cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የልደታ ሙስሊም ሴቶች ጀመአ

قال رسول الله (صلي الله عليه وسلم) ،"الدين النصيحة" ، قلنا :لمن؟، قال،"لله ولكتابه ولرسوله ولأءمة المسلمين وعامتهم" رواه مسلم

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
238
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-17 أيام
+230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

🔹የሙሀረም ወር ፆም ሁክሙ ምንድን ነው? ብዙ ሰዎች ሙሀረም ወር በገባ ሁል ግዜ ሙሀረምን ወር መፆም ይቻላልን ? ብለው ይጠይቃሉ ። የሸአባን ወርም ሲመጣ የዙልሂጃም ወር ሲገባ ፆም እንዴት ነው ይቻላልን የሚል ጥያቄ በየአመቱ የተለመደ ሆኗል ። ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ይህን ጥያቄ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ እንደሚከተለው ይሆናል የሙሀረም ወርን መፆም የተደነገገ ነው የሸእባን ወርም እንደዚሁ የዙል ሂጃ የመጨረሻ አስሩ ቀናቶች ግን በፆም ላይ የሚያዝ መረጃ የለም ነገር ግን ለየት ያለ ኢእቲቃድ ሳያደርግ ቢፆም ወይም እሷ ለየት ያለ የተነጠለችበት ነገር አለ ብሎ ሳያስብ ቢፆም ችግር የለውም ። የሙሀረም ወር ፆም ግን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል“ ከረመዳን በኃላ በላጭ የሆነው ፆም የአላህ ወር ሙሀረም ነው” ስለዚህም ሁሉንም ቢፆም መልካም ነው ወይም ዘጠነኛውን ፣ አስረኛውን እና አስራአንደኛውን ቀን ቢፆም ሱና ነው ። ከእናታችን አኢሻ እና ኡሙ ሰለማ እንደተወራው የአላህ መልክተኛ የሸአባን ወር እንዲሁ ሁሉንም ይፆሙ ነበር የዙል ሂጃ አስር ቀን የሚፈለግበት ዘጠኝ ቀናትን ነው ምክንያቱም የኢዱ ቀን አይፆምምና እነዚህን ቀናት መፆም ችግር የለውም ምንዳም ይኖረዋል የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለው በተናገሩት ሀዲስ መሰረት በእነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚሰሩ መልካም ተግባሮች አላህ ዘንድ የበለጠ የተወደደ የሆነ ምንም ተግባር የለም ሲሉ ሰሀባዎች እንዲህ ብለው ጠየቁ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ቢሆን ? አዎ በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ቢሆን ነገር ግን ግለሰቡ ነፍሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ሲያበቃ ከእነዚህ ነገር በምንም ያልተመለሰ ሲቀር አሉ ከነብያችን እነዚህን ቀናቶች ፆመው እንደነበረ የተወሩ እንዳልፆሙትም የተወሩ ዘገባዎች ያሉ ቢሆንም ፆመውታል የሚለውም ሆነ አልፆሙትም የሚለው የተረጋገጠ ዘገባ አይደለም ። T.me/dawudyassin
إظهار الكل...
በሙሀረም ወር ውስጥ ምን ተከስቷል?? - አላህ ሙሳንና ሙዕሚኖችን ከፊርአውንና ከወራደሮቹ ያዳነበት ወር ነው ። -በ6ኛው አመተ ሂጅራ ረሱል ﷺ ኡሙል ሙዕሚኒን ሰፊያህ ቢንት አኽጠብን አግብተዋል ። -በ7ኛው አመተ ሂጅራ ረሱልﷺ ወደ ኸይበር ዘመቻ ወጥተዋል ። -በ12ኛው አመተ ሂጅራ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ በሁርሙዝ ሲመራ የነበረውን የፋርስ ወታደር ላይ "ዛት አሰላሲል" በሚባለው ጦርነት ከባድ ሽንፈት አድሶባቸዋል ። ጀግናው ኻሊድም በዚሁ ጦርነት በአንድ ለአንድ ውጊያ ሁርሙዝን በማሸነፍ መግደል ችሏል ። -በ13ኛው አመተ ሂጅራ ኻሊድ ኢቢኑ ወሊድ ከኢራቅ ወደ ሻም በአቡበከር አሲዲቅ ትዕዛዝ የተመለሰበትና የሻም አጠቃላይ ሰራዊት መሪ የሆነበት ነው ። -በ16ኛው አመተ ሂጅራ የኢብራሂም እናት ማሪያቱል ቂብጥያህ ሞተች ። -በ23ኛው አመተ ሂጅራ በ23 ዙል ሂጃ ከኡመር ኢብኑል ኸጣብ ሞት በኃላ በ24ኛው አመተ ሂጅራ በሙሀረም ወር ኡስማን ኢብኑ አፋን ኸሊፋ ሁኗል። -በ61ኛው አመተ ሂጅራ እለተ ጁምአ የረሱል ﷺ የልጅ ልጅ ሁሰይን ቢን አሊ ተግድለዋል ። _ በ99ኛው አመተ ሂጅራ በመስለማህ ቢን አብዱል መሊክ መሪነት ቆስጠንጢኖጵልን ( የአሁኗን ኢስጠንቡል ከተማ ) ለመክፈት ሙስሊሞች ከበቡ ። -በ656ኛው አመተ ሂጅራ ተታሮች (መንጎሎች) የደጅላ ( tigris river) ወንዝን በማለፍ ምዕራባዊውን የበግዳድ ከተማን ክፍል የአባሲያዎችን ወታደር በማሸነፍ ተቆጣጠሩ ። ምስራቃዊውን የከተማዋን ክፍል ግን በከባድ ትግል እስክ ሙሀረም 19 ድረስ ማስጠበቅ ችለው ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆዩ ተታሮች ይህንንም ክፍል መቆጣጠር ችለዋል ። -በ687ኛው አመተ ሂጅራ ኦርሀን ቢን ኡስማን ቢን አርጦግሮል ሁለተኛው የኦቶማን ቱርክ ሱልጣን ተወለደ። -በ855ኛው አመተ ሂጅራ ሙራድ (ሁለተኛው) ስድስተኛው የኦቶማን ቱርክ ሱልጣን ሞተ። -በ1318 አመተ ሂጅራ ሱልጣን አብዱል ሀሚድ (ሁለተኛው) ሂጃዝ ላይ ሁጃጆችን ለማገልገል አዲስ መንገድ እንዲሰራ ትዕዛዝ አስተላልፏል። 📚ابن طباطبا، الفخري في الآداب السلطانية والدول الإسلامية ص 296، 298 📚الفكر العربي، القاهرة، ج 6 ص 385: 387 📚 الأزدي، تاريخ فتوح الشام، مؤسسة سجل العرب 1970 القاهرة ص 68 ✍ ቢንት አብደላህ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛
إظهار الكل...
01:00
Video unavailableShow in Telegram
ባሏ ራቅ ወደ አለ ቦታ የሄደ ወይም ባሏ በአካባቢዉ የሌለ ሴት እንግዳ ቢመጣባት እንዴት ታስተናግደዉ?? መልስ እንግዳ ማክበር ባህል ነዉ ማለት ተገቢ አይደለም ይልቁንም ከኢባዳ ነዉ ማለት ያለብን ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል በአሏህ እና በመጨረሻዉ ቀን ያመነ እንግዳን ያክብር እንግዳን ማክበር(ማስተናገድ) ኢባዳ ነዉ የሰዉን ልጅ ወደ አሏህ ያቃርባል በአሏህ ፍቃድ ለመስተካከል ሰበብ ምክንያት ይሆናል ባሏ ሳይኖር እንግዳ ቢመጣባት ይቅርታ ትጠይቅ ያጀማዓ ባሌ አሁን ላይ የለም ባሌ እስኪመጣ ድረስ ጠብቁት ወይም ባሏ እስኪመጣ ድረስ ትጠብቀዉ ባሏ ሲመጣ ለእንግዶቹ ግዴታ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ያቀርባል 👇👇👇 እኛ ብዙ ወንዶች የሚታይ ስህተት ባል ወደ ስራ ይሁን ለጉዳይ ሲሄድ የባል ወንድም ሚስቱ ብቻዋን ብትሆንም ይመጣል እሷም የባሌ ወንድም ነዉ ብላ ታስተናግደዋለች ከባሏ ወንድም ፊት አትሸፈንም ይሄ ስህተት ነዉ የባሏ ወንድም ሁን የቅርብ ጉዋደኛ ባሏ ከቤት ከለሌ መሄድ የለብህም የባል ወንድም ወንድምህ ስልክ ደዉለህ ከቤት የለሁም ካለ መሄድ የለብህም ሴቶችም የባል ወንድም ሲመጣ ግባ ተቀመጥ ጠብቀዉ ማለት የለባቹሁም የባላቹህ ወንድም ጋር መሳሳቅ መጫወት መቀላለድ የለባቹሁም እየሰማን ነዉ የባሌን ወንድም ወደድኩት የሚሉ በዚያ ላይ ባል ከሌለ ወንድሙጋ በመቀራረብ በመቀላለድ ወደ ሌላ ነገር ይገባል እናም ይሄን ባህል መቅረት አለበት የባሌ ቤተሰብ ይጠሉኛል አይወዱኝም ብለሽ አሏህን የፈጠረሽን አስቆጥተሽ ፍጡርን አስደስተሽ የቤተሰቡን ዉዴታ አይደለም የጎረቤት ዉዴታ ክብር አታገኝም እኛም ወንዶች ባል ከቤት ከሌለ የቅርብ ጓደኛህ ይሁን ወንድምህ ከቤቱ መሄድ የለብንም 👇👇👇 https://t.me/HuzeyfaAhmed
إظهار الكل...
2.57 MB
✍ ብዕረ ሐኒፍ #3 🔖ሟች እና አልቃሽ ☞የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ! በበስራ ከተማ ኗሪ የሆነ አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ። በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ። ከዛም ይህ ሞት የተጣደው ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ" አላቸው።  ደግፈው አስቀመጡት። ከዛ ወደ አባቱ ዞረና "አባቴ ለምንድነው ምታለቅሰው?" አለው።  አባትም" አንተን ማጣቴ ካንተ ቡሃላ ብቸኛ መሆኔ ነው ያስለቀሰኝ።" አለው። ወደ እናቱም ዞረና "እናቴ ምንድነው ያስለቀሰሽ?" አላት። እሷም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው ያስለቀሰኝ።" አለችው። ወደ ሚስቱም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅስሽ?" አላት እሷም "ያንተን መልካም ነገር ስለማጣ ወደ ሌላ ሰው ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን።" አለችው። ወደ ልጆቹም ዞረና "ምንድነው የሚያስለቅሳቹ?" አላቸው። እነሱም "ከአንተ በኋላ ወደ የቲምነት፣ ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደ ማጣት ስለምንጓዝ" አሉ። ይሁን ሁሉ ከሰማ በኋላ ሟቹ በጣም አለቀሰ። ቤተሰቦቹም  "ለምን ታለቅሳለህ?" አሉት። እሱም "ሁላቹም ለኔ ብላቹህ ሳይሆን ለራሳቹህ ጥቅም ነው የምታለቅሱት። ይህን ስላየሁ አለቅሳለሁ።" አለ። "ከናንተ ውስጥ ለጉዜዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስ የለም? ከእናንተ ውሰጥ ከዚህ  በኋላ አስደንጋጭ ሂሳብ ስለሚጠብቀኝ የሚያለቅስ ሰው የለም? ከእናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም? አለና በፊት ለፊቱ ተደፋ።  ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች። ሞቷል። سَفَري بَعيدٌ وَزادي لَنْ يُبَلِّغَنـي *وَقُوَّتي ضَعُفَتْ والمـوتُ يَطلُبُنـي وَلي بَقايــا ذُنوبٍ لَسْتُ أَعْلَمُها *الله يَعْلَمُهــا في السِّرِ والعَلَنِ. ጉዞዬ ሩቅ ነው ስንቄም አያደርሰኝ ሀይሌም ተዳከመ ሞትም ፈላለገኝ የማላቃት ወንጀል አለች አሰፍስፋ አላህ የሚያውቃት በምስጥር በይፋ ✍ በዐብዱረዛቅ አል–ሐበሺይ @HanifMultimedia
إظهار الكل...
አንድ ሰው አርባ አመት ሲሞላው፦ ”ወደ አኼራ ጎዞህ ተቃርቧልና ስንቅህን አዘጋጅ።˝ ብሎ ከሰማይ☝️ ተጣሪ ይጣራል። 📚ረውደቱ አል ዑቀላእ (52)
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
በሶስቱ የአያሙ አት-ተሽሪቅ ቀናቶች ዱዓ ማብዛት የተወደደ ነዉ ። http://t.me/+CL_1nL1UHLFhZjU8
إظهار الكل...
☁️ 🌟 🌟 🌟 ☁ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ የአላህ መልእክተኛ👉 🌱አያመ አልተሽሪቅ መብያና መጠጫ እንዲሁም አላህን ማውሻ ቀን ነው ብለዋል።🌱 👆👆👆👆👆👆👆 እዚህ ሀዲስ ላይ ምርጥና ድንቅ የሆነ ትልቅ ሚስጥር ይዟል። እሱም የሰው ልጅ በሁሉም ጊዜያትና ሁኔታዎች ላይ ከጌታው ባርነትነና ታዛዥነት ጋር የተቆራኝ እንደሆነ ያመላክታል 👉አንድ ሙስሊም ፆመኛ ሲሆን አላህን መገዛትን አስቦ ከምግብ ከመጠጥ እንደሚከለከለው ሁሉ ✅ 👉ነጌ ጀምሮ አስከ ሮብ ያሉት 3ቱ አያመተሽሪቅ ቀናቶች ላይ ሁሉም ሙስሊም በመብላትና በመጠጣት ለአላህ ኢባዳ ያደርጋል በዚህም ላይ የመልክተኛው ትእዛዝ መከተልም አለበትና.👍 ‼️ ያ ጀመዐ ነቃ እንበል‼️ ❌ነጌ ከነገወዲያና ሮብ የሱና ፆምም ይሁን❌ ቀዳእም ይሁን ❌የስለት ፆምም ባጠቃላይ ምንም አይነት ፆም ❌ መፆም የተከለከለ ነው አይቻልም 👌በዚህ ፆም ክልከላ ላይ ግን አንድ አካል ብቻ አይካተትም እሱም ሀጅ ላይ ያለና ሀድይ ማረድ ያልቻለ ወይም ያላገኘ ሰው ከእርዱ ቀን ቡሀላ 3ቱ የአያመተሽሪቅ ቀን ኢዚያው ፆሞ ሰባቱን ደግሞ ወደ ሀገሩ ሲመጣ ይፆመዋል። @bin_Husseynfurii 👆👆👆👆👆👆👆 ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ☁ 🌟 🌟 🌟 ☁
إظهار الكل...
* የዒድ አከባበር ደንቦች * ክፍል 1 በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው:: ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልእክተኛው ሙሀመድ፤ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን፡፡ * ዒድ ማለት ምን ማለት ነው? * ኢብኑል-ዓረቢይ ዒድ "ዒድ" ተብሎ ስለመሰየሙ ሲናገሩ በየአመቱ አዲስ ደስታን ይዞ የሚመለስ ከመሆኑ አንፃር መሆኑን እና "ዓደ" (ተመለሰ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንልን የሚገባው ዒድ ቂያማ እስኪቆም ተመላልሶ የሚመጣ ቢሆንም እኛ ግን የሚቀጥለውን ለመድረስ ምንም ዋስትና እንደሌለን ነው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ህግ ፈፅሞ ልንወጣ አይገባም፡፡ አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ:- ‹‹የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) መዲና ከተማ ሲመጡ የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን (ደስታቸውን የሚገልፁባቸው) የሚጫወቱባቸው ሁለት ክብረ-በዓላት ነበሮቸው። ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡፡ "አላህ በእነዚህ በሁለቱ ምትክ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ክብረ-በዓላትን ቀየረላችሁ፤ እነሱም "የፊጥር" እና "የአድሀ" በዓላት ናቸው፡፡" (አቡዳውድ እና አህመድ ዘግበውታል) ከዚህ ሀዲስ ዑለማዎች የተረዷቸዉን ሁለት ቁም ነገሮች ልናስተውል ይገባል። አንደኛ፡- ከእስልምና ውጭ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር መመሳሰል የተከለከለ መሆኑ:: ሁለተኛ ፡- በኢስላም የተደነገጉ ክብረ-በዓላት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ነው:: * ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው የሚገቡ ነገሮች * ከዚህ በላይ በአጭሩ ዒድ ማለት ምን ማለት እንደሆነና በኢስላም የተደነገጉ ክብረ-በዓላት ዒድ-አልፈጥር እና ዒድ-አልአድሀ ብቻ መሆናቸውን ከተረዳን፤ በእነዚህ ሁለት ዒዶች ዋዜማ እና በእለቱ ምን ማድረግ ይወደዳል? ምንስ ይፈቀዳል? ምን ከማድረግ ልንከለከል ይገባል? ወደ ሚሉት ነጥቦች እንሂድ፡፡ በመጀመሪያ ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው ከሚያስፈልጉ ነገሮች:- 1⃣በዒደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰአት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በዒደል-አድሀ ደግሞ ከዙል-ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ ይገባል፡፡ 2⃣መታጠብ እራስን ማሰማመር እና ከልብሶች መካከል የተሻለውን እና ቆንጆውን መልበስ ከሰለፎች የተዘገበ ተግባር ነው፡፡ 3⃣ሴቶችን በተመለከተ በዚህ እለትም ይሁን በሌላ ጊዜ ከቤታቸው እንዴት መውጣት እንዳባቸው በሸሪዓ የታወቀ ነው፡፡ እናም ከመገላለጥ እና ሽታ ያላቸውን ነገሮች ተጠቅመው ከመውጣት ተቆጥበዉ ከቤታቸው ወደ መስጊድ ወይም ወደ ዒድ መስገጃ ስፍራ ሊሄዱ ይገባል፡፡ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ለጋብቻ የቀረቡና የደረሱ እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዒድ ሰላት መስገጃ ቦታ ስፍራ እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠይቀው ነበር ‹‹አንዳችን ጅልባብ ባይኖራት ምን ታድርግ?›› እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹እህቷ (ጓደኛዋ) ታውሳት(ታልብሳት)››(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) በሌላውም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹‹ሴቶችን መስጊድ ከመሄድ አትከልክሏቸው ነገር ግን ከቤታቸው ሽታ ያለው ነገርን ተጠቅመው እንዳይወጡ፡፡››(አል-ኢማም አህመድና አቡዳውድ ሲዘግቡት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል) 4⃣በዒደል-ፊጥር ሰጋጁ ወደ መስገጃው ከመውጣቱ በፊት ዊትር (አንድ፤ ሶስት፤ አምስት …..) ቁጥር ያላቸውን ተምሮች በልቶ ወደ ዒድ መስገጃው መሄድ። 5⃣ለዒድ ሰላት ከመሄድ በፊት ዘካተል-ፊጥርን ለተገቢው ወገን መስጠት። 6⃣የዒድ ሰላትን ለመስገድ ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት ሊኖር ይገባል። ምክንያቱም ይህ ተግባር ከታላላቅ የኢስላም መገለጫዎች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) የዒድ ሰላትን ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሕልፈታቸው ትተውት አያውቁም ነበር። ከዚህ በተጨማሪም በመሰረቱ ሰላትን መስገድ የተከለከሉትን የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሳይቀር በቦታው ላይ እንዲገኙ አዘዋል፡፡ 7⃣ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በተቻለ አቅም ኹጥባን ማዳመጥ። 8⃣ወደ ዒድ ሰላት ከሄዱበት መንገድ በሌላ መንገድ መመለስ። 9⃣የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ፡፡ ይህም ”ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም" የሚል ሲሆን የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ከሰሃቦች መገኘቱን አረጋግጠዋል። 🔟ከዒደል-ፊጥር ጋር በተያያዘ ዘካተል-ፊጥርን መስጠት መታዘዙ የተለያዩ ችግረኞችን ማስታወስ እና አቅም በፈቀደ መጠን ችግራቸውን ለመቅረፍ ጥረት ማድረግ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን የሚያመለክት ነው። 1⃣1⃣በአጠቃላይ ሸሪዓው ያዘዘባቸውን እና የፈቀዳቸውን ተግባራት መፈፀም የሚፈቀድና የሚወደድ ይሆናል። ኢንሻ አላህ ክፍል 2 ይቀጥላል… ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

የዒድ አከባበር ደንቦች ክፍል 2 የተክቢራ አፈፃፀም 1⃣ ከመልክተኛው ትክክለኛ ሰነድን መሰረት ያደረገ እና የተክቢራን አባባል ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ መረጃ ባይገኝም ከሰሀቦቻቸው ግን "አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ" እና የመሳሰሉት አባባሎች በትክክለኛ ሰነድ ተዘግበዋል፡፡ ስለሆነም ሙስሊሞች እነዚህን አባባሎች የትኞቹ እንደሆኑ ማጥናትና እነርሱን ማዘውተር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢብኑ ሀጀር አል-ዓስቀላኒ ፈትሁል-ባሪ በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ይላሉ "በዚህ ዘመን (ተክቢራን በተመለከተ) ብዙ መሰረት የሌላቸው ጭማሪዋች ተከስተዋል፡፡" ይህ በሂጅራ አቆጣጠር (ከ773-852) የኖሩት የኢስላም ሊቅ ንግግር ነው። ታዲያ ባለንበት ዘመን ምን ያህል ጭማሪ ተከስቶ ሊሆን እንሚችል ስናስተውል በጉዳዩ ላይ ከባድ ጥንቃቄ ልናደርግ እንደሚገባ ያመላክተናል፡፡ 2⃣ በአንድ ድምፅ ወይም አንድን ሰው አዝማች (አውጪ) ሌላው ተቀባይ ሆኖ የሚደረግ ተክቢራም ሱናን የሚቃረን ተግባር ነው። በዚህ ዙሪያ ተምሳሳይ ድርጊት ከሚፈጽሙት ወገኖች እንደ መረጃ የሚጠቀሰው የዑመር ተግባር (ሚና ላይ በድንኳን ውስጥ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ሲያደርግ ሰዎችም ተክቢራውን ሰምተው ተክቢራን ማድረጋቸው) የሚያመለክተው የእሱን ድምፅ ሲሰሙ ተክቢራን ማድረግ እንዳለባቸው በማስታወስ እነርሱም ተክቢራ ያደርጉ እንደነበረ እንጂ ሌላን አይደለም። ስለሆነም ይህ ክስተት፤ በጋራ ድምፅ እርሱን እንደ አዝማች እነርሱ እንደ ተቀባይ ሆነው ይቀጥሉ ነበር የሚለውን እንድምታ አያስጨብጥም ሲሉ ዑለማዎች ይናገራሉ፡፡ ጥቂት ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶች 1⃣ኛ. ዒድ መሆኑ ከታወቀበት ሰአት ጀምሮ ወንዶች ከሰላተል ጀመዓ መቅረት ብሎም በረመዳን ሲሰግዱት የነበረውን ዊትር ሰላት ማቋረጥ፤ አንዳንዴም አምልኮዎች በዚህ ያበቃሉ የተባለ ይመስል እርግፍ አድርጎ መተው ይስተዋላል፡፡ 2⃣ኛ. የዒዱን ዋዜማ ለሊት በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው ማድረግን በተመለከተ የመጡት ሀዲሶች ከሰነድ አንፃር ደካማዎች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ለሊቱን በተለያዩ የሚጠቅሙም ይሁን ያማይጠቅሙ ነገሮች ላይ ማሳለፍ፤ በዚህም የተነሳ የፈጅር ሰላትን አለመስገድ እና ሰላተል-ዒድን እንደ ቀላል በመመልከት ችላ ብሎ መተው:: የዒድ ሰላትን በተመለከተ "ሰላተል-ዒድ በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው" የሚለው የአቡ ሀኒፋ አቋም ሲሆን ከኢማሙ አሻፊዒይ እና አህመድም ከተዘገቡት ሁለት የተለያዩ አቋሞች አንዱ የሚጠቁመውም ይህንኑ ነው። ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑ-ተይሚያህ እና ሌሎች ብዙ ዑለማዎችም ይህን አቋም የሚደግፉ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ 3⃣ኛ.በአለባበስና መቆነጃጀት ዙሪያ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል ብዙ ወንዶች ፂማቸውን መላጨትና ማሳጠር እንዲሁም ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች እነዲወርድ በማድረግ የሚፈፅሙት ስህተት ይገኝበታ። ሴቶች ደግሞ ሽቶን በመቀባት በመገላለጥ የሚፈፅሙት ስህተት እጅግ አደገኛ ነው፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የመጡት ነብያዊ አስተምህሮቶች በጣም አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( مَا أَسْفَلَ مِنْ الْكَعْبَيْنِ مِنْ الْإِزَارِ فَفِي النَّارِ) رواه البخاري (5787) ከአቡሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከሽርጥ ከቁርጭምጭሚት የወረደዉ የእሳት ነው" (ቡኻሪና በቁጥር (5787) ዘግበዉታል) ይህ ሁሉንም የልብስ አይነት እንደሚያካትት ለመግለፅ አል-ኢማም አል-ቡኻሪይ ለሀዲሱ "ከቁርጭምጭሚት የወረደው እሱ የእሳት ነው" የሚል ርዕስ ሰጥተውታል። በሌላ ሴቶች ከቤት ሲወጡ ምን አይነት ስነ-ስርአት መከተል እንደሚገባቸው በሚጠቁም ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:-"ማንኛዋም ሴት ሽቶን ተቀብታ ወደ መስጂድ የወጣች እንደሆነ እስክትታጠብ ድረስ ሰላቷ ተቀባይነት የለውም፡፡"(ኢብኑ ማጃህ እና አህመድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡) عن أبي هريرة قال: قال صلى الله عليه وسلم : "صِنفانِ مِن أهلِ النارِ لم أرَهما..... ونِساءٌ كاسياتٌ عارياتٌ مميلاتٌ مائلاتٌ، رؤوسُهُنَّ كأسنِمَةِ البُخْتِ المائلةِ لا يَدْخُلْنَ الجنةَ ولا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وإن رِيحَهَا لَيوجَدُ مِن مَسيرةِ كذا وكذا". رواه مسلم(2128) ሙስሊም አቡ ሁረይራን ዋቢ አድርገው ባስተላለፉት ሀዲስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል:- "ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች በእኔ (ዘመን) አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ)" አሉና፤ የመጀመሪያዎቹ ምን አይነት ባህሪ እንዳላቸው ካብራሩ በኋላ "ሌለኞቹ ሴቶች ናቸው፤ ለብሰው ያልለበሱ አካሄዳቸው እና እንቅስቃሴያቸው ወደርካሽ አላማ ያዘነበለ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ናቸው:: እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም" አሉ:: ክፍል 3 ይቀጥላል.… ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

የዒድ አከባበር ደንቦች ክፍል 3 ከዒድ ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶችን በተመለከተ ከክፍል ሁለት የቀጠለ። 4⃣ኛ. ባዕድ በሆኑ ወንዶችና ሴቶች መካከል መቀላቀል፤ አልፎም መጨባበጥና መሳሳም፡፡ ይህ ሸሪዓው ክፉኛ የኮነነው ተግባር ነው፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ከእለታት አንድ ቀን ከመስጂድ በመውጣት ላይ ሳሉ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመንገድ ላይ ተቀላቅለው ተመለከቱ ይህንን ክስተት በማስመልከትም "ከወንዶች ወደ ኋላ ሁኑ፤ የመንገዱንም መሀከል ይዛችሁ ልትጓዙ አይገባም" አሉ፡፡ ይህንን ሀዲስ የዘገበው ሰሃቢይ "ከዚህ በኋላ ሴቶች በጣም ወደ ዳር ከመውጣታቸው ልብሳቸው በአጥር ይያዝ ነበር፡፡" በማለት ይናገራል፡፡(አቡዳውድ ሱነናቸው ላይ ሲዘግቡት አልባኒ ሀሰን የሚል ደረጃ ሰጥተውታል) ይህ ሀዲስ ሸሪዓ በጥቅሉ ወደ ሀራም የሚያደርሱ ነገሮችን የከለከለ መሆኑን ከሚያሳዩ መረጃዎች አንዱ ነው፡፡ በሌላ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰለም በርሳቸው ላይ ይሁን) "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም" ማለታቸው ሰፍሯል፡፡ ሀዲሱ አንድ ሰው ምንም እንኳ የተቀደሰ አላማና ንፁህ ልቦና ነው የያዝኩት ቢልም ባዕድ ሴቶችን ከመጨበጥ ሊቆጠብ እንደሚገባ የሚያመለክት ነው፡፡ 5⃣ኛ. እንደ ሙዚቃ እና መሰል የተከለከሉ ነገሮችን ከማድመጥ፣ ፊልሞችን በመመልከት ጊዜን ከማጥፋት መቆጠብ ያስፈልጋል:: እንዲሁም ሌሎችንም ሀራም የሆኑ ተግባራትን በሙሉ መጠንቀቅ ይገባል:: 6⃣ኛ. በዒድም ይሁን በሌላ ጊዜ በኢስላም ማባከን እጅጉን የተኮነነ ተግባር ቢሆንም በዒድ እለት በአንዳንዶች ዘንድ ከሚታዩት ስህተቶች መካከል ምግብና መጠጥን ማባከን ነውና ልንርቀው ይገባል:: ኢስላም በራሱ የተሟላ ነው! እንደሚታወቀው ሀይማኖታችን ኢስላም ምሉዕ ነው፡፡ ስለሆነም ለሁሉም የአምልኮ ዘርፎች እንዲሁም የህይወት መስኮች ደንቦችን ደንግጓል ስርዐቶችንም አስቀምጧል፡፡ ሕግጋቶቹ ፍትሀዊ እና ሚዛናዊ ስርዐቶቹም ለሁሉም ቦታ እና ዘመን የሚበጁ ናቸው፡፡ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል:- {الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا} المائدة 3 ‹‹ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ከሀይማኖት በኩልም ለእናንተም ኢስላምን ወደደኩ...›› (አልማኢዳ፡ 3) ከዚህም በመነሳት መጨመርንም ይሁን መቀነስን አይቀበልም እንዲሁም ከሌሎች መኮረጅንም ሆነ መመሳሰልን ይከለክላል፡፡ ይህንን እዉነታ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን) በነዚህ ሁለት ነብያዊ አስተምህሮቶች ይገልፁታል፡፡ قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ) رواه البخاري (2697) ومسلم (1718) "በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)" (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል) قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ ) رواه أبو داود (4031) "ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡" (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) ስለሆነም ዒዳችንን ስናከብርም ይሁን ማንኛውንም አይነት ዒባዳ ስንፈጽም ከጭማሪ (ቢደዓ) እራሳችንን ልናርቅ እንዲሁም በማነኛውም የህይወታችን ክፍሎች ከሌሎች ጋር መመሳሰልን ትተን ሙሉ የሆነውን ሸሪዓን በማወቅ ወደ ተግባር ልንለውጥ ይገባል:: تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال. አላህ መልካም ስራችንን ይቀበለን!! ✍ *ጣሀ አህመድ (1431ሂ) የተፃፈ* 🌐 https://t.me/tahaahmed9
إظهار الكل...
🗞 ጣሀ አህመድ – Taha Ahmed 🗞

ይህ የተለያዩ ኢስላማዊ ትምህርቶች እና መልእክቶች የሚተላለፉበት መድረክ ነው። (ወደ መልካም አመላካች እንደ ተግባሪው ምንዳ አለው) በሚለው ነብያዊ ፈለግ መሰረት እርሶም ወደ ኸይር በማመላከትና እርሱን ለሌሎች በማስተላለፍ ስራ የበኩሎን አስተዎፅኦ እንዲያበረክቱ ተጋብዘዎል። (إن أريد إلا الإصلاح ما استطعت وما توفيقي إلا بالله عليه توكلت وإليه أنيب)

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.