cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ዳዕዋ ሠለፍያ በጊምባ ከተማ

አላማችን ለጊምባ ከተማ እና አካባቢዋ ህዝብ ዳዕዋ ሰለፍያን ማስፋፋት ነው ታማኝና እንቁ የሆኑ ዱአቶች እንድሁም ቂራአቶች እንለቃለን ቢኢዝኒላሂ ሱበሀነሁ ወተዓላ!!! ስህተትና ኸጦዕ ካለ በመረጃ መታረምን እንወዳለን

إظهار المزيد
لم يتم تحديد البلدلم يتم تحديد اللغةالفئة غير محددة
مشاركات الإعلانات
189
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله في شرح لشرح السنة للبر بهاري ✏️✏️✏️✏️✏️✏️ فعليك أيها المسلم وطالب العلم بالذات أنتتثبت ولا تستعجل مع كل ما تسمع عليك بتثبت ومعرفة من الذ ي قال؟ ومن أين حاء هاذ الفكر؟ ثم ما مستنداته وأدلته من الكتاب والسنة؟ ثم أين تعلم صاحبه ؟ وعمن أخذ العلم ؟ فهذه أمور تحتاج إلى تثبت. خصوص في هذا الزمان. أخو كم حسين ابن حسن
إظهار الكل...
➲አምስት ታላላቅ የሸይኽ ፈውዛን አደራዎች! ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ①🌱‏قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله : ✅ አንደኛው አደራ ✅ 〰〰〰〰〰〰〰 ◾️الذي نوصي به أنفسنا وإخواننا :تقوى الله والتمسك بمنهج السلف الصالح ↪️ እኛንም ሆነ ወንድሞቻችን አደራ የምንለው፦ 🔻አላህን በመፍራትና የሰለፎችን መንሀጅ አጥብቆ በመያዝ ላይ ነው። 📚 [( الأجوبة المفيدة (س112)] ②🌱‏قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله ✅ ሁለተኛው አደራ ✅ 〰〰〰〰〰〰〰 ◾️الذي نوصي به أنفسنا وإخواننا: الحذر من البدع والمبتدعين ↪️ እኛንም ሆነ ወንድሞቻችን አደራ የምንለው፦ 🔻ቢድአና የቢድአ ባለቤቶችን በመጠንቀቅ ላይ ነው። 📚[( الأجوبة المفيدة (س112)] ③🌱قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله : ✅ ሶስተኛው አደራ ✅ 〰〰〰〰〰〰〰 ◾️الذي نوصي به أنفسنا وإخواننا: العناية بدراسة العقيدة الصحيحة وما يضادها ↪️ እኛንም ሆነ ወንድሞቻችን አደራ የምንለው፦ 🔻ትክክለኛውን አቂዳና የሷ ተቃራኒ የሆነውን አቂዳ በመማር ላይ ትኩረት በመስጠት ላይ ነው። 📚 [( الأجوبة المفيدة (س112)] ④🌱قال العلامة صالح الفوزان حفظه الله : ✅ አራተኛው አደራ ✅ 〰〰〰〰〰〰〰 ◾️الذي نوصي به أنفسنا وإخواننا: الأخذ عن العلماء الموثوقين في علمهم وفي عقيدتهم ↪️ እኛንም ሆነ ወንድሞቻችን አደራ የምንለው፦ 🔻ዲናቸውን በእውቀትና በአቂዳቸው ታማኝ ከሆኑ ከሱና ኡለማዎች ዘንድ ብቻ እንዲወስዱ ነው። 📚[( الأجوبة المفيدة (س112)] ⑤🌱قال ‏العلامة صالح الفوزان حفظه الله : ✅ አምስተኛው አደራ ✅ 〰〰〰〰〰〰〰〰 ◾️الذي نوصي به أنفسنا وإخواننا :الحذر من دعاة السوء الذين يلبسون الحق بالباطل ↪️ እኛንም ሆነ ወንድሞቻችን አደራ የምንለው፦ 🔻ሀቅና ባጢልን ግልፅ ከማያደርጉና ከሚያለባብሱ የጥመት ተጣሪዎችን እንዲጠነቀቁ ነው። 📚[( الأجوبـة المفيـدة (س112)] ️ــــــ ✵✵ ــــــ ✵✵ــــــ ــــــ ✵✵ــــــ ــــــ ✵✵ــــــ እነዚህ አደራዎች ሲዘረዘሩ 〰〰〰〰〰〰〰〰 ①) አላህን መፍራት እንዳለብን ②) የሰለፎች መንገድ አጥብቀን መያዝ እንዳለብን ③) ቢድአን መጠንቀቅ እንዳለብን ④) የቢድአ ባለቤቶችን መራቅ እንዳለብን ⑤) ትክክለኛውን አቂዳና ተውሂድ መማር እንዳለብን ⑥) የተበላሸውን አቂዳና ሽርክ አውቀን መጠንቀቅ እንዳለብን ⑦) እውቀት ከሱና ባለቤቶች ብቻ መቅሰም እንዳለብን ⑧) ከቢድአ ባለቤቶች እውቀት ከመውሰድ መጠንቀቅ እንዳለብን ⑨) ሀቅና ባጢል ከሚያለባብሱ ዱአቶች መጠንቀቅ እንዳለብን የሚያመላክቱ ናቸው።
إظهار الكل...
"የኛዎቹ"ም ቢሞክሩት ~ ዛምቢያዊው ፓስተር ጀምስ ሳካራ "እንደ እየሱስ በሶስተኛው ቀን መቃብር ፈንቅዬ እነሳለሁና ከነህይወቴ ቅበሩኝ" በማለት ተከታዮቹን ባዘዘው መሰረት ከነ ነፍሱ ይቀብሩታል፡፡ (በኢስላም ዒሳ እንዳልሞቱም፣ እንዳልተቀበሩም ያዙልኝ።) ከሶስት ቀን በኋላ ቢመለሱ መቃብር ቆፍሮ አልወጣም። ሲቆፍሩ ጊዜ ሞቶ አገኙት። አሁን የዛምቢያ ፖሊስ ይህን ድርጊት የፈፀሙትን ማምሻውን ሰብስቦ ዘብጥያ ማውረዱ እየተዘገበ ነው፡፡ አጠፉ እንዴ ጎበዝ? . እዚህ ላይ አንዲት እናት ከአመታት በፊት ደሴ ከተማ ውስጥ ስታወራ የሰማኋት ነገር ትዝ አለኝ። አንዷ ቅጥ ያጣ የሴቶች መብት ስብከት ሰለባ የሆነች ሴት አንዱን ገበሬ ከፍ ዝቅ አድርጋ ህዝብ ፊት ታከላፍተዋለች። "ኧረ እረፊ" ብሎ ቢያስጠነቅቅ "እስኪ ጫፌን ንካኝ። ዛሬ እንደ ድሮው መስሎሃል!" እያለች ተንጣጣችበት። ያላሰበውን አሳሰበችው። አሁንም ቢያስጠነቅቅ በጣቷ ወደ ግንባሯ እየጠቆመች "እስኪ ይቺን ንካኝ" አለችው። ድንገት እራሱን መቆጣጠር አቃተውና በያዘው ዱላ የጠቆመችው ቦታ ላይ በዱላ መታት። "እሪሪይ!" ብላ መጮህ። "እየባሰ ሄደ! ምን አጠፋሁ ጎበዝ? 'እዚህ ላይ' አለችኝ እዚያው ላይ መታሁ። ቦታ ሳትኩንዴ?" አለ ሰውየው። ፖሊስ መጥቶ "ምራ!" ሲለው እንደለመደው፡ "እየባሰ ሄደ!" ይላል። ፖሊሶች፡ "ጭራሽ ሊስፈራራን ነው 'እየባሰ ሄደ!' የሚለው" ብለው ይጮሃሉ። ተሰብሳቢው ሰው "ኧረ ሲያወራ ልምድ ሆኖበት እንጂ ለናንተ ብሎ አይደለም" ይላሉ። ፖሊሶች እያዋከቡ ወደ እስር ቤት ወሰዱት። . እና እነዚህ በፖሊስ የታሰሩ ዛምቢያውያን ጉዳይ ገርሞኝ ነው። የዚህን ጣጠኛ አጭቤ ነቢይ ትእዛዝ ፈፅመው ተአምር ሲጠብቁ ካቴና አጠለቁ። ጉድና ጅራት በስተኋላ ነው። = Copy
إظهار الكل...
Hey, let's switch to Telegram+ Messenger: http://telegram.en.uptodown.com/android
إظهار الكل...
Telegram (Android)

A fast and -most importantly- secure messaging system

ጥቂት ነጥቦች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ~ 1. ወገኔ ሆይ! አገርህን አትልቀቅ። ባለፈው ተፈናቃዮች ላይ የደረሰውን አስታውስ። ደብረ ብርሃንና ባህርዳር ለተፈናቃዮች ከማጎሪያ ካምፕ የማይለዩ እንደነበሩ ሲወራ ነበር። አሁን ደግሞ ነገሮች ከቀድሞው ቢብሱ እንጂ የተሻሉ አይደሉም። ፖለቲከኛውን ተወው። ህዝብ እራሱ ኑሮ ስለከበደው ሊጨካከን፣ ሊሰላች ይችላል። ሩቅ አትሂድ። ደሴ ወልዲያን፣ ወልዲያ ቆቦን ሊሰለች ይችላል። የጎደለበት ደግሞ በትንሽ በትልቁ ይከፋዋል። ስለዚህ በተለየ እፈለጋለሁ ብሎ የሚሰጋ ካልሆነ በስተቀር ጦርነቱ ቀጥታ ከሚካሄድባቸው ቀጠናዎች ለጊዜው ዞር ከማለት ውጭ ካገር ርቆ መሄድ ስቃዩን የከፋ ያደርገዋል። 2. ወገኔ ሆይ! ንብረትህን ጠብቅ። ሩቅ ብቻ አትመልከት። እዚያው በዙሪያህ ለዘረፋ ተደራጅተው ከግለሰብ ንብረት እስከ ተቋም ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ዛሬም ይኖራሉ። ፍሪጅና ቴሌቪዥን ሳይቀር በግመል እየጫኑ የወሰዱ የገጠር ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። “መብራት የላችሁ ምን ያደርግላችኋል?” ሲባሉ “እንሸጠዋለን” ሲሉ ነበር። ስለዚህ ቅድሚያ ለህይወት ጥንቃቄ ካደረግክ በኋላ በቅርብህ ሆነህ በተቻለህ መጠን ንብረትህን ተደራጅተህ ጠብቅ። 3. ወገኔ ሆይ! ለፈተና እራስህን አዘጋጅ! ወደድንም ጠላንም ፈተና ላይ ነው ያለነው። መጠኑ ከህዝብ ህዝብ በእጅጉ እንደሚለያይ ግልፅ ነው። ፈተናው ምን ያህል እንደሚዘልቅም አናውቅም። የሆነች ያክል የምንዘጋጅባት ሰበብ ካለችን ባለችን መጠን ለሚመጣው ሁሉ ራሳችንን እናዘጋጅ። ምግቡ፣ ወፍጮው፣ ባንኩ፣ መብራቱ፣ ቴሌው፣ መድሃኒቱ፣ ... ብዙ ነገር ይቸግራል። እስካሁንም ብዙ የተፈተነ አለ። ልዩነቱ ብዙ ባይሆን እንኳ የተዘጋጁበትና የተዘናጉበት ፈተና አንድ አይደለም። አላህ ለሁሉም ፈረጃውን ያቅርብልን። 4. ወገኔ ሆይ! ጊዜ አይተህ አትለወጥ! ለሚያልፍ ቀን ትዝብት ላይ አትውደቅ። የትኛውም ቡድን አጠቃኝ በሚል ማመሃኛ ማንንም ብሄር ለይተህ እንዳታጠቃ። የአማራ ህዝብ ሆይ! ህወሓትን መነሻ አድርገህ ለፍቶ አዳሪ ትግሬን አታጥቃ። “ያው ናቸው” ከሚል ስሜት ወለድ ሂሳብ ራቅ። “ህወኃት እከሌን አካባቢ የተቆጣጠረው ተፈናቃይ ትግሬዎችን ተጠቅሞ ነው” እየተባለ የሚናፈሰው ብታምንም ባታምንም ከንቱ ውሸት ነው። እንዲህ አይነት አሉባልታ ይዘህ ደካሞችን እንዳትጎዳ። ትግሬው ሆይ! ህወኃት ሲገባ ጠብቀህ አደባባይ ለጭፈራ አትውጣ። ጠቋሚ፣ አፋኝ፣ አሳፋኝ ለመሆን አትሞክር። ሃይማኖት ወይም ሞራል እንኳ ባይገታህ ቢያንስ ለራስህ ፍራ! ነገሮች የተቀያየሩ እለት መግቢያ ታጣለህ። በባለፈው ግጭት አማራውም፣ ትግሬውም፣ ኦሮሞውም፣ አፋሩም ዘንድ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲወሩ ነበርና አላህን ልንፈራ ይገባል። 5. ወገኔ ሆይ! ለመጣ ለሄደው አታጨብጭብ። አንድ ኃይል አንድን አካባቢ ሲቆጣጠር ሆ ብሎ መውጣት፤ ሌላው በግሩ ሲተካ አሁንም ሆ ብሎ መነሳት ይሄ ግልብነት ነው። የሃገራችን ፖለቲካ ቂመኛና ተበቃይ ነው። እንኳን የገባበትን፣ የሌለበትንም ጊዜ ተጠግቶ ያጠቃል። ደግሞም በጣም ተገለባባጭ ነው። እዚች አገር ውስጥ ስንት አይሆንም የተባለ ነገር ሆኗል! መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ህወኃት ዳግም ያንሰራራል ብሎ የገመተ አልነበረም። ህወኃት ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ ይመለሳል ብሎ የገመተም አልነበረም። ስለሆነም ጥንቁቅ መሆን ያስፈልጋል። በሁለቱም አይንህ ዛሬ ላይ ብቻ አታፍጥጥ። በአንድ አይንህ ነገን ተመልከት። 6. ወገኔ ሆይ! ህይወት አትርፍ። አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የሚጠሉትን ለማጥቃት የማያመነቱ እርኩስ ፍጡሮች ይኖራሉና ቢቻልህ ያለ ጥፋታቸው የበደለኞች ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ወገኖችን አትርፍ። ከጎናቸው ቁም። በባለፈው ግጭት ህወኃት ሲገባ ጠብቀው ደካሞችን ያጠቁ ሰዎች አሉ። ከነሱ አንፃር ሲታይ ህወኃት በጣም የተሻለ ነበር። መረጃ ያለው ሰው የምለው ይገባዋል። ህወኃት ከወጣ በኋላም እንዲሁ ከየትኛውም ኃይል ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ምስኪኖች ተጎድተዋል። ከተቻለን ጊዜ አይተው ከሚያጠቁ ነውረኞች አንድ ነፍስ እንኳ ብናተርፍ ዋጋው የትና የት ነው!! በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ በነበረውን ግጭት የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ኦሮሞዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። አማራ ውስጥ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ትግሬዎችን ያተረፉ ስንት አማራዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ትግሬዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት! 7. ወገኔ ሆይ! ወቅታዊ ግጭቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሃይማኖት ጋር እንዳታጠላልፍ። የየትኛውም ቡድን ደጋፊ ልትሆን ትችላለህ። የኔ የምትለው ወገን ከሌሎች በተለየ እንደተገፋ ሊሰማህ ይችላል። ግን እወቅ! ሌሎችም መሰል ህመም አላቸው። ቢቻል በፖለቲካውም ሞራል ግብረ ገብነት ቢኖርህ እሰየው። ያለበለዚያ ግን የሃይማኖት ተቋማትም፣ አስተማሪዎች እና የደዕዋ መድረኮችም አንተ በምትፈልገው መልክና መጠን እንዲያወሩ፣ የፖለቲካ ፍጭቶች ማራገፊያ እንዲሆኑ አትፈልግ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ሆነ መሬት ላይ እየተከተልክ በአክቲቪስት ቋንቋ እንዲያወሩ አጉል አትወትውት። ልትረዳ ቢያቅትህ ቢያንስ አደብ ይኑርህ። ከፖለቲከኛ ጋር የለመድከውን እሰጥ አገባ በየደረስክበት አትድፋ። 8. የሃይማኖት አስተማሪ ሆይ! ከመንጋው ተለይ! ብሄርህን ተከትለህ ቅስቀሳ ውስጥ አትግባ። ሌላው አካል ለጦር ቢቀሰቅስ አንድ ሁለት ነገር ተመልክቶ ነው። አንተ ተጨማሪ አርቀህ የምትመለከትበት አላህን መፍራቱ ሊኖርህ ይገባል። ያለበለዚያ በምንህ ነው ከሌሎች የምትለየው? ኢን ሻአላህ ነገ ሰላም ይመጣል። እሱን ታሳቢ አድርግ። መንጋው ሊያግባባህ፣ ሊገፋፋህ፣ አልሆን ሲለው ሊያወግዝህ ይችላል። የፈለገውን ይበል እሱ በቀደደው አትፍሰስ። የሃይማኖት አስተማሪ ሆነው በቀጥታ የግጭት ተሳታፊ፣ ወይም ቀስቃሽ፣ ወይም ደጋፊ፣ ወይም የዘር ጥላቻ ጠማቂ የሆኑ መርዘኛ ሰባኪዎች ሁሉም ብሄር ጋር አሉ። እነዚህ አካላት ነገ ችግሩ ቢያልፍ እንኳ የማያልፍ ጠባሳ እየጣሉ ነው። ጦሳቸውም ከራሳቸው አልፎ ለህዝብ ይተርፋል። ከሃይማኖትህ ተማር። እስካሁን ካለፈው ተማር። ከሌሎች ድክመት ተማር። የትኛውንም ውሳኔ ብትመርጥ ከትችት ላታመልጥ ነገር የሰው ስሜት ተከትለህ እንዳትወስን። አላህን አስብ። በመጨረሻም አደራ የምለው እንተዛዘን፣ እንተሳሰብ፣ ዱዓእ እናድርግ፣ ወደ ጌታችን እንመለስ። አላህ ከገባንበት መከራ አውጥቶ የሰላም አየር የምንተነፍስ ያድርገን። ኣሚን። = Copy
إظهار الكل...
إياكم واييانا بلإم الشرعي ولحرص عليه . إنه ينجح صاحبوه فدنيا ولأخرة.كما قال الله يرفع الله الذين أمنو منكم ولذين أتو الإم درخجات
إظهار الكل...
# ሰባት አይነት ሰዎች! ረሱል ( ﷺ ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ ﺳَﺒْﻌَﺔٌ ﻳُﻈِﻞُﻢُﻫُّ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻓﻲ ﻇِﻠِّﻪِ، ﻳَﻮﻡَ ﻻ ﻇِﻞَّ ﺇﻟّﺎ ﻇِﻠُّﻪُ: ﺍﻹﻣﺎﻡُ ﺍﻟﻌﺎﺩِﻝُ، ﻭﺷﺎﺏٌّ ﻧَﺸَﺄَ ﻓﻲ ﻋِﺒﺎﺩِﺓَ ﺭَﺑِّﻪِ، ﻭﺭَﺟُﻞٌ ﻗَﻠْﺒُﻪُ ﻣُﻌَﻠَّﻖٌ ﻓﻲ ﺍﻝﻣَﺴﺎﺟِﺪِ، ﻭﺭَﺟُﻼﻥِ ﺗَﺤﺎﺑّﺎ ﻓﻲ ﺍﻟﻞِّﻩَ ﺍﺟْﺘَﻤﻌﺎ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺗَﻔَﺮَّﻗﺎ ﻋﻠﻴﻪ، ﻭﺭَﺟُﻞٌ ﻃَﻠَﺒَﺘْﻪُ ﺍﻣْﺮَﺃَﺓٌ ﺫﺍﺕُ ﻣَﻨْﺼِﺐٍ ﻭﺟَﻤﺎﻝٍ، ﻓَﻘﺎﻝَ: ﺇﻧِّﻲ ﺃﺧﺎﻑُ ﺍﻟﻠَّﻪَ، ﻭﺭَﺟُﻞٌ ﺗَﺼَﺪَّﻕَ، ﺃﺧْﻔﻰ ﺣﺘّﻰ ﻻ ﺗَﻌْﻠَﻢَ ﺷِﻤﺎﻟُﻪُ ﻣﺎ ﺗُﻨْﻔِﻖُ ﻳَﻤِﻴﻨُﻪُ، ﻭﺭَﺟُﻞٌ ﺫَﻛَﺮَ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﺧﺎﻟِﻴًﺎ ﻓَﻔﺎﺿَﺖْ ﻋَﻴْﻨﺎﻩُ . ﴾ “ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት በቂያማ ቀን በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። እነሱም፦ ፍትሃዊ መሪ፣ አላህን በማምለክ ላይ ያደገ ወጣት፣ ልቡ ከመስጂዶች ጋር የተንጠለጠለን ሰው፣ ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ፣ የልቅናና የቁንጅና ባለቤት የሆነች ሴት (ለዝሙት) ጠርታው ‘እኔ አላህን እፈራለሁ’ ያለ ሰው፣ ምፅዋትን ‘ሰደቃ’ የሚሰጥ ሆኖ ቀኝ እጁ የሚመፀውተውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ የሚደብቅ ሰው፣ አላህን በማስታወስ አይኑ የሚያነባ ሰው ናቸው።” ቡኻሪ (1423) ሙስሊም (1031) ዘግበውታል https://t.me/daewaselefyagimba
إظهار الكل...
ዳዕዋ ሠለፍያ በጊምባ ከተማ

አላማችን ለጊምባ ከተማ እና አካባቢዋ ህዝብ ዳዕዋ ሰለፍያን ማስፋፋት ነው ታማኝና እንቁ የሆኑ ዱአቶች እንድሁም ቂራአቶች እንለቃለን ቢኢዝኒላሂ ሱበሀነሁ ወተዓላ!!! ስህተትና ኸጦዕ ካለ በመረጃ መታረምን እንወዳለን

# በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ… ረሱል ( ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ ﺇﻥَّ ﻣِﻦ ﺃﻓﻀَﻞ ِﺃﻳّﺎﻣِﻜﻢ ﻳﻮﻡَ ﺍﻟﺠُﻤﻌﺔِ، ﻓﺄﻛْﺜِﺮﻭﺍ ﻋﻠﻲَّ ﺍﻟﺼﻼﺓَ ﻓﻴﻪ؛ ﻓﺈﻥَّ ﺻﻼﺗَﻜﻢ ﻣَﻌﺮﻭﺿﺔٌ ﻋﻠﻲَّ . ﴾ “ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።” አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1531 https://t.me/daewaselefyagimba
إظهار الكل...
ዳዕዋ ሠለፍያ በጊምባ ከተማ

አላማችን ለጊምባ ከተማ እና አካባቢዋ ህዝብ ዳዕዋ ሰለፍያን ማስፋፋት ነው ታማኝና እንቁ የሆኑ ዱአቶች እንድሁም ቂራአቶች እንለቃለን ቢኢዝኒላሂ ሱበሀነሁ ወተዓላ!!! ስህተትና ኸጦዕ ካለ በመረጃ መታረምን እንወዳለን

«ትክክል መሆኑን እያወቀ ክርክርን (ጭቅጭቅን) ለተወ ሰው በጀነት ቤት እንደሚኖረው እኔ ዎስትና እሆነዎለሁ»። ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ሱነን አቢ ዳውድ (4800) https://t.me/daewaselefyagimba
إظهار الكل...
ዳዕዋ ሠለፍያ በጊምባ ከተማ

አላማችን ለጊምባ ከተማ እና አካባቢዋ ህዝብ ዳዕዋ ሰለፍያን ማስፋፋት ነው ታማኝና እንቁ የሆኑ ዱአቶች እንድሁም ቂራአቶች እንለቃለን ቢኢዝኒላሂ ሱበሀነሁ ወተዓላ!!! ስህተትና ኸጦዕ ካለ በመረጃ መታረምን እንወዳለን

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.