cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

የንጉሱ ልጆች ነን የመድኃኔዓለም ትምህርት ክፍል

የንጉሱ ልጆች ነን የመድሀኒአለም የፀሎት እና የስግደት ማህበር የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚለቀቁበት ቻናል

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
362
المشتركون
-124 ساعات
+37 أيام
+1730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

ሼር እያደረጋችሁ ላልገቡት👇 https://t.me/medihanialmmahebr1
إظهار الكل...
إظهار الكل...
የንጉሱ ልጆች ነን የመድኃኔ ዓለም የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ማህበር

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን 🌼 የንጉሱ ልጆች ነን የመድኃኔ ዓለም  የፀሎትና የስግደት መንፈሳዊ  ማህበር እንኳን  በሰላም መጣችሁ 💮 🌼ይህ ማህበር በአባታችን በመምህር ግርማ አስተምህሮ የነቁ ልጆች የምንፀልይበት የምንሰግድበት መቁጠሪያ የምንቀጠቅጥበት እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት  ጠላታችንን ዲያቢሎስ የምናዋርድበት መንፈሳዊ ማህበር ነው 💮

🕊መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስኅ ግቡ🕊 (ማቴ ፫:፫) ርዕስ፦📝"" ለአሥራ አንዱ ደቀመዛሙርቱ ተገለጠላቸው! "" (፩ ቆሮ. ፲፭:፭) 🌷"የእመቤታችን በዓል"🌷        ✨ክፍል፪(2) 📅(ሰኔ 21 - 2016)    🎤 በመምህር ዲ/ዮርዳኖስ አበበ ✝ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት 🌿ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን! (የቅዱሳንን ዜና እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል) 🌿አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር)
إظهار الكل...
ለ፲፩ ተገለጠላቸው ፪.m4a36.16 MB
🕊 ✞  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞ [  ✞ እንኩዋን ለጻድቅ  አባ ኅልያን ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ] 🕊  ✞  አባ ኅልያን ገዳማዊ  ✞  🕊 ጻድቁ ተወልዶ ያደገው ዐይነ ፀሐይ በምትባል የቀድሞ የግብፅ ክፍለ ሃገር ሲሆን ወላጆቹ ዲስጣና ካልሞና ይባላሉ:: እነርሱ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩና ገና በልጅነት ይህንኑ አጥብቀው አስተምረውታል:: ቅዱሱ ኅልያን ጾምን: ጸሎትን ብቻ ያይደለ በሥጋዊ ሙያውም የተመሰገነ አንጥረኛ ነበር:: በወዙ በላቡ ሠርቶ ያገኘው ሃብት ነበረው:: በተለይ ወርቅና ብር እየሠራ ይተዳደር: ከገቢውም ነዳያንን ያስብ ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ሳለ አንድ ቀን ፈተና መጣበት:: አንዲት ዐረባዊት ሴት መጥታ የጀሮ ጌጥ [ጉትቻ] እንዲሠራላት ትጠይቀውና እርሱም ከወርቅ ይሠራላታል:: የጀሮ ጌጡን ከሰጣት በሁዋላ ግን "ዋጋውን አልሠጥህም" ትለዋለች:: እርሱም "ምነው እህቴ! የደከምኩበትን ለምን አትከፍይኝም?" ሲላት ገላዋን አጋልጣ "ሴትነቴን ልስጥህ" ብላ ለዝሙት ጠየቀችው:: ድንግሉ ኅልያን ከአነጋገሯና ከድርጊቷ የተነሳ በጣም ደነገጠ:: ከፊቷ ላይ አማትቦ: ገስጿት ወደ ቤቱ ሔደ:: ሙሉ ሌሊት ሲያዝን አደረ:: ሊነጋጋ ሲል በልቡ ወሰነ:: ይሕችን ዓለም ሊተዋትም ቆረጠ:: በወጣት ጉልበቱ ደክሞ ያፈራው ሃብቱ: ንብረቱ: ቤቱ: መሬቱ: ወርቁ: ብሩ አላሳሳውም:: ነዳያንን ሁሉ ወደ ቤቱ ጠርቶ ሙሉ ንብረቱን አካፈላቸው:: የተረፈችው የለበሳት ልብስ ብቻ ነበረችና ፈጽሞ ደስ እያለው ከተማውን ጥሎ ወደ በርሃ ተሰደደ:: ልቡናን የሚመረምር ጌታ ሊመራው ወዷልና ፫ [3] ቅዱሳን ስውራንን ሰደደለት:: ሦስቱም የብርሃን አክሊል ደፍተው: የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሰው: የብርሃን ዘንግ ይዘው ተገለጡለት:: እየመሩም ወስደው በግራና በቀኝ ውሃ ከሚፈስባት: ደኗ ለዐይን ደስ ከምታሰኝ ዱር አደረሱት:: አካባቢው እንኩዋን ሰው እንስሳትም አልነበሩበትም:: ፫ [3] ቱ ቅዱሳን ከቦታዋ እንደ ገቡ በላዩዋ ላይ ዕንቁ ያለባት የብርሃን ዘንግ ሰጥተውት "ወደ ፈጣሪ እንስገድ" አሉት:: ሰግዶ ቀና ሲል ግን ፫ [3] ቱም በአካባቢው አልነበሩም:: ተሠውረዋልና:: አባ_ኅልያን ከቅዱሳኑ በመለየቱ ፈጽሞ አለቀሰ:: ተጋድሎውን ግን በጾምና በጸሎት: በስግደትም አጠነከረ:: ቅዱሱ የሚመገበው: የሚለብሰውም ቅጠል ነበር:: በእርሱ ዘንድ ሌሊት የሚባል አልነበረም:: ምክንያቱም ያቺ ዘንግ ሲመሽ ግሩም የሆነ ብርሃን ታወጣ ነበርና ነው:: መንገድ መሔድ በፈለገ ጊዜም ትመራው: ጐዳናውንም ታሳጥርለት ነበር:: እንዲህ ባለ ግብር ለበርካታ ዓመታት ከሰው ተለይቶ ኖረ:: አጋንንት በተለያየ መንገድ ፈተኑት:: ግን አልቻሉትም:: አቅም ሲያጥራቸው ወደ ከተማ ሔደው: በሰው አርአያ ሽፍቶችን አናግረው ሊያስገድሉት ሞከሩ:: ነገር ግን ከፊት ለፊት እያዩት ሽፍቶቹ ሲራመዱ ቢውሉም ሊደርሱበት አልቻሉም:: እግዚአብሔር በኪነ ጥበቡ መንገዱን ያረዝምባቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ሽፍቶቹ በድካምና በውሃ ጥም ሊያልቁ ሆነ:: ጻድቁ ምንም እርሱን ለመግደል ቢመጡም አዘነላቸው:: ባሕሩን ያለ ታንኩዋ እየረገጠ ደረሰላቸው:: ከዱር ፍሬ አብልቶ: ንጹሕ ውሃም አጠጥቶ ሸኛቸው:: እድሜው እየገፋ ሲሔድ አንድ ቀን እነዛ በፊት የተሠወሩ ፫ [3] ቅዱሳን እንደ ገና ተገለጡለት:: በደስታ ሲጨዋወቱ አድረው ሲነጋ አባ ኅልያን ወደ ምሥራቅ ሰግዶ ዐረፈ:: ፫ [3] ቱ ቅዱሳንም ሥጋውን ገንዘው በበዓቱ ቀበሩት:: ዜና ሕይወቱንም ጽፈው አስቀመጡትና እንደ ገና ተሠወሩ:: የቅዱሳን አምላክ ለእኛም የአባቶችን ረድኤት ይላክልን:: ከጻድቁም በረከትን ይክፈለን:: 🕊 [  †  ሐምሌ ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  †   ] ፩. አባ ኅልያን ገዳማዊ ፪. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት [ዘሐምስቱ አሕጉር] ፫. ቅዱስ ታውድሮስ ሰማዕት ፬. ሰማዕታት ሉክዮስና ድግናንዮስ [በንስሃ ለክብር የበቁ የጦር አለቆች] [   †  ወርሐዊ በዓላት  †   ] ፩. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት] ፪. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ [ኢትዮዽያዊ] ፫. ፫፻፲፰ ["318] ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት [ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ] ፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን ፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ [ኢትዮዽያዊ] ፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ [ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት] " ጌታ ኢየሱስም "አትግደል: አታመንዝር: አትስረቅ: በሐሰት አትመስክር: አባትህንና እናትህን አክብር: ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ" አለው:: ጐበዙም "ይህንማ ሁሉ ከሕጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ:: ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው?" አለው:: ጌታ ኢየሱስም "ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሒድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ:: መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ:: መጥተህም ተከተለኝ" አለው::" [ማቴ.፲፱፥፲፰] (19:18) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ] ው          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን አደረሳችሁ ለአባታችን ለአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል🤲🤲🤲
إظهار الكل...
🥰 7😍 1
Photo unavailableShow in Telegram
#ሐምሌ 8 #አአቡነ__ኪሮስ #አባ_ሚሳኤል_ነዳይ መቼም ያ ዘመን (አራተኛውና አምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን) እጅግ የተባረከ ነው። ቅዱሳኑ በብዛት የባለጸጐችና የነገሥታት ልጆች ናቸው። አባ ሚሳኤልም የኬልቄዶን ንጉሥ ልጅ ሳሉ መንነው በበርሃ ለስልሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል። በመጨረሻ ግን በደዌ ምክንያት ወደቁ። ለአምስት ዓመታት መነኮሳቱ ሲጠይቋቸው ቆይተው ሰለቹ። ከዚያም ለአሥራ አምስት ዓመታት ላበታቸው በግንባራቸው እየተቀዳ ያለ ምንም ምግብ እያቃሰቱ በበዓታቸው ወድቀው ኑረዋል። ቸሩ አምላክ ግን አራቱን ሊቃነ መላእክት (ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤልና ሳቁኤልን) አዝዞላቸው ሲጠብቋቸው ኑረዋል። በዚህች ቀንም አቡነ ኪሮስ መጥተው አጽናንተው ጌታችንንም ጠርተው እንዲያርፉ አድርገዋል። መላእክት እያጠኑና እየዘመሩ ጻድቁ ቀብረዋቸዋል። በመቃብራቸውም ላይ ፈውስ የሆነ ጠበል ፈልቋል። እግዚአብሔር የእኛን ያይደለ የጻድቃኑን ቅድስና አስቦ ይራራልን። ከበረከታቸውም ይክፈለን።              #_ሰናይ__ቀን🙏
إظهار الكل...
1🥰 1
የሰኞ አርጋኖ 🕯🕯🕯 ለአባታችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያድልልን አሜን 💐💐
إظهار الكل...
የሰኞ_አርጋኖን_👆🏻_Aremiyas_Tesema_c6d41d90580ae694724bea90664ec153.mp341.48 MB
አንደበቱ ተከፈተ ||የሰው ተከታይ አትሁኑ✝          Size:-22.6MB Length:-1:04:53 በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
إظهار الكل...
_የሰው_ተከታይ_አትሁኑ_አንደበቱ_ተከፈተ_እጅግ_ድንቅ_ትምህርት_ርእሰ_ሊቃውንት_የኔታ_አ_b7A1wZFxVhQ.m4a22.60 MB
[ የእግዚአብሔር ሕግ - ፲፭ - ] .mp38.08 MB
اختر خطة مختلفة

تسمح خطتك الحالية بتحليلات لما لا يزيد عن 5 قنوات. للحصول على المزيد، يُرجى اختيار خطة مختلفة.