ar
Feedback
Atrafi Solution / አትራፊ

Atrafi Solution / አትራፊ

الذهاب إلى القناة على Telegram

ታምነው እቁቦትን ይጣሉ ፣ የስኬት ቁልፎን ከእኛ ይውሰዱ !

إظهار المزيد

📈 نظرة تحليلية على قناة تيليجرام Atrafi Solution / አትራፊ

تُعد قناة Atrafi Solution / አትራፊ (@atrafisolution) في القطاع اللغوي Amharic لاعباً نشطاً. يضم المجتمع حالياً 14 119 مشتركاً، محتلاً المرتبة 5 011 في فئة الأعمال والمرتبة 2 394 في منطقة Ethiopia.

📊 مؤشرات الجمهور والحراك

منذ تأسيسه في невідомо، حقق المشروع نمواً سريعاً وجمع 14 119 مشتركاً.

بحسب آخر البيانات بتاريخ 18 يونيو, 2026، تحافظ القناة على نشاط مستقر. خلال آخر 30 يوماً تغيّر عدد الأعضاء بمقدار -308، وفي آخر 24 ساعة بمقدار -2، مع بقاء الوصول العام مرتفعاً.

  • حالة التحقق: غير موثّقة
  • معدل التفاعل (ER): يبلغ متوسط تفاعل الجمهور 7.48‎%. وخلال أول 24 ساعة من النشر يحصد المحتوى عادةً 4.49‎% من ردود الفعل نسبةً إلى إجمالي المشتركين.
  • وصول المنشورات: يحصل كل منشور على متوسط 1 056 مشاهدة. وخلال اليوم الأول يجمع عادةً 634 مشاهدة.
  • التفاعلات والاستجابة: يتفاعل الجمهور بانتظام؛ متوسط التفاعلات لكل منشور يبلغ 9.

📝 الوصف وسياسة المحتوى

يصف المؤلف القناة بأنها مساحة للتعبير عن الآراء الذاتية:
ታምነው እቁቦትን ይጣሉ ፣ የስኬት ቁልፎን ከእኛ ይውሰዱ !

بفضل وتيرة التحديث المرتفعة (أحدث البيانات بتاريخ 19 يونيو, 2026) تحافظ القناة على حداثتها ومستوى وصول مرتفع. وتُظهر التحليلات تفاعلاً نشطاً من الجمهور، ما يجعلها نقطة تأثير مهمة ضمن فئة الأعمال.

14 119
المشتركون
-224 ساعات
-427 أيام
-30830 أيام
أرشيف المشاركات
الموقع الجغرافي

አድራሻችን አዉቶብስ ተራ ሰባተኛ ዮሎጊያ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ለበለጠ መረጃ 0903717173 / 0926090971

1 አጭር ጊዜ ብድር ምንድ ነው ? 2 አጭር ጊዜ ብድር መበደር የሚችለው ማነው ? 3 አገልግሎት ክፍያው ስንት ነው ? እነዚህን የመሳሰሉት ጥያቄዎች በአብዛኛው ሰው በመጠየቃችን እንደሚከተለው እናብራ
1 አጭር ጊዜ ብድር ምንድ ነው ? 2 አጭር ጊዜ ብድር መበደር የሚችለው ማነው ? 3 አገልግሎት ክፍያው ስንት ነው ? እነዚህን የመሳሰሉት ጥያቄዎች በአብዛኛው ሰው  በመጠየቃችን እንደሚከተለው እናብራራዋለን ። ፦ አጭር ጊዜ ብድር ነጋዴ ለሆኑ ግለሰቦች የምንሰጠው ብድር ሲሆን ማንኛውም አይነት ቁጠባ የማይቆጠብበት እና ከወለድ ነፃ የሆነ የብድር አይነት ነው ። ፦ ከስሙ እንደምንረዳው አጭር ጊዜ ብድር አንድ ተበዳሪ ከተበደረ በኋላ ክፍያውን በ3 ወር ከፍሎ ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል ። ፦ አጭር ጊዜ ብድር ለአዲስ ስራ ጀማሪዎች የማይሆን ብድር ሲሆን አንድ ተበዳሪ ይህን ብድር ለመበደር ቢያንስ አንድ ዓመት በስራ ውስጥ ማለፍ ይጠበቅበታል ። ፦ ብድሩን በአብዛኛው ተበዳሪዎች በሳምንት ጊዜ ውስጥ ስለሚበደሩት  ለቤት ኪራይ ፤ ለስቶክ ፣ ስራቦታቸውን በእቃ ለመሙላት ፣ ለግምሩክ ቀረጥ ፣ እጅግ አስቸኳይ ለሚፈለጉ ወጪዎችና እና ተመሳሳይ ለሆኑ ነገሮች ይበደሩታል ። ፦ ብድሩ ምንም አይነት ወለድ የማይታሰብበት ሲሆን 10% ያልበለጠ የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል ። ፦ ስልክ አይደውሉ በአካል ይምጡ በእርግጠኝነት ያተርፋሉ ። Atrafi saving and credit coop, ltd 0926090971 / 0903717173

የሁለተኛ ዙር የቤት አባላት ያሰሩት የህንፃ ዲዛይን ።
+4
የሁለተኛ ዙር የቤት አባላት ያሰሩት የህንፃ ዲዛይን ።

አሪፍ ሙድ ላይ ነን አዲስ ዓመት ቀን ጨምሮ 2 አለ እኛም ደስታችን በእጥፍ ጨምሯል ደንበኞቻችን በደስታ ረስርሰዋል እስታፋችን በብቃት መንጥቀዋል ። አዲሱ ዓመት እንደስሙ ብቻ አዲስ አይሆንም በአዲሱ
አሪፍ ሙድ ላይ ነን አዲስ ዓመት ቀን ጨምሮ 2 አለ እኛም ደስታችን በእጥፍ ጨምሯል ደንበኞቻችን በደስታ ረስርሰዋል እስታፋችን በብቃት  መንጥቀዋል ። አዲሱ ዓመት እንደስሙ ብቻ አዲስ አይሆንም በአዲሱ ዓመት ሲስተማችን ሙሉ ለሙሉ አዉቶሜትድ ይሆናል ። ደንበኞቻችን አዲስ በምናበለጽገዉ አፕ ተጠቅመዉ ሙሉ ወጪ ገቢያቸዉ ልክ በስዓቱ ይመለከታሉ  ። ምን አልባትም ከእኛ በፊት የተቋቋሙ ተቋማት ይህን አላሳኩ ይሆናል እኛ ግን እየበረርን ነዉ ። የምንበረዉ ክንፍ ኖሮን አይደለም ፤ የምንበረዉ እናንተን ለማገልገል እና የተቀላጠፈ መስተንግዶ ለመስጠት ካለን ከልብ የመነጨ ጉጉት ነዉ ። ለዛም ነዉ ጽሑፉን ስንጀምር ደስታችን በእጥፍ ጨምሮዋል ያልነዉ ። በዚህ ዘመን ሰዉ ለመበደር በእግር ፣ በኪሱ እየባዘነ በሙስና በተጨማለቀበት ዘመን ። እኛ ግን ለደንበኞቻችን ረፍት ነን ። ሙስና ካንገሸገሾት እና ጉዳይ ለማስፈጸም አላስፈላጊ ክፍያ በሌላ ተቋም ከተጠየቁ ። እኛ ጋር መጥተዉ ለህሊናዎ እና ለጊዜዎ ዋጋ ይስጡ ። አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ነን አላማችን እርሶን ከፍላጎቶ ጋር ባልተንዛዛ አገልግሎት ማጨባበጥ ነዉ ። 0903717173 / 0926090971

https://forms.gle/bMY2CgWAb68ACJYMA እንኳን አብሮ አደረሰን 2015 ለእኛ እንደ ተቋም እጅግ የተሳካ ነበር ። የስኬታችን ምንጭ ደሞ እናንተን ማገልገላችን ነዉ ። በ2016 ደሞ
https://forms.gle/bMY2CgWAb68ACJYMA እንኳን አብሮ አደረሰን 2015 ለእኛ እንደ ተቋም እጅግ የተሳካ ነበር ። የስኬታችን ምንጭ ደሞ እናንተን ማገልገላችን ነዉ ። በ2016 ደሞ የበለጠ እናንተን እናገለግላለን ! ከማገልገል ዉጪም አማራጭ የለንም ። ያዉ የስራ ሰዉ ብዙ አያወራም ። በቤት መርሃ ግብራችን በአትራፊ የቤት መፍትሄ በኩል አባላትን ደስተኛ አርገናል ። 2ኛ ዙሮች በተቋቋሙ ሁለት ወር ሳሞላቸዉ ግንባታ ቦታ ገዝተዉ አሁን ክረምት ሲወጣ ግንባታ ለመጀመር እያሟሟቁ ነዉ ። 3ኛ ዙር ተመዝጋቢዎች ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የመግዢያ ብር አሟልተዉ የግንባታ ቦታ ለመግዛት መሬት አስተዳደር እስኪከፈት ድረስ እየጠበቁ ይገኛል ። ባይዘጋ ኖሮ እሰከ አሁን ገዝተዉ ጨርሰዉ ነበር ። አሁን ደሞ ብዙዎቻችሁ የእዚህ እድል መከፈት እየጠበቃችሁ እንደሆነ የታወቀ ነዉ ። ከታች ባለዉ ፎርም ይመዝገቡና 2016 በስኬት ይጀምሩ ። https://forms.gle/bMY2CgWAb68ACJYMA

አዲስ አመት ቀለል አረጉት ስሙን ። እዚህ ለመድረስ 👇 👉 ታመናል 👉 ተጨንቀናል 👉 ብዙ ነገር በህየወታችን አልፈዋል 👉 ከቤተሰብ ፣ ከወዳጅ ፣ ከጓደኛ ብዙዎችን ወደ ማይመለስ አለም ሸኝተናል
አዲስ አመት ቀለል አረጉት ስሙን ። እዚህ ለመድረስ 👇 👉 ታመናል 👉 ተጨንቀናል 👉 ብዙ ነገር በህየወታችን አልፈዋል 👉  ከቤተሰብ ፣ ከወዳጅ ፣ ከጓደኛ ብዙዎችን ወደ ማይመለስ አለም ሸኝተናል ( ነብስ ይማር ) ። ➯ ትራሳችን ላይ ቆዝመን ፣ ➯ እንባ አምልጦን አልቅሰን ፤ ➯ በሰዉ ፊት ጀግና ለመምሰል ሁሉን ዋጥ አርገናል ። ➯ ለበጎ ያልነዉ መሮብናል ➯ ያመናቸዉ ከድተዉናል ➯ ባልናገር ኖሮ ብለን በቃላችንን አዝነናል 😯 አንዳንዶች ከቁመት እና ከመሸበት ዉጪ ምንም አልጨመርንም ይሆናል ። ግን በእርግጠኝነት 2016 እንዳለፈዉ ዓመት ብቻ አይሆንም 🙏 እናብባለን 🙏 ያዩን ይገረማሉ 🙏 የፊታችን ወዝ ከተነጠረ ቂቤ በላይ ያበራል 🙏 ሰላማችን በጥይት እና በሁካታ መሐል እንኳን  በሳቅ ይሞላል 🙏 ማንም ቢመጣ ማንም ቢሄድ ላየን ሁሉ ፍቅር  ለቀረበን ሁሉ ረፍት እንሆናለን ። 🙏 በኑሮ ዉድነት መሐል አካዉንታችን ፈገግ ይላል ። 🙏 ነገራችን ወንዝ ዳር እንደተተከለ ዛፍ ሁሌም ያምርበታል ። 2016 ለእኔ ፣ ለአንቺ ፣ ለአንተ መጥቷል ። 📌የመጣዉ ዓመት አንጠባጥበነዉ እንጂ በፍጹም አንጠባጥቦን አያልፍም ። ከእኛ ጋር አዲሱን ዓመት በስኬት ያንጠባጥቡ በዚህ ኑሮ ዉድነት እንዴት ብቻዎትን ይችሉታል ? ወዳጅ ፣ አጋዥ ፣ ረዳት የሚሆን  ከፈጣሪ በታች አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ያስፈልጎታል ። መልካም ዋዜማ በአላፊነት እና በአግባቡ አዲሱን ዓመት እንቀበል ።

ቀን 04/13/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 30 የወጣ እጣ ቁጥር 65
ቀን 04/13/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 30 የወጣ እጣ ቁጥር 65

ፍጥነት ላይ ነን ፍጥነትን መጽሐፈ ባህል ሲተረጉመዉ ፦ ፈጠነ ፣ ፈጣጠነ ፣ በረር ይለዋለል ፣ ተፈነጠረንም ይጨምርበታል 😂 መጽሐፈ ባህል ብዙ ጊዜ የሚደሰኩረዉ ሰሌን ላይ ተኝቶ በጻፈ ፀሐፊ ነዉ ፣
ፍጥነት ላይ ነን ፍጥነትን መጽሐፈ ባህል ሲተረጉመዉ ፦ ፈጠነ ፣ ፈጣጠነ ፣ በረር ይለዋለል ፣ ተፈነጠረንም ይጨምርበታል 😂 መጽሐፈ ባህል ብዙ ጊዜ የሚደሰኩረዉ ሰሌን ላይ ተኝቶ በጻፈ ፀሐፊ ነዉ ፣ ወይም የምርቃና ዓለም ወዳጅ የተከተበ ነዉ ። ይቅርታ አርጉልኝ እና እኔ ምክር ካልተሳካለት ፣ ኑሮ ከከበደዉ ፣ ህ ይወት ከመረረዉ ። ከባህላዊ አስተሳሰብ ዉስጥ ካለ ሰዉ ላይ ምንም ሀሳብ ሆነ ምክር አልቀበልም ። 💥 እንፍጠን ካልን በደንብ እንፈጥናለን ምክንያቱም ፍጥነት አንዱ የስኬት ቁልፍ ነዉ። 👉 ፍጥነት ማለት ጊዜዉን መዋጀት ነዉ ። 👉 ፍጥነት ማለት ሙስና ባስመረረዉ ህዝብ ላይ በፍቅር ማገልገል ነዉ። 👉 ፍጥነት ማለት የብሔር ማንነት ካሰከረዉ ህዝብ ዉስጥ ነፃ ሆኖ በተለያየ ማንነትን መሰባሰብ እና ማገልገል ነዉ ። 👉 ፍጥነት ማለት በአንድ ቀን የምትጨርሰዉን ስራ አላማሳደር ነዉ ። 👉 ፍጥነት ማለት የሚከተሉህን የስራ ባልደረቦችህን በደሞዝም ሆነ በጥቅማ ጥቅም አስደስተህ ፤  ደንበኞችህን በፍቅር እንዲያገለግሉ ቅድሚያ እነሱን ማገልገል ነዉ ። 👉 ፍጥነት ማለት ልክ እንደ አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ተቋም ደንበኞችን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ በማረግ የተሻለ ነገን እንዲኖሩ ከወንድምም በላይ ወንድም መሆን ነዉ ። 👉🙏 እዉነት ለመነጋገር የዘንድ ወንድም በገንዘብ አትምጣበት እንጂ ምንም ይሆንልካል ። እኛ ግን ከወንድምም በላይ ገንዘብ በደንብ ሰጥተን ሰዎችንን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ በመሪነት እየሰራን ነዉ። እንወዳችኋለን ይህን የተባረከ እና ለብዙዎች ረፍት የሆነዉን ተቋማችንን ተቀላቅለዉ ከወንድም በላይ ወንድም የሆነዉን ህብረት የራሶ ያርጉ ። Atrafi saving and credit coop,Ltd 0903717173 / 0926090971

ቀን 27/12/15 ነባር እቁብ ክፍያ 55 የወጣ እጣ ቁጥር 02
ቀን 27/12/15 ነባር እቁብ ክፍያ 55 የወጣ እጣ ቁጥር 02

ክቡራን ደንበኞቻችን ከቀን 28/12/15 ጀምሮ በዉስጥ አሰራር ማስተካከያዎች ምክንያት እስከ አሁን አባል ከሆናችሁ አባላቶቻችን ዉጪ አዲስ አባላትን መቀበልም ሆነ የብድር ጥያቄዎችን የምናስተናግደዉ
ክቡራን ደንበኞቻችን ከቀን 28/12/15 ጀምሮ በዉስጥ አሰራር ማስተካከያዎች ምክንያት እስከ አሁን አባል ከሆናችሁ አባላቶቻችን ዉጪ አዲስ አባላትን መቀበልም ሆነ የብድር ጥያቄዎችን የምናስተናግደዉ ፦  በሰባተኛ ዮሎጊያ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ባለዉ ቢሮአችን ብቻ መሆኑንን ልናሳዉቅ እንወዳለን ። መልካም አትራፊ ሳምንት ። Atrafi saving and credit coop, Ltd 0903717173 / 0926090971

ቀን 20/12/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 29 ሽያጭ የወጣ እጣ ቁጥር 31
ቀን 20/12/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 29 ሽያጭ የወጣ እጣ ቁጥር 31

ስኬት ላይ ነን 💥💥💥 ታላቁ መጽሐፍ አንተ የምትተኛ ንቃ ይላል ። ያዉ ለመንፈሳዊ ነገር ቢጻፍም ለምድራዊ ህይወታችንም ያገለግለናል። ⚡️ ነቃ ነቃ እንልና ከስኬት መንገዳችን ላይ ፍጥነትን በሶስ
ስኬት ላይ ነን 💥💥💥 ታላቁ መጽሐፍ አንተ የምትተኛ ንቃ ይላል ። ያዉ ለመንፈሳዊ ነገር ቢጻፍም ለምድራዊ ህይወታችንም ያገለግለናል። ⚡️ ነቃ ነቃ እንልና ከስኬት መንገዳችን ላይ ፍጥነትን በሶስተኛ ደረጃ እናየዋለን። ☀️ የእኔ ፍጥነት በጠዋቱ ከሁሉም በፊት ከበረከቴ ፣ ከስኬቴ ምንጭ ከሆነዉ አምላኬ ጋር ጊዜዬን በማመስገን ይጀምራል ። ➯ ብዙ ሰዉ ለማመስገን ስኬትን ፣ ➯ ለማመስገን ሀብትን ፤ ➯ለማመስገን መኪና ፣ ቤት ወዘተን እንደ ቅድሚያ መስፈርት ይደረድራል ። ❗️ ለእኔ ግን ከፈጣን መርሆቼ አንዱ ማመስገን ነዉ ፤ 🙏 በባዶ ሜዳ አመሰግነዋለዉ ፣ 🙏 ገና እንደ ግልም እንደተቋምም ድክ እያልን በነበረበት ጊዜ አመሰግነዋለዉ ፤ 🙏 ተስፋ ባልኖረበት ቦታ አመሰግነዋለዉ ፣ 🙏 በጨነቀኝ ጊዜ አመሰግነዋለዉ ። እሱን ሳመሰግን አንደተወጠረ ባላ ተስፈንጥሬ ፥ የጎደለኝ ሞልቶ ፤ የሌለኝ ከእጄ ገብቶ ፤ እለት እለት እያበብኩ ፣ እየፈካዉ እሄዳለዉ ። ➯ ስለዚህ ፍጥነት ማለት መሮጥ አይደለም ፤ ጌታዬ ጌታዬ እያሉ መጸለይም ብቻ አይደለም 👉 ፍጥነት ማለት ሳያዩ ዘዉ ብሎ መግባትም አይደለም ፤ 👉 እያሰቡም ፕሮፖዛል ላይ ዓመት መጋደምም አይደለም ። 👉 ፍጥነት ማለት ዛሬ መጀመር ነዉ ፣       ነገ ያንተ ባልሆነዉ ነገር ለምን ትጨነቃለህ ? ❗️ዛሬዉኑ ሀሳብክን ከተግባር ጋር አጋምደዉ ። አትሳሳት አንተ እያሰብክ በአህምሮክ ላይ ያለዉ በሌሎች ቢሊየን ሰዎችም ሀሳብ ዉስጥ ላይ አለ ። የተግባር ሰው ከሆንክ ብቻ ቀሪዉ ቢሊየኖችን ላይ ሀሳብክን ታነግሳለክ ። ከፍጥነቶት ጋር ለመጨባበጥ በእርግጠኝነት እናስፈልጎታለን አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድሮች ነን ። ዛሬዉኑ ወደእኛ ይምጡና የሚያፈጥኖትን ነዳጅ ገንዘብ ይዘዉ ይመለሱ ። 0903717173 / 0926090971

ቀን 20/12/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 28 የወጣ እጣ ቁጥር 47
ቀን 20/12/15 አዲስ እቁብ ክፍያ 28 የወጣ እጣ ቁጥር 47

ሰዎችን እንዲሳካላቸዉ ማረግ የመጨረሻዉ ። እና ሰዉን እንዴት ከስኬቱ እንዲጨባበጥ ማረግ ይቻላል ? ወደ ህዝባችን እንመለስ የተለያዩ 10 ሰዎችን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ አርግ ብትለዉ ። 10 ብር ዘ
ሰዎችን እንዲሳካላቸዉ ማረግ የመጨረሻዉ ። እና ሰዉን እንዴት ከስኬቱ እንዲጨባበጥ ማረግ ይቻላል ? ወደ ህዝባችን እንመለስ የተለያዩ 10 ሰዎችን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ አርግ ብትለዉ ። 10 ብር ዘርዝሮ አንድ አንድ ብር ይበትናል ። ሰዎችን ከስኬት ማጨባበጥ ማለት ሰደቃ አይደለም ወይም ሰንበቴ ቤት ሄደህም ማብላትም አይደለም ። ማጨባበጥ ማለት የጎደለን መሙላት ነዉ ። የሰዉ ጉድለቱ ምንድነዉ ትል ይሆናል ? 👉 አንተ ነጋዴህ ነህ ገበያ ያጣዉን አቅርብ 👉 አንተ ሹፌር ነህ ተሳፋሪህን በምቾት ዉሰድ 👉 አንተ መሪ ነህ የተቋምህን ግብ አሳካ አኛ እንደ አትራፊ ሺዎችን አበደርን መቶዎችን የመሬት ባለቤት አድርገናል ። ይህ ሁሉ የሆነዉ በዓመት አይደለም ሰዎች የመሬት ባለቤት ሲሆኑ 2ወር አልፈጀባቸዉም ብድር ለመዉሰድ እንደምርጫቸዉ ሳምንት አልፈጀባቸዉም ። ❗️ሙስናን እንጠየፋለን እኛ ቢሮ ሆኖ ሙስና ያማረዉ የስራ ባልደረባ በራሱ ፈቃድ ራሱ ላይ ቀይ ካርድ ይመዛል ። በዚህም አቋሚችን ምርጥ ስታፍ ገንብተናል አባል መጥቶ የኋላ ኪሱ የመዘዘ ያህል ገንዘብ ይዞ ይሄዳል ። ስናጠቃልለዉ ማጨባበጥ ማለት ፦ በምትመራዉ ፣ በምትነግደዉ ተቋም ለተጠቃሚዉ ደንበኛህ ነገሮችህን ቀለል አርገህ አንጀቱን ማራስ ነዉ ። እኛ እንደ ተቋም ለብድር መስፈርታችንን ቀለል አርገን አባላችንን እናስደስታለን ። ቤት ለፈለገ 2ወር ሳይሞላ መሬት አስገዝተን ኢንቨስት ያረገዉ ላይ 50% በላይ እንዲያተርፍ እናረጋለን 👍 ። አትራፊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ነን ዓለማችን አንድ ነዉ 👇👇👇 ወደ እኛ የመጡትን ካላቸዉ ላይ ከእጥፍ በላይ ጨምረን ወደ መጡበት መመለስ ነዉ ። ለዚህም ነዉ ከብርሃን ፍጥነት በላይ እያደግን ያለነዉ  👏👏👏

ከስኬት መንገዱ አንዱ ሰዎች ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረግ ነዉ ብለናል እንቀጥል ፦ ሰዎች ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረግ ማለት ሰዉን መርዳት ፣ ገንዘብ መስጠት የመሳሰሉት አይደለም ። ይህ እርዳታ ነ
ከስኬት መንገዱ አንዱ ሰዎች ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረግ ነዉ ብለናል እንቀጥል ፦ ሰዎች ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረግ ማለት ሰዉን መርዳት ፣ ገንዘብ መስጠት የመሳሰሉት አይደለም ። ይህ እርዳታ ነዉ ፤ እርግጥነዉ የደከሙ ፣ የተጎዱን መርዳት መልካም ነዉ ። እኛ ግን ይደገፍ የምንለዉ ፦ ➯ ለሚሰራዉ ነዉ ፤ ➯ ለፍቶ ደክሞ ቢያንስ 50ሺ ለያዘዉ  ፤ ➯ ስራ ሳይንቅ 500ሺ ላለዉ ። ➯ ስራዉን እየወደደ ሚሊየኖች ላደረሰዉ ፤ አትራፊ ከስኬቱ የሚያባብጠዉ ለዚህ አይነት ሰዉ ነዉ ፦ ለሚለፋዉ ፣ ለሚደክመዉ ፣ ለሚበረታዉ ማደግ ለሚወደዉ አዎ እንደዚህን አይነት ሰዎችን ከስኬታቸዉ ጋር ማጨባበጥ ተልዕኳችን ነዉ ። 👉 ስራን ለሚወዱ ፤ ነጋቸዉን ለማሳመር ለሚጥሩ ፣ በጎደላቸዉ እንሞላን ሰዉ በሚፈልጉበት ጊዜ ከወዳጅ በላይ ሆነን እንገኛለን ። ያዉ መጽሐፉ እንዳለዉ ላለዉ ይጨምራል እንደሚል ፦ አንተም ሰዉን ከስኬታቸዉ ማጨባበጥ ከፈለክ የምታረገዉ ፦ 👉 ተስፋ እያለዉ ተስፋዉ የራቀዉን አቅርብለት ፤ 👉 መሰላል አቀብለዉ ፤ 👉 ከስኬቱ ጋር እንዲጨባበጥ አስፈንጥረዉ ። በድጋሚ ላለዉ ጨምርለት ፦ እየለፋ እየሰራ 10 ብር አለዉ ? መቶ አርግለት ። ሁሌም በስራዉ እየተጋ የገንዘብ ምንጩ ከጠፋዉገንዘብ አሰራሩን አሳያዉ ። ግን በፍጹም በፍጹም ለመለወጥ ላላመነ እና በራሱ ሙሉ እምነት ለሌለዉ ሌክቸር ስጠዉ እንጂ ገንዘብ አትስጠዉ ለምን ብትል እሱ አምሮዉን ባላዘገጀበት አንተ ምን ቤት ነህ ? ለዚህ ነዉ እኛ አትራፊዎች መለወጥ የፈለገዉን ቀድመን የምንደርስለት ። እንቀጥላለን ። Atrafi saving and credit coop, ltd 0926090971 / 0903717173

ከስኬት መንገዶች አንዱ እራስን ስለመሆን በስሱም ቢሆን ተነጋግረናል ። ቀጣዩን ደሞ እንመልከት ፦ ለምን ተወለድክ ? ለምን ወደዚህ ዓለም መጣክ ? አሁን በዚህ አለም ላይ ምን እያረክ ነዉ ? መሞትህ
ከስኬት መንገዶች አንዱ እራስን ስለመሆን በስሱም ቢሆን ተነጋግረናል ። ቀጣዩን ደሞ እንመልከት ፦ ለምን ተወለድክ ? ለምን ወደዚህ ዓለም መጣክ ? አሁን በዚህ አለም ላይ ምን እያረክ ነዉ ? መሞትህ አይቀር ከሞትክ በኋላስ ያንተ ነገር እንዴት ነዉ  ? እኔ የዚህ ጽሑፍ ፀሐፊ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ ከማምንበት እና የህይወቴ መርህ ከሆነዉ ከክርስቶስ ስለምነሳ ፤ ምን አልባት ነገሩን ወደ መንፈሳዊ እንዳትወስዱት እና ሳይድ እንዳትከቱት ቀድሜ አሳስባለዉ ። ለስኬት አንዱና ወሳኙ ቁልፍ ነገር ሰዎች እልማቸዉን እና ሃሳባቸዉን እንዲያሳኩ መርዳት እና መቻል ነዉ ። ለዚህ ደሞ ከእምነታችን ፈፃሚ ከክርስቶስ መዉሰድ እንችላለን እሱ በሚደነቅ ብርሃን እየኖረ ሳለ በበረት ለመመወለድ ደግሞ አላሰበም ። መላህክት በፍጹም ፍርሃት እየታዙለት እየኖረ ሳለ እናቱን ለመታዘዝ ዝቅ ማለት ከክብር መዉረድ አልሆነበትም ። ከሁሉም በላይ ሞትን ድል አርጎ ሲነሳ ለወጉት እና ለገደሉት ሁሉ የዘላለምን ህይወት ሲሰጥ ፍጹም የፍቅር ጥግ አሳይቶናል  ። እንመለስ በዚህ በመገባደድ ባለዉ  ዓመት ላይ ምን ያህል ሰዉ ህልሙን እንዲያሳካህ ረዳክ ? ምን ያህል ሰዉን ከህልሙ ጋር እንዲጨባበጥ አረክ ? በፍጹም ቅንንነት ምን ያህሉን ማህበረሰብህን ከፍ እንዲል መሰላል አቀበልክ ? ሰዎችን እልማቸዉን እንዲያሳኩ እና ከፍ እንዲሉ ማረግ ዋናዉና በረከት ያለዉ የስኬት መንገድ ነዉ ። የእኔ እራሴን ከመሆኔ በተጨማሪ ሰዎችን ከስኬታቸዉ እንዲጨባበጡ ማረጌ ትልቁ የስኬቴ ቁልፍ ነዉ ፣ አዲሱንም ዓመት ከዚህ በተሻለ በግልም በተቋምም እቀጥላለዉ !!! እርሶስ ??? የሚያግዞ እና የሚደግፍዎ ወንድምም ተቋምም ያስፈልጎታል ዛሬዉኑ አትራፊን ይቀላቀሉ ። 0903717173 / 0926090971