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖ መቆየቱን ጠቅሰው ምስጋና ለተወላጅ ባለሃብቱ ይግባና አሁን ላይ የተደረገው እገዛ ሆስፒታሉ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እንዲችል ምቹ ዕድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ የባለሙያዎችን ሸክም የሚያቀል ስለመሆኑ አብራርተዋል። የሆስፒታሉ ተገልጋዮች በበኩላቸዉ ከዚህ ቀደም የግብዓት ዕጥረት መኖሩን ተከትሎ ሪፈር ወደ ተለያዩ አጎራባች ወረዳዎችና ክልሎች ይላኩ እንደነበር አስታውሰው ምስጋና ለተወላጅ ባለሃብት አቶ ጀማል አህመድ ዛሬ ላይ የተደረገው ድጋፍ ከአላስፈላጊ ወጪና እንግልት የሚታደጋቸው ስለመሆኑ ተናግረዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ሐምሌ 19/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከመስፈንጠር ከፍታ፣ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ምዘና መጠናቀቁ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙረድ ያሲን ምዘናው በወረዳው የተጀመሩ ተግባራት በማጠናከር የተገኙ ስኬቶችን ዘላቂነት ማረጋገጥ እንዲቻል አመራሩ ላይ ትልቅ አቅምንና መነሳሳትን ሊፈጥር የሚችል መሆኑን ገልጸዋል። በምዘናው ‎አመራሩ የነበሩበት ጉለቶችን ለይቶ በማረም በተጠያቂነትና በሀላፊነት ስሜት የተሻለ ስራ እንዲሰራ የሚያደርግ ነው ብለዋል። አቶ ሙራድ አክለውም አመራሩ የፓርቲውን መርሆችና እሳቤዎች በተገቢው ተገንዝቦ መርህን መሠረት ባደረገ መልኩ ተግባራትን ፈጽሞ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ እንዲችል ትልቅ አቅምን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ‎ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው የግምገማና ምዘና መድረኩ አመራሩ ቀሪ ተግባራትን በጊዜ የለኝም መንፈስና በቁጭት መፈጸም እንዲችል አዲስ መነሳሳትን የፈጠረለት መሆኑን ጠቅሠው አጠቃላይ የነበረው ሂደት እንደ ወረዳ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ለማጽናትም ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል በማለት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። የወረዳው ዋና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም የምዘና ስርዓቱ በአመራሩ መካከል የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት ይበልጥ የሚካጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ምዘናው አመራሩ ባለፉት ጊዜ የነበሩ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች በመለየት ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ምዘና መሆኑን ጠቁመው የአስተሳሰብ፣የአደረጃጀትና የተግባር ውህደት በመፍጠር የህዝቡን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ ስራዎች መስራት እንደሚገባው አስገንዝበዋል። አጠቃላይ በሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ የነበረው የግምገማና ምዘና መድረክ ሪፖርት በቡድን መሪዎች ቀርቦ ሃሳብና አስተያየቶችን በመስጠት መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የ2017 በጀት አመት ግምገማና ምዘና መድረክ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከመስፈንጠር ከፍታ፣ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የኮሚቴ አባላት ምዘና መድረክ ተካሄደ። በምዘና ሂደቱ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ስራ አመራር ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል፡፡

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከመስፈንጠር ከፍታ፣ ወደ ላቀ እምርታ"በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የአመራር ማጠቃለያ ምዘና መድረክ መካሄድ ጀመረ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ እንደገለጹት የአመራር ምዘና ስርዓቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የምዘና ስርዓቱ መደበኛ የመንግስት ተግባራትንና የፓርቲ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመወጣት አቅም የሚገነባ መሆኑንም ተናግረዋል። የ2017 ዓ.ም ከተግባር አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የተስተዋሉ ጉድለቶችን መነሻ ያደረገ የሰላ ግምገማ ማድረግ እንደሚገባ አብራርተዋል። የፓርቲውን እሳቤና መርህ መነሻ አድርጎ ተግባራትን ከመፈጸም አኳያ፣የተቋማት የተግባር አፈጻጸም፣ስነ-ምግባርና አጠቃላይ ውጤታማነትን መነሻ ያደረገ ግምገማ መደረግ እንዳለበት አቶ አ/ረሂም ርዳ አሳስበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አሁን ላይ የምናካሄደው የ2017 ዓ.ም የማጠቃለያ ግምገማና የአመራር ምዘና ለቀጣይ የተግባር ወቅቶች ተጨማሪ አቅምን በመፍጠር ለተሻለ አፈጻጸም የሚያዘጋጅ በመሆኑ ሁሉም መድረኩን ጉድለቱን ሊሞላ በሚችል መልኩ ማስኬድ ይኖርበታል ብለዋል። የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ ወረዳዊ የአመራር ነባራዊ ሁኔታንና ሌሎች ነጥቦች አጣምሮ የያዘ ሰነድ ቀርቦ በጥልቀት ውይይትና ግምገማ ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል። የግምገማ መድረኩ ለሁለት ተከታታይ ቀናቶች እንደሚቆይም ተገልጿል።

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ህብረተሰቡን በመንገድ ልማት መስክ የማስጠቀሙ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ፅህፈት ቤቱ የ2017 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ መድረክ ዛሬ አካሂዷል። በዚህም ወቅት የፅህፈ ቤቱ ልማት ባለሙያ አቶ አንዋር መሐመድ የ2017 ዓ.ም አራተኛ ሩብ ዓመት በሚል ለመድረኩ የተዘጋጀ ሠነድ አቅርበው ውይይት ተደርጓል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸዉ አስተያየቶች መካከል ፅህፈት ቤቱ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ተግባራት ተደናቂና ሊታዩና ሊቆጠሩ የሚችሉ በመሆናቸው ህብረተሠቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል በአንፃሩ የተጀመሩ የመንገድ፣ የድልድይ፣ የቱቦና መሠል ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ፣ መጠንና ጥራት ከማጠናቀቅ አኳያ የሚስተዋሉ ጉድለቶች ላይ ጠንካራ ስራ መሠራት እንደሚገባው ያነሱት ተሳታፊዎቹ ከትራንስፖርት ዘርፍ ጋር በተያያዘ በተሳፋሪም ሆነ በጭነት ዕቃ ላይ ያልተገባ የታሪፍ ክፍያ ተገልጋዩ እንዲከፍል እንደሚገደድ፣ የመንገድ ዳር ምልክቶች የመትከል ስራ በተጠናከረ መልኩ ቢጠናከር፣ ከተፈቀደዉ ፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ ደንብ የማስከበሩ ሂደት መጠናከር ይገባዋል የሚሉት በዋናነት ተጠቃሾች ናቸው። የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ርጋ በማጠቃለያቸው ከውይይት መድረኩ የተነሱ ርዕሠ-ጉዳዮች ገንቢና ለቀጣይ ስራ እንደ ስንቅ ተወስደው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎባቸው እንደሚሠራ ገልፀዋል። አክለውም ህብረተሰቡ የተዘረጉ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በባለቤትነት ወስዶ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው የህብረተሠቡን የመንገድ ልማት ተደራሽነት ችግር ሙሉ በሙሉ ለመፍታት የተጀመረዉን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ሊያግዙት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም አቶ አሸብር ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡን በመንገድ ልማት መስክ የማስጠቀሙ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል ሲል የዘገበው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ሐምሌ 17/2017 ዓ.ም "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና የተሟላ ክብር'' " በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ደሳ ቀበሌ ከ36 ሄክታር በላይ በክላስተር በተዘጋጀ መሬት ላይ የመኸር የስንዴ ዘር ተዘርቷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ከረጂነት ወደ ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነትና የተሟላ ክብር'' በሚል መሪ ሀሳብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ደሳ ቀበሌ ከ36 ሄክታር በላይ በክላስተር በተዘጋጀ መሬት ላይ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ የሚሆን የስንዴ ዘር መዝራት ተጀምሯል። በዕለቱ የመኸር ስንዴ ዘር ማስጀመሪያ ላይ የጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙረድ ያሲን፣የወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አ/ረሂም ርዳ፣የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊና ም/አስተዳዳሪ አቶ ከድር መርጋ ጨምሮ ሌሎች የአስተባባሪ አካላት በመገኘት አስጀምረዋል።