cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ንፅሕይት◈ሙሽራ▸tube ▸-ደረጄ

👉በዚህ #የቴሌግራም ቻናል መንፈሳዊ ነገር መዝሙርም ሆነ ትምህርቶች ይተላለፋሉ👈🌿🌿🌿🌿 🌿🌿🌿 https://ye_tewahdo_lij ◂▹ይህን Channel Share በማድረግ ቤተሰብ እናፍራ👈🌿🌿🌿 ▹◂የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያሳየን▹◂ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 💦💦💦💦💦💦💦💦💦💦❄️💦💦💦💦💦💦💦💦

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
201
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Watch "መንግስት የማዘናጋት ስራ እየሰራ ነው! 👋 ከባድ ጥንቃቄ❗️ሰልፉ መቅረት የለበትም አባቶች ❗️ንቁ ❗️📢📢❌ #መምህር_ምረተዓብ ታስሯል !" on YouTube https://youtube.com/watch?v=nAxx-UpBD0k&feature=shares
إظهار الكل...
መንግስት የማዘናጋት ስራ እየሰራ ነው! 👋 ከባድ ጥንቃቄ❗️ሰልፉ መቅረት የለበትም አባቶች ❗️ንቁ ❗️📢📢❌ #መምህር_ምረተዓብ ታስሯል !

ወዴት እየተሔደ ነው ግን ❌ ኧረ አባቶቼ ንቁ ! ሰውዬው እየተሞዳሞደብን ነው,🙄

Watch ""ያሳደገችን እናት ቤተ ክርስቲያን" ወቅታዊ የንሰሀ ዝማሬ_በዘማሪ ደረጄ ዳኜ @dereje_dagne #channel #ማኅቶት_ቲዩብ #ethiopia" on YouTube https://youtube.com/watch?v=vf-KIwCV4ng&feature=shares
إظهار الكل...

Watch "ስለ ህፃናት ብለህ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ታደግልን !😪😪#ማኅቶት_ቲዩብ #ቤተ_ቅኔ" on YouTube https://youtube.com/shorts/cQGSNxXF7Jc?feature=shares
إظهار الكل...

Photo unavailableShow in Telegram
ያሳደገችን እናት ቤተ ክርስቲያን" በቅርብ ቀን በ #ንፅሕይት_ሙሽራ tube" ይጠብቁ👋 https://www.youtube.com/@dereje_dagne
إظهار الكل...
የዋልድባ አባቶች መልእክት "…የዋልድባ አብረንታንት አንድነት ገዳም ዘቤተ ሚናስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጠረውን ችግር አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና  በቅዱስ ሲኖዶስ የወጣውን መመሪያና ትእዛዝ ተከትሎ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ/ም ማኅበረ መነኮሳቱ በአብረንታንት ቤተ እግዚአብሔር ተስብስበው የቅዱስ ስኖዶስ ውሳኔ በገዳማችን እንዲተገብር በማለት ማኅበረ መነኮሳቱ ወስነዋል። "…በተጨማሪም ማኅበረ መነኮሳቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ለቅዱስ አባታችንም፣ እንዲሁም ልህዝበ ክርስቲያኑ የማጽናኛና የማበረታቻ አይዟችህ የሚል ገዳሙ ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤም እንዲጻፍ ሲሉ ማህበረ መነኮሶቱ ወስነዋል። በተጨማሪም በቋርፍ ቤትና በሞፈር ቤቶች ከቀድሞው (ዘወትር ከምናደርገው) በተለዬ መልኩ ጸሎተ ምህላው ተጠናክሮ ይቀጥል። "…በገዳሙ የሚኖር ማንኛውም መነኩሴ ከሊቅ እስከ ደቂቅ 150 መዝሙረ ዳዊት በቀን እንዲደግም። ከደገመ በኋላም መጸሐፉን መሬት ላይ ደፍቶ ያስቀምጥ። መቁጠሪያውንና መቋሚያውን ጸሎት ከጨረሰ በኋላ መሬት ላይ ይጣል። ምግብን በተመለከተ በቋርፍ ቤትም ሆነ ብእህል ቤቶችና  በአትክልት ቦታዎች ጨው፣ በርበሬ፣ ያለበት ምግብ ከሰኞ ጀምሮ ለ3 ቀን እንዳይመገብ። በማንኛውም ቦታ የገዳማችን መነኮሳት ባእት እሳት እንዳይነድ። ከቤተ እግዚእብሔር የሚሰጠውን ብቻ እንዲመገብ። የተመገበበትን ፋጋ ከጨረሰ በኋላ ባፉደፍቶ እንዲያሳድር። ከምሽቱ 12 ሰዓት ውጭ የመቁንን ደውል እንዳይደውል። ውኃ ከአንድ ብርጭቆ በላይ እንዳይጠጣ። ሻይ እንዳይፈላ። ጭልቃ እንዳይጨለቅ ወስኗል።  "…ይህ ትእዛዝ በሁሉም የቋርፍ ቤት፣ የአትክልት ቦታ፣ የሞፈር ቤቶች፣ በየዋሻው እና በየፍርኩታው ላሉ ባህታውያን አባቶች መልክቱ ይተላለፍ። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንና በሀገራችን የመጣው አደጋ ቀላል አይደለም በሚል ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ከትናንት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ተደርጓል። "…በአባቶች በኩል ነገሩ በጥብቅ ተይዟል። ነገሩን ያከበዱት ይመስለኛል። የሰማይም የምድርም አምላክ አልፋና ኦሜጋ የሰራዊትጌታ ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ስለ ሚስኪናን ባሮችህ ስትል ማረን ይቅርም በለ😪 @zemari_dereje_dagne
إظهار الكل...
የንሰጥሮሳውያንን ሹመት እንቃወማለን /የባለ ጊዜነት ሹመትን/👼🙅‍♂️🙅‍♂️ የአረመኔውን የቤተክርስቲያን ቀንደኛው ጠላት መንግስት ነኝ ባዩን አካል አጥብቀን እንቃወማለን 🙅‍♂️ የተዋህዶ ልጆች አሁን ካልነቃችሁ መቼም እንደማትነቁ ልነግራችሁ እወዳለሁ !! በቃ ተነስ እንዴ እንደ ፍራቻ እየቆጠሩብን ነው ! @zemari_dereje_dagne
إظهار الكل...
​​እንኳን ለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ወላዲተ አምላክ ማርያም ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †✝† † #ዕረፍተ_ድንግል † እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር:: ዓለም ተፈጥሮ: አዳምና ሔዋን ስተው: መርገመ ሥጋና መርገመ ነፍስ አግኝቷቸው: በኃዘን ንስሃ ቢገቡ "እትወለድ እም ወለተ ወለትከ - ከ5 ቀን ተኩል (5500 ዘመናት) በሁዋላ ካንተ ባሕርይ ከምትገኝ ንጽሕት ዘር ተወልጄ አድንሃለሁ" ብሎ ተስፋ ድኅነት ሰጠው:: ከአዳም አንስቶ ለ5500 ዓመታት አበው: ነቢያትና ካህናት ስለ ድንግል ማርያም ብዙ ሐረገ ትንቢቶችን ተናገሩ:: መዳኛቸውን ሱባኤ ቆጠሩላት:: ምሳሌም መሰሉላት:: ከሩቅ ዘመን ሁነውም ሊያገኟት እየተመኙ እጅ ነሷት:: "እምርሑቅሰ ርእይዋ: ወተአምኅዋ" እንዲል:: የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ - ከአዳም በሴት - ከያሬድ በሔኖክ - ከኖኅ በሴም - ከአብርሃም በይስሐቅ - ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ - ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች:: ከሌዊ ደግሞ በአሮን: አልዓዛር: ፊንሐስ: ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች:: አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ ኢያቄም ወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7) "ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ:: (ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ) ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12 ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት:: በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው:: ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር: ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ:: (ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ) ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ: እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14) "ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በገሊላ ለ2 ዓመታት ቆዩ:: አርዌ ሔሮድስ እገድላለሁ ብሎ በተነሳበት ወቅትም ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም: በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር ሲሆነው: ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ:: በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች:: እርሷ 45 ዓመት ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3 ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም እያደረች ትምሕርቱን ሰማች:: የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች:: ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች:: ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮንም ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች:: በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ: ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና: ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች:: ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ: ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል:: "ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:: ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ::" እንዲል:: ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:- "ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:: እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:: ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል:: በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ: እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል:: በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል:: በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ 1 ቀን ሱባኤገቡ:: ለ2ሳምንታት ቆይተው: ሁሉንም ወደ ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት ተመልሰዋል:: ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን: ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን: ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን:: #ቅዱስ_ጐርጐርዮስ_ሊቅ ለዚህ ቅዱስ አባት ብጹዕ መባል ተገብቷል:: ክቡር: ምስጉን: ንዑድ ሰው ነውና:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቂሣርያ ቀዸዶቅያ የተወለደው ቅዱሱ ሰው ለደሴተ ኑሲስ ብርሃኗ ነው:: አባቱ ኤስድሮስ: እናቱ ኤሚሊያ: ወንድሞቹ ቅዱሳን "ባስልዮስ: ዼጥሮስ: መክርዮስና መካርዮስ" ይባላሉ:: የተቀደሰች እህቱም ማቅሪና ትባላለች:: ከዚህ የተባረከ ቤተሰብ ለቅድስና ያልበቃ አንድም ሰው የለም:: ሊቁ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከማር በጣፈጠ ዜና ሕይወቱ እንደ ተጻፈው:- በልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምሯል:: ሥጋውያን ጠቢባንን ያሳፍር ዘንድም የግሪክን ፍልሥፍና በልኩ ተምሯል:: በታላቅ ወንድሙ ቅዱስ ባስልዮስ መሪነት ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በመንኖ ጥሪት ተመስግኗል:: ተገብቶትም በኑሲስ ደሴት ላይ ዻዻስ ሆኗል:: እርሱ ሲሔድ በከተማው የነበሩ ክርስቲያኖች 11 ብቻ የነበሩ ሲሆን እርሱ ሲያርፍ ክርስቶስን የማያመልኩ ሰዎች ቁጥር 11 ብቻ ነበር:: ቅዱስ ጐርጐርዮስ ፍጹም ሊቅ ነበርና ከቁጥር የበዙ ድርሳናትን ደርሷል:: ታላቁን ጉባኤ ቁስጥንጥንያን (በ381 ዓ/ም) መርቷል:: ብዙ መናፍቃንንም አሳፍሯል:: ከንጽሕናው የተነሳ መላእክት ያቅፉት: እመ ብርሃንም ትገለጥለት ነበር:: ለ33 ዓመታት እንደ ሐዋርያት ኑሮ በዚህ ቀን ድንግል ጠራችው:: ቀድሶ አቁርቦ: ሕዝቡን አሰናብቶ: የቤተ መቅደሱን ምሰሶ እንደ ተደገፈ ዐርፎ ተገኝቷል:: በዝማሬና በፍቅር ቀብረውታል::
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
❖ የድንግል ማርያም ወዳጆች ✞ እንኳን አደረሳችሁ ☞ አስተርዮ _ ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ፦ መታየት ወይም መገለጥ ማለት ነው፡፡ 👉 ጥር 21 ቀን ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይቶ በደመና ተነጥቃ ወደ ገነት በመግባት በሰማይና በምድር የተሰጣትን ፀጋና ክብር የገለፀችበት እለት ስለሆነ በዓሉም አስተርዮ ማሪያም ይባላል። ❖ የድንግል ማሪያም ጥበቃ ምልጃዋ አይለያቹ👏👏👏
إظهار الكل...
የመከላከያ ሚንስቴሩ አብርሃም በላይ እንዲህ ተብሎ ተጠይቋል "እናንተ እዚህ አራት ኪሎ ተቀምጣችሁ፤ ሌላው ቦሌ ሆኖ መንግሥት መስርቻለሁ ቢል ዝም ብላችሁ ትቀበላላችሁ፣ በሽምግልና እንፍታው ትላላችሁ?” አብርሃም የሚልሰው አጥቶ በመጣበት ተመልሷል። በጣም አስገራሚ ነገር እኮ ነው። አባቶች እንዳሉት እነሱ አራት ኪሎ ተቀምጠው ሌላው ቦሌ ላይ ሆኖ መንግሥት መስርቻለሁ ቢል በዝምታ ያዩታል? በሽምግልና ይፈቱታል? የሆነ ወቅት ዶክተር አብይ አሕመድ "ሥልጣን መያዝ የሚቻለው በኃይል ሳይሆን በምርጫና በምርጫ ብቻ ነው" ብሎ ሲደሰኩር ሰምተነዋል። አቡነ አብርሃም ያሉት ይሄንኑ ነው፣ “ይሄ ጉዳይ የሃይማኖት፣ የቀኖና፣ የሥርዓተ ቤተክርስቲያን እና የህግ የበላይነት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ በእርቅ የሚፈታ አይደለም፡፡” ብለው ቁርጡን ነግረውታል። ዳግም በዚህ መልኩ መምጣት እንደሌለባቸው ተነግሯቸው በመጡበት ተመልሰዋል።
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.