cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ቤተ መጻሕፍት

@ጌሰም24

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
384
المشتركون
+124 ساعات
-17 أيام
-130 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
✨✨✨እንኳን ለአጋእዝተዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን✨✨✨
ሰላም ለአብ ዘቅምቅድመ ዓለም ነጋሤ ፣ ለወልድ ሰላም ሥጋ ማርያም ለባሲ። ለመንፈስቅዱስ ሰላም ኃጢአተ ዓለም ደምሳሲ ፣ ኀይልየ ሥላሴ ወፀወንየ ሥላሴ ፣በስመ ሥላሴ እቀጠቅጥ ከይሴ ። (መልክአ ሥላሴ)
በዚህች ዕለት ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው እርሱንስ የባረኩበት ዕለት ነው ፤ የአብርሃምን ቤት የባረኩ የእኛን ሕይወት ይባርኩልን @gesem24
إظهار الكل...
3
ኦሪት ዘፍጥረት ፴፱ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 1 ፤ዮሴፍ ግን ወደ ግብጽ ወረደ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብጽ ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብጽ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው። 2 ፤እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ነበረ፥ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ በግብጻዊው ጌታውም ቤት ነበረ። 3 ፤ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋራ እንዳለ፥እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ። 4 ፤ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፥እርሱንም ያገለግለው ነበር በቤቱም ላይ ሾመው፥ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። 5 ፤እንዲህም ሆነ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ። 6 ፤ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም።የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ። 7 ፤ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይኗን ጣለች።ከእኔም ጋራ ተኛ አለችው። 8 ፤እርሱም እንቢ አለ፥ለጌታውም ሚስት እንዲህ አላት፦እነሆ፥ጌታዬ በቤቱ ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፥ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል 9 ፤ለዚህ ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም ሚስቱ ስለ ሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኀጢአትን እሠራለሁ ? 10 ፤ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር እርሱም ከእርስዋ ጋራ ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋራ ይሆን ዘንድ አልሰማትም። 11 ፤እንዲህም ሆነ በዚያን ጊዜ ሥራውን እንዲሠራ ወደ ቤቱ ገባ በቤትም ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም አልነበረም። 12 ፤ከእኔ ጋራ ተኛ ስትል ልብሱን ተጠማጥማ ያዘች እርሱም ልብሱን በእጇ ትቶላት ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ። 13 ፤እንዲህም ሆነ ልብሱን ትቶ ወደ ውጭ እንደ ሸሸ ባየች ጊዜ፥ 14 ፤የቤቷን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው።እዩ ዕብራዊው ሰው በእኛ እንዲሣለቅ አግብቶብናል እርሱ ከእኔ ጋራ ሊተኛ ወደ እኔ ገባ፥እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮህሁ 15 ፤ድምፄንም ከፍ አድርጌ እንደ ጮህሁ ቢሰማ ልብሱን በእኔ ዘንድ ጥሎ ሸሸ ወደ ውጭም ወጣ። 16 ፤ጌታው ወደ ቤቱ እስኪገባ ድረስም ልብሱን ከእርስዋ ዘንድ አኖረች። 17 ፤ይህንም ነገር እንዲህ ብላ ነገረችው፦ያገባህልን ዕብራዊው ባሪያ ሊሣለቅብኝ ወደ እኔ ገባ 18 ፤እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮህ ልብሱን በእጄ ተወና ወደ ውጭ ሸሸ። 19 ፤ጌታውም፦ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ ብላ የነገረችውን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ። 20 ፤የዮሴፍም ጌታ ወሰደው፥የንጉሡ እስረኞችም ወደሚታሰሩበት ስፍራ ወደግዞት ቤት አገባው ከዚያም በግዞት ነበረ። 21 ፤እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋራ ነበረ ምሕረትንም አበዛለት፥በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው። 22 ፤የግዞት ቤቱም አለቃ በግዞት ያሉትን እስረኞች ሁሉ በዮሴፍ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው በዚያም የሚደረገው ነገር ሁሉ እርሱ የሚያደርገው ነበረ። 23 ፤የግዞት ቤቱም አለቃ በእጁ ያለውን ነገር ከቶ አላሰበም፥እግዚአብሔር ከእርሱ ጋራ ነበረና የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር ያቀናለት ነበር። +++++ወስብሐት ለእግዚአብሔር +++++ወወላዲቱ ድንግል +++++++ወመስቀሉ ክቡር+++++
إظهار الكل...
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ✨ እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደተለመደው ዘወትር ቅዳሜ የኑ እናንብብ መርኃግብራችን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ሠላሳ ዘጠኝ ይሆናል። ✨ በባለፈው ምዕራፍ የተመለከትነው ስለ ይሁዳ ሲሆን ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው እንደገባ እና በዚያም የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ እንዳየና እንደወሰዳት ከእርስዋም ሶስት ወንድ ልጆችን እንደወለደ ለበኵር ልጁ ለዔር ትዕማር የምትባል ሚስት እንዳጋባው እርሱም ክፉ ነበርና ተቀሰፈ ከዛም አውናም ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ ተብሎ በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ ዘሩን ምድር ላይ በማፍሰሱ መቀሰፉንም ከእነርሱ ታናሽ የሆነው ሴሎም እስከሚያድግ እንድትጠብቅ መደረጉን ከዛም ትዕማርም ሄዳ በአባቷ ቤት ከተቀመጠች በኃላ የሆነውንም እንዲሁ አይተናል። ✨ በአሁኑ ምዕራፍ የምንመለከተው ዮሴፍ ወደ ግብጽ እንደወረደና የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብጽ ሰው ከእስማኤላውያን እጅ እንደገዛው ፣ በግብጻዊው ጌታውም ቤት ሣለ በጌታው ፊት ሞገስን እንዳገኘና እንደተሾመ በሥራውም ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ከአጠገቡ እንደነበር እንዲሁም በሹመቱ እያለ የሚሆነዉን እናያለን። መልካም ንባብ 😊😊😊 ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
إظهار الكل...
3
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው እንዲሁም ለፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ መታሰቢያ በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን።
" ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ ። ዘእያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ ።እንዘ ትረውጽ ጥቡዕ ለመልእክተ ክርስቶስ ።እመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድወእመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ። "
"ሰላም ለጳውሎስ ለልሳነ እረፍትከ ሐዋርያሆሙ ለአህዛብ ፈልፈለ ጥበብ "
@gesem24
إظهار الكل...
🙏 2
† † † በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † † † ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦             📖 ከመጽሐፍት አንደበት 📖 ◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦               ውስጣዊ ሠላም በዚህኛው ሠላም አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ትሆናለህ፤ የእግዚአብሔር ልጆች ሰውነቶቻቸውና ነፍሶቻቸውን እርስ በእርሳቸው አይቀወሙም ። ሁለቱም በእግዚአብሔር ፍቅር ተስማምተውና አንድ ሆነው ይኖራሉ እንጂ ። የእግዚአብሔር ልጆች ውስጣዊ ሕይወታቸው የተከፋፈለ አይደለም ። ልቦናቸውን ፈንቅሎ የሚያወጣው ሠላም ሌሎችንም ያጥለቀልቃል በእርግጥም ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በሠላም የሚኖር ሰው በውስጡ በሚፈጥረው ደስታ ሁልጊዜ ሀሴት ያደርጋል ። ይህ ሠላም የአእምሮ እና የልብ ሰላም ነው። ይህ ሠላም ያለውሰው አእምሮው የተረጋጋ ነው ፣  ሕይወቱም በእምነት የተሞላ ነው ፤ ልቦናውም የሰከነ እና የማይታወክ ነው ። አይረበሽም አይፈራምም ። ጭንቀት ተስፋ መቁረጥ መደነጋገርና ጥርጣሬ በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም ስለሆነም ይህ ሰው ሰላማዊ ኑሮ ይኖራል ። የእግዚአብሔር እንክብካቤ እና አርቆ አስተዋይነቱ እንደሚጠብቁት ያምናል ። ምንም እንኳ የከፋ እና የበረታ የርኩሳን መናፍስት ኃይል ቢከበውን እግዚአብሔርእጅጉን እንደሚበረታ ያውቃል። እግዚአብሔር እንዲህ ነው የሚለው " እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ፤ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚያነሣብህ የለምና አትፍራ'' የሐዋ. ሥራ ፲፱ ÷ ፱ ~ ፲ በእርግጥም የሰው እምነቱ ደካማ ከሆነ ሰላሙን ስለሚያጣ በቀላሉ ይታወካል። ነቢዩ ዳዊት በሞት መካከል እንኳ ሲሄድ ውስጣዊ ሠላም ስለነበረው አልፈራም ። መዝ. ፳፪ " እኒያ ሠለስቱ ደቂቅም ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ውስጣዊ ሠላማቸውን ጠብቀው ስለነበር አልፈሩም " ምንጭ ፦ የተራራው ስብከት                ( ገጽ 79 በአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ  ) ◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◍◆◆◆◍◍◍◍◍◍◍◍ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን † † †    ወስብሐት ለእግዚአብሔር   † † †
إظهار الكل...
1
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ያኔ እመረቃለሁ 🔖🔖🔖🔖🔖 👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓👩‍🎓👨‍🎓 ሀሁ ABCD ፊደላት ቆጥሬ ጥበብን ለመማር መፃሕፍት ደርድሬ ሀገሬን ወገኔን እናቴን ለመርዳት ድንቁርናን ጥዬ ከችግር ለመውጣት ጋራውን ስወጣ ቁልቁለት ወርጄ ከአንድ ወደ ሌላ ማለፍ ተላምጄ ነገን ለማሸነፍ እቅድ እነድፋአለሁ ተስፋ ስንቅ ሆኖልኝ እሩቅ አልማለሁ፡፡      ደግሞ መቼነው የማያት ያቺን የብርሃን ቀን? ነፃ ምወጣባት ከቴንሽን ሰቀቀን መች ትሆን እያልኩኝ አማትሬ ሳያት ያቺን የቀናት ቀን እንዲሁ ስናፍቃት ቀናት ተሰብስበው ወራት አቀናጁ ወራትም አብረው አመታት አበጁ የዘመን ባለቤት ጊዜያት አቀዳጅቶ ጉዞና መንገዴን ጥርጊያዬን አቅንቶ በጊዜው ውብ አርጎ ሁሉን አስተካክሎ የምርቃቴን ቀን ለገሰኝ በቶሎ፡፡ የእናት የአባቴ ህልም የተስፋ ቀናቸው የብርሃን ቀን መጣች ሀሴት ልትሞላቸው የምመረቅባት....የልፋት ካባዬን የምደርብባት ራዕይ ዓላማዬ ግብ የሚመታባት፡፡    ሀገሬን ወገኔን የምጠቅም ዜጋ ለእውነት ለቅንነት ጦር ይዜ ምዋጋ የማይነቃነቅ ብርቱ ትውልድ ሆኜ ለጥፋት የማልቆም የማልቀር ባክኜ አንድነት ሰላምን ፍቅርን ተነቅሼ የዳዊትን ትምክህት የምጓዝ ለብሼ     እንድሆን ብሩህ ትውልድ ሥላሴ ድረሱ     መላ ማንነቴን ህይወቴን ቀድሱ፡፡ የአብርሃምን ቤት እንደባረካችሁ ትውልዱንም ታላቅ እንዳደረጋችሁ ብርቱ መጠለያ ዋስ ድጋፍ ሁኑልኝ ዓጋዕዝተ ዓለም ቀኔን መርቁልኝ፡፡ እንደ ያዕቆብ ሌሊት ይባረክ ህይወቴ ሙሉ ሀሴት ይሁን የምርቃት ለቴ፡፡       ባላቅን ልካችሁ ሰዓታት ዕለታት ቀኔን መርቁልኝ        በጴጥሮስ መክፈቻ የገዛ ሀጥያቴን አጥባችሁ አጥሩልኝ፡፡ መልአከ ምክራችሁን ወደኔ ላኩልኝ ዲግሪዬን በትንፋሹ እንዲቀድስልኝ አብሳሪውን መልአክ ጠርታችሁ ላኩልኝ የምስራች ነግሮ ደስታ እንዲበዛልኝ፡፡ ጆሮዬ ይሰማው የድንግል ሰላምታ ይታጠፍ ጉልበቴ ይስገድ ለአንተ ጌታ ጉዞዬን በሙሉ ባንተ ላይ ስጥለው መቻል እስቂያቅተኝ ያኔ እመረቃለሁ፡፡ ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ ለ2016ዓ.ም ተመራቂ የተዋህዶ ልጆች በሙሉ እንኳን ደስ አላቹ እንላለን። +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ++++ ++++ ወወላዲተ ድንግል ++++ ++++ ወመስቀሉ ክቡር++++ ምንጭ : መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
إظهار الكل...
3🙏 1
<<<<<<<<ሰኞ ሐምሌ 1  >>>>>>>>          †††      ስንክሳር     ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡           †   እንኳን አደረሳችሁ   †               🕊 ቅድስት ቅፍሮንያ 🕊 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የተባረከ የሐምሌ ወር ቀኑ ዐሥራ አራት ሰዓት ነው ። ከዚህም በኋላ ያንሳል ። ሐምሌ አንድ በዚች ቀን ሰውነቷን ለእግዚአብሔር የሰጠች ቅድስት ድንግልና መስተጋድልት ቅፍሮንያ ሰማዕት ሆነች ። እርሷም በደናግል ገዳም ቁጥራቸው ሃምሳ ለሆኑ ለደናግሉ እመ ምኔት እኅት ነበረች ። የእመ ምኔትዋም ስሟ ኦርያና ነው ። ይህችንም ቅድስት በፈሪሀ እግዚአብሔር አሳደገቻት ። በትሩፋት ሥራ ተጋዳሊት እስከሆነችም ድረስ አምላካውያት የሆኑ መጻሕፍትን አስተማረቻት ። ከዚህም በኋላ ፍጹም ገድልን ጀመረች በየሁለት ቀኑ ትጾም ነበር ብዙ ጸሎታትንም ትጸልይ ነበር ። ያቺም እመ ምኔት ሥራዋ ያማረ በሃይማኖቷም የጸናች ነበረች ። በበጎ ሥራ ሁሉ እንዲጸኑ ወገኖቿን ታስተምራቸው ነበር ። ከዚህም በኋላ ሰዎች ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልኩ ከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ በአዘዘ ጊዜ ብዙዎች ክርስቲያኖችን ይዘው አሠቃዩአቸው ሰማዕታትም ሆኑ ። እሊያ ደናግልም ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም ከገዳም ወጥተው ሸሽተው ተሠወሩ ። እመምኔቷ ግን ከዚች ቅድስት ቅፍሮንያ ጋራ ብቻዋን ቀረች ። በማግሥቱም የንጉሡ መልክተኞች ወደ ዚያ ገዳም በመጡ ጊዜ እመ ምኔቷን አግኝተው ያዟት ሌሎችንም ደናግል ፈለጓቸው ግን አላገኟቸውም ። ቅድስት ቅፍሮንያም በእርሷ ፈንታ እኔን ውሰዱኝ ይቺንም አሮጊት ተውዋት አለቻቸው ። እነርሱም ያዟት በብረት ሰንሰለትም አሠሩዋት መኰንኑ ወደአለበትም ከተማ ወሰዱዋት እመ ምኔቷም እያለቀሰች ተከተለቻቸው ። ወደ መኰንኑም በአደረሷት ጊዜ ለአማልክት ሠዊ አላት ብዙ ቃል ኪዳንም ገባላት እርስዋ ግን ቃል ኪዳኖቹን አቃለለች ትእዛዙንም አልተቀበለችም እንዲደበድቧትም አዘዘና በበትሮች ደበደቧት ። ዳግመኛም ልብሷን ገፍፈው ሥጋዋን ግልጥ እንዲያደርጉ አዘዘ እመ ምኔቷ ኦሪያናም አንተ ከሀዲ ይቺን ታናሽ ብላቴና እንዳጐሳቈልሃት እግዚአብሔር ያጐሳቍልህ ዘንድ አለው ብላ ጮኸች ። መኰንኑም እጅግ ተቈጥቶ ይህቺን ቅድስት ቅፍሮንያን አሥረው በመንኰራኵር ውስጥ እንዲያሠቃዩዋት በብረት መጋዝም እንዲሠነጥቋት አዘዘ ሁሉንም አደረጉ ይህንም ሁሉ ፈጸሙባት እርሷም ርዳታን ሽታ ወደ እግዚአብሔር ጮኸች ወዲያውኑ ከሕመሟ ሁሉ ድና ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ሆነች ። ሕዋሳቷን ሁሉ ቆረጡ ጥርሶቿንም ሰበሩ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ሕማም አስነሣት ። መኰንኑም እሷን ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራሷን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ቆረጧት በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀች ። አንድ ባለ ጸጋ ምእመን ሰውም መጥቶ የቅድስት ቅፍሮንያን ሥጋ ወሰደ በአማሩ የሐር ልብሶችም ገንዞ በወርቅ ሣጥን አኖራት ከሥጋዋም ብዙ ድንቅ ታአምር ተገለጠ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚች ቅድስት ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም  በዕለቱ ታስበዉና  ተዘክረዉ ከሚዉሉ   ቅዱሳን     ጻድቃን ሰማዕታት እንዲሁም መላዕክት  ረድኤት  በረከታቸዉ  አይለየን † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † ምንጭ:- ስንክሳር ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟ @gesem24bot  ያስቀምጡልን https://t.me/gesem24
إظهار الكل...
አ/አ/ሳ/ቴ/ዩ ግቢ ጉባኤ ቤተ መጻሕፍት

@ጌሰም24

👍 4
ኦሪት ዘፍጥረት ፴፰ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ 1 ፤በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወረደ፥ስሙን ኤራስ ወደሚሉት ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው ገባ። 2 ፤ከዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ ወሰዳትም፥ወደ እርስዋም ገባ። 3 ፤ፀነሰችም ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው። 4 ፤ደግሞም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙንም አውናን ብላ ጠራችው። 5 ፤እንደ ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች፥ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው እርሱንም በወለደች ጊዜ ክዚብ በሚባል አገር ነበረች። 6 ፤ይሁዳም ለበኵር ልጁ ለዔር ትዕማር የምትባል ሚስት አጋባው። 7 ፤የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። 8 ፤ይሁዳም አውናን፦ወደ ወንድምህ ሚስት ግባ፥አግባትም፥ለወንድምህም ዘርን አቁምለት አለው። 9 ፤አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን ዐወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይሰጥ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር። 10 ፤ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ ሆነበት፥እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው። 11 ፤ይሁዳም ምራቱን ትዕማርን፦ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ አላት እርሱ ደግሞ እንደ ወንድሞቹ እንዳይሞት ብሎአልና።ትዕማርም ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች። 12 ፤ከብዙ ዘመንም በኋላ የይሁዳ ሚስት የሴዋ ልጅ ሞተች ይሁዳም ተጽናና፥የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ፥እርሱም ዓዶሎማዊው ወዳጁም ዔራስ። 13 ፤ለትዕማርም፦እነሆ፥አማትሽ ይሁዳ የበጎቹን ጠጕር ይሸልት ዘንድ ወደ ተምና ይወጣል ብለው ነገሩአት። 14 ፤እርስዋም የመበለትነትዋን ልብስ አወለቀች፥መጐናጸፊያዋንም ወሰደች፥ተሸፈነችም፥ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች ሴሎም እንደ አደገ ሚስትም እንዳልሆነችው አይታለችና። 15 ፤ይሁዳም ባያት ጊዜ ጋለሞታን መሰለችው ፊቷን ተሸፍና ነበርና። 16 ፤ወደ እርስዋም አዘነበለ፦እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና።እርስዋም፦ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ ? አለችው። 17 ፤የፍየል ጠቦት ከመንጋዬ እሰድድልሻለሁ አላት።እርስዋም፦እስክትሰድድልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህን ? አለችው። 18 ፤እርሱም፦ምን መያዣ ልስጥሽ ? አላት።እርስዋም፦ቀለበትህን፥አንባርህን፥በእጅህ ያለውን በትር አለች።እርሱም ሰጣትና ከእርስዋ ጋራ ደረሰ፥እርስዋም ፀነሰችለት። 19 ፤እርስዋም ተነሥታ ሄደች፥መጐናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበሰች። 20 ፤ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በወዳጁ በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት እርስዋንም አላገኛትም። 21 ፤እርሱም የአገሩን ሰዎች፦በኤናይም በመንገድ ዳር ተቀምጣ የነበረች ጋለሞታ ወዴት ናት ብሎ ጠየቃቸው።እነርሱም፦በዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉት። 22 ፤ወደ ይሁዳም ተመልሶ እንዲህ አለው፦አላገኘኋትም የአገሩም ሰዎች ደግሞ፦ከዚህ ጋለሞታ አልነበረችም አሉኝ። 23 ፤ይሁዳም፦እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ፥የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት፥አንተም አላገኘሃትም አለ። 24 ፤እንዲህም ሆነ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ፦ምራትህ ትዕማር ሴሰነች ደግሞም በዝሙት፥እነሆ፥ፀነሰች ብለው ነገሩት።ይሁዳም፦አውጡአትና በእሳት ትቃጠል አለ። 25 ፤እርስዋም ባወጡአት ጊዜ ወደ አማቷ እንዲህ ብላ ላከች፦ለዚህ ለባለገንዘብ ነው የፀነስሁት ተመልከት ይህ ቀለበት፥ይህ አንባር፥ይህ በትር የማን ነው ? 26 ፤ይሁዳም ዐወቀ፦ከእኔ ይልቅ እርስዋ እውነተኛ ሆነች ልጄን ሴሎምን አልሰጠኋትምና አለ።ደግሞም አላወቃትም። 27 ፤በመውለጃዋም ጊዜ፥እነሆ፥መንታ ልጆች በሆዷ ነበሩ። 28 ፤ስትወልድም አንዱ እጁን አወጣ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰረች፦ይህ መጀመሪያ ይወጣል አለች። 29 ፤እንዲህም ሆነ እጁን በመለሰ ጊዜ፥እነሆ፥ወንድሙ ወጣ እርስዋም፦ለምን ጥሰህ ወጣህ ? አለች ስሙንም ፋሬስ ብላ ጠራችው። 30 ፤ከእርሱም በኋላ ቀይ ፈትል በእጁ ያለበት ወንድሙ ወጣ ስሙም ዛራ ተባለ። +++++ወስብሐት ለእግዚአብሔር +++++ወወላዲቱ ድንግል +++++++ወመስቀሉ ክቡር+++++
إظهار الكل...
+++ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ ✨ እንደምን ቆያችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደተለመደው ዘወትር ቅዳሜ የኑ እናንብብ መርኃግብራችን ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ሠላሳ ስምንት ይሆናል። ✨ በባለፈው ምዕራፍ የተመለከትነው የያዕቆብ ልጆች አንዱ የሆነውን የዮሴፍን ሲሆን ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ አብልጦ ይወደው ነበር፥እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና በብዙ ኀብር ያጌጠችም ቀሚስ አለበሰው  ወንድሞቹም አባታቸው ዮሴፍን አብልጦ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ዮሴፍ ላይ ጥላቻ አደረባቸው ዮሴፍ ህልም አየ እርሱም የዋህ በመሆኑ ያለማቸውን ህልሞች  እንደ ራዕይ የነበረና ለቤተሰቦቹ ሲነግራቸው በተለይ ወንድሞቹ ሊያጠፉት ተነስተው ነበር እናም በእርሱ ላይ እንዳደረጉበትም አይተናል። ✨ በአሁኑ ምዕራፍ የምንመለከተው ስለ ይሁዳ ሲሆን ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው እንደገባ እና በዚያም የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ እንዳየና እንደወሰዳት ከእርስዋም ሶስት ወንድ ልጆችን እንደወለደ ለበኵር ልጁ ለዔር ትዕማር የምትባል ሚስት እንዳጋባው ከዛ የሚሆነውን በስፋት እናያለን። መልካም ንባብ 😊😊😊 ሀሳብ እና አስተያየቶን ➟➟➟➟@gesem24bot ያስቀምጡልን
إظهار الكل...
👍 1 1
+++በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን +++ መጽሐፍትን እንዴት እናንብብ 😃 መጽሐፍ ማለት በላዩ ቃል የተፃፈበት ብራና ፣ ነዶ ፣ በአንድነት የታሰረ ፣ የተያዘ ወይም የተጠረዘ ቅዱስ ክታብ ነው። ፫ የመጽ ሐፍት አይነቶች ሲሆን እነርሱም:- ፩) መንፈሳዊ መፃሕፍት :- በመንፈስ ቅዱስ ምረት ስለ ሰማያዊ ምስጢር ፣ ፈጣሪ እና ዘላለማዊ ሕይወት የሚጽፍ ነው፡ ፪) ርኵሳት መጽሐፍት፦ እነዚህ እንግዳ የሆነ ትምህርትን የሚያስተምሩ እና ከ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚያሰውጡ ናቸው :: ፫) ምኑናት መጽሐፍት:- እነዚህ ደግም ዓለማዊ መጻሕፍት ናቸው። የንባብ አይነቶች 1) Elementary :- በዚህ የንባብ ደረጃ አንባቢው ለመመለስ የሚሞክረው ጥያቄ "ይህ ሐረግ ምን ይላል?" የሚለውን ነው 2) Inspectional Reading :- ይህ መጽሐፉ ስለምን እንሚያወራ መቅድሙን ቀማንበብ የምንረዳው ነዉ 3) Analytical Reading: በዚህ የንባብ ዓይነት ደግሞ ስለ መጽሐፉ ጭብጥ በጥልቀት የምንረዳበት ነው:: 4) synoptic reading፦ በዚህ የንባብ ዓይነት ውስጥ ያነበብነውን ከሌሎች መጽሐፍት ጋር የምናመዛዝነበት ነው:: መጽሐፍትን ለማንበብ መደረግ ያለባቸው ድርጊቶች 1) ላለማንበብ ምክንያት መደርደር ማቆም 2) ከማንበባችን በፊት ማህበራዊ ድህረ ገፆችን አለመጠቀም 3) በምናነብበት ጊዜ ማስታወሻ መያዝ  4) በተቻለ መጠን ያነበብነውን ተግባር ላይ ማዋል ተጠቃሽ ወሳኝ ነጥቦት ናቸዉ። * አገላብጠ ማንበብ ፣ ጥልቀት ያለው ንባብን ማካሄድ እና ጥሩ አንባቢ መሆናችን ያነበብነውን እንዳንረሳ ያደርገናል። የመጽሐፍት ዳሰሳ :- ማለት አንድ መጽሑፍ የተፃፈበትን ዓላማ አሳክቶ እንደሆነ የሚመረመርበት ሲሆን ለፀሐፊው፣ ለአንባቢው እና ለሚዳስስለት ሰው ጠቀሜታው የጎላ ነው። በዚህም ዕይታዊ (ውጫዊ) ፣ ቅርፃዊ ( ውሳጣዊ) እና ሀሳባዊ ዳሰሳ ይስጣል ። የመጽሐፍ ዳሰሳ አይነቶች 1)Summary review ፦ እንደ አጠቃላይ ከመጽሐፍ የሚወስዱ ስለ ዋና ሀሳቡ ብቻ የሚኖሩ ዝርዝር ያልሆኑ ትንተናዎች ናቸው። 2) critics ( analyst ) review ፦ ሒሳዊ ግምገማዎች የምንላቸው በባለሙያዎች የሚፃፍ  ስለ መጽሐፉ ጥንካሬ እና ድክመት የሚዳስሱ ናቸው :: 4) comparative review:- የንፅፅር ግምገማዎች ሁለት ከዚያ በላይ መጽሐፎችን በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የተፃፉትን ያወዳድራሉ፤ ያነጻጽራሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የመፅሐፍቱ እውቀቶችን እውነተኛነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል :: እውነተኛነታቸውን ከምናረጋግጥበት ዘዴዎች  መካከል :- 1) የደራሲውን ማንነት ማወቅ 2 የመጽሐፉ መብት በህግ የተጠበቀበትን ቀን ማስተዋል እና 3) ዋቢ መጽሐፍትን መመልከት ይጠቀሳሉ :: ምንጭ :- የአ/አ/ሳ/ቴ/ዩ/ግቢ ጉባዔ ትምህርት ክፍል +++ ወስብሐት ለእግዚአብሔር +++
إظهار الكل...
👍 4
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.