cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ኦርቶዶክሳዊነት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

እዚህ Channel ላይ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት ፣መዝሙር ፣ኬነጥበቦች እና መፅሕፍት ይለቀቁበታል "ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
2 148
المشتركون
-2024 ساعات
+1857 أيام
+1 00530 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

[ ስንክሳር ሐምሌ - ፲ - ] .mp34.75 MB
🕊 [ †  እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።  † ] † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † 🕊   †  ቅዱስ ናትናኤል  †   🕊 † በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ከቅዱሳን ሐዋርያት መካከል ዘግይቶ ሰማዕትነትን የተቀበለ ይህ ቅዱስ ሐዋርያ ነው:: ቅዱሱ ሐዋርያ የተወለደው ከእሥራኤላውያን ወላጆቹ ጌታችን በተወለደበት ዘመን አካባቢ ነው:: ይህ በምን ይታወቃል ቢሉ እርሱ ሕፃን እያለ ሔሮድስ 144,000 ሕፃናትን ሲፈጅ እርሱ ግን በእግዚአብሔር ጥበብ ተርፏል:: እናቱ በቅርጫት ውስጥ አድርጋ የበለስ ዛፍ ላይ አስቀምጣው ተደብቃ ታጠባው ነበር:: ለሐዋርያው ወላጆቹ ያወጡለት ስም ስምዖን ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ናትናኤል ብሎታል:: በባልንጀሮቹ ሐዋርያት ደግሞ የቃናው ስምዖን [ገሊላ ቃና አካባቢ ስላደገ] አንዳንዴም ቀናተኛው ስምዖን ይሉት ነበር:: ምሑረ ኦሪት ነበርና ዘወትር ለሕግ ይቀና ነበር:: በገሊላ ቃና ሰርግ የደገሰው ዶኪማስ የቅዱስ ናትናኤል የአጎት ልጅ ነው:: ጌታና ደቀ መዛሙርቱን ዶኪማስ የጠራበት አንዱ ምክንያትም ይሔው ነው:: ቅዱስ ናትናኤል ኦሪትን ከገማልያል ተምሮ: ከበለስ ቁጭ ብሎ ይተክዝ ነበር:: "መሲሕ ምነው ቀረህ?" እያለም ይተክዝ ነበር:: ማዕምረ ኅቡዓት አምላካችን ክርስቶስ ይህንን አውቆ በፊልጶስ አማካኝነት ጠርቶታል:: ናትናኤል ለጊዜው ተከራክሮ ነበር:: በኋላ ግን የጌታችንን ማንነት በደቂቃዎች ተረድቶ አምኗል:: ጌታችንም "ክዳት ሽንገላ በልቡ ውስጥ የሌለበት ንጹሕ እሥራኤላዊ" ሲል አመስግኖታል:: ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል ከጌታችን እግር ሥር ምሥጢረ መንግስተ ሰማያትን ተምሮ: በጸጋ መንፈስ ቅዱስም ሰክሮ: ብዙ አሕዛብን ከጨለማ [ጣኦት አምልኮ] ወደ ብርሃን [አሚነ ክርስቶስ] መልሷል:: እጅግ ብዙ መከራንም ተቀብሏል:: የጌታችን ወንድም የተባለ ቅዱስ ያዕቆብ በአይሁድ ከተገደለ በኋላም ቅዱስ ናትናኤል የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አገልግሏል:: ከአይሁድም ዘንድ ብዙ መከራ ደርሶበታል:: በመጨረሻም በዚህች ዕለት በሰማዕትነት አልፏል:: በገድለ ሐዋርያት ላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሱ ሰማዕት የሆነው በመቶ ሃምሳ ዓመቱ ነው:: ያ ማለት ደግሞ ከሐዋርያት አባቶች በመጨረሻ ያረፈው እርሱ ነው ያሰኛል:: 🕊   †   አባ ብስንዳ   †     🕊 † ዳግመኛ በዚህ ቀን ታላቁ አባ ብስንዳ ይታሠባል:: አባ ብስንዳ በዘመነ ጻድቃን ምድረ ግብጽ ውስጥ ከነበሩ ታላላቅ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱን ከገድሉ ጽናት የተነሳ መላእክት በእጅጉ ይወዱት ነበር:: "እኔ ልሸከምህ - እኔ ልሸከምህ" እያሉ ይሻሙበት: በተራ በተራም ተሸክመውት ይውሉ ነበር:: እርሱም ለበርካታ ዓመታት ውኃ የሞላበት ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ይጸልይ ነበር:: እንደ እሳት በሚባላው በረዶ ውስጥ ገብቶ መጸለዩ የፈጣሪውን ሕማማት ለመሳተፍ እና ለኃጥአን ምሕረትን ይለምን ዘንድ ነው:: ሁሌም በዘጠኝ ሰዓት መላእክት ተሠብስበው ይመጡና በብርሃን ሠረገላ ይሸከሙታል:: ከመሬትም ዘጠኝ ክንድ ከፍ ያደርጉት ነበር:: ከብዙ ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ፈጣሪው ሒዷል:: † እግዚአብሔር በቅዱስ ናትናኤል ምልጃ ሃገራችንን ከጥፋት: ሕዝቦቿንም ከመቅሰፍት ይሰውርልን:: ከሐዋርያው እና ከጻድቁ አባ ብስንዳ በረከትም አይለየን:: 🕊 [  †  ሐምሌ ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ [ቀናተኛው ስምዖን] ፪. ታላቁ አባ ብስንዳ ጻድቅ ፫. አባ ከላድያኖስ ሊቀ ጳጳሳት [   †  ወርኀዊ በዓላት   ] ፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ ፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ ፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ] ፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት ፮. ቅዱስ ዕፀ መስቀል † " ጌታ ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ 'ተንኰል የሌለበት በእውነት የእሥራኤል ሰው እነሆ' አለ:: ናትናኤልም 'ከወዴት ታውቀኛለህ?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም መልሶ 'ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ' አለው:: ናትናኤልም መልሶ 'መምሕር ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ:: አንተ የእሥራኤል ንጉሥ ነህ' አለው::" † [ዮሐ. ፩፥፵፰-፶፩] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
01:41
Video unavailableShow in Telegram
                       †                         - የካህን ሀገሩ የት ነው  ? !       የካህን ርስቱ ምንድን ነው ? !    የካህን ወገኑ ማን ነው  ? !       🕊                        💖                     🕊
إظهار الكل...
6.51 MB
[ + ሸክማችሁ የከበደ + ] .mp36.51 MB
Photo unavailableShow in Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  ❝ ሸ ክ ማ ች ሁ   የ ከ በ ደ ! ❞ [ 💖 [ " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ " ] 💖 ]  [                        🕊                        ] --------------------------------------------------- " እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ፥ ወደ እኔ ኑ ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" [ ማቴ . ፲፩ ፥ ፰ ] 🕊                       💖                   🕊
إظهار الكل...
                         †                           [      🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊      ] [ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  ተርእዮን [ መታየትን ] አለመውደድና ለታይታ ብሎ ምንም ነገር አለማድረግ !  ] 🕊 "  በእንዲህ ያለ ያረጀ ልብስ .... !  " ........ አባ ዮሴፍ እንዲህ አለ ፦ " በደብረ ሲና ሳለሁ አርአያው ደስ የሚል በመልካም ተጋድሎ የሚኖር አንድ ወንድም ነበር። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ ያለቀና እሳት የበላው የማቅ ዕራፊ እንደለበሰ ነበር። ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ሲገባ አየሁትና አንድ ቀን ፦ ' ወንድሜ ሆይ ፣ ወንድሞች በጸሎት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ሲቆሙ በአምሳለ መላእክት ሆነው አታያቸውምን ? አንተ እንዴት በእንዲህ ያለ ያረጀ ልብስ በመካከላቸው ትሆናለህ ? እባክህ ልብስህን ለውጥ ' አልኩት። እርሱም ፦ " አባ ፣ ይቅርታ አድርግልኝ ፣ ሌላ ልብስ ስለሌለኝ ነው። " አለኝ። ያን ጊዜም ወደ ማደሪያዬ ወሰድኩትና ልብስና ሌላም የሚያስፈልገውን ሁሉ ሰጠሁት። ከዚያ በኋላ ሌሎቹ መነኰሳት እንደ ለበሱት ለበሰ። ከዚህ ጊዜ በኋላ ከአኃው መካከል ለገዳሙ ጉዳይ ወደ ንጉሡ የሚላኩ አባቶችን በፈለጉ ጊዜ አብሯቸው ይሄድ ዘንድ ይህን ወንድም መረጡት። እርሱ ግን ይህን ነገር ባወቀ ጊዜ አባቶችን ፦ " ስለ እግዚአብሔር ስትሉ እባካችሁ ይቅርታ አድርጉልኝ ፣ እና ከዚያ አገር ታላላቆች ሰዎች መካከል የአንዱ ባሪያ ነበርኩ ፣ ምናልባት ሲያየኝ እንዳያውቀኝና እንዳይጣላኝ ፣ ወደ ባርነትም እንዳንመልሰኝ እፈራለሁና ተዉኝ " ብሎ ለመናቸው። አበውም እንዲህ ባላቸው ጊዜ ተውት። ከዚያ በኋላ ቀድሞ የሚያውቀው ሰው ወደ ገዳሙ መጣ ፤ እንዲህም አላቸው ፦ " ይህ ሰው ከንጉሥ መኳንንት አንዱ ነበር ፤ ክብሩም ታላቅ ነበር ፤ ነገር ግን የነበረውን ሁሉ ትቶ ወደዚህ ቦታ መጣ። ባሪያ ነበርኩ ያለውም እንዳያውቁትና ነገሩ በቁስጥንጥንያና በአገሩ እንዳይታወቅበት ነው። " የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
إظهار الكل...
                          †                           [    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ] [        ክፍል  አሥራ አምስት         ] 💛 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ [ ወደ አስቄጥስ መመለሱና ከዲያብሎስ ጋር ተጋድሎ መጀመሩ ! ]                          🕊                          ❝ ቅዱስ መቃርዮስም ከራስ ቅሉ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ቦታው ተመልሶ ለእግዚአብሔር እየተገዛ በእርሱ ብቻ በመታመን መኖር ቀጠለ ፤ ኪሩባዊውም ዘወትር ይጎበኘው ነበር፡፡ አንድ ቀን ማታ ጊዜ ላይ ቅዱስ መቃርዮስ ውኃ ይቀዳ ዘንድ ወደ ምንጩ ሲሄድ በመንገድ ላይ ቃለ እግዚአብሔርን በልቡ እየመላለሰ በንባብ ልብ ሳለ ፦ "መቃራ ፣ መቃራ ሆይ ! " የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ይህን በሰማ ጊዜ ቆሞ ወደ ቀኝና ግራ ቢመለከት ምንም ነገር አላገኘም ፣ ነገር ግን ያንኑ ቃል ደጋግሞ በሰማ ጊዜ በመሬት ላይ ቁጭ አለ፡፡ እንዲህ የሚል ቃል ሰማ ፦ "ቃሌንና ትእዛዜን ሰምተህ ወደዚህ ቦታ መጥተህ ስለኖርክ ከወገን ሁሉ እጅግ ብዙ የሆነ ጉባኤን በዚህ እሰበስባለሁ፡፡ እነርሱም ያገለግሉኛል ፣ በመልካም ምግባራቸውና በተወደደ ቃላቸውም እመሰገናለሁ ፣ ስሜንም ይቀድሳሉ፡፡ ወደ አንተም ይመጡ ዘንድ ከሚወዱ መካከል ማንንም እንዳትከለክል ተጠንቀቅ" አለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ይህን በሰማ ጊዜ ልቡ ጸና ፣ ተበረታታ፡፡ ከዚያም ውኃውን ቀድቶ ወደ በአቱ ሲመለስ ፀሐይ ገባ ፤ ጸሎቱን ጸልዮ ኅብስቱን ቀምሶ ተኛ፡፡ እንደ ልማዱም ለጸሎት በተነሳ ጊዜ እግዚአብሔር ጆሮውን ከፈተለትና ሰይጣናት እርስ በእርሳቸው እንዲህ ሲባባሉ ሰማቸው ፦ "ይህን በረሃ በዓለም ውስጥ በእኛ የሚሰቃዩ ሰዎችና ዘላለማዊ ሕይወትን ተስፋ የሚያደርጉ ብዙዎች ተሰባስበው መጠጊያና መጽናኛ ወደብ በማድረግ ሀገራቸው ካደረጉት እኛ ይህን በረሃ ጥለን እንሰደዳለን፡፡ በዚህም ለእኛ ኃይልና ሥልጣን አይኖረንምና ከእነርሱ ከጸሎታቸው የተነሣ በታላቅ ድብደባ እየተደበደብን እንሰደዳለን፡፡ ታዲያ ይህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው ልንተወው ይገባልን? ስለዚህ አሁን ኑና ሁላችንም በአንድነት ተሰባስበን በተለያየ መንገድ በመገለጥ ከዚህ ቦታ እናሳድደው ዘንድ እንችል እንደሆነ እናስፈራራው" ሲባባሉ ሰማቸው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስ ይህን በሰማ ጊዜ በሰይጣናት ላይ ልቡ ተበረታታ ፣ በልቡም ቸርነቱን ያደረገለትና የሰይጣናትን ነገር ይሰማና ድካማቸውን ያውቅ ዘንድ ጆሮውን የከፈተለትን እግዚአብሔርን እየመሰገነ ለጸሎት ተነሣ፡፡ ❞ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡ ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.