ar
Feedback
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

الذهاب إلى القناة على Telegram

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.

إظهار المزيد
3 519
المشتركون
+424 ساعات
+157 أيام
+4430 أيام
أرشيف المشاركات
የመሪዎችና እረኞች ስልጠና በአዶላ ገናሌ ተካሄደ * * * * በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ አዘጋጅነት የአራት ቀን የመሪዎችና ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የመሪነት እና የእረኝነት ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል። በስልጠናውም ከ19 የሲኖዶሱ ሰበካዎ የመጡ ቁጥራቸው ከ1,100 በላይ ለሚሆኑ የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች፣ ቄሶችና ወንጌላውያን ስለጠናው የተሰጠ ሲሆን የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ እና ቄስ ወርቁ ኤባ አሁን ባለንበት አውድ ሊኖር ስለሚባው የመሪነት እና የእረኝነት አገልግሎት ዙሪያ በሰፊው አሰልጥነዋል። በተጨማሪም የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት በአዶላ ከተማ በሲኖዶሱ የእየተገነባ ያለውን ባለ አራት ብሎክ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል። - - - - - Leaders and pastors training was held at Adola Genale * * * * Organized by the Adola Genale synod, consecutive four day’s of training were given under the title of leadership and pastoral care. On the training, more than 1,100 participants containing Elders, Reverends, and Evangelists attended from 19 parishes of the synod. The Churches President, Rev Dr Yonas Yigezu, and Rev Worku Eba gave intensive training about what “leadership and pastoral care should looks” on the current context of today’s church. At the same time, the president visited the progress of the synods school building project at Adola City, which will contain four blocks.

“ቤተ ክርስቲያን ባሳለፍነው አመት 2.63% አማካይ እድገት በማስመዝገብ ጠቅላላ የአባላትዋ ቁጥር 11.38 ሚሊየን ደርሷል . . .”። ይህንን ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ተሾመ አመኑ ለ19ኛው ካውንስል አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው። * * * * የቤተ ክርስቲያኒቱ እስታትስቲካዊ መረጃዎች፣ የሲኖዶሶች የስራ ክንውን፣ በዋናው ጽሕፈት ቤት ደረጃ የተሰሩ ስራዎች፣ አስተዳደራዊና የፋይናንስ ጉዳዮች፤ የአገልግሎት መምሪያዎች ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች፣ የቦርዶችና የኮሚሲዮኖች እንቅስቃሴዎችና የስራ ክንውኖች በሰፊው የቀረበው ሪፖርት ካካተታቸው ጉዳዮች የሚጠቀሱ ሲሆኑ በተጨማሪም ቤተ ክርስቲያኒቱ በ2015 ያጋጠሟት ችግሮችና ካውንስሉ እንዲመክርባቸው እና ውሳኔ አንዲያስተላልፍባቸው የሚሹ ጉዳዮች ተካተውበታል። በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ከፍተኛ የወንጌል ማዳረስ ስራዎች መሰራታቸው፣ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት በዲግሪ ፕሮግራም መሰጠት መጀመሩ፣ የሴቶች የሰላም ግንባታና ግጭት አፈታት ኔትወርክ መቋቋሙ፣ የፋይናስና አቅም ማጎልበቻ ስራዎች ተጠናክረ መቀጠላቸው፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ የጡረታ ፕላን ለታቀፉ አባሎች የሚሰጠው አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉ እና በቤተ ክርስቲያኒቲ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ከ1.54 ቢሊየን ብር በላይ ፈሰስ የተደረገባቸው 278 ፕሮጀክቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ መተግበራቸው በሪፖርቱ ከተመላከቱ ውጤታማ አፈጻፀሞች የሚጠቀሱ ናቸው። በመጨረሻም ጠቅላይ ፀሐፊው ያቀረቡትን ሪፖርት ካውንስሉ አድምጦ ሰፊ ውይይቶችን ካደረገ በኋላ ውሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል እንዲሁም ጥናት ተደርጎ ይቅረብልኝ ያላቸውን ጉዳዮች ወደየ ክፍሎች መርቷል። - - - - "Waggaa dabarsine kana keessa Waldattiin giddu galeessaan qabxii 2. 63% tiin guddina agarsiifteetti. Walumatti qabaatti yeroo ammaa baayyinni miseensota ishee miliyoona 11.38 ga'ee jira..." Kana kan ibsan Barreessaa Walii Galaa Waldattii kan ta'an Luna Tashoomee Amanuu yammuu ta'an; ibsa kanas gabaasa hojii Waldattii walii galaan Kaawonsiliif yeroo dhiyeessanii dha. * * * * Odeeffannoo Staatiksii Waldattii, raawwii hojii Sinoodosootaa, hojiiwwan karaa waajjira ol-aanaa hojjetaman, dhimmoota bulchiinsaa fi faayinaansii wajjin wal qabatan, qajeelchota tajaajila garaa garaa, Seminaarota Waldattii, sochii fi raawwii hojii Boordotaa fi Komiishinoota garaa garaa ilaalchisee gabaasni bal'aan dhiyaateera. Dabalataanis rakkoowwan bara 2015 keessa Waldatti mudatan irratti Kaawonsiliin mariyatee murtoo akka dabarsuuf gabasni dhiyaateera. Hojiin Wangeela biyya keessaa fi alatti bal'isuu guddaan hojjetamuu isaa, barumsi tajaajila Dargaggootaa fi Micoolii sadargaa Digiriitti banamuu isaa, walitti dhufeenyi (network) Dubartootaan nagaa eeguu fi rakkoo hiikuuf cimsu dhaabbachuu isaa, hojiiwwan faayinaansii fi ijaarsa dandeettii jabaatanii itti fufuu isaanii, miseensota karoora Sooramaa Waldattii keessatti hammatamaniif tajaajilli godhamu cimee itti fufuu isaa fi tajaajilli Misoomaa fi Haawwasummaa Waldattii qarshii Biliyoona 1.54 ol kan itti baasee pirojectiin 278 karaa bu'a qabeessa ta'een hojjetamuun isaanii gabaasicha keessatti warra dhiyaatanii dha. Gabaasa Barreessaan Walii Galaa Waldatti dhiyeessan Kaawonsiliin erga dhaggeeffatee booda dhimmoota murtoo barbaadan irratti murtoo dabarseera.Akkasumas dhimmoota qorannoo barbaadan immoo gara kutaawwan garaa garaatti qajeelcheera.

የቄስ አለሙ ሼጣ የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ አምስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ወዳጅ ዘመዶች፣ የአገልግሎት ባልደረቦች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ምዕመናን በተገኙበት ተከናውኗል። በሽኝት ሥነ-ስርዓቱም ላይ ቤተ ክርስቲያናቸው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ በርካታ ሀገር አቀፍና አለማቀፍ የሚስዮን ተቋማት ሀዘናቸውን ገልጠው የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

"...የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።" መዝሙር 112:6 *ዜና እረፍት* በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ለበርካታ አመታት በተለያዬ ከፍተኛ የአመራር ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩትን የቄስ አለሙ ሼጣን ዜና እረፍት በታላቅ ሀዘን ሰምተናል፡፡ ቄስ አለሙ ሼጣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የቀድሞ ደቡብ ኢትዮጵያ ሲኖዶስ ፕሬዚደንት፣ የደቡብ ሲኖዶስ መስራችና የመጀመሪያ ፕሬዚደንት በመሆን እና በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪዮም ለበርካታ አመታት በማስተማር፤ በመቀጠልም በቤተክርስቲያኒቱ ዋናው ጽ/ቤት የወንጌል እና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር በመሆንም ቤተክርስቲያኒቱን በትጋትና በታማኝነት አገልግለዋል:: ከዚህም በተጨማሪ ቄስ አለሙ ሼጣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ከመጋቢት 1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም በዋና ጸሐፊነት/ፕረዝደንትነት አገልግለዋል:: የቄስ አለሙ ሼጣ አስከሬን ሽኝት ረቡዕ መስከረም 30 ቀን 2016ዓ.ም አምስት ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን በ5ሰዓት ሥርዓተ ጸሎት ከተደረገ በኋላ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ከቀኑ በ7:30 ሰዓት ይፈጸማል፡፡ ለባለቤታቸው፣ ለልጆቻቸው፣ ለመላው ቤተሰቦቻቸው እና ምዕመናን ሁሉ እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጠን ጸሎታችን ነው።