cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

🙏የተዋህዶ ልጆች🙏

በስምአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን። 🙏🙏🙏 (የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው።) እግዚአብሔር እንዲ ይላል። ''በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ።''🙏🙏🙏 ሀሳብ አስተያየት ካሎት 👉👉👉 @therapist_19

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
250
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-57 أيام
-930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

00:52
Video unavailableShow in Telegram
አባታችን እግዚአብሔር ያክብርልን 🙏❤️🙏 #ሀይማኖት #የሚገለባበጥ #አይደለም ሀይማኖት አይገለባበጥም ❤️❤️ @kettegawa_ewnet
إظهار الكل...
1.62 MB
ናዛዚትነ እም ኀዘን ወኃይለ ውርዙትነ እም ርሳን፤ በማኅጸንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን፤                                     ኦ! ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን፤ በጊዜ ጸሎት ወእጣን ወበጊዜ ቅዱስ ቁርባን፤ለናዝዞትነ ንዒ ኀበ ዝ መካን ።                   🌷ልደታ ለማርያም ወሩን ባርኪልን ሁላችሁን ትጠብቅ🌹
إظهار الكل...
#መድኃኒዓለም_አዳነን @AndEmnet @igziyabhern
إظهار الكل...
መድኃኔዓለም_አዳነን(128k).mp33.54 MB
#መጽሐፍ_ቅዱስ በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡ አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው” ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡ ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡ ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡ (ከምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ) (በድጋሚ የተፖሰተ)
إظهار الكل...
#መርቆዎሬዎስ መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ ፪ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ #አዝ... ባስልዮስ ጎርጎርዮስ ሰምሯል ልመናችሁ ስህሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ እናተን የረዳ መቶ በፈረስ ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ #አዝ... ኦላኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል ብሎ መሰከረ መርቆሬዎስ ሀያል ገፀ ከለባቱ ባህሪ ቀየሩ እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ #አዝ... ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ መርቆሬዎስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ #አዝ... ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዮስ ወደደ ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ ስሙ ተሰየመ ከሰማዕታት ጋር #አዝ... አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር መፍቀሬ አብ ካለ ያፕሎ ጳድር ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ ወይኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ #አዝ... #ዘማሪ፦ ዲ/ን ታድዮስ ግርማ @AndEmnet
إظهار الكل...
መርቆርዮስ የችግሬ ደራሽ.mp36.14 MB
ፒያሳ ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ⛪
إظهار الكل...
❤️#አየኋት_ባይኔ_አሻግሬ❤️ አየኋት ባይኔ አሻግሬ የያሬድን ውብ ዝማሬ ተቀኘው እንደ አባቶቼ እጄን ለክብሯ ዘርገቼ/2/ 🌺 #አዝ....... 🌺 ድካም እና እንቅልፍ እንደምን ሊረታኝ ድንጋይ ብንተራስ ፍቅርሽ አያስተኛኝ አይኔ ቢከደን አለሽ በምናቤ አልተከለልሽም ነግሰሻል በልቤ/2/ 🌺 #አዝ....... 🌺 መረማመጃ የሎዛ መሠላል የዜማ ቤቴ የመቅደስ ጽናጽል የሰማይ ንጉስ በበላይሽ አለ ድንኳን አድርጎ አንቺን የተከለ/2/ 🌺 #አዝ....... 🌺 ስምሽ በሁሉ ስለተወደደ ድንግል ለክብርሽ ፍጥረት አረገደ ካላመኑት ዘንድ ቢሆንም ዝምታ ከገብርኤል ነው የስምሽ ሠላምታ/2/ 🌺 #አዝ....... 🌺 ሳደርስ ውዳሴ መፃፋን ገልጬ ተመለከትኩሽ አይኔ እምባ እየረጨ በገናን ዳዊት መሰንቆንም እዝራ ሰጡኝ ላነሳሽ በክብሩ ተራራ/2/ 👉ለዘማሪ ዲ/ን ዕዝራ ሀ/ሚካኤል ዝማሬ መላእክት ያሰማልን ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲዳረስ 👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ 👉@enatachinmaryam 👉@enatachinmaryam 👉@enatachinmaryam
إظهار الكل...
ማርያምን_አየዋት_በዓይኔ_አሻግሬ_ዲ_ዕዝራ_jXeGDDIAZjI_599.m4a9.46 KB
Photo unavailableShow in Telegram
ህዳር 21 አክሱም ጽዮን ማርያም ☞︎︎︎ ኅዳር ጽዮን በአክሱም አክሱም ማርያም ጽዮን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ መሠረታቸው ስትሆን ከተማዋም የኢትዮጵያ ሥልጣኔ መነሻ ናት፡፡ አክሱም በሕገ ልቡና የጸናች፣ ሕገ ኦሪትን የፈጸመች፣ በሕገ ወንጌል ያመነች ናት፡፡ ህዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል ነው ብለን በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦ ☞︎︎︎ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤ ☞︎︎︎ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤ ☞︎︎︎ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ለማሰብ፤ ☞︎︎︎ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤ ☞︎︎︎ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ ☞︎︎︎ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን። ከእመቤታችን ረድኤትና በረከት ይክፈለን @eotcy         
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
✝️🌷           ገብርኤል አባቴ 🙏❤️          ------------------------ አብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ይጠብቃችሁ ያሠባችሁትን የልባችሁን መሻት ይፈፅምላችሁ
إظهار الكل...
መልካም የፆም ጊዜ ይሁንልን🙏 የበረከት ያድርግልን ❤️ ፆመ ነቢያት
إظهار الكل...