cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ግጥም ለኛ✍️

➥ CRATER፦ @kaleab_abi

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
225
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-37 أيام
-1230 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
አዲስ የተከፈተ ስለ ሊቨርፑል ፈጣን መረጃዎችን የሚያቀርብ ቻናል ለእናንተ
إظهار الكل...
ONLEY Liverpool
Here we go💥
ልስምሽ ዞር ስል💋💋                                      ልስምሽ ዞር ስል                  የሳትኩሽ አሳሳት        አልረሳ ብሎኝ ፊቴ ላይ ታትሟል                ልክ እንደ ንቅሳት          ድጋሜ አስበላኝ ይሄ ሞኝ ከንፈሬ   ይኸው ሳማት ስለው ይላል ነው አፍሬ           ምኔ ነው ያስጠላሽ ፊቴ ነው አይኔ👁           ወይ ደግሞ ሊስምሽ ያሰበው                  ያ ሞኙ ከንፈሬ   ምኔን ጠልተሽው ነው እንደዛ ሽል ያልሽኝ                   ያ ሞኙ ከንፈሬን💋           ልክ እንደ አበባ ያገረጣሽብኝ🌺 ቆይ ምን አስበሽ ነው እንደዛ ሽል ያልሽኝ።
إظهار الكل...
ጠብቄሽ ነበረ! (ደበበ ሰይፉ) መንፈሴን አንጽቼ                ገላዬን አጥርቼ አበባ አሳብቤ                አዱኛ ሰብስቤ                ጠብቄሽ ነበረ፤ ብትቀሪ ጊዜ፣                መንፈሴን አሳደፍኩ                ገላዬን አጎደፍኩ አበባው ደረቀ                 አዱኛው አለቀ ብትቀሪ ጊዜ፣                 የጣልኩብሽ ተሥፋ                 እኔን ይዞ ጠፋ። 𝕥𝕒𝕘𝕖𝕝 𝕤𝕖𝕪𝕗𝕦
إظهار الكل...
አንቺዬ እንደው የግድ ግዴን  የግዴን አቃተትኩ በተረታ አልረታም ፍልሚያ እዬዋተትኩ ከእኔ ስገዳደር እንደው በደመነፍስ በመሀል ደክሜ  ሽንፈት ሆኜ ልፈርስ ልረታ ነው መሰል  ድካም ድካም አለኝ ያዘልኩት ማዘሎ  የግደን አዛለኝ የግዴን በረታሁ የግዴን ተረታሁ በጀርባዬ አዝዬ  እያልኩ እሽሩሩ ለልብ ትርታ  አንቺ ሆነሽ ግብሩ ላንድ አፍታ             እንድመታ ጥቂትን ለመኖር  ሰከንድ ለመተንፈስ ወኔው እዬከዳኝ  ባንቺ ስልፈሰፈስ መኖር ጣዕም ሲያጣ ህይወት ስትገረጣ የግድ መረታቱ  የግድ መበርታቱ እጣዬ ሆነና  ታምሜ ኖርኩ እቱ ስታመም ኖሬ አለሁ ስበረታም ኖሬ አለሁ እንደው የግድ ግዴን መኖርን ሳልኖረው  አለመኖርን ኖርኩ አዝዬ መውደዴን 💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕💕 ✍️кαℓєαв g.
إظهار الكل...
❤️❤️❤️አፉ በይኝ አቦ❤️❤️❤️ እባክሽ የኔ ዓለም የኔ ብሶት ሠሚ የልቤ ትርታ የህመሜ አካሚ። የጭንቄ ተካፋይ የእኔነት ጓደኛ ሚስጥር ጠባቂዬ አድማጭ እውነተኛ በዘመን በግዜ ያልሆንሽ ወረተኛ። ሁሉን ሠው አድማቂ ሁሉን ብሶት ሠሚ ሁሉን እንባ አባሽ ከቦታው ስጠፋ እውነት ግን ምን አሰብሽ። አፉ በይኝ አቦ          ንገሪኝ አለሜ ያኔ ትዝ ይልሻል ከደጃፍሽ ቁሜ። ትዝ አለኝ የፊቴ ፈገግታ የልቤ ትርታ የመንፈሴ እርካታ ታስታውሽዋለሽ ያንን ሁሉ ደስታ። አፉ በይኝ አቦ ረሰቼሽ ሳይሆን ከቦታው ብጠፋ ይቅርታ የኔ ዓለም ባንች አልቆርጥም ተስፋ። አለም አሸንፋኝ ከስርሽ ባልኖርም መንገዴ ተሰልቦ ከጎንሽ ባልቆምም በኑሮ ጦርነት ካንችጋ ባላድርም ስትመጭ በናፍቆት ባልቀበልሽም ስትሔጂ በእንባ ቁሜ ባልሼኝሽም ማጣት ማገኜቴን ማዘን  መከፋቴን ሁሉን ባልነግርሽም በጣም ናፍቀሽኛል እውነት ነው አልዋሽም። አፉ በይኝ አቦ እኔ ከንቱ ሠው ነኝ ውለታ ምረሳ በትዝታ ብሶት ያለፈ እማወሳ። የኔ ዓለም የኔዋ የሌሊት መብራቴ መተንፈሻ ዋሴ ሰሚ የጭንቀቴ መርሻዬ የምልሽ የብቼኝነቴ አፉ በይኝ አቦ ልለምንሽ እቴ። የህመሜን ልኬት የማጣቴን ግነት የሀዘኔን ክፋት የጭንቀቴን ስፋት የሠው ማጣት ስሜት ሁሉን የምታውቂ የልቤን ሰቆቃ ሰው የመራብ ደዌ የበሽታን ሲቃ አፉ በይኝ አቦ እባክሽ ጨረቃ። ✍𝕜𝕒𝕝𝕖𝕒𝕓 𝕘.𝕤𝕖𝕝𝕒𝕤𝕤𝕚𝕖
إظهار الكل...
2👍 1🔥 1👏 1
የዐይን ፍቅር ጠዋቱን ማልጄ፣ ነቃሁ ያለወትሮው በንጋቷ ጀምበር፣ ዕለቱ ደማቅ ነው ልብሴን ለባብሼ፣ ጫማ ተጫምቼ ወጣሁኝ ከቤቴ፣ ኑሮዬን አስልቼ። መንገዴን ጀምሬ፣ ብዙ ሳልጓዘው አየሁኝ ወጣት ልጅ፣ ተላለፍን ምነው ወግና ስርዓቱን፣ በገሀድ ዘንግቼ አንገቴን አዞርኩኝ፣ ለማየት አጥርቼ። አቤት አፈጣጠር፣ እያልኩ ስገረም የፈጣሪ ጥበብ፣ ብዬ አግራሞት ስደግም እንዲህ በማይባል፣ በብርሀን ፍጥነት ልቤን የወሰደው፣ ሳላስበው ድንገት። እሱን እያየሁ፣ መዋሉ ለምዶብኝ እመላለሳለሁ፣ ፍቅሩ አይሎብኝ። አሁን ጥሩ ሂዷል፣ ወቅቱ ደስ ያሰኛል ዐይን ለዐይን ተግባብተናል ጥሩም ተሰምቶናል አንድ መንገድ ተራምደናል እሱም ልክ እንደኔ፣ ፍቅር ነካክቶታል። ያወጋኛል እሰማለሁ፣ በጨዋታው እዝናናለሁ ቃል ባይወጣኝም፣ ፍቅሬን በድርጊት ገልጬለታለሁ እሱም ቃል አውጥቶ፣ ምንም ባያሰማኝ ፍቅር እንዳለበት፣ ዐይኑ መች ደበቀኝ። በሴትነት ወጉ፣ እራሴን ከብቤ ፍቅሬን እዴት ልግለፅ፣ አውጥቼ ከልቤ ደሞም የሚያምረው፣ ቢሆን ደስ የሚለው በእሱ ነበር እንጂ፣ ጥያቄ ሚቀርበው። ህይወት በመንገዷ፣ ድንገት አገናኝታ ትላንት የነበረ፣ የዐይን ፍቅር ደስታ ሳይገለፅ በቃል፣ ድንገት አራርቃ ይኸው ነጠለችን፣ ፍቅር ሳያበቃ። ጊዜው ምን ቢረዝም፣ ዓመታት ቢነጉዱ ሌላ ህይወት ቢጀምር፣ ቢቀየር መንገዱ አላስተወኝ ዛሬም፣ እሱን ከመውደዱ። ያላለቅ ፍቅር፣ በብዙ ያደክማል በዐይን መራራቁ፣ መች ከልብ ያርቃል በባዶ ተስፋ ውስጥ፣ ናፍቆት እያመመኝ አለሁልህ ዛሬም፣ ፍቅር እያሞኘኝ።                    
إظهار الكل...
👍 2 2🔥 1
ሰው ዓለም ሰዋሰው አልሸሽ፣ ከእምነት እዳ ለአንቺ ልብ፣ እንግዳ እኔ አለሁ፣ ፍቅር አዳም አንቺ አለሽ፣ ሰው ዓለም አንቺ አለሽ ሰዋሰው፣ ኖረን እንለፈው ፣ሞተን ከምንቀምሰው አወይ የሞት ቀንጃ ፣የመሳሳብ ጸሩ እንዴት ከቅጽር አምባሽ፣ ድፍድፍ ሃኬት ይስሩ? ዙሪ ከድጥ መንገድ፣ ከኩርንችት ገላ መውደዴን ተከተይ፣ እንዋል ከእረፍት ባላ ሰው ዓለም ሰዋሰው፣ ከምኔው ተንፍሶ፣ ከምኔው ወረሰው? ከምኔው ደልድሎ፣ ከምኔው አረሰው? ሰው ዓለም ሰዋሰው፣ የልብሽን ሙዳይ፣ በሃዘን አመሰው። ሰው ዓለም ከጉበኔ ቆሜ፣ በአመሻሽ ብዥታ በዓይኔ ስንቀዋለል፣ አንድ የጊዜ አውታታ አለፍሽ አንቺም ለካ፣ መቃኔን ተራምደሽ ከተምሽ ወደ ነገ፣ ዛሬን ደጄ እረግጠሽ ምን ይሉታል ታዲያ፣ ምንድን የምን መላ? መሸሽ ከአንቺ ሲሆን፣ ማሰብ ከአንቺ ሌላ ምን መላ ምን ባላ፣ የምን አንዳች ስቁረት? ከመውደድ ተሰዶ፣ መውደድ ሊስቡበት አቤት ዓለም ዘበት፣ ውጪ ከሃዘን ውርስ፣ ዝመች ከእምባ ጣቢያ ያለፈው ጉዞ ነው ፣ የነገ ዓለም ምንጣፍ፣ የመክሰም ቡቃያ ቢያድልሽ ዝንጋኤ፣ ቢቸርሽ ሚስጥሩ ሞት የሚጠብቀው፣ ሞት ነበር መኸሩ ትንሳኤ የሚያሻ ፣ህይወት ነበር ግብሩ መውደድን የሚያልም፣ ፍቅር ነበር ዝክሩ። ሰው ዓለም ሰዋሰው ትንሳኤን ለምኖ፣ ሞትን ግን ከሰሰው ፍቅርን ጠይቆ፣ ተንኮልን ለበሰው ሰው ዓለም አንቺስ የጊዜ እጣ፣ የመውደድ ነጭ ምንጣፍ በሃዘን ተገምደሽ ፣ ጉበኔን ገርምመሽ ፣ተራምደሽው ማለፍ ምን ይሉት ፈሊጥ ነው፣ የምን ክብር ካባ? አሳድዶ መሸሹ፣ ሰው አፍሮ ሊገባ ሰው ደፍሮ፣ ሰው አፍሮ አላፊን ቆስቁሶ፣ ከአላፊ ጋር መክሮ ሰው ነፍሮ፣ ሰው አፍሮ ላይቦጭቀው ሞቱን፣ ላይጎምድ የፍቅር ስር አንቺን ከእኔ ነጥሎ፣ ሊከተብሽ ከእሱ እግር ይስባል በክንዱ፣ ይግጣል በጥፍሩ የአንቺም አምኖ መትመም፣ ምን ይሆን ምስጢሩ? ሰው ዓለም ተመለሽ፣ አልፏል የስጋ አባት በመጓዙ አይደለ፣ ያንቺስ እንዲህ መምጣት የለም ልብ መሳይ፣ አይፈጠር አቻ አይደጎስ ድርሳን፣ ገድል ለአንቺ ብቻ ነይ እኔን ተመልከች፣ እይኝ ከጉበኔ፣ ቆሜ ከመቃኑ ስሚኝ ሹክሹክታዬን ፣ ለቃል ነው ዘመኑ እይኝ እንደ ጊዜ፣ መስይኝ እንደ ሞት ለብቻ ብንኖርም፣ ነገአችን ያው መሬት ዘርጊልኝ ቀይ ግምጃ፣ መውደዴን ነው እንጂ፣ መኖሪንስ እንጃ መከተሌን እንጂ ፣መድረሴንስ እንጃ እናልሽ ሰዋሰው፣ መኖርን ሞግተን፣ ሞትንም ላንከስሰው ሰው መሆንን ኖረን፣ ፍቅር እንቅመሰው በእምነት አንዳች ገድል፣ ፍጡርን ላንወርሰው እናማ ሰዋሰው፣ ነይ ገድልሽን ጻፊ፣ እኔ ልደጉሰው የሰው ልጅ ሰዋሰው! ✍️✍️ kaleab g.
إظهار الكل...
ሚጣ... በከንፈሬ የጣልሽውን ሻንጣ ያክል ስደካክም፣ ለንቦጬን ያስጥለኛል አሳሳምሽን ስገመግም፣ ደሞ ነሽ ሚጢጥዬ ለመሳምም አትበቂ....? ደሞ አዛኝ ትልቅዬ መጠላት ላይ አትነቂ...? ልጅነትሽ ብዙ ሰበዝ ወተትሽ አይገፋ፣ ስታለቅሽ ጡት ጠቢ አራስ ልጅን የሚያለፋ፣ አሳሳምሽ ማይታወቅ ሙቀት ይዞ መቀዛቀዝ፣ ወንድነቴን ይፈትናል ካንቺ ጋራ ስወዛወዝ፣ ሲታሰብ ውሎ ያድራል ታዛ ቤቴን ከቃኜሁት! ከሳሎኑም ከእርሻውም የጡት ልብስሽን አገኜሁት ?! ጥላ ይዘሽ ዝናብ ሳለ መመታቱን የምትወጂ፣ አሳሳሜን እዬረሳሽ ንክሻዬን የምትለምጂ፣ ልጅነትሽ ያስረጀኛል ወጣትነቴን ተርም አልፎት፣ ንፍስ ልብሽ እንደ አቧራ ዕድሜዬን ባንዴ ልፎት፣ ደሞም ይገርመኛል😏 አንቺ አይተው ሲጎመጁ በየካፌው ስንሰዬም፣ በምን ልንገር አፍሽ ምላጭ ሲቅለሰለሱ አልቀዬም፣ አንቺን ከእኔ የወሰደ ውለታ ያህል ይመስለኛል ደሞ ሳስብ አካሄዷን ፣ የትም አድረሽ ስትመጭ አቅፍሻለሁ አውቄ እንኳን፣ ጫማሽ ቁጥሩ ሰፊ ታኮ አለው ሴንቲው ብዙ፣ ማጠሬን ለመናገር ለማንጋጠጥ መጋበዙ፣ አንዳንዴ...ፍቅር ሚሉት ከልጅ ሲሆን ያስፈርጃል፣ ሚጥሚጣ በመብያ ዕድሜ ከሚጣ ጋር ያጃጅላል! ✍️✍️𝔨𝔞𝔩𝔢𝔞𝔟 𝔤.
إظهار الكل...
አምላክን አመስግን         በምግብ እጦት ቢገረጣ ፊትህ ልክ እንደአውሬ ሰው ሁሉ ቢሸሽህ ቤተሰቤ ያልከው እንደባዳ ቢያይ የልብ ጓደኛ ቢሆንም ገዳይ የለበስከው ልብስህ ከብርድ ባያድንም የምቆጥረው ገንዘብ ከኪስህ ባይኖርም ምትመኘው ነገር ሆኖቢቀር ቅዠት ያፈቀርካት ላንተ ክብር ባይኖራት ሞላውትም ያልከው ሁሌም ቢጎልብ በጎ ያልከው ነገር ክፋ ቢመዝብ እጅ ስትዘረጋ ሰጪ ባታገኝም የሰጠከው ሁሉ ምላሽ ባይሰጥህም ጊዜ ያንተ ጠላት ሆኖ ቢዋጋህ አምላክ ነው ብለህ አትዘን በድልህ ይቺን እንድታነብ እድል የሰጠህን ጎንበስ በልና አምላክን አመስግን               ተ መ ስ ገ ን
إظهار الكل...
👍 1
Repost from N/a
📌ይነበብ ይነበብ ! ከ 200መቶ ሺ በላይ ተከታይ ባለው ቻናል ላይ ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ……… 🎖ምን ማሰተዋወቅ ይፈልጋሉ ? •➜ቻናል 🗞 •➜የኮስሞቲክስ እቃዎች 💄💅 •➜ድርጅት💼 •➜Events 💃🕺 •➜Consultancy🔅 •➜የልብስ እና የጫማ ማስታወቂያዎች👗👠 ➜እና ሌሎችም .. 🫴 ሁሉንም በተመጣጣኝ ዋጋ ማስተዋወቅ ምትፈልጉ 📥 ✅በሳምንት 1500 ✅በሁለት ሳምንት 2500 ✅በወር ደሞ 5500
@BobbyAaron10 ያናግሩን !   
ከሁለት መቶሺ በላይ ለሆኑ ኢትዮጲያውያን ምርት እና አገልግሎቶን በማስተዋወቅ ትርፉማ ይሁኑ !
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.