cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

መልካም ልቦች

ቅን ልቦች ሁሌም ስለ መልካምነት ያስባሉ መልካም ሰዎች ለሰዎች ይጨነቃሉ ። መልካምነት ዎጋ አያስከፍልም ነገር ግን ሰዉ መምሰልን ሳይሆን ሰዉ መሆንን ይሻል✍️✍️✍️ 😍😍😍

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
207
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
لا توجد بيانات7 أيام
لا توجد بيانات30 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በሚያያቸዉ ነገሮች ተገርሟል ። ከዛም ጮክ ብሎ "አባቴ ፥ ዛፎቹን እያቸዉማ ወደ ኀላ እየሄድኩ ነው ። ሲለዉ አባትየዉ ፈገግ አለ ፤ በቅርብ ያሉ ተሳፋሪዋች ግን የ 24 አመት ወጣቱን በሀዘን ስሜት እንደ ልጅና ህመምተኛ ተመለከቱት ፡፡ ወጣቱ በድንገት በመደነቅ ደግሞ "አባቴ ፥ ተመልከት ደመናዉ እኮ አብሮን እየሄደ ነዉ!" አለው ፡፡ አባትየዉ አሁንም ልጁን በፈገግታ ተመለከተዉ ፤ በቅርብ ያለ አንድ ሰዉዬ ግን ወጣቱ በሚያሳየዉ የልጅ ፀባይ አላስችል ብሎት በንዴት ... "ለምን ልጅህን ወደ ጥሩ የአዕምሮ ሆስፒታል አትወስደዉም?" አለዉ ለወጣቱ አባት ፡፡ አባትየዉ በአንዴ ፊቱ በሀዘን ተሞላ ፣ አይኖቹ እንባ እየተናነቀው በእርጋታ እንዲህ ብሎ መለሰለት "ሆስፒታል ወስጄዋለሁ... ፥ አሁን ራሱ ከዛ እየተመለስን ነዉ ፥ ልጄ ከልጅነቱ ጀምሮ ማየት አይችልም ነበር ለወራት ከታከመ በኀላ ዛሬ ነው ታክሞ አይቶ ከሆስፒታል የወጣዉ" አለዉ ፡፡ በዚህ ምድር እያንዳንዱ ሰዉ የራሱ የሆነ ታሪክ አለው ፡፡ የሰዉን ታረክ ሳናዉቅ ሰዉ ላይ ለመፍረድ አንቸኩል ፡፡ ምክንያቱም እዉነታዉን ስንሰማና ስናዉቅ ሁሌ የተናገርነው ይቆጨናልና ፡ #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
መድረሻህን ሳታውቅ ጉዞ አትጀምር! በአንድ ወቅት አንድ ውሻ አንዲት ጥንቸል አይቶ ለመያዝ ሲሞክር ትሮጥበታለች ይከተላታል በአከባቢው የነበሩት ውሾች መሮጡን እንጂ የሮጠበትን ምክንያት ሳያውቁ ተከተሉት ብዙ ከሮጡ በኋላ ስለደከማቸው ሩጫውን አቆሙ ያ ውሻ ግን ሩጫውን አላቆመም ምክንያቱም ጥንቸሏ ከፊቱ ነበረች ሁሌም የምንሮጥለት ምክንያት ሲኖረን ድካማችን ከስኬታችን ያንሳል ። እና ጀግናዬ...! ምትሮጥለትን ነገር አስብ ፤ ራስህን እንጂ የሮጠን ሁሉ አትከተል ፤ የምትከተለው ሰው የሚሮጥለትን ሲያገኝ መንገድህ እንዳይጠፋብህ ሯጭ እንጂ አሯሯጭ አትሁን ። #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የጣፈጠ ህይወትን ይፈልጋሉ? አንተ ልዩ ሆነህ የተፈጠርከው በፈጣሪ ፈቃድ ነውና ምንም ሳታማርር ህይወትህን ኑራት። ባለህ እየኮራህ ህይወትህን አጣፍጣት። ሰዎችን ለመምሰልና የነሱ ግልባጭ ለመሆን አትጣር። የአንተ ንጹህና እጹብ ድንቅ ያልታየ ማንነት የሚወጣው በራስህ መተማመን፣መኩራትና እራስህን ማክበር ስትጀምር ነውና። በዙሪያህ ምንም አይነት ዝነኞች ትልቅና ልዩ ሰዎች ቢኖሩም በአንተ ውስጥ ያለው ልዩ ስጦታ ግን ከሁሉም ይለያል! ይልቃል! ይበልጣል! እነዚህ ልዩ ያልካቸው ሰዎች በአፈጣጠራቸው የተለዩ ሆነው ሳይሆን ይህንን ምስጢር ስላወቁትና ስለተገበሩት ብቻ ነው ከሌሎች ተለይተው አሁን ያሉበት የደረሱት። አንተም እንደነሱ የደረሱበት እንደውም ከነሱበላይ መስጠት መስራትና ማበርከት ከፈለክ ወደ እኔ ጠጋ በልና ጆሮህን ስጠኝ እኔም ሚስጢሩን ሹክ ልበልህ። ተጠጋኸኝ ልጀምር? "እራስህን ሁን! እራስህን አክብር! እራስህን ውደድ!" እራስህን እንደማትወደው እንደማታከብረውና እንደማትሆነው ስታስብ ከማይመረመረው ከፈጣሪ እውቀት ጋ እየተደራደርክ ነውና ሁለቴ አስብ። ሰዎች ከሚሉህ በላይም ፈጣሪ ሲፈጥርህም ምክንያት አለውና የሌለህን ትተህ ያለህን ዋጋ ስጥ። በሌለህ ነገር ስለምታገኘው ሳይሆን ባለህ ነገር ስለምትለውጠው ተመራመር። በሌለህና ባልተጨበጠው ነገር ትልቅ ነገር ለመስጠት ከማሰብ ይልቅ ባለህ ነገር ትንሽ ነገር ለመስጠት ሞክር። ያኔ አንተ ውስጥ የተደበቀው ከሌሎች የተለየው ድንቅ ፍልቃቂ ማበብ ይጀምራል። ብርሀንህ በዓለም ሁሉ ይሰፋል። ስምህም በሰዎች ልብ ውስጥ ይነግሳል። በምድር ላይ በኖርክበት ዘመን ሁሉ ዘመንህ የጣፈጠ ይሆንልሀል። #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
"ይህን_አስብ!" . 1. ከጭንቀትህ የተነሣ በምሽት ለመተኛት ትቸገራለህ ፤ ራሳቸውን የሚያሳርፉበት ቀርቶ የሚያስጠጉበት እንኳን የሌላቸውን አስብ ፡፡ 2. በሥራህ ደስ የማይል ቀን ያጋጥምሃል ፤ ላለፉት ዘመናት ዛሬንም ጨምሮ እንኳን ሥራ አጥቶ የተቀመጠውን ሰው አስብ ፡፡ 3. ወዳጅነትህ ወደ ከፋ ጎዳና እያመራ ስለሆነ ተስፋ ቆርጠሃል ፤ ማፍቀርና በምላሹ ደግሞ መፈቀር ምን ዓይነት እንደሆነ ጭራሹኑ የማያውቁትን ሰዎች አስብ ፡፡ 4. የምትወደውን አንድ ሰው በሞት ስላጣህ ቀኑ ጨልሞብሃል ፤ ሙሉ ቤተሰቡን አንድ ቀን የቀበረውን ብቸኝነት እንደ ሳማ ቅጠል የሚለበልበውን እርሱን አስብ ፡፡ 5. በሕይወትህ ባጋጠሙህ ጭንቀቶችና በገጠምካቸው ፈተናዎች ትማረራለህ ፤ ሁሉም የሆነው ስለኖርክ ነው ፡፡ በመቃብር ሥፍራ ካሉት አንዱ እንኳን እንደ አንተ ደስታና ሐዘንን ፣ ከፍታና ውድቀትን የማየትም ሆነ የማስተዋል አቅሙም አጋጣሚውም የለውምና ይህንኑም አስብ ፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ጊዜ ሁሉ ላለፈው ለሚመጣውና እየሆነ ላለ መጨነቅን አቁም! መልካምና ወብ ይሁንላችሁ ። #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ላንተ ካንተ ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም ፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም ። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው ። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው ። እራስህን በደንብ ተንከባከበው ። ሲያጠፋ ይቅር በለው ፤ ሲደክም አበርታው ፤ ሲሳካለት አሞካሸው ። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
📬ታነቡት ዘንድ❤️ መኖራችንን ሠው በመሆን እናድርገው ፤ ሠው ነንና ። በተፈጠርንበት የፈጣሪ አምሳያ ለተፈጠርንለት የፈጣሪ አላማ ሠው ሆነን እንኑር! ሠው ከመሆን ያለፈ የረባ ነገር ለተፈጠርንለት አላማ ከመኖር ያለፈ ትርጉምና ጣዕም ያለው ነገር የለም ። እመኑኝ ከምንም ጊዜ በላይ በታላቅ ጩኸት ውስጥ ነኝ ። አዎ ውስጤን አሞኛል እናንተስ ? ሠው ሆኖ የሚኖር ትውልድ ለተፈጠረለት አላማ የሚታገል ትውልድ በመናፈቅ ፤ እኛ እስቲ ታጋይ ለመሆን እንቁረጥ► ታጋይነታችንን ለራሳችን በራሳችን እናውጅ► የተፈጠርንለትማ አላማ አለ ። እኔ የፈጠረን አምላክ ሰው እንድንሆን በፈለገበት መንገድ ሆነን እንድንገኝ በመሻት ፤ በመልካም ህመም መድሀኒቱ ሰው ሆነን በመገኘታችን ልክ የመዳን በሆነ ፤ ለትውልድ በመጨነቅ ፣ በማዘንና በመቆርቆር የምር ዛሬ በልዩ ሁኔታ ታምሜያለሁ ። እናንተስ ? እኔ አዳም እባላለሁ ፤ ልክ እንደእናንተው ሠው! እኔ ለተፈጠርኩለት አላማ መኖር እፈልጋለሁ እናንተስ❓ የምር አዎ ሠው መሆናችን ውስጥ ትልቅ ነገሮችን የሚቀይር ነገር አለ ። እርሱም የፈጣሪ ንፁህ ሀይል አብሮነቱ ነው ፤ ከብቸኝነት ነፃ የሚያወጣ! ሠው በመሆናችን ሠው ሆነን በመኖር የተፈጠርንለትን አላማ መኖር እንጀምር ። ብቻ አላርዝምባችሁ በፈቃዳችሁ ለቻላችሁት ሠው ሁሉ ሼር አድርጉ ሠው እንሁን እንደሠው እንኑር ሠው ነንና!!! # fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ዝምታ ! ለትክከለኛው ነገር ተገቢውን ምለሽ የመስጠት እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ አንዳንድ ጊዜ ላያችሁት ፣ ለሰማችሁት ፣ ላነበባችሁት ፣ ለተደረገባችሁና እንደተነካችሁ ለቆጠራችሁት ነገር ሁሉ የግድ መልስ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መምረጣችሁ እየበሰላችሁ የመምጣታችሁ ምልክት ነው ፡፡ ለሁሉም ነገር ምላሽ ለመስጠት የተቀባበለና በሆነ ባልሆነ ያንን የተቀባበለውን የታመቀ ሃሳብ የሚተፋ ሰው ፣ ልክ አንድ ጥይት የጎረሰና የተቀባበለ መሳሪያ በእጁ ስላለው ብቻ ድምጽና እንቅስቃሴ ወዳለበት ሁሉ በየአቅጣጫው የሚተኩስን ሃላፊነት የጎደለውን ሰው ይመስላል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ዝምታ መልስ ሲሆን! አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ለውስጣችን ሰላም ሲሰጠን! አንዳንድ ጊዜ ዝምታ መሸነፍ እንዳልሆነ ሲገባን! አንዳንድ ጊዜ ዝምታ የብስለት መለኪያ ነዉ
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ስኬት የሰው ልጅ ከልጅነቱ ጀምሮ መድረስ የሚፈልግበት ህልም አለው ያንን ህልም ለመኖር አልያም ለማሳካት ግን በብዙ ወንፊቶች ውስጥ ማለፍ ይጠበቅበታል ። በትምህርት በሚያገኘው እውቀት መንገዱን እንዲመራ በማለት የታጨቀ የትምህርት አሰጣጥ ይሰጥሀል ከዛም ደግሞ እሱን አለፍ እንዳልክ የትምህርት ተቋሙ መምሪያዎች ውጤትህን ያማከለ በሚል በተለያዩ ዘርፎች እንድትበተን ያረጉሃል ፤ ያ ደግሞ በጣም ጥቅጥቅ ያለ ወንፊት ማለት ነው ። ሳትወድ በግድህ የተጣለብህን ትማራለህ ፤ ጨርሰህም ብትወጣ በዛ በተማርከው ቀርቶ ለዕለት ጉርስህ የምትሆንህን ስራ ለማግኘት ይከብድሀል ። ከዛ ብዙ ሀሳቦች በህሊናህ ይመላለሳሉ አንዱና ዋነኛው ከሀገር መውጣትና መሰደድ መፍትሔ መስሎ ይታይሀልና በገኘሀው አጋጣሚ ለመውጣት በመሞከር ገሚሶቹ ለባህር አሳ ቀለብ ሲሆኑ ዕድለኞቹ ደግሞ ወተው ከውጪ ኑሮን ይመለከቷታል ። ለጊዜው በሚያገኟት በትንሽ ስራ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ህልማቸው ምቾታቸው የተጠበቀና ያገኙ ይመስላቸዋል ። የኋላ ኋላ ግን እርሱም ይሰለችሃል ለምን ? የምታልመው ነገር ስኬቴ ብለህ ምታስበው ነገር በዕውንህ ሆኖ ስላላየሀው ፤ ሆኖም ስኬትህን በመጀመሪያ ምታገኘው ህሊና ውስጥ ነው ቀጥሎ የመኖርህ ትርጉም እሱ እንደሆነ ሲገባህ ለስኬትህ እንጂ ሆድህን ለመሙላት አትኖርም ። የፈለገ ሀገር ብትቀይር ፣ ኑሮህ ቢሳካ ህልምህን ካልኖርክ / ካላሳካህ ሒወትህ በከፊል መደብዘዙ ማይቀር ነው ። ለስኬትህ ፣ ለህልምህ ኑር። #fobi
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አንብቦ ለመጨረስ ትዕግስት ላለው ብቻ አንድ የመንደር ሰው ገንዘብ ገንዘብን ይስባል የሚል ጥቅስ የሆነ መፅሀፍ ላይ ያነባል።እጁ ላይ ያለው አንድ ብር ብቻ ሲሆን በጣም ድሀ ነበር።ገንዘብ ገንዘብን የሚስብ ከሆነ ብዙ ገንዘብ ያለበት ቦታ በመሄድና አንዷን ብር ከገንዘቡአጠገብ በማስቀመጥ ብዙ ገንዘብ መሳብ እንደሚችል አሰበ።እናም ወደ ከተማ ሄደና ከአንድ ሀብታም ነጋዴ ሱቅ ደረሰ።ምሽት ላይ ስለነበር ሁሉም የሽያጭ ገንዘቦች በመቆጠር ላይ ነበሩ።በሱቁ የመግቢያ ደረጃ ላይ ቁጭ ብሎም የያዛትን አንድ ብር ማርገብገብ ጀመረ።ለረጅም ጊዜ ቢያርገበግብም ሌላ ምንም ብር ተስቦ ሊመጣ አልቻለም።ይሄን ጊዜ በጣም ስለራቀ እንደሆነ አሰበ።እናም የያዘውን አንድ ብር ባልኮኒው ላይ ከተከመሩት የነጋዴው ረብጣ ብሮች ላይ ወርውሮ ጣለው።የሱ አንድ ብር ከሌሎች ብሮች ጋር ሆኖ ተመልሶ ይመጣል በሚል ጥቂት ጠበቀ።ይህ ግን አልተከሰተም።ከዛም ወደ ነጋዴው ሄደና:-"መፅሐፉ ትክክል አይደለም፤እባክህን ብሬን መልስልኝ።"ሲል ጠየቀው። ነጋዴውም:-"የትኛው መፅሀፍ?"ሲል ጠየቀው። መንደሬውም:-"ገንዘብ ገንዘብን ይስባል የሚል ጥቅስ አንድ መፅሀፍ ውስጥ አንብቤ ነበር፤"ሲል መለሰ። ነጋዴውም:-"ታዲያ ትክክል ነዋ፤ገንዘቦቹኮ ገንዘብን ስበዋል።አሁን ቀጥ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ፤ሁለተኛ አንድን ነገር ባንድ አቅጣጫ በኩል ማየት የለብህም የግብፅ ፒራሚድ እንኳን ከተለያየ አቅጣጫ ሲታይ የተለያየ ቅርፅ አለው።"አለው።ከዚያ ቀን ወዲያ ያ ምስኪን ሰው መፅሐፉ ስህተት እንደነበር ለማንም ተናግሮ አያውቅም፤ምክንያቱም መፅሐፉ ትክክል መሆኑን አረጋግጧል። #fobi
إظهار الكل...
ጊዜ ውሰድ፣ እራስህን ጠግን፣ በደጋሜ ጠንክረህ ተመለስ። ሽንፈትና ወድቀት በዛው ወድቀህ፣ ተሸንፈህ ፣ ተስፋ ቆርጠህ ስትቀር ብቻ ሽንፈትና ውድቀት ይባላሉ ። እራስህን በድጋሜ ማነሳሳት ፣ መጠገን ለቀጣይ ፍልሚያም መዘጋጀት ይኖርብሃል ። አንዴ ወድቀህ ተሰብረህ የሚያበቃና የሚደመደመ ነገር የለም ፤ ሁሌም ሌላ እድል አለህ ። አዎ! ጀግናዬ..! ተነስ ደጋሜ ጥንክረህ ተፋለም ለመጣብህ ነገር እጅ እንዳትሰጥ ፣ ጥርስህን ንከስ ፣ ጡንቻህን አጎልበት ፣ አፈርጥም ፣ አዕምሮህን ለሌላ ፈተና አዘጋጅ ። ውድቀት ባለበት ሁሌም መነሳት አለ ፤ መሰበር ባለበት ሁሌም መጠገን አለ ፤ ማዘን ባለበት ሁሌም መደሰት አለ ፤ ማልቀስ ባለበት ሁሌም መሳቅ አለ ፤ መዋረድ ባለበት ሁሌም መከበር ፣ ከፍ ማለት አለ ። አዎ! የዚህ ሁሉ ፍሬ ድጋሜ ስትሞክር ፣ ስትፋለም ፣ ስትታገል ነው ። ወድቀህ ከቀረህ ግን ሁሉም በዛው ይቀራል ፣ ያበቃል ። አንተ ግን አትፍቀድ ዳግም ተነስ ፣ ዳግም ተፋለም ፣ እጅ እንዳትሰጥ ፣ በፈተናዎችህ መሃል አብብህ ታይ ፣ ጎልተህ ውጣ! #fobi
إظهار الكل...
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.