cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Loza Health Jobs 3

ያገለግላሉ የህክምና ማሽኖችን እንገዛለን እንሸጣለን፥የህክምና ባለሙያዎችን ለግል ጤና ተቋም እናገናኛለን ፤ድርጅቶችን በ3ቱም የቴሌግራም ቻናሎቻችን ማስታወቂያ እንሰራለን፤ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን በቻናላችን እናጋራለን፤ትኩስና ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እናጋራለን 0917171781/0918706464

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
5 105
المشتركون
-324 ساعات
+117 أيام
+4030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከነገ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ በሕጻናት፣ በማህፀንና ጽንስ፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገና እና በውስጥ ደዌ ተመላላሽ ሕክምና እንዲሁም የተለያዩ የላቦራቶሪ እና ኢሜጂንግ አገልግሎቶች አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል፡፡ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው ሆስፒታሉ፤ 600 የህሙማን አልጋዎች እና የተለያዩ ዘመናዊ የህክምና ግብዓቶች የተሟላለት ነው፡፡ #tikvahuniversity
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የቅጥር ማስታወቂያ ነርስ 2 ዓመት ልምድ ዲርቤቴ ለመካከለኛ ክሊኒክ ፆታ ሴት 1 ዓመት በላይ ልምድ ያላት 0917171781 0918706464 @loza
إظهار الكل...
"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል" #Ethiopia | በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡ ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡ ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡ በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ከሐምሌ 3 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ Via EBC
إظهار الكل...
👆👆👆አሁን አሁን እኔ በግሌ የምታዘበው አብዛኛው የማህበረሰባችን ክፍል ሺሻ ይስባል ስለዚህ ይህን ፖስት ያነበባችሁ ሁሉ ሸርርርርርርር አድርጉት
إظهار الكل...
ሺሻ ወጣቶችን ለስትሮክ እያጋለጠ ነው። <ሺሻ እንጂ ሲጋራ በፍፁም አላጨስም> የሚሉ ሰዎች ሁለቱ ተመሳሳይ መሆናቸውን ካለማወቅ የመጣ ስለሆነ ይኸን ጉዳይ ለማሳወቅ በዚህ መልኩ ልፅፍ ወደድኩኝ ። ሺሻ ቶባኮን በትነት መልክ የመውሰድ ስልት ነው። አላማው ጎጂ ንጥረ ነገሮችን አጣርቶ ለመውሰድ ያለመ ነበር። ይኸ እሳቤ ውድቅ የተደረገ እና ሰዎችን እያሳሳተ ወደ ችግር እየከተታቸው እንደሆነ በተደረጉ ጥናቶች ተረጋግጧል። ሺሻ መርዛማ እና ሱስ አምጪ ንጥረ ነገሮችን በጭስ መልክ ወደ ሰውነት የሚያጓጉዝ ትውልድ አምካኝ ሒደት ነው። ቶባኮ እናት ተክል ነው። ከተባኮ ተክል ለቁጥር የሚታክቱ ምርቶች ገበያ ላይ ይገኛሉ። ልክ ከስንዴ ድፎ ዳቦ ፣ ገበር ዳቦ ፣ አነባበሮ ፣ እንጀራ ፣ ቆሎ ፣ ቆሎ ዳቦ ፣.. እያለ ብዙ እንደሚዘጋጅ ሁሉ ከተባኮም ብዙ ይዘጋጃል። በሺሻ እና በሲጋራ መልክ የሚቀርቡት በስፋት የሚታወቁ ናቸው። ሺሻ ብዙ ስሞች ያሉት የቶባኮ ተክል ተረፈ ምርት የሚሳብበት አንዱና በፋሺን መልክ የሚዘወተር አሳሳች መንገድ ነው። ሺሻ ቶባኮ/ሆካኽ/ዋተር ፓይፕ/ሞላሰስ... ለአንድ ነገር የተሰጡ ብዙ የቤት ውስጥ መጠሪያዎች ናቸው። ሺሻ በሆካኽ መለኪያ ይለካል። አንድ ሆካህ ማለት ሁለት መቶ ጭስ መሳብ /200 puff/= 100 ሲጋራ ማጨስ ማለት ነው። ታዲያ ቶባኮን በሺሻ እየሳቡ ሲጋራ በፍፁም አላጨስም የሚለው ሐሳብ እዚህ ጋር ፉርሽ መሆኑን ልብ ይበሉ። <ከመረቁ አውጡልኝ ከጮማው ፆመኛ ነኝ > አይነት ዳር ዳር ከጉዳት አያስጥልም። በወጣትነት እድሜ ክልል ስትሮክን ሊያመጡ ከሚችሉት ዋነኞቹ አንዱ ቶባኮን በሺሻ መሳብ ነው። ሌሎችም በርከት ያሉ ህገ ወጥ መድሐኒቶች ለስትሮክ የሚያጋልጡ አሉ። ሺሻ መሳብ በቀጥታ ለድንገተኛ ስትሮክ ይዳርጋል። በከቶሞች ብዙ ቤቶች ውስጣቸው በገዳይ እና ሱስ አምጪ ጭስ የታመቁ እንደሆኑ የተጠቃሚዎቻቸው ብዛት ህያው ምስክር ናቸው። ብዙ ሰዎች 'ሺሻን መሳብ' ቀላልና ለጤና አስጊ እንዳልሆነ ያስባሉ ፤ እውነታው ተቃራኒ ነው። ሲጋራ ማጨስ ጎጂ መሆኑን ያወቀ ሺሻ ማሳብን ጤናማ ነው ሊል የሚችለው የሁለቱን አንድነት ያላወቀ ብቻ ነው። በሁለቱ መካከል በንጥረ ነገር ይዘት አንዳችም ልዩነት የለም። የመጠን ካልሆ... እንዳውም ለሺሻ የሚውለው መርዛማ ንጥረነገሮችን በብዛት ይዞ ይገኛል። ከድንገተኛ ስትሮክ በተጨማሪ ሺሻ መሳብ በርከት ላሉ እና ስር ሰዳጅ ህመሞች ያጋልጣል። በውስጡ ያለው ካርቦን ሞኖ እክሳይድ/CO/ የኦክስጂን እጥረት ያስከትላል። ለመተፈሻ አካል ችግር ፣ ለሳንባ ካንሰር ፣ ለአጀትና ለአፍ ውስጥ ካንሰር እራሱን የቻለ መንስኤ ነው። ለስኳር ፣ ለደም ግፊት መጨመር ፣ ለልብ ህመም ፣ ለኩላሊት ህመም ፣ ... ለደም ስር መጥበብ ተጠቃሽ መንስኤ ነው። ኢንፌክሺንን በማዛመት ይታወቃል። ይኸ የሚሆነው የሚጨሰው የሚዘጋጅበት ሒደትና መሳቢያ ገመዱን እየተቀባበሉ በጋራ በመጠቀማቸው ነው። መከላከያ ለመጠቀም የሚሞክሩ አሉ። ሺሻን ከባድ የሚያደርገው ልክ እንደ ሲጋራ ሱስ ማሲያዙ ነው። ሱስ የአእምሮ ህመም ነው። ሱስን ፈቅዶና ወዶ የሚያመጣ ባይኖርም እያንዳንዱ ሰው እራሱን ከሱስ የማራቅ ሐላፊነት አለበት። በሺሻ የሚሳብ ቶባኮ ከሲጋራ በላይ ጎጂ ነው። የሱስ ተጠቂ ያደርጋል። የሱስን አስከፊነት የሚያቀው ሐኪም ፣ የተጠቂዎች የቅርብ ሰዎችና የችግሩ ተጠቂዎች ናቸው። ሌሎች ለጤና መርዝ የሆኑ heavy metals የሚባሉ በውስጡ ተከማችተው ይገኛሉ። ባጠቃላይ ሺሻን ማስቆም የመንግስት ሐላፊነት ነው የኛ ሐላፊነት አስከፊ መሆኑን ማስረዳት ነው። በጭስ የሚታፈኑ ቤቶችን አነፍንፎ እርምጃ ለመውሰድ ብዙ ከባድ አይመስልም ከልብ ከሰሩ። በጭስ መልክ የሚወሰድ ቶባኮ ከሲጋራ በላይ መርዛማ ነው። 1)Tabrizi R, Borhani-Haghighi A.Hookah Smoking: A Potentially Risk Factor for First-Ever Ischemic Stroke. J Stroke Cerebrovasc Dis. 2020 Oct;29(10):105138. doi: 10.1016/j.jstrokecerebrovasdis.2020.105138. Epub 2020 Jul 18. PMID: 32912523. 2) Eissenberg T, Shihadeh A. Waterpipe tobacco and cigarette smoking: direct comparison of toxicant exposure. Am J Prev Med. 2009;37(6):518–23 3) Urkin J, Ochaion R, Peleg A. Hubble bubble equals trouble: the hazards of water pipe smoking. Sci World J. 2006;6:1990–7. 4) Blachman-Braun R, Del Mazo-Rodríguez RL, López-Sámano G, BuendíaRoldán I. Hookah, is it really harmless? Respir Med. 2014;108(5):661–7. ዶ/ር መስፍን በኃይሉ ፡ ጥቁር አንበሳ Telegram: t.me/HakimEthio
إظهار الكل...
Hakim

Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ በእንጅባራ ከተማ  ልምድ ባላቸው ስፔሻሊስት ሀኪሞችና ሲቲ ስካንን ጨምሮ ዘመኑን በዋጁ  የህክምና መሣሪያዎች ተደራጅቶ ስራ ከጀመረ የወራት ዕድሜ ብቻ ያስቆጠረው አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል  ፈዋሽነቱን ብዙዎች መስክረዉለታል። ስለሆነም የአገልግሎት አድማስን ከፍ ለማድረግ ተጨማሪ ስፔሻሊስቶችንና ሰብስፔሻሊስቶችን መቅጠር ስለሚፈልግ  ከታች በተዘረዘርዉ መስፈርት መሰረት እንድታመለክቱ እናሳውቃለን ፡  ፡ 1ኛ,የስነ-ደዌ ስፔሻሊስት (pathologist) ብዛት=01 የቅጥር ሆኔታ:-በቋሚነት አገልግሎት ፡ -ሁለት ዓመትና ከዚያ በላይ ልዩ ሁኔታ ፡ -ቢያንስ ለአንድ ዓመት Biopsy set ባለበት ተቋም የሠራ ቢሆን ይመረጣል ፡  ፡ ደምወዝ:-አመርቂ+ክዳሜ ከ6 ፡ 30 በኋላእና ዕሁድ የዲዩቲ አበል 2ኛ,የልብህክምናሰብስፔሻሊስ(Cardiologist) ብዛት:-01 የቅጥር ሁኔታ ፡ -በቋሚነት የስራ ልምድ:-ስድስት ወርና በላይ ደምወዝ:-እጅግ አመርቂ +ዕሁድ ቅዳሜ ዲዩቲ አበል+የቤት ኪራይ አበል+15%/ፕሮሲጀር 3ኛ, የጨጎራ፣የጉበት፣የቆሽትና የአንጀት ሰብስፔሻሊስት(Gastroenterologist) ብዛት:-01 የቅጥር ሁኔታ ፡ -በቋሚነት የስራ ልምድ:-ዜሮና  ከዚያ በላይ ደምወዝ:-እጅግ አመርቂ  +እሁድ-ቅዳሜ ዲዩቲ አበል+የቤት ኪራይ አበል+10%/ፕሮሲጀር 4ኛ,ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት(ENT) ብዛት:-01 የቅጥር ሁኔታ ፡ -በቋሚነት ደምወዝ:-እጀግ አመርቂ +እሁድ-ቅዳሜ ዲዩቲ አበል+የቤት ኪራይ አበል+10%/ፕሮሲጀር 5ኛ,የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻስሊት(Internist) ብዛት:-01 የቅጥር ሁኔታ ፡  -በቋሚነት የስራ ልምድ:-አንድ ዓመትና በላይ ሆኖ በግል ሆስፒታል/ሴንተር የሠራ ቢሆን ይመረጣል ደምወዝ:-አመርቂ+እሁድ-ቅዳሜ ዲዩቲ አበል+15%/ፕሮሲጀር የምዝገባ ጊዜ:-ይህ ማስታወቂያ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ስራ ቀናት የምዝገባ ቦታ :-በሆስፒታሉ ሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ወይም በስልክ ቁጥር 0923-55-55-52 ዶክመንት በመላክ መነጋገርና መመዝገብ ይቻላል።      አገዉ ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል    የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል !!
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
👆👆👆የቀሚስ ቤታችን እና የሽቶ ቤታችን ቲክቶክ አካውንት follow and like ያድርጉ
إظهار الكل...
Repost from Loza Health Jobs 3
إظهار الكل...
Visit TikTok to discover profiles!

Watch, follow, and discover more trending content.

إظهار الكل...
@ Loza

ያገለግላሉ የህክምና ማሽኖችን እንገዛለን እንሸጣለን፥የህክምና ባለሙያዎችን ለግል ጤና ተቋማት አገናኝ ህጋዊ ፈቃድ ያለው ኤጀንሲ፤ድርጅቶችን ብዙ ሺ ተከታይ ባለን በ3ቱም የቴሌግራም ቻናሎቻችን ማስታወቂያ እንሰራለን፤ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ከመንግስትና ከግል ተቋማት የሚወጡ የስራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን በቻናላችን እናጋራለን፤ትኩስና ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እናጋራለን 0917171781/0918706464

اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.