cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

✍ግጥም እና ቅኔ✍

ኪነት ለዛው ነጣ፣ ቅኔ ውበት አጣ፣ የሰቆቃ ሳቄን፣ የጠኔ ቁንጣኔን፣ ሊነግረኝ ሲቃጣ! የራሳችሁን ግጥም ለመላክ ወይም አስተያየት ለመስጠት 👇👇👇 @mejnun_poem_bot

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
1 254
المشتركون
+224 ساعات
+147 أيام
+3030 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

የውበትን አምላክ--- በቅርበት የሚያውቁት ፣ ❝ውብ ማለት ምንድነው?❞ ብለው ሲጠይቁት ፣ በጥያቄው ቅለት እየተገረመ ፣ ❝በቃ ልክ እንደሷ❞ ብሎ እንደጠቆመ...... (እንዲሁ እንደ ዘበት.....) እንዲሁ እንደ ቀላል፣ (ባንድ ዕይታ ብቻ....) መገመት ይቻላል። ⬤ (አታምርም??) ውብ ናት ---- የሱ ተአምር፣ (የውቦች የውበት ድምር ) ያደይ አበባ--- የፅጌ ክምር። አጀብ! መገን ያንትያለህ ! ፊደላት ቃላት ተልፈሰፈሱ....! ከውበቷ ስር (መ)ቅኔ ጨረሱ፣ መቆም አልቻሉም... (መግለፅ አልቻሉም ) እያነከሱ...! ብቻ ግን እሷ.... (ብቻ ግን እሷ....) ⬤ ₁ በነፍስ ጭራ እንደወጠሩት.... እንደ ልብ ወዳጅ (እንደ ማሲንቆ፣) ድምጿ ሚያባባ ከልብ ዘልቆ። ⬤ ₂ አበባ ናት -- ግን እሾህ የላትም...! ወዳጇን ማድማት አያስችላትም። እንስፍስፍ አንጀት... (ሩህሩህ ማጀት) የማታስመስል ፣ በስጋ ገጿ ቅጥፈት አት'ስል ፣ (ውሸት አት'ኩል............!) "ነፍሷን አየሁት ባይኖቿ በኩል" ። ⬤ ₃ ገር ናት የተረጋጋች !! በዘመን ሰማይ ድንገት የነጋች ! (የጠዋት ፀሐይ የጀምበር አምሳል...) የጥርሷ ጨረር ገላን ያድሳል ፣ ሳቋ ብቻውን ሳቅ ይመልሳል። ⬤ ₄ በመልኳ ጓዳ በጉንጯ ስርጉድ ፣ የመውደድ አሽከር ይላል ሽርጉድ ። (ወይ ጉድ !!) ⬤ የወርቅ ካባ...! የጣኦስ ላባ ....! የባህር ዕንቁ......! ሙሉ ጨረቃ.......! እንደ ህፃን ሳቅ..... (እንደ ቡረቃ.....!) እንዲያ ናት በቃ !!!! ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
👏 3👍 2
ኦ አምላኬ ! ስቃይ ፈርቼ . . . የሲዖል ወበቅ ነፍሴን ኣርዷት አምልኬህ እንደኹ በቋፍ በስጋት እንዳትራራልኝ አቃጥለኝ በእሳት  ! ደግሞም ለስሙ እንደ ተራ አማኝ ፤ ከጅዬዉ እንደኹ የገነቱን ወይን ልክ እንደ ለማኝ  ፤ የሆዴ ነገር . . . የእረፍቴ ነገር አቅሌን ቀምቶኝ ድሎት ናፍቄ ፤ አምልኬህ እንደኹ እንደ ማስመሰል  ፡  እንደ ኑፋቄ       ፋቅ ይኼን ስሜን         ከገነት መዝገብ        አንድደኝ በእሳት              ነፍሴ ትንገብገብ ! ነገር ግን እኔ  ! በኹለንተናህ በጣዕም ጥፍጥናህ በሽቱ ቃናህ . . . አምልኬህ እንደኹ ... በዉብ ቁመናህ አትደብቅብኝ የዉበትክን ፀዳል  የዉበትህን ጉንጉን               የዉበትህን ጓል ፤ ስጠጣዉ ልኑር      የፍቅርህን ኑር  ። ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
👍 4 2
2
በዚህ በኩል ሳቅ ጨዋታው መጀናጀን መቃለዱ ፣ ከአንዳንዶች ጋ ትግል መግጠም ነጋ ጠባ መሳደዱ ፣ ቀኔን ሌቴን እየበላ ትኩረት ቀልቤን እያላላ ቃላት አምሮት ቀረ የሀዘኔ ምዕራፍ። በምን ሰዓት ይፃፍ? ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
👍 8
አየር ላይ (በእውቀቱ ስዩም) ትናንት ከፓሪስ ወደ አዲስአበባ የሚበረውን የኢትዮጵያ አውሮፕላን ተሳፈርሁ፤ የአውሮፕላኑ ነጂ ከፊትለፊቱ የተደቀኑትን የግብጽ እና የሴኔጋል አውሮፕላኖች ደጋግሞ “ ክላክስ “ በማድረግ ከፊትለፊቱ ገለል እንዲሉ ካደረገ በሁዋላ ለማኮብኮብ ተዘጋጀ፤ ሰማይ ላይ እንደተደላደልን ካፒቴኑ ፤ “ ክቡራን እና ክቡራት መንገደኞቻችን ዛሬ ወደ አዲስአበባ በምናደርገው በረራ፤ በመካከላችን አንድ የተከበሩ እንግዳ ይገኛሉ” በማለት አወጀ፤ እሰይ! ኢትዮጵያ በመጨረሻም ለልፋቴ የሚመጥን ክብር ሰጠችኝ፤ ሀብቱ እና ንብረቱ ደግሞ ቀስ ብሎ ይደርሳል! “ ብየ አስቤ ደስ አለኝ፤ ካፒቴኑ ግን “ እኒህ የተከቡሩ እንግዳ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሳህለ ወርቅ “ ብሎ በመጀመር የደስታየን እድሜ አሳጠረው፤ በግሪክ አየር ክልል ውስጥ እንደገባን አንድ ወጣት የበረራ አስተናጋጅ ቀረበኝና በትህትና “ እንኩዋን ደና መጣህ! ምን እንጋብዝህ አለኝ?” “ አመሰግናለሁ! ግን አትቸገር !” “ የምትፈልገውን ንገረኝ” ‘ ከተቻለ ወደ ፈርስት ክላስ ብታሻግሩኝ ደስ ይለኛል" “ ፈርስት ክላስ እድሳት ላይ ሲሆን ቢዝነስ ክላስ ደግሞ ሙሉ ነው” “ መንገድ ላይ እሚወርድ ወይም እሚዘል የለም?” “ርግጠኛ አይደለሁም” “ እሺ! ቀይ ወይን አምጣልኝ '፤ ሞቅ ሲለኝ ኢኮኖሚክ ክላስ ውስጥ እንደተቀረቀርሁ እረሳለሁ" ብዙ ሳይቆይ አንዲት ትንሽየ ጠርሙስ ወይን እና ሰሀን ሙሉ ቆሉ አቀረበልኝ የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በግርምት ያዩኛል፤ የንጉስ ልጅ ሳልመስላቸው አልቀረሁም! ቆሎውን አፈፍ አርጌ አጠገቤ የተቀመጡትን እንግሊዛዊና ፈረንሳዊ ፥ “ Let us mange “ አልኩዋቸው ( “ እንብላ “ ማለቴ ነው) ፈረንሳዩ፤ “ የተባረከ ይሁን” ይለኛል ብየ ስጠብቅ፥ “ ከሌላው መንደኛ ሁሉ ለይቶ ወይን ያቀረበልህ ለምንድነው ?” ሲል አፋጠጠኝ፤ “ ታዋቂ ሰው ስለሆንኩ ነው” “ እውቅናህ በምን ዘርፍ ነው?” “ ታዋቂ ጸሀፊ ነኝ ልልው አሰብኩና ጽሁፍህ ስለምንድነው ፤ እስቲ ተርጉምልኝ እያለ ሊያደርቀኝ ታየኝ፤ “ታዋቂ የወይን ቀማሽ ነኝ ዠለስ” አልሁት! ፈረንጁ በጣም ተደንቆ ፓስፖርቱ ላይ አስፈረመኝ ፤ ከራት በሁዋላ ከፊትለፊቴ ባለው ስክሪን ፥ በሞንጎልያ አርብቶ አደሮች ዙርያ የሚያጠነጥን ዶክመንታሪ ማየት ጀመርሁ፤ በመሀል ግን ወደ ቢዝነስ ክላስ አካባቢ፥ የበግ ጩኸት የሰማሁ መሰለኝ! ወድያው አስተናጋጁዋን ጠርቼ “ ለእኛ ሩዝ በቲማቲም ቅንጣቢ አቅርባችሁልን ለፕሬዚዳንትዋ ሙክት ማረዳችሁ ከህገ መንግስቱ አንጻር አግባብ ነው ? “ ብየ ልሞግታት ተሰናዳሁ፤ ወድያው ግን የበጉ ጩኸት ፥ ከማየው ዶክመታሪ እንደመነጨ ተገንዝቤ አደብ በቅናሽ ገዛሁ፤ ( ትግስት ካለዎት የዙረቱን ታሪክ በቀጣይ አቀርብልዎታለሁ) ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
👍 6
ትርጉሜ ነሽ ! - አንቺ ማለት- የእኔነቴ ዕጣ ቀለም፣ የዘመኔ ስሪት አንኳር ትርጉምም አይነት አለው- ኩልል ያለ እንደ ጅረት፣ ጥፍጥ ያለ እንደ ስኳር። ትርጉሜ ነሽ። - ቅኔ ሆኖ የሚፈታ፣ ግዘፍ ነስቶ እንደ ጥበብ በፍጥረትሽ ሰሌዳ ላይ፣ ታሪኬ ነው 'ሚነበብ። ትርጉሜ ነሽ። - ለባሻገር ልዕልናው፣ ቢፈተንም መውደዳችን ታምር መርቶ ገንብቶታል፣ አይናድም ህብረታችን። ካስማው ዘሞ ቢጎነበስ፣ ቁም ገጽታው ውሉን ስቶ ፍቅር እንደሁ መንገሱ አይቀር፣ በትንሳዔ ተከስቶ። ደሞስ- በተስፋ-አልባ ድቅድቅ ሌሊት፣ የጠበቀ ዕምነት ኪዳን ከናፍቆት መብሰልሰል ጋር፣ ድል አድርጎ የሰበረ፣ የብቻነት ምድረ-በዳን መች ይረታል!? መች ይፈታል!? የአብሮነትሽን ጀንበር ሞቆ፣ ካለገኘ ፍጽም መዳን። ትርጉሜ ነሽ። ** ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
ኤልያስ ሽታኹን "ወንበሩ ሰው አለው?" *    *    *     *     *     *    * እሷ "ወንበሩ ሰው አለው?" እኔ "ነበረው" (የለም የለም ውሸቴን ነው) እመጣለሁ ካለች ዘመን ያስቆጠረች፡፡ ደርሻለሁ ብላኝ መጠበቅ የበላኝ አይሃለሁ ያለች ልክ ነሽ ሰው አለች፡፡ (ነበረች) እሷ "ወንበሩ ሰው አለው?" እኔ "ነበረው"  እንዳልል "አለውም" እንዳልል ቁጭ በይ እንዳልል ያንገበግበኛል ቃሏን እንደመጣስ ግራ ገባኝ እኮ ግን ደሞ ብትመጣስ ግን ደግሞ የለችም መጣለሁ በላኝ ይኸው አልመጣችም.... ወንበሩ ሰው አለው እንጃ ቀርታለች እላለው እንጃ መንገድ ሰነከላት እንጃ ወይ ሌላ ከጀላት እንጃ መስከረሟ ጠባ እንጃ እግዜር መሀል ገባ እንጃ ብቻ ወንበሩ ሰው...አለው ብቻ ወንበሩ ሰው...የለው፡፡ መቀመጥ ያውም ወንበር ይዞ ትመጣለች ብሎ ሽንት እንኳ ቀዝቅዞ መናፈቅ ሳቅን ሲጠብቁ ስትቀር መነፍረቅ መጎለት ለመጣ ሰው ሁሉ ትመጣለች ማለት መጠበቅ እንደድሮ ፅሁፍ ላይታዩ መድመቅ ነብዝዞ ደብዝዞ መገኘት ሰውን ለመቀበል ራስን መሸኘት... "ወንበሩ ሰው አለው?" እንጃ... ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ። ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ። በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ። ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ። አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው። አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ። ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ። እጄን ይዞ አትጣ ሞገስ ልበስ የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው) ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!! © Adhanom Mitiku @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
የቀረኝ ኑዛዜ ግዜ አልፎ በሚጣል፡ በወረቀት ግጥም፣ የትውልዱን ተስፋ፡ ልምላሜ አልቆርጥም። ዛሬ ነጻነቴ፡ ሲያሳጣኝ ገደብ፣ ቋንቋዬ አደረኩኝ፡ መንግስትን መሳደብ ። የሚሳደቡትን፡ የሚያልፍ በትግስት ድሮ ቢሆን ኖሮ፡ እንዲህ አይደለም መንግስት። መወያየት ሲቻል ከላይ ተጠግቶ ድድብና አይደል ወይ መስደብ በስክቢርቶ? ነባራዊ ሁኔታ፡ ነባራዊ ሁኔታ፣ ሁሉም ማለት ይሻል የጠገበ እለታ። ጥጋበኛ ሁላ ማለት ነው በዱላ ተምሮ ተምሮ፡ ውጤት ይዞ አብላጫ ዛሬም ለተቃውሞ፡ ኮብል ይዞ ሩጫ፣ ማለት ነው በርግጫ ራሱን መምራት አቅቶት፡ ሱሪ እየጎተተ፣ ሀገር ጥራ ሲሉት ፡ጎጡን እያተተ፣ ዳዎን ዳዎን ይላል፡ ያደረ ምርቃናው ካፉ እየሸተተ፣ ምናለ በሞተ፣ ጠላት የሚማርክ ፡ባገሩ አንበርክኮ፣ ዜግነት ሚገባው ፡ወጣት የለምኮ፣ ይሄ  ፡  ብኮ። እንካ ምራ ብለው ፡መሪውን ቢሰጡት፣ መች ያውቃል፡ ያለጡት፣ እዝያው በፈለጡት። ከወንድምየው ላይ፡ የለት ጉርሱን ሚዘርፍ፣ ጎረቤትየውን፡ ባደባባይ ሚገፍ፣ ክብር ይንሳው ፡ጥርሱ ይርገፍ፣ ክፍል ቆጥሮ ቆጥሮ፡ ዩንቨርሲቲ የገባ፣ ታሪክ የሚያበላሽ ፡እውቀት የለሽ ጀዝባ፣ ሞልቶ ባገራችን፣ ሰው ጥብስ ሰው ቅቅል፡ ሆነ ምግባችን፣ የዜግነት ክብር ፡የሚለውን መዝሙር፣ በሹክሹክታ ይለዋል፡ እስኪመስል አሽሙር ፣ እሱን ብሎ ወጣት፣ ፈጣሪ ህይወቱን ፡መድረሻ ያሳጣት። አለ ደግሞ አንዳንዱ፡ ባንዲራ የሚያቃጥል፣ ሀይማኖት ሚያጣጥል፣ በተስኪያን የሚያፈርስ፡ መስጂድ የሚያቃጥል፣ ሚካኤል መላኩ ዘቅዝቆ ያንጠልጥል! ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━    ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘 አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ ➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ @Mejnun_Leyla_poem
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
አንድ እንኳን የቅርብ ዘመድ ያልሞተበት የለም። የሞቱት ነባር ወታደሮች ብቻ አልነበሩም ። ሌላ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው የነበሩ በሌላ ዘርፍ ለመኖር ፣ለማትረፍ ፣ለመትረፍ ህልም የነበራቸው ነበሩ ። ህልም ከእናት ፣ ከአባት፣ ከልጅ ከእውነት አይበልጥም ለካ !! ጀጋኑን !! አለመዋጋትም መዋጋትም ውስጥ በመሞት አማራጭ ተከበው ነበር ። አይናቸው እያየ መረሸን እና መራብ ከቧቸው ነበር። መገፋት እና ምሬት የወለደው ትግል ነበር ። ፅናት እና እውነት ያለውን ማን ያሸንፋል ?! ሃዘኑ መራር ነው። ቀና ተብሎ የሚታዘንበት ነው !! ኩራቱ አድዋን ያህላል !!
إظهار الكل...
👍 1