cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethio French™

⚜ Bɪᴇɴᴠᴇɴᴜᴇ! (Wᴇʟᴄᴏᴍᴇ!) ⚜ ✅ የትም መሄድ ሳይጠበቅብዎ እዚሁ በነፃ ፈረንሳይኛ ይማሩ! 🇫🇷 🔰 ፈረንሳይኛ ቃላትን ወደ አማርኛ 🔰 የተለያዩ Quizኦች 🔰 የቃላቱን አጠራር በአምርኛ 🔰 አጋዥ ቪድዮዎች Cᴏɴᴛᴀᴄᴛ: @lameog

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
537
المشتركون
-424 ساعات
-117 أيام
-830 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

በዚህ መሠረት ትክክለኛው የቱ ነው? ___ Autriche. /In Austria /ኦስትሪያ ውስጥAnonymous voting
  • En
  • Au
  • Aux
0 votes
en 🆚au 🆚 aux -> ሶስቱም ከሃገራት ጋር "in" ወይም "ውስጥ" ለማለት እንጠቀማቸዋለን። ልዩነታቸው: ⚜️ en // ከfeminine (የሴት ፆታ ካላቸው) ሃገራት በፊት ይገባል። #ለምሳሌ: 🇨🇳 en Chine /ኦ ሺን/ -> In China (ቻይና ውስጥ) 🇫🇷 en France /ኦ ፍሆንስ/ -> In France (ፈረንሳይ ውስጥ) ⚜️ au // ከmasculine (የወንድ ፆታ ካላቸው) ሃገራት በፊት ይገባል። #ለምሳሌ: 🇵🇹 au portugal /ኡ ፖህቹጋል/ -> In Portugal (ፖርቹጋል ውስጥ) 🇯🇵 au Japon /ኡ ዣፖን/ -> In Japan (ጃፓን ውስጥ) ⚜️ aux // ከplural (ብዛት ያለው ስም ካላቸው) ሃገራት በፊት ይገባል። #ለምሳሌ: 🇺🇸 aux États-Unis /ኡዝ ኢታዙኒ/ -> In USA (አሜሪካ ውስጥ) ❗️በተጨማሪ፤ በvowel ሚጀምሩ ሃገራት plural ካልሆኑ በቀር (እንደ USA) en ነው ምንጠቀመው። #ለምሳሌ: 🇮🇹 en Italie /ኦን ኢተሊ/ -> In Italy (ጣልያን ውስጥ) 🇪🇹 en Ethiopie /ኦን አቶፒ/ -> In Ethiopia (ኢትዮጵያ ውስጥ) ✨ስለ ሃገራት ፆታ ማብራሪያ ከፈለጉ እዚህ ጋር ይጫኑ። @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
Vehicles in French ተሽከርካሪዎች በፈረንሳይኛ 🚗 la voiture /ላ ቮይቹ/ -> መኪና (car) 🚈 le train /ሎ ትሃ/ -> ባቡር (train) ✈️ l'avion /ልኣቪዮ/ -> አውሮፕላን (plane) 🛳 le bateau /ሎ በቶ/ -> መርከብ (ship) 🚕 le taxi /ሎ ታክሲ/ -> ታክሲ (taxi) 🚲 le vélo /ሎ ቬሎ/ -> ሳይክል (bicycle) 🎯 ምናልባት le, l' እና la ምን እንደሆኑ ለማታውቂ እዚህ ጋር ተጭናችሁ ሙሉ ማብራሪያ ማግኘት ትችላላችሁ። @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
👍 1
አቅጣጫዎች በፈረንሳይኛ: ⬆️ le nord /ሎ ኖህ/ - ሰሜን (The North) ➡️ l'est /ሌስት/ - ምስራቅ (The East) ⬇️ le sud /ሎ ስዩድ/ - ደቡብ (The South) ⬅️ l'ouest /ሉዌስት/ - ምዕራብ (The West) ➡️ la droite /ላ ድዋት/ - ቀኝ (The right) ⬅️ la gauche /ላ ጎሽ/ - ግራ (The left) ⬆️ en haut /ኦሁ/ - ወደላይ (up) ⬇️ en bas /ኦንባ/ - ወደታች (down) @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
De/D' in FrenchDe/D' በፈረንሣይኛ ውስጥ "of/የ..." ወይም "from/ከ..." ለማለት ወይም አንድ ነገር ከምን እንደተሰራ ለመናገር ነው ሚጠቅመው። ✅ De እና D' ሚለያዩት d' በአናባቢ (vowel) ከሚጀምሩ ስሞች በፊት ይገባል ሌላው ተመሳሳይ ነው። ⚜️ De/d'ን እንደ "of /የ.../" 🔰C'est la voiture de John /ሴ ላ ቮይቹ ዶ ጆን/ -> ያ የጆን መኪና ነው 🔰C'est le café de Mary /ሴ ሎ ካፌ ዶ ማሂ/ -> ይሄ የማሪ ቡና ነው። ⚜️ De/d'ን እንደ "from/ከ..." 🔰il est de France. /ኢሌ ዶ ፍሆንስ/ -> እሱ ከፈረንሳይ ነው (የመጣው) 🔰elle est d'ici /ኤሌ ዶ ኢሲ/ -> እሷ ከዚሁ ናት ⚜️ De/d' አንድ ነገር ከምን እንደተሰራ ለመናገር። 🔰Ballon d'or /ባሉን ዶህ/ -> ወርቃማ ኳስ 🔰Jus de mangue /ዡ ዶ ሞንጌ/ -> የማንጎ ጁስ @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
Adjectives in French ዋና ዋና የፈረንሳይኛ ቅፅሎች ⚜️ አብዛኞቹ የፈረንሣይኛ ቅፅሎች የፆታ ልዩነት አላቸው፤ ነገር ግን በቀላሉ በ'-e' የሚያልቁ ቅፅሎች ለfeminine ስሞች ነው ምንጠቀማቸው። #ለምሳሌ_ጥቂቶቹ: ✅ Small (ትንሽ): - Petit /ፖቲ/: ለወንድ - Petite /ፖቲት/: ለሴት ✅ Big/tall (ትልቅ/ረጅም) - Grand /ግሆን/: ለወንድ - Grande /ግሆንድ/: ለሴት ✅ Nice (ጥሩ) - Bon //: ለወንድ - Bonne /ቦን/: ለሴት ✅ Bad (መጥፎ) - Mauvais /ሙቬ/: ለወንድ - Mauvaise /ሙቬዝ/: ለሴት ✅ Beautiful/Handsome (ቆንጆ) - Beau //: ለወንድ - Belle /ቤል/: ለሴት ⚜️ አንዳንዶቹ ደሞ ለሁለቱም ፆታ ተመሳሳይ ናቸው። #ለምሳሌ_ጥቂቶቹ: ✅ Fast (ፈጣን) -> Rapide /ሃፒድ/: ለሁለቱም ፆታ ✅ Dirty (ቆሻሻ) -> Sale /ሰል/: ለሁለቱም ፆታ ✅ Rich (ሀብታም) -> Riche /ሂሽ/: ለሁለቱም ፆታ ✅ Poor (ደሃ) -> Pauvre /ፖቭህ/: ለሁለቱም ፆታ @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
⚜️ አንዳንድ ዋና ዋና ስሜቶችን ለመግለፅ በፈረንሳይኛ:Je suis content -> I'm happy (ተደስቻለሁ) ✅ Je suis triste -> I'm sad (አዝኛለሁ) ✅ Je suis fatigué -> I'm tired (ደክሞኛል) ✅ Je suis malade -> I'm sick (አሞኛል) ✅ Je suis ébahi -> I'm amazed (ተገርሜያለሁ) ✅ Je suis choqué -> I'm shocked (ደንግጫለሁ) ✅ J'ai peur -> I'm scared (ፈርቻለሁ) @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
🧑Le visage (the face) 👱‍♂ የፊታችን ክፍሎች በፈረንሳይኛ: ⚜️ Les yeux -> The eyes (አይን) ⚜️ Les oreilles -> The ears (ጆሮ) ⚜️ Le nez -> The nose (አፍንጫ) ⚜️ La bouche -> The mouth (አፍ) ⚜️ La joue -> The cheek (ጉንጭ) ⚜️ Le menton -> The chin (አገጭ) ⚜️ Le sourcil -> The eyebrow (ቅንድብ) ⚜️ Les cheveux -> The hair (ፀጉር) ⚜️ Le cou -> The neck (አንገት) ⚜️ Le front -> The forehead (ግንባር) @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
Ce 🆚 Cet 🆚 Cette 🆚 Ces ✅ አራቱም Demonstrative pronouns ናቸው፤ ማለትም "this/that" ወይም "ይሄ/ያ" ማለት ናቸው። ልዩነታቸው: ⚜ Ce እና Cet masculine ለሆኑ (የወንድ ፆታ ላላቸው) ስሞች ነው የምንጠቀማቸው። የሁለቱ ልዩነት: 🔰Ce /""/ በተናባቢ (consonant) ከሚጀምሩ masculine ስሞች በፊት ነው ሚገባው። #ለምሳሌ: - Ce garçon /this boy/ይሄ ልጅ - Ce taxi /that taxi/ያ ታክሲ 🔰Cet /"ሴት"/ በአናባቢ (vowel) ከሚጀምሩ masculine ስሞች በፊት ነው ሚገባው። #ለምሳሌ: - Cet homme /that man/ ያ ሰውዬ - Cet hôtel /this hotel /ይህ ሆቴል - Cet avion /that plane /ያ አውሮፕላን ⚜️ Cette /"ሴት"/ feminine ለሆኑ (የሴት ፆታ ላላቸው) ስሞች ነው የምንጠቀመው። -> ለfeminine ስሞች በvowel ጀመረ በconsonant ጀመረ ችግር አያመጣም ለሁለቱም cette መጠቀም ነው። #ለምሳሌ: - Cette maison /this house /ይህ ቤት - Cette femme /that woman /ያቺ ሴት - Cette eau /this water/ ይህ ውሃ ⚜️ Ces /""/ plural ለሆኑ (ብዛት ላላቸው) ስሞች ነው የምንጠቀመው። ፆታው አይወስንም። #ለምሳሌ: - Ces maisons /these houses /እነዚ ቤቶች - Ces femmes /those women /እነዛ ሴቶች - Ces avions /these planes /እነዚ አውሮፕላኖች @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
Objective pronouns in French (የተሳቢ ተውላጠ ስሞች በፈረንሳይኛ): ⚜️ me (m'): me (እኔን) Ex:- Tu me vois. - You see me /እኔን ታየኛለህ/ ⚜️ te (t'): you (አንተን/አንቺን) Ex:- Je t'aime. - I love you /አንቺን እወድሻለሁ/ ⚜️ le (l'): him (እሱን) Ex:- Je l'aime. - I love him /እሱን እወደዋለሁ/ ⚜️ la (l'): her (እሷን) Ex:- Je la vois. - I see her /እሷን አያታለሁ/ ⚜️ nous: us (እኛን) Ex:- Tu nous vois. - You see us /እኛን ታየናለህ/ ⚜️ vous: you (እርሶን) Ex:- Je vous vois. - I see you /እርሶን አይዎታለሁ/ ⚜️ les: them (እነሱን) Ex:- Je les vois. - I see them /እነሱን አያቸዋለሁ/ ❗️እንደምታዩት የፈረንሳይኛ ተሳቢ በስም እና በግስ መሃል ነው ሚገባው (እንደ አማርኛ ሁሉ)። ❗️ሌላው (') ምንጠቀመው ቀጥሎ ያለው ግስ በአናባቢ ድምፅ ሲጀምር ነው። @EthioFrenchTM @EthioFrenchTM
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.