cookie

نحن نستخدم ملفات تعريف الارتباط لتحسين تجربة التصفح الخاصة بك. بالنقر على "قبول الكل"، أنت توافق على استخدام ملفات تعريف الارتباط.

avatar

Ethiopian Business Network

ያለንን መረጃ እና የደረስንበትን ደረጃ በማጋራት ለስኬት እንተጋገዝ

إظهار المزيد
مشاركات الإعلانات
6 317
المشتركون
لا توجد بيانات24 ساعات
-457 أيام
-16730 أيام

جاري تحميل البيانات...

معدل نمو المشترك

جاري تحميل البيانات...

Photo unavailableShow in Telegram
በ2023 በአለማቀፍ ጎብኝዎች የተጎበኙ ከተሞች የቱርክ ግዙፍ ከተማ ኢስታንቡል የአለማችን ቀዳሚዋ የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ሆናለች። ባለፈው አመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ ሰዎች ከሀገራቸው ውጭ ለጉብኝት ተንቀሳቅሰዋል። በ2023 በርካታ ጎብኝ የነበራቸውን ከተሞች ይመልከቱ፦ https://bit.ly/3X65AoH
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
ከ10 ሺህ 238 የትምህርት ማስረጃዎች ትክክለኛውን መስፈርት ያሟሉት 1 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ ናቸው ተባለ‼️ 👉ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑ ተገለጸ። ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በማሳጣትና በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ችግር በመፍጠር በሀገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ።  የትክክለኛነት ማረጋገጫ ከተሠራላቸው 10 ሺህ 238 የትምህርት ማስረጃዎች 1 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ ትክክለኛውን መስፈርት ማሟላታቸውን የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ለኢፕድ ገልጸዋል። ሕገወጥ የትምህርት ማስረጃ የብቃት መመዘኛና የመቁረጫ ነጥብ ያላሟሉ፤ ተዛማጅ ባልሆኑ የትምህርት ዘርፍና ፍቃድ በሌለው ኮሌጅ ማስረጃ የሚያገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ሕገ-ወጥ የትምህርት ማስረጃ የዜጎችን ብቃትና የተወዳዳሪነት አቅም በማሳጣት በተቋማት ላይ ብልሹ አሠራሮች እንዲሰፍንና በሀገር የኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ብለዋል። የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚዋ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሥራው ለትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት፣ የፌዴራልና የክልል መሥሪያ ቤት ሠራተኞችን እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ የማጣራት ስራ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ======================
إظهار الكل...
የሚሸጥ አውቶብስ! 👉 ሞዴል 2006 👉 ሞተር ያልተነካ 👉 መለዋወጫ ብዙ አማራጭ አለው 👉 በጥሩ ይዞታ ላይ ያለ 👉 ዋጋ 2.1 👉 ሰርቪስ እየሰራ ይገኛል +251911134893
إظهار الكل...
#መልካምዜና የዘንድሮው የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ- አቶ አድማሱ ታደሰ ሞሪሺየስ መቀመጫውን ያደረገው የንግድ እና ልማት ባንክ (Trade and Development Bank- TDB) ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አድማሱ ታደሰ 'Banker of the Year' ወይም 'የአፍሪካ ምርጡ የባንክ ባለሙያ' በመባል በትናንትናው እለት በናይሮቢ፣ ኬንያ በተደረገ ትልቅ ፕሮግራም ላይ ሽልማት ተቀብለዋል። የአፍሪካ ልማት ባንክ በዋና አዘጋጅነት በተሳተፈበት በዚህ ፕሮግራም ላይ አቶ አድማሱ ከሰባት ሌሎች እጩዎች መሀል በአንደኝነት በመመረጥ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል። የባንክ ባለሙያው ከዚህ ቀደም በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት በአለም አቀፍ ፋይናንስ አማካሪነት፣ በኮርፖሬት እቅድ አስተባባሪነት፣ እንዲሁም ኒውዮርክ በሚገኙ ድርጅቶች ውስጥ በፋይናንስ ተንታኝ ባለሙያነት ሰርተዋል። በአሁን ወቅት የሚመሩት TDA ባንክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የበርካታ ቢልዮን ዶላሮች ፕሮጀክቶችን ያንቀሳቅሳል። (ለትርፍ የሚሰሩ የጋና፣ ናይጄርያ... ወዘተ መፅሄቶች እና ጋዜጦች የሀገራችን የመንግስት የስራ ሀላፊዎችን ሸለሙ ብለው በዜና የሚያጨናንቁን የመንግስት ሚድያዎች ይህን በአፍሪካ ልማት ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደ፣ በርካታ የኢትዮጵያ የባንክ ሀላፊዎች ጭምር የተገኙበትን እና አንድ ኢትዮጵያዊ 'ምርጥ የባንክ ባለሙያ' የብሎ የተሸለመበትን ፕሮግራም አልፈውታል) Photo: Zemedeneh Nigatu
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#ጥቆማ በነገው እለት ፥ በአሜሪካ ኤምባሲ SATCHMO CENTER ፥ "Aligning Business Ideas with Funding" በሚል ርዕስ ውይይት የሚካሄድ ሲሆን ፥ መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ተጋብዛችኋል። በውይይቱ ⚡️የኦርቢት ሄልዝ መስራች ፓዚኦን ቸርነት፣ ⚡️የጠብታ አምቡላንስ መስራች ክብረት አበበ ፣ ⚡️የእናት ባንክ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አክሊል ግርማ እንዲሁም ⚡️የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቀጠና መሪ የሆኑት መአዛ ወልዴ የሚሳተፉ ይሆናል። ፕሮግራሙ ከ ቀትር 08:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። ለውይይቱ ለመመዝገብ ፦ https://forms.gle/1UdAHBJ3kqvyMTTo7 ወደ ሳችሞ ማዕከል ለመግባት አባልነት መሰረታዊ በመሆኑ በቅድሚያ አባል ለመሆን ፦ https://bit.ly/SatchmoCenterMembership ©️ US EMBASSY ADDIS ABABA #Ethiopreneur_Picks #Events #Share @ethiopreneure
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
#Ethiopia: #Jigjiga University hosts panel on leveraging ‘Berbera Economic Corridor’ for regional development Jigjiga University, alongside Jigjiga City Administration and the Ethiopian Cities Forum, recently hosted a panel discussion titled "Leveraging Migration Dynamics Along the Berbera Economic Corridor." The discussion featured prominent figures, including Abdukarim Ahmed Moge, Mayor of #Hargeisa City, Abd Shekur Mohamed (#Berbera City Mayor), Mohamed Ahmed Warsame (#Borama City Mayor), and Mohamed Amin Omar (#Gabiley City Mayor). According to state media reports, academics from both Somaliland and Ethiopia presented research and engaged in discussions on the Berbera Economic Corridor's potential benefits for the region. These benefits include infrastructure development, improved road networks connecting Ethiopia, and broader social and economic advantages. Tesfaye Beljige, Chairman of Jigjiga University's Board and Chief Government Whip at the House of Representatives, emphasized the transformative potential of development initiatives along the Berbera Corridor. He highlighted its critical role in facilitating the movement of African trade, services, and capital Tesfaye further underscored the corridor's significance in advancing the African Union's Agenda 2063, promoting regional trade, and stimulating investment activities. Somali Region President Mustafe Muhumed Omer also participated, emphasizing the "Berbera Economic Corridor's" critical role in fostering regional development and strengthening people-to-people connections. President Mustafe stressed the importance of utilizing the corridor for port and maritime transport services, highlighting its potential to significantly enhance regional connectivity and economic growth.
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የዓለማችን ምርጥ 10 ዩንቨርሲቲዎች እነማን ናቸው? ሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ደረጃውን በማሻሻል የዓለማችን ምርጥ ዩንቨርሲቲ ሆኗል ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ፣ ጎንደር እና መቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል #EBN
إظهار الكل...
Photo unavailableShow in Telegram
የኢትዮጵያ መንግስት ለዉጪ ሀገራት ካቀረበዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ከ 78.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን ተነግሯል። በ2016 ዓ.ም . ዘጠኝ ወራት ዉስጥ ለዉጪ ሃገራት ከቀረበው ኃይል ከ 78 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ሲገኝ ለሀገር ዉስጥ ከቀረበዉ የኃይል ሽያጭ ደግሞ ከ 14.8 ቢሊዮን ብር በላይ መገኘት መታሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታዉቋል ። የኃይል ማስተላለፍና ማከፋፈል ሥራዎችን አስተማማኝ ለማድረግ የጥገና ሥራዎች በትኩረት ቢሰሩም በተለያዩ አካባቢዎች ባሉ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት ዕቅዱን ማሳካት እንዳልተቻለ ተቋሙ ገልጿል ። በዘጠኝ ወራቱ ከ 15 ሺህ ጌጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የገለፀው ተቋሙ ከውዝፍ የንብረት ኢንሹራንስ ካሳ ከ113 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱንና ከአላስፈላጊ የመድን ሽፋን ክፍያ፣ ነዳጅ፣ ተሽከርካሪና ማሽነሪ ጥገናዎች ከ112 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉንም በሪፖርቱ አብራርተዋል ።
إظهار الكل...