ar
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

الذهاب إلى القناة على Telegram
918
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
+17 أيام
+730 أيام
أرشيف المشاركات
የካቲት 13/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ6 ወር የትምህርት ቤቶችን ተግባር አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት የ2018 የመጀመርያ መንፈቅ አመት የትምህርት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማና በቀጣይ ቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ የ2018 የመጀመርያ መንፈቅ አመት ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የጽ/ቤቱ የፈተናና ምዘና ባለሙያ የሆኑት አቶ ሱሩር ኸይረዲን የሴሚስቴሩን የተማሪዎች ውጤት አቅርበዋል። በግምገማ መድረኩ የየትምህርት ቤቱ ርዕሳና መምህራን እና የተቋም ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ በቡድን ተከፋፍሉ እየተካሄደ ሲሆን በነገው እለትም እንደሚቀጥል ተመላክቷል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!!!

የካቲት 13/2018 ዓ.ም ‎"ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ7 ወር ስራ አፈፃፀም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ "ክህሎት መር ስራ ዕድል ፈጠራ ለብልጽግናችን" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ ዕድል ፈጠራ ምክር ቤት የ7 ወር ስራ አፈፃፀም እና እዳ አስመላሽ ግብረ ሃይል የግምገማ መድረክ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ የ2018 በጀት አመት የ7 ወራት አፈጻጸም እና እዳ አስመላሽ ግብረ ሃይል ሰነድ አቅርበዋል። በመድረኩ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የጽ/ቤቱ እና የቀበሌ አደራጅ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን!!!

የካቲት 12/2018 ዓ.ም ውስን የሆነውን የመንግስት በጀት በአግባቡ በመጠቀም፣በመቆጣጠርና በመከታተል በጀቱ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህን ያስታወቀው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍይናንስ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ አባላት በተገኙበት ውይይት በዛሬው እለት ባካሄደበት ወቅት ነው። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በጽ/ቤቱ የልማት እቅድ ባለሙያ በአቶ ኤሊያስ ለማ አማካይነት ቀርቡ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓበታል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ካነሷቸው አስተያየቶች መካከል ተቋሙ ህዝቡን በቀጥታ ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣የሀብት ብክነትን ለመከላከል እየተሰራ ያለው ስራ ፣የመንግስት ሰራተኛው የደረጃ ዕድገት ለመስራት እየሰራ ያለው ስራ ሊበረታታ እንደሚገባ የገለጽት አስተያየት ሰጪዎቹ ያልተጠናቀቁ ካፒታል ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት ቢሰጣቸው፣ የኦዲት ግኝት በተገቢው ማስመለስ እና ተጠያቂ ማድረግ እንደ ሚገባ እና ተቋማትን ተደራሽ ሆኖ ኦዲት ከማድረግ ጋር ተደራሽ መሆን እንዳለበት ፣በቀሪ ጊዜያት የተጀመሩ ካፒታል ፕሮጀክቶች ከአሰሪ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እንዲጠናቀቁ ማድረግ እንደሚገባ ፣በታችኛው ተቋም ሂሳብ አያያዝ ምን እንደሚመስል ክትትል መደረግ እንዳለበት በየ ቀበሌው ያሉ ደረሰኞችገቢ እንዲሆኑና ገንዘቡ ለታለመለት አላማ መዋል እንዳለበት የሚሉት ይገኙበታል ከተሳታፊዎች ለተነሱት ጥያቄ እና አስተያየቶች ከመድረኩ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበታል። የወረዳው ፍይናንስ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ መኪ ሀጂ ሃይደር ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት በስድስት ወራቱ የተከናወኑ መልካም ስራዎችን ማጠናከር በውስንነት የታዩትን ደግሞ በቀጣይ ለማሻሻል የሚያግዝ መድረክ መሆኑን ጠቅሠው ተቋማት በጀት በአክሽን ፕላን መጠቀም ይገባል በማለት ለተያዙ እቅዶች መሳካት የገቢ እቅድ አፈፃፀም ከፍ ማድረግ እና የኦዲት ግኝቶች በየትኛውም ተቋም የሚገኙ ግኝቶችን ማስመለስ ያስፈልጋል ብለዋል። የፋይናንስ ተቋም የልማት የጀርባ አጥንት በመሆኑ የሚያመልጡን ገቢና ያልተመለሱ ደረሰኞች ገንዘብ የያዙ በመሆናቸው እንዲመለሱ እና ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ሁሉም የበከሉን ድርሻ መወጣት ይገባል ሲሉ አቶ መኪ መልዕታቸው አስተላልፈዋል። የፋይናንስ ጽ/ቤት የስነ ምግባር ኦፊሰር አቶ ናስር ጫካ በበኩላቸው ፈጣን ቀልጣፋና ግልፀኝነት የተላበሰ የፋይናንስ ስርዓትን በማስፈን በወረዳው በመደበኛና በካፒታል በጀት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በሚመልስ አግባብ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በመግለፅ የተቋማት የልማት እቅድ ባለሙያዎች የመንግስት በጀቶች ለታለመለት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ላይ በተገቢው ሚናቸው  መወጣት እንዳለባቸው ፤ከኦዲት ግኝት ጋር ተቋማት ራሳቸው መከላከል እንደሚገባቸውና እና ሁሉም ተቋም እገዛ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ መልዕታቸው አስተላልፏል ። በመድረኩ የተቋማት የልማት እቅድ ባለሙያዎችና የህዝብ ክንፍ አባላት ተሳትፈዋል።

የካቲት 12/2018 ዓ.ም የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን የመንገድ ፍላጎት ለማሟላትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው:- (ዶ/ር) መሀመድ ኑሪዬ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባው የሻፋሞ ወርደነ ዊንቄ ድልድይ ፕሮጀክት ተመረቀ። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ እንዳሉት የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን የመንገድ ፍላጎት ለማሟላትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው። በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮ አቀማመጣቸው ምክንያት የተገለሉ ማህበረሰቦችን ለማገናኘት ድልድይ፣ ስትራክቸርና ተንጠልጣይ ድልድይ በመገንባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። የድልድዩ መገንባት ከዚህ ቀደም የነበረው የህብረተሰቡን እንግልትና ስቃይ ከማቃለል ባለፈ የእርስ በእርስ ግንኙነትና ትስስር ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ተናግረዋል። የመንገድ ፍላጎት አዳጊ ነው ያሉት ዶ/ር መሀመድ ነርዬ የክልሉ መንግስት ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመንገድ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት እንደሚሰራ አመላክተዋል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው ድልድዩ የእኖርና የቸሃ ወረዳ ህዝቦችን እርስ በእርስ ከማገናኘቱም ባለፈ ከዚህ ቀደም የነበረው የማህበረሰቡን እንግልትና ስቃይ በማቃለል ረገድ ፋይዳው ትልቅ ነው ብለዋል። የጉራጌ ማህበረሰብ ተንቀሳቃሽና የመንገድ ልማት ጥቅም አስቀድሞ በመረዳቱ የጉራጌ የመንገድ ስራ ድርጅት በማቋቋም በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን አስታውሰው የአሁኑ ትውልድም ይህንን ተግባር እያስቀጠለ ይገኛል ነው ያሉት። በዞኑ ማህበረሰቡና ተወላጅ ባለሀብቶችን በማስተባበር ዋና መንገድ- ከቀበሌ፣ ቀበሌ-ከቀበሌና መንደር- ከመንደር እንደ ሸረሪት ድር ለማገናኘት እየተሰራ መሆኑ ያነሱት አቶ ላጫ በዘንድሮ አመትም 3 መቶ ኪሎሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም የማህበረሰቡን የእርስ በእርስ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ የግብርና ልማት ስራዎችን ለማሳለጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም አስረድተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምስጋናው ማቲዎስ የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ድልድዩ መገንባቱን አመላክተዋል። የድልድይ ፕሮጀክቱ 28 ሜትር ርዝመት ያለው መሆኑን አንስተው ይህም የህብረተሰቡ የእርስ በእርስ ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አገልግሎቶችን ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ተናግረዋል። የድልድይ ፕሮጀክቱ ለዚህ ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የእኖር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መብራቴ ተክሌ እንደገለጹት በአካባቢው ድልድይ ባለመኖሩ ከዚህ ቀደም የህብረተሰቡ ህይወት ከመቅጠፍ ባለፈ ለበርካታ እንግልትና ስቃይ ይዳረጉ እንደነበር አንስተዋል። ዛሬ የተመረቀው ድልድይ ለአካባቢውና ለዙሪያው ማህበረሰብ እንዲሁም ለወረዳውና ለአጎራባች ወረዳ በኢኮኖሚ ትልቅ መነቃቃት እንደሚፈጥር አንስተው በወረዳውም የህብረተሰቡን አቅም በማስተባበር በዘርፉ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት ከዚህ ቀደም በአካባቢው ድልድይ ባለመኖሩ ለበርካታ እንግልትና ስቃይ ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰው ድልድዩ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በመደረጉ መደሰታቸውን አመላክተዋል።

የካቲት 11/2018 ዓ.ም "በመደራጀት ወደ ተግባራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የሴቶች ልማት ህብረት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀመረ። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎"በመደራጀት ወደ ተግባራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል ዞን አቀፍ የሴቶች ልማት ህብረት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄድ ጀመረ። ‎ ‎በዞኑ ሁለንተናዊ  ብልጽግና ለማረጋገጥ፣  ሰላም ለማስፈንና የሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው ለማጠናከር  በየመዋቅሩ የሚገኙ የሴቶች ልማት ህብረት ማጠናከር እንደሚገባ ተጠቁሟል። ‎ ‎በበጀት አመቱ በዞኑ 185 ሺህ 5  የልማት ህብረት አባላት በማደራጀት 105 ሚሊዮን ብር እንዲቆጥቡ የተደረገ ሲሆን በየ መዋቅሩ ሞዴል አደረጃጀቶች በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመላክቷል። ‎ ‎በመድረኩ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አፈፃፀም፣ የሴቶች ልማት ህብረት የዳታ ቤዝ አፈፃፀም፣ በአንድ ቀበሌ አንድ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ የማደራጀት ኢንሼቲቭ አጀንዳዎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከነድረኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ‎ ‎በመድረኩ የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ናስር ሀሰን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ምክትል እና የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ ራህመቶ፣  የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ነጅሚያ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የዞኑ፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች፣ የጤና እና ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሴክተር ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የካቲት 10/2018 ዓ/ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አዘጋጅነት የልማት ስራዎች ጉብኝት በዛሬው እለት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ 6 ወራት አፈጻጸም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት መገምገሙን ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል። በዛሬው እለት በተደረገው የልማት ስራዎች ጉብኝት HLS ሃላፊነቱ የተወሰነ የአበባ ልማት እንዲሁም ከኢሎ ማዞሪያ መሃል አምባ የአስፓልት መንገድ የተቋሙን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ የመስክ መስክ ምልከታ ተካሄዷል። በዛሬው እለት የተጎበኘው HLS የአበባ ልማት እስካሁን 11.3 ሄክታር መሬት ላይ 2.3 ሚሊዮን ማዘር ፕላንት ችግኝ የተተከለ ሲሆን ከ270 በላይ ሰራተኞች የስራ እድል መፈጠር የቻለ ድርጅት መሆኑ የተገለኀ ነው ድርጅቱ  ከወረዳው መንግስት ጋር በመቀራረብና በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኙ ተመላክቷል። በውይይቱና በልማት ስራ ጉብኝቱ ላይ የወረዳው የመንግስት ተቋማት የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ  ባለሙያዎችና የህዝብ ክንፍ አባላት የተገኙ ሲሆን የHLS አስተዳደር አቶ መኪ ዘይኑ ፣ የፍርም ማናጀር አቶ አክሊሉ አሰፍ እና የፕሮዳክሽን ማናጀር የሆኑት አቶ ሚርከና ከበደ ስለ ድርጅቱ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ገለጻ አድርገዋል።