cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ›› ት.ኢሳ 58÷3 መታረም ያለበትን ወይም አስተያየቶች @Ortodoxawi04 በዚህ ይንገሩኝ::

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
512
المشتركون
-224 ساعات
+67 أيام
+3930 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
ፕትርክናን እምቢኝ አሉ 🤔 ዘንድሮ ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት አባቶች እየተሰማ ያለው ዜና በአግራሞት አፋችንን እያስከፈተ መቀጠሉን ቀጥሏል ብጹዕ አቡነ ኒኮሎዝ ይባላሉ የፕሎፕዲቭ ሊቀ ጳጳስ ናቸው ሊቀ ጳጳሱ የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ዕረፍትን ተከትሎ ለቀጣይ ፓትርያርክነት በእጩነት ቢቀርቡም እርሳቸው ግን #እምቢኝ ብለዋል ከፕትርክናው እጩነትም ራሳቸውን አግለዋል። አሉ የኛዎቹ ቆብ በጉልበት የሚቀሙ! @ortodoxtewahedo
إظهار الكل...
#ግንቦት_27 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮሐንስ አረፈ፣ የማርያና የማርታ ወንድም #ጻድቅ_አልዓዛር አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሊቀ_ጳጳሳት_አባ_ዮሐንስ ግንቦት ሃያ ሰባት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ደግ የተማረም ነበር። ከልጅነቱም ጀምሮ በገድል ተጠምዶ የሚኖር ነበር። ከዚህም በኋላ በዋሻ ውስጥ ራሱን እሥረኛ አደረገ። የትሩፋቱና የዕውቀቱም ዜና በተሰማ ጊዜ በእስክንድርያ አገር ላይ ይዘው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ እግዚአብሔርም በዘመኑ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን አጸና። ይህ አባት በተሾመበት ወራት ደግ ምእመን አንስጣስዮስ የሚባል ንጉሥ ነበር። በአንጾኪያም የከበረ አባት አባ ሳዊሮስ ነበረ እርሱም ወደ አባ ዮሐንስ ስለ ቀናች ሃይማኖት እንዲህ ብሎ በመልእክቱ ውስጥ ጻፈ። ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶው በኋላ እንደ አባቶቻችን እንደ አባ ድሜጥሮስና እንደ አባ ዲዮስቆሮስ እምነት ያለ መቀላቀል ያለ መለወጥ ያለ መለያየትና ያለ መጨመር አንዲት ባሕርይ አለችው። አባ ዮሐንስም መልእክቱን ተቀበለው ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ተለያይተው የነበሩ ሕዋሳትም ተመልሰው አንድ ስለ ሆኑ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት። ከዚህም በኋላ ለመልእክቱ መልስ አባ ዮሐንስ ለአባ ሳዊሮስ እንዲህ ብሎ ጻፈለት። ይኸውም ስለ መለኮትና ትስብእት የአንድ ባሕርይ ህልውና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ያለ መለያየት ያለ መቀላቀልና ያለ መለወጥ ሁለት ያይደለ የሰውን ባሕርይ ከመለኮቱ ባሕርይ ጋራ አንድ አድርጎ በመዋሐድ ሰው ስለ መሆኑ። ጌታችንንም የሚከፋፍሉትን ወይም ተጨመረበት የሚሉትን ወይም ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ የሞተው ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚሉትን በመለኮቱ ባሕርይ መከራ ተቀበለ የሚሉትን አወገዘ። የቀናች ሃይማኖትስ ይቺ ናት እግዚአብሔር ከእኛ በነሣው ሥጋ ስለ እኛ መከራ እንደ ተቀበለ እናውቃለን እኮን። ይቺም የሚጓዝባት የማይሳሳትባትና የማይደናቀፍባት የሕይወት መንገድ ናት አለ። አባ ሳዊሮስም ይቺን የአባ ዮሐንስን መልእክት በአነበባት ጊዜ በመልካም አቀባበል ተቀበላት። በአንጾኪያ አገርም ሰበከባት ስለ ቀናች ሃይማኖትም በመካከላቸው ሰላም ፍቅርና ስምምነት ሆነ። ይህም አባት ሕዝቡን እያስተማረ ዐሥራ አንድ ዓመት ኑሮ ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ጻድቅ_አልዓዛር በዚችም ዕለት የማርያና የማርታ ወንድም ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኃኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ። አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ በሰላም በፍቅር አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት_27)
إظهار الكل...
#የምስጥሬ_ሚስጥረኛ ሰው ሆኜ ይህንን አደርጋለሁ ብዬ ማላስበውን በደል ፈፅሜያለሁ።ምናልባት ሰው ቢሰማው በአደባባይ ሞት ይፈርድብኝ ይሆናል አልያም የበደልኩት ሰው ቃታ ስቦ ግንባሬን ይበትነዋል።ብቻ ግን ሰሞኑን ከራሴ ጋር እያወራሁ እድሜ ልኬን የሚረብሸኝን ሀጥያቴን ዘርዝሬ ንሰሐ ለመግባት ወስኜ ከከተማ ወጣ ወዳለ ገዳም አመራሁ።አንዳንድ ተሸክመን የኖርናቸው በደሎቻችን ህይወታችንን ተጭነውት ህመም ሲሆኑብን ይከርማሉ ምናልባት ከዚ ህመም ለመገላገል ይሁን ከፈጣሪዬ ለመታረቅ ባላውቅም በድኔን እየጎተትኩት ገዳም ገባሁ የአከባቢው ፀጥታ ይጨንቃል ለመንፈሳዊነት የቀረበ ማንነት ስለሌለኝ የማየው ነገር ሁሉ አዲስ ሆኖብኛል በዛላይ ነብሴ ተጨንቃለች ፍርሀት አከላቴን ወሮታል ገና ሳላወራው ጫን ጫን ያለኝ ስናገረው ምን እንደምሆን እያሰብኩ መጠለያው ስር አረፍ አልኩኝ።ግቢ ውስጥ ሰው የሚባል አይታይም።ለየቱ ካህን ልናገረው ነው?ቢቀርብኝስ? ደሞስ አምኜው የነገርኩት ቄስ ሚስጥሬን ቢዘራልኝ የማን ያለህ ልል ነው? ከራሴ ጋር እየታገልኩ ለመውጣት ስነሳ ግቢ ውስጥ ጀሪካን ተሸክሞ የሚጣደፍ ወጣት ወደ ቤተልሄሙ ጀርባ እልፍ ሲል አየሁት።ወደጓሮ ማለፉ ስለገባኝ የመውጣት ሀሳቤን ትቼ ተከተልኩት።ውስጤ ፈርቷል ግን ደሞ እግሬ ወደወጣቱ ይራመዳል ልብሱን ከሳፋ ውስጥ አለቅልቆ ቀና ሲል አጠገቡ ደርሻለሁ ሰላም ወንድሜ እግዜር ይመስገን(ቀና ብሎ ግራ በመጋባት እያየኝ እዚህ የመጣሁት ካህን ፈልጌ ንሰሐ ለመግባት ነበር በዚህ ሰአት ካህናት የት ይገኛሉ ብለህ በጠዋት አትመጣም ነበር? አይ በቃ እሺ ተወው ሌላ ቀን እመለሳለሁ.. ሌላ ትርፍ ቀን አለክ ማለት ነው?ቆይ ነገ ራሱ መቼ ነው? ማለት? አይ እንደው እኛ ሰወች ለነገ ቀጠሮ ስንሰጥ ነገ ለመኖራችን እርግጠኛ ስንሆን ይደንቀኛል ነገኮ ላይኖርም ይችላል።በኛ ቁጥጥር ስር ያለችው አሁን ናት ነገ ብንል እንኳ እግዜር ቢፈቅድ የምትለው የተስፋ ቃል ልትኖር ይገባል። እሺ እግዜር ቢፈቅድ ነገ መጣለሁ ጥሩ ነው ወዳጄ ታድያ ካላስቸገርኩህ አንድ ጥያቄም ልጨምራ? ችግር የለውም አሁን ስትመጣ የወጣከውን ተራራ በዚህ ጀሪካን ሙሉ ውሀ ተሸክመህ ብትወጣና እጅግ ደክሞህ ተመልሰህ ይዘከው ውረድ ብትባል እሺ ትላለህ? አረ በፍፁም..በምን እዳዬ ወንድሜ?ተራራውን እያወቅከው? ታድያ የከበደክን የሀጥያት ሸክም በንሰሐ ለማራገፍ መጥተህ እንደገና ሀጥያትክን ተሸክመከው በመመለስ ለምን ትደክማለህ? እሱማ ቄስ የለም አልከኛ እና ምን ማድረግ አለብኝ? ንሰሐኮ አምነህበት ፈልገህ ወስነህ ለመናዘዝ የምትመጣው እንጂ እያመነታህ እየቸኮልክ ትዕግስት በማጣት የምታደርገው አደለም። ሸክም ከብዶህ ከመጣህ ትንሽ ታግሰህ መጠበቅ አለብህ።እድሜክን የተሸከምከውን ለማራገፍ ትንሽ መጠበቅ ምን ኪሳራ አለው? አረ ምንም።እንደው ግን ቄስ እስካገኝ አንተ የጨነቀኝን ብታማክረኝ ምናለበት (አጠገቤ ያለው ሀውልት ላይ ቁጭ እያልኩ ችግር የለውም ግን መጀመርያ ለኔ ጀርባህን ስጠኝና ፊትህን ወደ ቤ/ክኑ አዙረህ የምትሻውን አውራ እኔም ልብሴን እያለቀለቅኩ ሰማካለሁ።ታድያ ስታወራ በዋናነት ለኔ ሳይሆን ለሚያይህ አምላክ እንደምትነግር አስብ እሺ..ከምን እንደምጀምር አላውቅም ግን እኔ መጥፎ ሰው ነኝ።ይህንን ሚስጥር ለማንም ነግሬ አላውቅም አሁን ግን ሁሉ ነገሬን እያስጨነቀኝ ጭራሽ ህመም እየሆነብኝ ነው። ከአመታት በፊት ነበር አዲስ አበባ ወንድሜ ጋ ለትምህርት ብዬ የመጣሁት።ባለትዳር እና የልጆች አባት ነው ሚስቱም ለኔ መልካም ሴት ስለነበረች በቆይታዬ እየተቀራረብን እንመጣ ጀመር።ወጣት ናት በዛላይ የቤት እመቤት።ብዙ ጊዜ ከቤት አትወጣም።ከትምህርቴ መልስ ከእሷጋ ስለምውል ቅርርባችን እየጨመረ ልፊያችን እየበረታ ሲመጣ ማንም በሌለበት ስጋዊ ፍላጎታችን ገፋፍቶን አብረን ተኛን።ያቺን ቀን የሠራኋት ሀጥያት በየቀኑ ሌሎች በደሎች እየጨመረች ከወንድሜ ሚስት ጋ ሀጥያቱን ገፋንበት። ተመርቄ ከዛ ቤት እስክመጣ የወንድሜን ሚስት ሳባልጋት ኖሬያለሁ።ይህንን ሁሉ እሱ ባያውቅም እኔ የሠራሁት ስራ እለት እለት እያሳመመኝ ሰላሜን ነሳኝ።ከተናገርኩት ትዳራቸው ይፈርሳል፤ወንድሜን አጣለሁ፤ዝም ብል ስራዬ እንቅልፍ ይነሳኛል በቃ አቅቶኛል.. (እንባዬ እየፈሰሰ የሰራሁትን ሀጥያት ሁሉ ለፍልፌ ፀጥ ስል ወጣቱ ሙሉ ጥቁር ቀሚስ ነጭ ጋቢ እና ቢጫ ቆቡን ደፍቶ መስቀሉን እንደያዘ ፊትለፊቴ ቆመ። እንባ በሞላው አይኔ እየታገልኩ እሱነቱን ለማረጋገጥ አይኔን በአይበሉባዬ ስጠራርግ ፈገግ ብሎ እያየኝ አይዞህ አትደንግጥ ካህን ባልሆን ቅድም በየዋህነት ሚስጥሬን ልንገርህ ስትል እሺ አልልክም ነበር።ስራ እየሠራሁ ስለነበር የአገልግሎት ልብሴን አውልቄ እንጂ ካህን ነኝ ያን ሁሉ የሞገትኩህ ንሰሐክን ከልብ ተረጋግተህ እንድታደርገው ነው።ማወቅ ያለብህ አንድ ነገር ቢኖር ምንም ሀጥያት ከእግዜር ምህረት አንፃር ኢምንት መሆኑን ነው ይህ ግን በእንባ የሆነ መፀፀት እና መመለስ ሲኖርበት ነው።አይደለም ንሰሐ ብለህ መጥተህ ለንሰሀ የተራመድካት ሳትቀር በአምላክ ፊት ዋጋ አላት።ደሞም''እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።''ሉቃ15፥7ይላል ወንጌል። ወጣቱ ካህን ከማስበው በላይ የረቀቀ ጥበቡን ተጠቅሞ ንሰሐዬን መቀበሉ ሳያንስ በየቀኑ ሊያስተምረኝ ቃል ገብቶልኝ ቀኖናውን ሰጥቶኝ በቀጠሮ ቀን እንድመለስ ተነጋግረን ቀሎኝ ገባሁ።በነጋታው የወንድሜ ልጅ ክርስትና ነው። እርግጥ ቀኖናዬን እስክጨርስ ላለመገኘት ብሞግተውም ብቸኛ ያለሁት እኔ ስለሆንኩ በጠዋት እቤቱ ደርሼ እንደገባሁ ንሰሀዬን የነገርኩት ካህን ሶፋ ላይ ከነቆቡ ቆጭ ብሎ አየሁት።መመለስ ፈለኩኝ ነገር ግን ሙሉ ቤተሰቡ አይቶኛል አማራጭ ስላልነበረኝ ካህኑን ተሳልሜ እየተደናበርኩ ቁጭ ስል የወንድሜ ሚስት ሌላኛውን ተአምር ነገረቺኝ አባ እኮ ወንድሜ ናቸው ኑሯቸው ገዳም ስለሆነ ማንም አያቃቸውም አሁን እራሱ በልመና ነው የመጡት ተዋወቁ.. (ስትለኝ ደንዝዤ ቀረሁ። ካህኑ ላይ ፍፁም መረጋጋት ይታያል እህታቸው ላይ ይህንን ሁሉ ደባ ፈፅሜ በንሰሀ ሚስጥሬን ዘክዝኬ ነግሬያቸዋለሁ።በቃ እግዜር ሊያዋርደኝ ነው?የምገባበት አጥቼ ስደናበር ካህኑ ብድግ ብለው ወደገዳም መመለስ እንዳለባቸው አስረድተው ተሰናብተው ሲወጡ ተከትዬ አስቆምኳቸው አባ ይቅር በሉኝ ሁሉንም በእግዚአብሔር ፊት ተናግሬያለሁ እባክዎ ሚስጥሬን.. ምን እያልክ ነው?ለመሆኑ ያኔ ምን አልከኝ? እንዴ ያንን ሁሉ ስናገር አልሰሙኝም ማለት ነው? ያኔምኮ ነግሬክ ነበር የሠራከውን ሀጥያት ካህን ፊት አውራው እንጂ የሚሰማውም የሚፈርደውም የሚስጥራችን ሚስጥረኛ እሱ ፈጣሪ ብቻ ነው።ያን ቀን አንተ ስትናዘዝ እኔ ቤቴ ውስጥ ልብሴን እየቀየርኩ ነበር ያወራከውን አልሰማሁትም።አንተ ግን እኔ እንደምሰማክ አድርገህ ለእግዚአብሔር እያለቀስክ ሁሉንም ነገር ስታወራ ከሩቁ አይቼሀለሁ።ዋናው ለባለቤቱ መናገርክ ነው እኔም እሱ እንደመራኝ በፀሎት ታግዤ ቀኖናህን ሰጠሁክ ስላንተ ምንም አልሰማሁም ይህ የሆነውም በምክንያት ይሆናል ስለዚህ አትደንግጥ ሚስጥርህን ሚያቀው አንድ ፈጣሪህ ነው አንተ ለሰው ሚስጥር ብለክ ሳታወራው አይቶካል ደፍረህ በመናዘዝክም ደሞ ይቅር ብሎካል።አሁን ተረጋጋ ሌላውን ስትመጣ እናወራለን ደና ሁን "የምስጥሬ ሚስጥረኛ"በአደባባይ ክጄው በምስጢር ማረኝ በምህረቱ ይጎብኘን! ✍️ቻቻ
إظهار الكل...
IMG_4258.MP433.21 MB
IMG_4257.MP428.65 MB
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_26_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²² ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና። ²³ እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን። ²⁴ በተስፋ ድነናልና፤ ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? ²⁵ የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን። ²⁶ እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ²⁷ ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። ²⁸ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ ³⁰ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። ³¹ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ይሁዳ 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤ ¹⁸ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና። ¹⁹ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው። ²⁰ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ²¹ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ። ²² አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥ ²³ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ። ²⁴ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው ²⁵ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ሐዋርያት 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፦ እንጃ ይህ ምን ይሆን? እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ። ²⁵ አንድ ሰውም መጥቶ፦ እነሆ፥ በወኅኒ ያኖራችኋቸው ሰዎች እየቆሙ ሕዝቡንም እያስተማሩ በመቅደስ ናቸው ብሎ አወራላቸው። ²⁶ በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና። ²⁷ አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው። ²⁸ ሊቀ ካህናቱም፦ በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ብሎ ጠየቃቸው። ²⁹ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_26_ቀን_የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ "ብፁዕ ብእሲ ዘእምኀቤከ ረድኤቱ እግዚኦ። ወዘይሔሊ በልቡ ዘበላዕሉ። ውስተ ቈላተ ብካይ ብሔር ኀበ ሠራዕኮሙ"። መዝ 83፥5-6። "በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘላለምም ያመሰግኑሃል። አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው። መዝ 83፥5-6። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ #ግንቦት_26_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇 ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ ዮሐንስ 14 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። ² በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ³ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ። ⁴ ወደምሄድበትም ታውቃላችሁ፥ መንገዱንም ታውቃላችሁ። ⁵ ቶማስም፦ ጌታ ሆይ፥ ወደምትሄድበት አናውቅም፤ እንዴትስ መንገዱን እናውቃለን? አለው። ⁶ ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። ⁷ እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው። ⁸ ፊልጶስ- ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው። ⁹ ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ? ¹⁰ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። ¹¹ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ። ¹² እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ ¹³ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️የ #ሚቀደሰው_ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ የዕረፍት በዓልና የአቡነ ሀብተ ማርያምና የአቡነ ኢየሱስ ሞዐ የልደት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
إظهار الكل...
1
✝ እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞ ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) 2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ) 3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
✞ ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
✝️ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን
::
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
✝ እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
✞ ግንቦት 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት) 2.ቅድስት አርሶንያ (የቅዱስ ቶማስ ተከታይ) 3.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
✞ ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 3.አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
✝️ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአገልጋዩ ቅዱስ ቶማስ ጸጋ በረከት ይክፈለን::
إظهار الكل...